Tuesday, October 27, 2020

ተከበናል! ስለዚህ ሓለፈነት አንወስድም? What? ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay) Tuesday, October 27, 2020

 

ተከበናል! ስለዚህ ሓለፈነት አንወስድም? What?

ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay)

Tuesday, October 27, 2020

አብን ላይ ብዙ ሰዎች ተሰፋ አድርገው ውሃ ዘግነው ቀሩ። ምናልባትም ለተወሰነ ወቅት አብን መደራጀቱ ውጤት ማግኘት ይችል ይሆናል ብየ አምን ነበር - ይህ እምነቴ መጀመሪያ ሲደራጁ በነበረበት ወቅት ነበር። የአመራሩ አባል የነበረው ክርስትያን ታደለና ሌሎች ምስኪን አማራ ገበሬዎች ከየ አፓርታይድ ክልሎቹ እየታፈሱ ከጀኔራል አሳምነው ግድያ ጋር አያይዘው ወደ እስር ሲወረውርዋቸው፤ ሳይታሰሩ የቆዩ ‘ብዙዎቹ አመራሮች’ በሰላማዊ ሰልፍ ወይንም ሕዝባዊ አመጽ በማስነሳት ያስፈትዋቸው ይሆናል ብየ ብጠይቅ “አይጥ ውስጥ የገባች አይጥ” ሆነው ሳያቸው ከዚያ ወዲህ በነሱ ላይ የነበረኝ ተስፋ ወርውሬ ጣልኩት።

 

ከዚያም አማራን በመግደልና በማስገደል እጆቻቸው ከተጨማለቀው ከታወቁት የኦሮሞ ፖለቲከኞች እና የዘርና የሃይማኖት ጭፍጨፋ በማካሄድ የተካፈለው የሥርዓቱ መሪዎች ጋር ተሰባስበው እርስ በርስ “አንዱን አንዱን አያጋልጥ” ወዘተ በሚል ተዋውለው አብይ አሕመድ ከሰበሰባቸው በሗላ “እነዚህ የአኢዘማ ሁለተኛው ጓዳ ናቸው” አልኳቸው። ከስንት ጊዜ የመግለጫ መንጋጋት በሗላ ይኼው እንደገና ሰሞኑን መጡ እና መሬት አርዕድ አንቀጥቅጥ ተቃውሞአችን እናሰማለን ብለው ሕዝቡን በማሳወቅ “የዋህ አማራ ወጣቶችን” በስሜት ሲየስጋልቡዋቸው ሰንብተው ይኼው እንደገና ተመልሰው “ጽ/ቤታችን እያለን ስለተከበብን መውጣት አልቻልንም እና እኛ በሌለንበት የሚደረግ ተቃውወሞ ሓላፊንት አንወስድም”  የቅንጅት አይነቱ ቅዠት ቃዥተው “የተከታዮቻቸውን ሓሞት አፈሰሱት”፡ ይህ ድርጊት ካሁን በፊት አድርገውት እንደነበር ታስታውሳላችሁ፡ ዛሬም  ይኼው ደገሙት።


 ብትከቡንም  እምቢ አታግዱንም ብለው ግብግብ ፈጥረው ወደ እስር ላለመጋዝ ስለወሰኑ “የኦሮሙማው አፓርታይድ ፖሊሶቹም” ይህን እሺታ ተመለክተው በመጡበት መኪና ተሳፍረው ተመለሱ፡ እነሱም በሚገርም ሁኔታ ወደ ጽ/ቤታቸው ተመልሰው ተወሸቁ። ሰናይ ወሰናይ!!!

የሰላማዊ ተቃውሞ ዋናው መሳሪያ ምንድነው? ተቃውሞን የሚመሩ መሪዎች/አመራሮቹ ሰላማዊ የፖለቲካ ዓይነት ሲከተሉየተወሰኑ ሕጎችን በተለይ  አገዛዙ የሚፈጽማቸው ኢሰብኣዊ ተግባሮችን እና የሰላማዊ ሰልፍ እገዳዎችን ያጸደቀ አዋጅ ወይንም የራዲዮ መግለጫን ለማክበር ፈቃደኛ አለመሆን ማለት ነው (በአጭር አማርኛ!!!):፡ እነዚህ ግን ፖሊሶች ስለከበቡን ተከበናል የተጠራው ሰላማዊ ሰልፍ ሰርዘናል አሉና ሊቃወሙት የወጡትን እና “ማንም ምድራዊ ሃይል ሰላማዊ ተቃውሞአችንን ከማድረግ የሚያግደን ሃይል የለም” ብለው ፎከሩና መጨረሻ ምድራዊ ሃይል ሳይሆን የ 18 እና የ20 አመት ማሃይም ወጣት ፖሊሶች እጅ ጓንቲ እና ብትር ይዘው ሲመጡባቸው ተከበናል ብለው እርፍ!

ፖሊሶቹ ስትመለከትዋቸው ጓንቲ አጥለቀው ነበር የመጡት። እነሱ የገመቱት አብኖቹ “ምድራዊ ሃይል የሚያግደን የለም ሲሉ ስለተሰማ፤ አማራሮቹ “ታዘዝ አንታዘዝም” ግብግብ ተፈጥሮ ደም እንዳይበከሉ እጃቸውን በጥቁር “የፕላስቲክ ግላቭ’” ሸፍነው ነበር  ውጥረቱን ለመጋፈጥ የመጡት። ሆኖም የተፎከረውና የታየው መልስ ግን እንደጠበቁት ስላላገኙዋቸው ወዲያው ከጥቂት መወያየት በሗላ ፖሊሶቹ ወደ ጣቢያቸው እየተዘባነኑ ተመለሱ። እስክንድር ነጋ የእግር ኳስ ጨዋታ ለማየት ቲኬት ይዞ ወደ በሩ ሲሄድ፤ ፖሊሶች “አትገባም ብለው በሩን ሲዘጉበት “አትዝጉብን አንገባለን “በሕግ አምላክ!!!” እያለ እየጮኸ ለሕዝቡ እይታ ሲያስመሰገብ ነበር”።፡እነኚህ ግን እጃቸውን አጣጥፈው ከጥቂት መነጋገር በሗላ ፖሊሶቹ ወደ መጡበት ተመሉ። ውጥረት የለ ምን የለ!

ፖሊሶቹ ከዚህ ቤት እንዳትወጡ ብለው “ኮምፕላይ” አድርጉ (የምንላችሁን ፈጽሙ) ብለው ጠየቅዋቸው፡ አብኖቹ  ደግሞ በሚገርም መለማመጥ ፖሊሶቹ ያዘዝዋቸውን አደረጉ። እኔ አገር ቤት ነበነበርኩበት ወቅት ከፖሊሶችና ከጦር ሰራዊቶች (ከተማውን ሲጠብቁና ሲያውኩ ከነበሩ ካድሬዎች እና የነበልባል ጦር አለቆች በእምቢተኛነት ቢያንስ ሦስት ጊዜ ከነዚህ ሃይሎች እና ወንጀል ምርምራ ጋር ከዚይም ከጥቂት ዕረፍት በሗላ “እንጠርጥርሃል” እያሉ 4 ጊዜ መጥፎ እስርና ድብደባ ደርሶብኝ እምቢተኛነቴን አሳይቼ ለከፋ እንግልት ለመጋፈጥ ወስኜ በተግባር ማሳየቴን አስታውሳለሁ። በቀዳማዊ ሃይለስላሴ ጊዜም ሥርዓቱን በመቃወም አዳራሽ ውስጥ ንግግር አድርገሃል ተብየ አሁን አውሮጳ በሚኖሮው ፌሰድ ቡክ ውስጥ የምታውቁት “የወዲ ሻምበል” አባት በመቶ አለቃ አማረ ታስሬ ተንገላትቼአለሁ:: አሁንም አብሮኝ ከታሰሩት ውስጥ ዋሺንገቶን ከተማ የሚኖሮው ዶ/ር አበበ ተሰማ ነበር። አበበ ተሰማ የታወቀ የተማሪዎች መሪ ነበር (አዲስ አበባ ዩኒቨረሲቲም ሆነ ትግራይ ውስጥም)።

 

ከሚገርማችሁ ወደ ሱዳን ስሻገር ሸራሮ ውስጥ ከወያኔ መሪዎች ሰብሓት፤ መለስ፤ ክንፈ ሳሞራ፤መረሳ፤ እና አንድ የረሳሁት ሰው ለሦሰት ቀን ተከታታይ የተካረረ ውጠረት የበዛበት ውይይት ከስብሓት ጋር ሳደርግ አብሮኝ የነበረ ጓደኛ ማታ ወደ መኝታችን አሰናብተውን ስንሄድ “እባክህን ረገብ በል እንዳታስገድለን አንተንም አንዳይገድሉህ” ብሎኝ እንደነበር አስታውሳለሁ። የክርክራችን ርዕስ ደግሞ አሁን እየገዛት ያለው ብሔር ማን ነው? የሚል ነበር፤ ሰብሓት አማራ ነው ሲለኝ እኔ ደግሞ ብሔር የሚባል የለም አማራ የሚባል ብሔርም እየገዛ አይደለም የሚል ነበር፡ እንደ ድፍረቴ ምክንያቱን ባላውቀውም እነሱም አከበሩኝ እንጂ ምንም የደረሰብኝ ነገር አልነበረም።)፤ ስለዚህ  አለመታዘዝ ማለት አንድ ዜጋ የተወሰኑ ህጎችን ፣ ጥያቄዎችን ፣ ትዕዛዞችን ወይም የመንግስትን ትእዛዛት ለመታዘዝ  እምቢተኛነትን ማሳየት ማለት ነው። ሌላ ዝባዝበንኬ የለውም። አጭርና ግልጽ ነው። ሰላማዊ ስለተባለ “ውጥረት የለውም ማለት አይደለም። አላማው ውጥረትን ለመፍጠር ነው እንጂ ለመለማመጥ አይደለም።  ከሰላማዊ ሰልፎች ከፀጥታ ኃይሎች ውጥረት መፍጠር ማለት ነው። ያ ግን አገራችን ውስጥ አይታወቅም። አንዳንድ ጊዜ ምነው ኢትዮጵያ  ዓረብ በሆነችና እነዚህን አጋስሶች “አላህ ወ አክበር” እያለ የቱኒዚያ፤ የግብጽ የሌባኖስን አይነት ተቃውሞ በታየ እላለሁ። የአበሻ እንጀራ “እሽታን” የሚያስተምር ማደንዘዣ ሳር ነው። ኤርትራን ተመልከቱ ኢትዮጵያን ተመልከቱ “ሕዝቡ ጭለማ ቀንበር ውስጥ ገብቶ” ዛሬም “እሺታን” አማራጭ አድርጎ “ጫወነቱን” እያስመሰከረ አነገቱን ቀርቅሮ “በብትር በቢላዋ ፣ ሲታሰር ፣ ሲፈታ ፣ ሲገደል ፣ ሲባረር ፣ ሲሰደድ ፣ ሲፈናቀል 29 አመት ገሃነም ውስጥ እንደታሰረ ነው”። እስኪ ደግሞ አብኖች ይህንን ትችት ሰምተው ቢታረሙና  የሚቀጥለው ምን እንደሚሰሩ አብረን እንጠብቅ!

አመሰግናለሁ

ጌታቸው ረዳ