Monday, July 13, 2009

ፀሐይዋ ሞቅ እያለች በሄደች ቁጥር ወያኔ እየተደናበረ ነዉ!

www.Ethiopiansemay.blogspot.comጌታቸዉ ረዳ
አንድ ሊቅ እንደገለጹት “ወደ ስልጣን የመጣዉ ሁሉ የሰንደቃላማን መልክ መቀያየር ብሔራዊ መዝሙር መለወጥ፤ የክፍለ -ሃገሮችን ያስተዳድር መዋቅር ማዘዋወር፤ታሪክ ማጥፋት፤ራስን ማንንት መገንባት ፤ማዳላት፤ ተንኮልን መጎንጎን እና በሕዝብ እየማሉ ሕዝብን መበደል...”ጥቂቶቹ የመጥፎ አስተዳደር ምልክቶች እንደሆኑ ገልጸዉ ነበር። ወያነ ትግራይ ወደ ሥልጣን ከመጣበት ቀን ጀምሮ ያስተዳዳር ብቃቱ እጅግ ደካማ ከመሆኑ የተነሳ በዉጭ ሃይሎች ሴራ እየተመከረ እና እየተረዳ የአገሪቱን ህልዉና አደጋ ላይ ስለጣላት፡ በዚህ ሕዝቡ በመቆጣቱ የተነሳ ተቃዉሞዉን በማሰማት ወያኔ/ኢሕአዴግ እንደ “የዉጭ ሃይሎች ቅጥረኛ” ያገር ጠላት በመታየቱ፤ ተቃዉሞዉን ለማርገብ ፣ሕዝቡን ፀጥ ለበጥ አድርጎ ለመግዛት እንዲቻለዉ የተጠቀመበት መሳሪያ “ዱላ”-እንደነሆነ ሁላችን የምናዉቀዉ ነዉ። ሰሞኑን በጎንደር ክፍለሃገር በኢንጂኔር ሃይሉ ሻዉል የሚመራ የ “መኢአድ” ድርጅት አደራጆች ከፍተኛ የድብደባ ግፍ በፋሺስቱ ወያነ ትግራይ መንግሥት “ብርጭቆ አጣቢዎች” እና “ቡቹሎች” እንደደረሰባቸዉ ዜናዎች ያስረዳሉ። ከማንኛቸዉም ድርጅቶች በላይ ወያኔ የሚፈራዉ እና በኩፉ ዓይን የሚያየዉ ቢኖር “መ ኢኣድ”ን እንደሆነ የፖለቲካ ታዛቢዎች የምታዉቁት ሃቅ ነዉ። መ ኢኣድ ድርጅቱን በስፋት በሃገሪቱ ዉስጥ ባሉት ገጠሮች እና ከተሞች በስፋት እና በፍጥነት ጽ/ቤቶቹን በመክፈት እና በማጠናከር ሥራ ላይ መሆኑን እንደታወቀ፤ የወያኔ መሪዎች ባለፈዉ ምርጫ የሃይሉ ሻዉል”-ድርጅት እና ጥንካሬ በብቃት ስላየዉ፤ ዛሬ ያንኑ የድርጅቱ ሕዝብን ባንድነት የማሰለፉ ብቃት መልሶ እየደገመዉ ስለተመለከተ፤ ወያነ በዚህ ምክንያት ኩፉኛ ተደናግጦ የለመደዉን ወረበላ ልማዱ በ“መኢኣድ” ድርጅት አባሎች እና አደራጆች ላይ “ዱላ” እየሰነዘረ መሆኑን ታዉቋል። ሰሞኑን የወያነ ትግራይ “ጀስታፖ” ወረበላ ታጣቂዎች በጎንደር ክፍለ ሃገር ዉስጥ የመ ኢአድ አደራጅ አባል ከፍተኛ ደብደባ ተፈጽሞባቸዉ ባሁኑ ሰዓት ሕይወታቸዉ በአደጋ ላይ ይገኛል። “ዞን”-እያለ በጌቶቹ ቋንቋ ያገሪቷን መስተዳደር የሚጠራዉን በደቡብ ጎንደር-“ዞን’-የመኢአድ ስራ አስፈጻሚ አባል እና የድርጅት ጉዳይ ሓላፊ የሆኑት አቶ “ዋለልኝ መንግሥት” የተባሉት ከደቡብ ጎንደር ጽ/ቤት ታዘዉ የደራ ሓሙሲትን ወረዳ ለማደራጀት እአንደተሰማሩ በወያኔ/ኢሕአዴግ ታጣቂዎች እና በፖሊሶች እጅ ከፍተኛ የሆነ ድብደባ ተፈጽሞባቸዉ ባሁኑ ጊዜ በጽኑ ቆስለዉ እየተሰቃዩ እንደሆነ ተገልጿል። አቶ ዋለልኝ ድብደባ ከተፈጸመባቸዉ በሗላ እርዳታ በማያገኙበት ሁኔታ በመጣላቸዉ ምክንያት፣ በድበድባዉ ምክንያት ብዙ ደም ስለፈሰሰባቸዉ ጉዳታቸዉ ተባብሷል። በመሳሪያ አፈሙዝ “ጭንቅላታቸዉ” በፈንከቱ “ባፍንጫቸዉ በኩል ብዙ ደም ፈሷቸዋል።”በተጨማሪም በደረሰባቸዉ ድብደባ የመተንፈሻ አካላቸዉ በመጎዳቱ መቆም እና መንቀሳቀስ እንደማይችሉ የተላለፉት ዜናዎቹ ያስረዳሉ። አቶ ዋልልኝ ከወደቁበት ቦታ በሞት ጣር ሲሰቃዩ ያገኝዋቸዉ ያካባቢዉ ኗሪዎች ከሞት ሊታገዳቸዉ እና እርዳታ ሊያደርግላቸዉ በመቻሉ ወደ መኖርያ ቤታቸዉ ወደ ደብረ ታቦር ከተማ በማድረስ ተባብሯቸዋል። ባሁን ወቅት እኚህ ዜጋ ወደ ከፍተኛ ሕክምና ወደ ባሕር ዳር ተወስደዉ በመ ኢአድ ድጋፍ ድርጅት ጽ/ቤት አባላት በኩል ድጋፍ እየተደረገላቸዉ ሕክምና ላይ እንዳሉ ተነገሯል። ከዚህ ሌላ ደግሞ በእዛዉ በጎንደር ዓለም ሰጋ አካባቢ የመ ኢአድ እንቅስቃሴ ለማስተጓጎል ሲባል ብዛት ያላቸዉ የወያኔ “ጄስታፖ”ታጣቂ ሃይሎች በአካባቢዉ በማሰማራት ማታ ማታ ኗሪዉን በማስፈራራት ሰላም እንደነሱትም ታዉቋል። ያካባቢዉ ገጠር ወጣቶችም እየደረሰባቸዉ ካለዉ ድንጋጤና ሽብር ዉጥረት ለመላቀቅ ሲሉ ወደ ተለያዩ ከቶም እየሸሹ እንደሆኑ ናቸዉ። ይህ የወጣቶች ከመኖርያ መንደሮቻቻዉ ወደ ሌሎች መተሞች እና ክፈላተሃገሮች መሸሽ የደርግን ጊዜ ስርዓት እየተደገመ እንደሆነ ያስታዉሰናል። ተያይዞም ከዚህ በፊት “ተጠባባቂ ሃይል” በሚል ስም ወታደራዊ ማስልጠና ተቋም ገብተዉ የነበሩ ባሁኑ ጊዜ ከነ ሙሉ ትጥቃቸዉ በደቡብ ጎንድር 12ወረዳዎች ዉስጥ ተሰማርተዉ በመ ኢአድ ላይ ማስፈራራትና ዛቻ እየሰነዘሩ እንደሆኑ ታዉቋል። ማስፈራቱም ቱኩረት ያደረገዉ አባላቱ ከ “መ ኢ አ ድ”-የማይወጡ ከሆነ ፤ “በአሸባሪነት” በመከሰስ ለእስር እንደሚዳረጉ እና የሚጠብቃቸዉ ዕድልም “ሞት” መሆኑን በመግለጽ እንደሚዝቱባቸዉ ሪፖርቶቹ ይገልጻሉ። ባጠቃላይ በሚፈጸመዉ ማስፈራራት እና ዛቻ ዉጥረት መፈጠሩ እና ኗሪዉ ተረጋግቶ የዕለት ተለት ስራዉን ለማከናወን እየተቸገረ እንደሆነ የደቡብ ጎንደር የአንድነት ጋዜጦች ያብራራሉ። ባልታጠቀ ሕዝብ ላይ የወያነ ትግራይ ወረበላ ታጣቂ “ጄስታፖዎች”-እየደረሱበት ያለዉን ግፍ የሚያመላክተን “ጎጃም”ዉስጥ ጅበላ (ሞተራ አምባ)-ላይ መሽገዉ አጼ ዮሓንስን የተዋጉዋቸዉን ንጉሥ ተክለሃይማኖት ማሸነፍ ሲያቅታቸዉ ጊዜ የንዴታቸዉ ብዛት አጼ ዮሃንስ በሕዝቡ ላይ አሰቃቂ ብትር እንዳሳረፉባቸዉ በአጼ ዬሐንስ ታጣቂዎች ልብሷን ልብሷን የተገፈፈች እና ከብቶቿ የተነዱባት አንዲት የጎጃም ሴት “በላይኛዉ ጌታ በባልንጀራዎ በቅዱስ ሚካኤል በጋሻ ጃግረዎ በጽላተ ሙሴ በነጭ አበዛዎ ጎጃምን ይማሩት ፈሪም አንልዎ።” ያለቺዉን ግጥም አስታወሰን።የትግሉ ምጣድ እየጋለ ፀሃይዋም እየበረታች በሄደች ቁጥር በግራ ቀኝ ሙቀቱ እየወበቀዉ ያለዉ ወያኔ እየተደናገጠ መሆኑን ከላይ ያየነዉ አመላካች የመደናገጡ ምልክት ነዉ።የጀረምን ጄስታፖዎች ዜጎችን በመደብደብ አና በማሸበር ሥልጣን ቢቆጣጠሩም ይዘዉት የነበረዉን ዱላ እና የተመኩበት ወረባላ የጀስታፖ ቡድን ከዘላለማዊ ዉድቀታቸዉ ሊያድናቸዉ አልቻለም። ወያነ ዱላ ያዘም አልያዘም ከሕዝቡ ልቦና የተተፋ በነብሰ እና በሃገር ጥፋት የፈጸሙ ግለሰቦች የሚመራ ቡድን በመሆኑ ዉድቀቱ አይቀሬ ነዉ። ኢትዮጵያዊነት ያሸንፋል! www.Ethiopiansemay.blogspot.com