Tuesday, August 21, 2018

የትግሬው አብርሃ ደስታ አክራሪ ብሔረተኛ ባሕሪ የወያኔ ተፈላጊዎችን አሳልፈን አንሰጣቸውም ይላል ከጌታቸው ረዳ (ETHIOPIAN SEMAY)


የትግሬው አብርሃ ደስታ አክራሪ ብሔረተኛ ባሕሪ የወያኔ ተፈላጊዎችን አሳልፈን አንሰጣቸውም ይላል
 ከጌታቸው ረዳ (ETHIOPIAN SEMAY)

          "አብርሃ ደስታ ሆይ!"

ጃዋር  በኦነግ የፊደል መማርያ ማደጉን እና አንተም በወያኔ የጥላቻ መማርያ ደብተር ማደግህን ለዛሬ የተበረዘ አስተሳሰባችሁ አስተዋጽኦ ቦኖረውም (ለዛወም ይሆናል “ኢትዮጵያ አውት ኦፍ ኦሮሚያ” ብሎ ጃዋር ሲል ፖለቲካው ይመቸኛል ያልከው) ትንሽ ስታድግ አክራሪ ብሔረተኛነትክን ትንሽም ቢሆን ማሻሻል ነበረብህ። ሆኖም ፈቀቅ አላልክም። አፈር በል! በፖለቲካው እየሸበትክ ስትመጣ “ሰከን ስትል” የላ የምትናገራቸው ነገሮች መልሰው ይከነክኑሃል።   አብርሃ ደስታ ዞሮ ዞሮ የወያኔ ጀሌ ነው እያልን ስናገር፤ ብዙ ሰዎች አላመኑም ነበር።ጀሌ ማለት የግድ አባል መሆን ማለት አይደለም። ድሮ የተከናነበበትን ማጃጃያ ነጠላውን ጥሎ ዛሬ በግልጽ ስለወያኔዎች ወንጀለኞች ጥብቅና ቆሞ እየተከራከረ ነው። ድሮም ዛሬም ከወያኔ የተደመረ እንጂ ከወያኔ የተለየ ሰው አልነበም ብለናል።

ዛሬ አብርሃ ደስታ ጀሌነቱን ለማሳየት በግልጽ ሚጽፋቸው ጽሑፎቹ የወያኔ ወንጀለኞች ሲከላከልላቸው ታያላችሁ። ወያኔ በፋሺዝም ርዕዮት የተመራ የፋሺስት ድርጅት ነው ብለን ብዙ ጩኸናል። ያውም አንዳንዶቹ የስድብ ደብዳቤ ሁሉ ጽፈውልኛል። አንዳዶቹ የነፃ ሚዲያ ብለው ራሳቸውን በከንቱ የሚያወድሱ “የሚዲያ አምባገነኖች እና ቡድንተኞች” ሳይቀሩ ስለ አብርሃ የምንጽፈውን አፍነውታል። ሓፍረት አያውቁም እንጂ ማፈር በተገባቸው፤ ይቀርታም በጠየቁን ነበር።ከነፈሰው ጋር ስለሚነፍሱ ለይቅርታ  አልታደሉም
 

እነ አብርሃ በፋሺስቶች የፖለቲካ ጡጦ እየጠቡ በማደጋቸው ዛሬም የፋሺስቶቹን ቁንጮ መለስ ዜናዊን እንደ… እንደ ወንድም..እንደ…. ያከብረዋል። በሂትለር የተጎዱ አይሁዶች አንድ አይሁድ አሂትለርን እንደ ወንድሜ እንደ..አከብረዋለሁ የሚል ሲሰሙ የሚሰማቸው ስሜት ምን እንሚመስል እናንተው ፍረዱ። አብርሃ ደስታ ድሮም አክራሪ ብሔረተኛ ነበር፡ ዛሬም ስለ ወያኔዎች ጥብቅና በመቆም እንዲህ ይለናል፦

ልጥቀስ፦

“….. (ህወሓት) ወደ ድሮ መጥፎ ማንነቷ ተመልሳ በትግራይ ህዝብ ስም እየነገደች የባለስልጣናትን ኪስ መሙላት ነው። ህወሓት አሁንም ለትግራይ ህዝብ ጥቅም ሳይሆን ለስልጣኗ እንደምትቆም እያስመሰከረች ነው።” ይላል።

ወሓት በሕገ ወጥ የባለሥልጣናቶቿን ኪስ ስትሞላ እንደነበረች እየነገረን፤ ዛሬም ለሥልጣኗ እንደምትቆም እየነገረን፤ በሌላ በኩል ደግሞ በሕዝብ የሚፈለጉ ወንጀል የፈጸሙ ፥ ሲገርፉ፥ ሲገድሉ፥ ሲዘርፉ፥ ሕዝብ ከሕዝብ ሲያባሉ እና ሲጨፈጭፉ የነበሩ የህወሓት ባለሥልጣኖች እና ተባባሪዎቻቸው ፥ እንዲሁም ሥልጣን ተጠቅመው የባለሥልጣኖቹን ኪስ ሲሞሉ የነበሩ የህወሓት ባለሠልጣናትን ለጥያቄ ሕግ ሲፈልጋቸው (የሚፈልጋቸው ከሆነ) አበርሃ ደስታ እየነገረን ያለው በትግርኛው ጽሑፉ “አሕሊፍና አይክንህቦምን፤ ክገዝኡና ግን አይክነፍቅደሎምን! (አሳልፈን አንሰጣቸውም ፤ ገዙን ግን አንፈቅድላቸውም) ይላል። ይህ ምን ማለት ነው? የህወሓት መሪዎች በሕግ ከተፈለጉ ወደ ሕግ እንዳይቀርቡ እንከላከልላቸዋለን። አሳልፈን ለሕግ አንሰጣቸውም ማለት ነው።

ይህንን በሕግ ትንታኔ የወንጀለኞች /ተፈላጊዎች አባሪ/ደባቂ/ ተባባሪ/ተከላካይ ነው በሚል ይተረጎማል (ሌላ ጋር ቢሆን ኖሮ ‘ሕግን በማደናቀፍ/ በኢንተርፈራንስ/ ያስከስሳል)። ይህንን በስነ ልቦና ብንመለከተውም፤ አብርሃ ደስታ አክራሪ ብሔረተኛ መሆኑን በግልጽ ማየት እንችላልን። አክራሪ ብሄረተኛነት ደግሞ በሰዎች ላይ የሚያስከትለው ስነልቦናዊ ለውጥና የሚፈጥረው ተፅዕኖ እጅግ ክፉ ስለሆነ ፡ የተማረም ያልተማረም በአክራሪ የጎሳ ልክፍት ወይንም በአክራሪ የሃይሞኖት ልክፍት የተለከፈ ሁሉ ምንም ቢሆን የገዛ የጎሳ አለቆቹ/የሃይማኖት መሪዎቹ በሌሎች ላይ ለፈጸሙዋቸው ወንጀሎች ሌላ አካል በሕግ ሊጠይቅ የሚመጣውን ክፍል አሳልፈው ሊሰጡዋቸው አይፈልጉም። “ምክንያቱም ሕሊናቸው የተቀረጸው  “በባዕድ እና በወገን” ወይንም ‘በኛ እና በእነሱ’ የሚል ክፍተት/አጥር ስለሚፈጥሩ ነው።

 ትግሬው አብርሃ ደስታ በዚያ በጎሳ አጥር ተንጠልጥሎ እየነገረን ያለው ወያኔዎች “የፈለገው ወንጀል ቢፈጽሙም በኔ ላይም ድብዳበ እና እስራት ቢፈጽሙም የህወሓት መሪዎች “የኛ” ስለሆኑ ለሌሎች አሳልፈን አንሰጣቸውም” ነው እያለን ያለው። የአብርሃ ደስታ ቀጥተኛ ትርጉም *ምንም ቢሆን ቢደበድበኝም፤ ሌላ ሰው ደብድበሃል ተብሎ በሕግ ቢጠየቅም “አባቴ ነውና አሳልፌ አልሰጠውም”፡. ምንም ብትበድለኝም “እህቴ ናት እና ለሌላ አሳልፌ አልሰጣትም።” የሚለው ቀጥተኛ ትርጉም ተያያዥነት አለው። “በሰብኣዊ መብት ረጋጣ እና በሥልጣን መማገጥ” የኢትዮጵያን ሕዝብ ያስለቀሱ (አብርሃንም ጭምር ያስለቀሱ) ወንጀለኞችን ለጥያቄ ሲፈለጉም አሳልፈን አንሰጥም ብሎ  ለወንጀለኞች ‘መከላከል’ የምሁርነቱን ብስለት ጥያቄ ውስጥ  የሚገባ ቢሆንም፤ በዋናነት ግን አክራሪ የጎሳ ባሕሪው ጎልቶ የሚያሳይ አባባል ነው። “አሳልፈን  አንሰጣቸውም እንዲገዙን ግን አንፈቅድላቸውም”  ማለት የአብርሃ ደስታ አክራሪ ብሔረተኛነት አስቀድማችሁ ስትጠራጡ ለነበራችሁ ሁሉ ዛሬ የዚህ ልጅ ብልሹ ሕሊና ኮለል ያለ ስዕል እንድታዩ የረዳችሁ ይመስለኛል። የትግራይ ብሔረተኞች ማፈሪያዎች ናቸው ብየ የምከራከረውም ለዚህ ነው።   
  ጌታቸው ረዳ (ኢትዮጵያን ሰማይ ድረገጽ አዘጋጅ)