Tuesday, April 25, 2023

አማራ ሕዝብ ቁጥርና የአገዎች ቁጥር የተደረገው የአታካራ ውይይት በሚመከት ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay 4/25/202


የአማራ ሕዝብ ቁጥርና የአገዎች ቁጥር የተደረገው የአታካራ ውይይት በሚመከት

ጌታቸው ረዳ 

Ethiopian Semay 4/25/202

በፎቶግራፉ የቀረቡት ውብ ኢትዮጵያዊያን ሴቶች አገውና አማራ ናቸው። የቋንቋ ልዩነት ቢኖርም ጥንታዊ አመጣጥ መሰረታቸው መልካቸውም ሆነ ታሪካቸው ከአንድ ግንድ የተወለዱ መሆናቸውን እዚሀ ላይ የሚታዩት የአገውና የአማራ ሴት ፎቶዎችን ስትመለከቱ ልዩነት እንደሌላቸው ማሳያ ነው። የፊልም ተዋናይትና የሰው ልጅ መብት ተማጋችዋ የሐረር ወርቅ ጋሻው እና  አገዋዊት የአገው ባህል አስተዋዋቂ የምትባል ወጣት ነች።

ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያ ሕልውና በአማራ ወሳኝ ድምዳሜ የተመሰረተ ነው ሲባል በሌላ አነጋጋር ኢትዮጵያ “በአማራ ትድናለች ወይንም ትፈርሳለች” የሚል ንግግር በብዙ ፖለቲከኞች ሲብለጠለጥ በተለይ ትግሬዎቹ ሲያሾፉበት አድምጫለሁ። ይህንን በሚመለከት << የማፊያዎቹ አዲሱ የእፍ እፍ ፍቅርና የትግሬዎች ሰቆቃና የመዳን ዕጣ ፈንታ በአማራዎች እጅ የወደቀ ነው>> የሚል ርዕስ ሰሞኑን አቀርባለሁ፤ ኢትዮጵያ የመዳን እና የመፍረስ ዕጣ አሁንም አማራው ወሳኝ (ጃየንት) ሚና አለው ብየ እከራከራለሁ። አማራው “ከምድረ ኢትዮጵያ ተጨፍጭፎ ሲጠፋም ወይንም ሲጎለብትም” ኢትዮጵያ የመጥፋትና የመጎለብትዋን ወሳኝ ሚና ከአማራው ጋር የተያያዘ ነው። ይህንን እውነታ ለምን እንደሚያሹፉበት ባይገባኝም ደመናው ላይ የተሳለው ስዕል ግን የሚያሳየው ያ ነው።

ባለፈው ወራት (አሁንም አልበረደም) ኦርቶዶክስ ፈረሰ ሲባል ኢትዮጵያ ፈረሰች እንደተባለው ሁሉ (አብይም ኦርቶዶክስ ማለት አገር ማለት ነው ብሏል- አደለም እንዴ?) አማራ ፈረሰ ሲባልም አብሮ የተሰፋ ክር በመሆኑ ሃቁን መካድ አይቻልም። ይህንን በሚመለከት ለሚቀጥለው ቀናት አቀርባለሁ።

 ለዛሬ ግን ባለፈው ሰሞን የወያኔ ሽጉጥ ታጣቂ የነበረው ዛሬም የፋሺቶቹ የወያኔዎችና የኦሮሞ ናዚዎች ፍቅርና ምስጋና ያልተለየው ዛሬም በቀጣይ ሲቸረው የምናየው ልደቱ አያለው “ትግራይ ፕሬስ” ከሚባል ሚዲያ ቀርቦ ሲወያይ የፕሮግራሙ አዘጋጅ “አማራ፤ አማራ እየተባለ ቢጠራም በክልሉ ውስጥ ያሉት ብሔረሰቦች ቢቀነሱበት ራሱ የቻለ ብዛት የለውም/ኢምንት ነው፡እያለ ሲቀላብድ ሰምቼው፤ ይህ አማራን የማሳነስ ዘመቻ “አማራ የሚባል ነገድ የለም” ከሚለው “ፉርሽ ሆኖ ዛሬ የወደቀ” ያ አልሳካ ሲል ከዚያ  የመነጨ የዘመቻው ሁለተኛ ዙር አካል በመሆኑ እየተደረገ ያለው ዘመቻ መጋፈጥ የግድ ይላል።

በወራሪ ጣሊያኖች ከዚያም በመለስ ዜናዊና እንዲሁም በአሜሪካኖች ደጋፊነት የተዋቀረው “ክልል” በተብሎ በተዋቀረው አፓርታይዳዊው “ንኡሳን አገሮች” አማራ ክልል ውስጥ ያሉት ኦሮሞዎች እና አገዎች ቢቀነሱበት እንኳ ራሳቸው ቆመው ሊኖሩ የማይችሉ በጣም ጥቂት ማሕበረሰቦች ስለሆኑ አማራው ልክ እንደ ትግሬው በውስጡ ካሉት ጎሳዎች በብዛት የበላይ ነው። የአገው ነፃ አውጪ ብሎ ራሱን የሚያታልል ቡድን ምን  ሊያደርግ ጫካ እንደወጣ ሳስበው ከመሳቅ ባለፈ ወያኔ እጅህን አትጣ እላለሁ።

አርጎባዎችና ኦሮሞዎችን እንዲሁም አገዎችን አግዝፎ በማሳየት የሚደነቁሩ ሰዎች ከእውነታው የራቁ ናቸው።

የአገዎችን ብዛት ዕውቀት የሌላችሁ ሰዎች ግንዛቤ እንዲሰጣችሁ እንደምሳሌ ይህንን ልውሰድ።

ከ1994 እስከ 2007 በተለያየ የኢትዮጵያ እስታትስቲክስ ሚኒሰትር የጥናት ሰንጠረዥ እና በጥናቱ “ልዩ ዕውቀት ያለው ዶ/ር ብርሃኑ አበጋዝ” ባቀረበው እኔ ጋር ያለ የጥናቱ ዝርዝር ሰንጠረዥ አገው በ1994 ዓ.ም ሕዝብ ብዛት 555,733 መታወቂያ የያዘ ሰው ነበር፤ ከ13 አመት በሗላ (በ2007) “500,323” ደረሰ (55,410 አማራ ነኝ አለ።ወረደ ማለት ነው) ፤ ምክንያቱ የናት ቋንቋህ ምንድነው ተብሎ ሲጠየቅ  አማራ ነኝ አለ። አማራው በ1997 መታወቂያ  የያዘ ሰው “16,013,618” ሲሆን ኦሮሞው በወቅቱ መታወቂያ የያዘ ሰው “17,086,454” ነበር። ሆኖም እንደ አገዎቹ ኦሮሞዎችም የእናት ቋንቋህ ምንድ ነው ተብሎ ሲጠየቅ  አማራ “17,278,551” ሆኖ ጨመረ፡ ኦሮሞው ደግሞ የእናት ቋንቋህ ምንድነው ተብሎ ሲጠየቅ  “16,701,645” ሆነ፤ (ከ17,086,454  ወደ 16,701,645 ወረደ ማለት ነው፡ የናት ቋንቋየ አማራ ወይንም ሌላ ነው አለ ማለት ነው)።

ስለዚህ አማራው እንኳን በውስጡ ያሉት በጣም ጥቂት ኦሮሞዎች አገውና አርጎባ ተደምረው ሊበልጡት ይቅርና በአገሪቱ ያሉት ኦሮሞዎችም ቢጠየቁና ያለፍርሃት ሕዝቡ ማንነቱ እንዲገልጽ ቢደረግ (በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ እንደ አብይ አሕመድና እንደ ጃዋር መሓመድ ወይንም ብዙዎቹ የኦነግ መሪዎች ትውልድ ሐረግ በትክክል ቢቆጠር አማራ ወይንም ክልስ የሆነ አማራ የአገሪቱ ሕዝብ ብዛት የበለጠ ነው ብሎ በሙሉ ልቦና መከራከር ይቻላል።

 ስለዚህ በመቶ ሺዎቹ የሚቆጠሩ ጥቂት ማሕበረሰቦች በሚሊዮኖች የሚቆጠረው “ጃየንት” (ግዙፉ) የሆነው አማራው ማሕበረሰብ የአገሪቱ ትልቁ ዋርካ መሆኑን መጠራጠር ጅልነት ነው።

በሚቀጥለው ጊዜ << የማፊያዎቹ አዲሱ የእፍ እፍ ፍቅርና የትግሬዎች ሰቆቃና የመዳን ዕጣ ፈንታ በአማራዎች እጅ የወደቀ ነው>> በሚል ርዕስ አቀርባለሁ።

ርዕሱ ትምክሕት መስሎት ብዙ ሰው ላይወደውና ሊያሾፍ ይችል ይሆናል  በመሬት ላይ ያለው “መጪው ዳመና” የሚያሳየው ግን ያ ነው ብየ ምከራከርባቸው ነጥቦችን አቀርባለሁ። እስከዚያው ሰላም እንሰንብት!

ጌታቸው ረዳ

Ethiopian Semay