Tuesday, August 29, 2023

ኦሮሞ በኦነግ እና በደርግ የጸደቀ መጠሪያ ስም ነው! ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay) 8/28/2023


ኦሮሞ በኦነግ እና በደርግ የጸደቀ መጠሪያ ስም ነው!

ጌታቸው ረዳ 

(Ethiopian Semay) 

 8/28/2023

እስኪ በዚህ ልጀምር፡

በነገራችን ላይ ኦሮሙማው መንግሥት በ19ኛው የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የተሳተፈው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ብሔራዊ ቡድን  አዲስ አበባ ሲገባ አቀባባል ሲያደርግላቸው በያንዳንዱ እስፖርተኛ አንገታቸው ላይ ያጠለቀላቸው የአበባ ጉንጉን የያዘው ቀለም አያችሁት? አባ ገዳ ብሎ ራሱን የሚጠራ የባንዴራ ቀለም መለያ ነጭና ቀይ ነበር (ጥቁርዋን እንዳይጨምሩዋት የሃዘን እንዳታስመስለብቻው ተውዋት)። ይገርማል! አሁን ውነት ኢትዮጵያን ሰንደቅ  ዓላማ የሚያመለክት አበባ አረንጓዴ ቢጫና ቀይ” አበባ የለም ተብሎ ነው? የዘንድሮ ጉድ አያልቅም።

እንደምን ናችሁ?

ችግራችን ለመፍታት በግልጽ እንነጋገር አደለም እየተባለ ያለው? ከላይ የተጠቀሱት ማሕበረሰቦች እንዳፈለጋቸው ሜዳውን ሲጋልቡበት ዘመን አልፎባቸው ሌላው ግን በአርምሞ ነበር እያለፈው አሁን እያየነው ላለው የዘር ጭፍፋና ጋጠወጥ ወረራ የተጋለጠው። ማነው ዘመድኩም በቀለ ነው “ነጭ ነጭዋን” ያለው?

 (መጎስ የተባለው ሕግ ተማሪና ድሮ ዳኛ የነበረ ፤ ዛሬ አውስትርያ ለዶክተሬት (ይመስለኛል) እየተማረ ያለው ወጣት ምሁር “በራሱ መድረክ የጋበዘው አንድ “ጋዜጠኛ ነኝ የሚል አክራሪ እስላም” አማራ የሚባሉት ሰዎችን ስለ እስልምና እና አገር ምስረታ የተናገሩትን እየለቃቀመ በራሱ ወገን ያሉትን አክራሪ እስላሞችና (የታወቁ የእስልምና ዩዜና ማሰራጪያዎችና መወያያ መድረኮች) ፤ድፍን ኦሮሞ የፖለቲካ ድርጅቶችና መሪዎች እንዲሁም በመንግሥትነት የተቀመጠው ኦፒዲኦ እና የሥርኣቱ መሪና ሹሟሙንቶችና ፖሊሶቹ ሚዲያዎቻቸው፤ ድርጅቶቻቸው ቀበሌ ሹሟምንቶች የሚናገሩትንና የሚሰሩትን አክራሪና ሰልቃጭ ጸረ ክርስትና፤ ጸረ አማራና ጸረ ኢትዮጵያ ተግባር ግን “እየደበቀ” ለውይይቱ የጋበዘው ያንን መሳይ አክራሪ “ጤነኛ” ነው ብሎ ሲጋብዘው  ዘመድኩንን ከዚያ መሳይ አክራሪ ጋር በመስማማት “ዕብድ” ወዘተ…. ሲለው ሰምቼ “ወይ ዘመን አልኩኝ” (ይህን ብየም- እዚህ ላይ ‘መጎስ ተሾመ’ አክራሪውን ጋዜጠኛ በደምብ ስለሞገተውና በሃሳብ መፈናፈኛ ስላሳጣው ሳላመሰግነው አላልፍም)

የሆኖ ሆኖ ወደ ሃሰቤ ልግባና  አሁን በዚህ ስም የሚጠሩ ማሕበረሰቦች በድሮ ስማቸው ላለመጠራት የሚሸማቀቁበት  ምክንያት ምስጢሩ የተደበቀ አይደለም። ምስጢሩም ያ የ16ኛው ክ/ዘመን “ እራሱ ታሪክ” በሚያውቃቸው መጠሪያ ላለመጠራት በደርግ ዘመን የቀየሩት የዛሬ መጠሪያ በ16ኛው ክ/ዘመን ታሪክ አይታወቅም (ጀርመኑ ፕሮተስታንት ዮሃንስ ክራፈት ያንን ስም እንዳወጣላቸው እራሱ መዝግቦታል ያውቀዋል) የጥንቱን ስማቸውና አኗኗራቸው በዛው በ16ኛው ክ/ዘመን  እንደያዙ ከየት ተነስተው እስከየት ድረስ ኢትዮጵያን እንዳጥለቀለቁዋት እና ሌሎችን ማሕበረሰቦች አጥፍተው የዋጡበትና ቋንቋቸውም እንዲናገሩ ያደረጉበት ሰነድ በዛው በጥንት ስማቸው ታሪክ ስለመዘገበው በዛው ስም ላለመጠራት ይፈራሉ።

መጎስ በገበታ መድረኩ ለምን በዛው መጠሪያ ሊጠሩ እንደማይፈልጉና መጠሪያቸው ምን ሲባሉ እንደነበረና እራሳቸው ታወቂ ኦሮሞ መሪዎችም ሳይቀሩ በዛው በጥንቱ ስማቸው በኩራት ሲጠሩበት የነበሩትን የሚከራከሩ ምሁራንን ሁለቱን ወገኖች ጋብዞ ቢያወያይ ጥሩ ነበር። ቃሉ ሲነሳ “አንወያይም ብለው ካላቋረጡ (ላለመወያየት እንደ ሽፋን ካልተጠቀሙበት- እንዲያ ብለው የሸሹ ታዋቂ ሰዎች ካሁን በፊት ስላደመጥኩ ነው)። ቢሆንም መሮጥ ይቻላል፤ መደበቅ ግን አይቻልም።

 ታሪክ የራሱ ሰንሰለት አለውና መስተዋቱ በሰንሰለቱ አስሮ ተከታታይ ትውልዶች እንዲመለከቱት ያደርጋል። እነዚያ ዛሬ በሕግም በታሪክም በምናምንም ዲግሪ ጭነናል እያሉ በየ ዩቱብ “ምን ይሻላል” እያሉ የሚቦተልኩ “ምሁራንና ፖለቲከኞች” ለ35 አመት አድክመውናል። “አትጥራኝ ካለህ በዛው ስሙ አትጥራው” በቃ  ‘አትጥራው” እያሉ ታሪክን በሚጻረር መልኩ ወደ ጉሮሮአችን ሲደነቅሩብን ሰምተናል። እሺ አንጠራቸውም ግን ታሪክ ስንጽፍ ቃሉን እነሱ ባልነበሩበት ዘመን እንዴት ሲጠሩበት የነበረውን ትተን በዛው ወቅት በማይታወቁበት መጠሪየቻው ጥሩዋቸው እንባላለን?

  ያረጁት በሰላማዉያን እና  በሃገራዊ አርበኛነት በታሪክ ተመዝግበው ሲሄዱ ዛሬ የነዚህ ክቡራን ዜጎች ልጆች ነን የሚሉን የዛሬዎቹ ወጣት ምሁራኖች ግን የ18 እና ዩ19ኛዎቹ ክ/ዘመን ክቡራን ኦሮሞ ወገኖቻችን ሳይሆኑ የነዚያን የ16ኛው ክ/ዘመን ዘመኑ የፈቀደላቸው ያልተማሩ “የከብት አርቢዎቹ” ባሕሪ በዚህ በዛሬው በሠለጠነው ዘመን እንደገና “ህያው” በማድረግ ታሪካዊ ሃውልቶችና ግንቦችን አገርና ሃይማኖትን ቅርስን ቤተጸሎቶችን እያፈረሱ፤ ባንድ ነገድ ያነጣጣረ የዘር ፍጅት የሚያራምዱ “ሁሉም የኛ” ባዮችን ሊነገራቸው የሚገባውን መነገር አለበት።

 በዚህ በኩል የመልስ ምት ሲሰጥ ግን  “ነገር ያባብሳል” እያሉ እውነተኛውን ታሪክ እንዳትናገሩ እያሉ አክራሪዎች ብቻ እንዲናገሩና እንዲጽፉ ተፈቅዶላቸው፤ የልብ ልብ ለዘመናት ተሰምቷቸው “ውሸት እውነት መስሎ ሲደጋገም ዘመናት አልፈው” ይኸው እዚህ ደርሰን አባራሪና ተባራሪ ማሕበረስ ሆነናል።ይህን ታሪክ ስናቀርብ አንዳንዶቹ በቅንነት እንደ እሳት ይቃጠላሉ። ቢቃጠሉም ባይቃጠሉም “በቃ ማለት በቃ ነውና” ማስተማራችን ይቀጥላል።

እነዚህ ስማቸው ሲወሳ የሚደናገጡ የ16ኛው ክ/ዘመን የወራሪ ታሪካቸው እንዳይጋለጥ “ከፌስቡክ አስተዳዳር ቡድን ጋር ስለተቧደኑ” ታሪካቸውን ለመደበቅ እጅግ ተመችቷቸዋል። አምሐራ እና ትግሬ ወርረውናል እያሉ የመጻፍ መብታቸው ሲከበርላቸው በዚህ በኩል ያለው ወገን ስለ እነሱ ሲጻፍ ግን ወዲያውኑ እየተሯሯጡ እንዳይነበብ በፍርሃት እጠንቀጠቀጡ እንዲታደግ ያደርጋሉ። በራስ መተማመን ካለ መልስ መስጠት እንጂ ታሪክን መፍራት አያስፍልግም እና እንዲለማማዱት ዛሬም እንጠይቃቸዋለን።

ጊዜው የመነጋገር ነውና እንነጋገር። ዝምታ ለአህያም አልተመቻት” አደለም የሚባለው? ስለዚህ እንነጋገር። በዛው በጥንት ስማቸው ሲጠሩ የነበሩት የያኔው የ16ኛው ክ/ዘመን ከብት አርቢዎች’ "ግጦሽ ፍላጋ"  ወደ መላው አገራችን ሲስፋፉ ተወራሪዎቹባለገሮች” ቁጥራቸው "ብዛት" ስለነበራቸው በዚያው በሰፊው ባለሐገር ባሕር ውስጥ ገብተው በመካከላቸው ተጋብተው በሂደቱ ራሳቸውን እንዲዋጡ አድርገው  ተወራሪዎቹን ወደ ገባርነት (ገርባ) ለውጠው ቋንቋቸው በሂደት እንዲናገሩበት በማድረግ በቁጥር የነዚያ የ16ኛዎቹ መስለው ከፍተኛ ሕዝብ ያለቸው መስለው ታዩ (ዛሬ ያለው ብዛት የዚያው ውጤት ነው)።

የሆነውም እንዲህ ነው። በዚህም እነዚያ ግጦሽ ፍላጋ ወደ ሰፊው አገራችን የገቡ ከብት አርቢዎች የጎሳ ማንነታቸውን እያጡ፣ በአካል፣ በባህል፣ በቋንቋ የመዋጣቸው የመሰባጠራቸው ሂደትም  “በባለገሬው ነባር ሃይማኖቶች (የኦርቶዶክስ ክርስትናም ሆነ የኢትዮጵያ እስላም መቀበላቸውን ተከትሎ) ኢትዮጵያዊያን ሆነዋል።

በቋንቋም ቢሆን፣  – ኦሮሚፋ፣ አፋን ኦሮሞ ወዘተ… (የፈላገችሁት አጠራር ጥሩት) እሱም እንደ አካላዊ ቅርጻቸው ተቀይጧል።

ከብዙ አማታት በፊት የታሪክ መምህሬ እንደጻፉልኝ  “እነዚህ በኬንያ ድንበር ክልል የሚገኘውን የቦረና እና ባሬንቱ  ጥንታዊ ቀበሌኛ ኗሪዎችን ከሌሎች ማለት  ወደ ደቡብ ፣ሰሜን ፣ምስራቅ እና ምዕራብ ስትሄዱ እነዚህ ጎሳዎች በየሰፈሩበት መሬት በኬንያ ውስጥ ፣ሶማሊያ ውስጥ ቋንቋቸው ከአካባቢው ጋር ስብጥር እንጂ ወጥ አይደለም። ለምሳሌ ይላሉ፡… “ለምሳሌ ሶማሌ ውስጥ ያሉት ከጉተራ፣ በኢትዮጵያ ውስጥም እንደ በደናኪል መካከል ያሉት የአፋርኛ ቋንቋን ወስደዋል፣ ከሀዲያ፣ ከሲዳማ፣ ከጉራጌ እና ከኦሞቲክ ተናጋሪዎች ጋር በቋንቋ ተለዋውጠዋል።

ወደ አማርኛ ስንሄድም፤ በወቅቱ በከብት አርቢነት ሲኖሩ የነበሩት እነዚህ ዎች ከሸዋ አማራ እና አንጎት ከአማርኛ ተናጋሪዎች መካከል ሲኖሩ እንዲሁም እንደ ወሎ እና የየጁ አይነት አማርኛን አንስተዋል። እንዲሁም ከአባይ በስተደቡብ ከሚገኙት ጋፋት፣ ጊያንጀሮ እና ኤናሪያ የተሰባጠረ አካላዊ ቅርጽ እንዲሁም የባህል እና የቋንቋ ባህሪያት ስብጥር ወርሰዋል።

ከአገው የአገው ጎጃም እና ከአባይ ሰሜናዊ ላስታ መካከል አገውን አንስተዋል። ከዚያ የቆቱ ዘዬ አንስተዋል። እንዳውም በእርግጥም "አፋን ቆ" ይሉታል።

ለምሳሌ ይላሉ ወዳጄውና የታሪክ ተመራማሪው መምህሬ፦

 “የወለጋ ተወላጅ የሆነው ‘ኦኔሲሙስ ነሲብ‘ ፣ ምናልባትም የጋ*ኛ የመጀመሪያ ምሁር፣ ሙሉውን መጽሐፍ ቅዱስ ወደ ጋ**ኛ የተረጎመ እና የጻፈው። ጋ*ኛ አንባቢ “የጋ*ላ” ሆሄያት መጽሐፍ እንዲሁም “ጋ*ላ-አማርኛ መዝገበ-ቃላት” በሚል ርዕስ የሐረርን ቆቱ ካነጋገራቸው በኋላ እርሱን ከመረዳት ይልቅ እሱን ሊረዱት እንደቀለላቸው ተናግሯል። ልብ በሉ የዛዎቹ ኦሮሞ ፖለቲከኞች የሚያደንቁት የፕሮተስታንት ተከታይ የወለጋ ተወላጅ የሆነው ‘ኦኔሲሙስ ነሲብ‘  በየመጽሃፍቱ ውስጥ “ኦሮሞ” የሚባል ነገር አንዲትም ቃል አታገኘበትም፡ የለም።”

በሌላ መልኩ “ኦሮሞዎች አንድ ነን” የሚሉን ያዛሬ ኦሮሞ ምሁራን እርስበርሳቸው እንኳ እንዳያችሁት በደምብ መረዳዳት እንደማይችሉና ላቲን የመፍጠራቸው ዘዴም ይህ ምክንያት ነበር። ለዚህም ነበር ከላይ እንደጠቀስኩላችሁ “የወለጋ ተወላጅ የሆነው ‘ኦኔሲሙስ ነሲብ‘ የሐረርን ቆቱ ካነጋገራቸው በኋላ እርሱን ከመረዳት ይልቅ እሱን ሊረዱት እንደቀለላቸው የተናገረው።

 ባጭሩ ለሦስት መቶ ዓመታት የዘለቀውን የነዚህ ጎሳዎች ታሪካዊ ወረራ የኢትዮጵያን ቋንቋዎችን ሁሉ አንስተዋል ብለው የቋንቋ ሊቃውንት ይነግሩናል።

በዚህ ልደምድም፡ መምህሬ እንዲህ ሲሉ በውይይታችን በዚህ መደምደሚያ ተሰናበቱኝ፡

<< አየህ ጌታቸው አንድ ነገር ልንገርህና ልሰናበትህ። በአሩሲ፣ በወለጋ እና በቆቱ ኦሮምኛ ተናጋሪዎች መካከል ያለው ልዩነት የቋንቋ እና የሀይማኖት ብቻ ሳይሆን አጠቃላይ የባህል አመለካከት፣ የአኗኗር ዘይቤ ወዘተ... ብትመለከት አንድ ነን የሚሉት የዛሬዎቹ አስተሳሰብ ሙሉ በሙሉ “ፌዝ” ይሆናል። ለቆቱ ኦሮሞዎች ከወለጋ ወይም ከኢሉባቦር ኦሮምኛ ተናጋሪዎች ይልቅ ኦሮምኛ ላልሆኑ ሰዎች አኗኗራቸውን ለሚጋሩት ቅርብ ናቸው። የሰሜን የራያ ወይም የአዘቦ ኦሮሞ ተናጋሪዎችን ብታመጣ እማ ደግሞ ልዩነቱ እጅግ በጣም የከፋ ይሆናል።>>  ሲሉ መምህሬ ውይታችንን በዚሁ ደመደሙት።

አዎ “ኦሮሞ” በኦነግ ወያኔ እና በደርግ የጸደቀ መጠሪያ ስም ነው! የምልበትም  ምክንያት በጸደቁባቸው ሕገ መንግሥቶችና ዘመኑን ማየት ይቻላል። ብግሃድ እንድንከራከር ይፈቀድልን አታፍኑን!

ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay)