Thursday, January 7, 2016

ተቃዋሚዎችና ሚዲያዎቻቸው በኦሮሞ ወጣቶች ያላቸው አሳዛኙ ግንዛቤ!


ተቃዋሚዎችና ሚዲያዎቻቸው በኦሮሞ ወጣቶች ያላቸው አሳዛኙ ግንዛቤ!

ጌታቸው ረዳ (ኢትዮጵያን ሰማይ አዘጋጅ)

በአለፈው ሰሞን “ሦስተኛው ዙር የኦሮሞ ፋሺዝም” ጹሑፌ በርካታ የምስጋና ደብዳቤዎች ደርሰውኛል። አመሰግናለሁ። በርከታዎቹ ደብዳቤዎቹ የሚናገሩት ስለ የኦሮሞ ፖለቲከኞችና የገዳ ስርዓት ምንነት የነበራቸው ግንዛቤ መቀየሩ ነግረውኛል። አዎን፤ ዛሬ ደግሞ የወያኔ ተቃዋሚዎችና ሚዲያዎቻቸው በኦሮሞ ወጣቶችም ሆነ በኦሮሞ ታሪክ ያላቸው የተጃጃለ (foolish) ግንዛቤ እንመለከታለን።

‘ፓልቶክ’ ክፍሎች ለመጎብኘት ሳት ብዬ ስገባ፤ የሚሰነዘሩ ግንዛቤዎች እጅግ የጫጩ ናቸው። እንደ ሰደድ እሳት በሁሉም “ክፍሎች” ማለት ይቻላል የሚሰነዘሩት ንግግሮች “ባሁኑ ሰዓት ዋናው ጠላቴ ወያኔ ነውና ወያኔ መጀመሪያ እናውርድ፤የሌሎቹ ፖለቲካ ወያኔ ሲወርድ የምንመለከተው ይሆናል” የሚል ነው። ይህ ግብዝ መስምር እንዲስፋፋ አስተዋጽኦ ያደረገው “ግንቦት 7” የተባለው ዱርዬና አታላይ ቡድን ነው። ግንቦት 7 ትምህርቱን የቀሰመው ለበርካታ አመታት ይህንን ማጃጃያ መስመር አጥብቆ ሲሰብከን ከነበረው ከ“ኦነጎች/OLF” ነው። ኦነግ ደግሞ ይህንን ‘ስልት/ታክቲክ’ የቀሰመው ከ“ወያኔዎች” ነው። ሦስቱም ይህንን ስልት ሊጠቀሙት የቻሉት፤ወያኔ ስልጣን ለመንጠቅ መጀመሪያ “ደርግን” እንጣል ሲል ነበር፤ደርግ ጣለና ዋና ጠላት አድርጎ የፈረጃቸው “ድህነት፤ኦነግ፤ኦብነግ፤ግንቦት7፤ሻዕቢያ…” ናቸው። በሁለተኛ አስቀምጦአቸው የነበረው ክፍሎች ወደ አንደኛ ደረጃ ጠላት አድርጎ መድቦ እስካሁን ድረስ ስልጣኑ በሰላም መምራት አልቻለም። በሁለተኛ ደረጃ አስቀምጦአቸው የነበሩት ክፍሎች ‘የህልውናው’ ተፈታታኝ ሆነው አግኝቶአቸዋል።አስገራሚ የሚያደረገው ደግሞ’ ወያኔ እነኚህ ክፍሎች (ኦነግ፤ ሻዕቢያና ኦብነግን) ፖለቲካቸውን በማስፋፋት ከፍተኛ ቅስቀሳ በማድረግና፤ አልፎም ፕሮግራማቸው እንዲተገበር ቡዱኖቹ ከጠበቁት በላይ ረድቶአቸዋል።ዞሮው ህልውናውን ተፈታተኑት!!

ግንቦት 7 የተባለው የተገንጣዮች አቀንቃኝ የሚመራው ኢሳት ደግሞ እንዲህ ዓይነቱ ማጃጃያ መስመር በስፋት የሚያስተጋባ ነው። ድርጅቱ ጸረ አገር መሆኑንና “አማራ ሆነው” ጸረ አማራ ግለሰቦች የሆኑ ያሉበት የተገንጣይ አደግዳጊ ሚዲያ መሆኑ ከጅምሩ የምናውቀው ነው። ተድላ አስፋው “ቪ ኦ ኤ” የተባለው የአሜሪካ ፖሊሲ አራማጅ “መናፍሕ” የፕሮፓጋንዳ ጣቢያ፤ ጃዋር መሓመድ የተባለው “ኢትዮጵያዊያኖች ከኦሮሞ ክልል አንዲባረሩ” ጥሪ በማስተጋባት የታወቀው “የሁከት ሚሊሺያ መሪ” የሆነው አደገኛው ሰው፤ ቪ ኦ ኤ ጋብዞት ስለነበር “አቶ ተድላ አስፋው” ይህንን አስመልክቶ “ለአሜሪካው መናፍሕ” ተቃውሞውን በጻፈው ደብዳቤ ውስጥ ኢሳትን አስመልከቶ አንዲህ ብሎ ነበር፤

Neamin Zeleke position is the G7 position. They talk with nothing back home. His movement is known for Talking a.k.a ESAT and I do not give any credibility for his group being a unifying factor. The ESAT broadcast is more a divider than a uniter. Their airtime is filled with sensationalism incorporated with Kilil terminology. The only thing we have is the name Ethiopia on their station.” አጽንኦት የተጨመረ።

እነዚህ የመሳሰሉ ሚዲያዎች የጠላት መሳሪያዎች እየሆኑ ነው። ሕዝቡም ግንዛቤ እንዳይኖረው ጫና አድርገዋል።የጠላት ዓይነት ቢኖሮውም፤መርህ የለቀቀ፤ከጠላት ጋር ትከሻ ለትከሻ እየተሻሹ፤ በየአዳራሹ እየዞሩ የጠላትን ፖለቲካ እየደገፉና የአማራ ሕብረተሰብ “ነፍጠኞች በቁጥጥራችን ስር አድርገንላችሗል” የሚሉ ጠላት ለማስደሰት፤ወገን ለማሳዘንና ግንዛቤ የጎደለው ክፍል እያሳሳቱ እንዲቀበላቸው ማድረጉ፤ በሁለተኛ ደረጃ የተመደቡ ጠላቶች የሚሏቸው (እንዲያውም አጋር እንጂ በጠላትነት ቀርቶ በጥርጣሬ እንኳ አያዩዋቸውም)። ይግረም ብሎ፤ ዋና ጠላት የተባለው ጠላት (“ወያኔ”) ሲወድቅ፤ ህልውናህን የሚፈታተኑት እነዚህ መሆናቸው ከታሪክም ከተሞኩሮ የታዬ ነው። ለዚህ ውድቀት ዓይነተኛ ሽንፈት የሆነው “መርህ አልባ” የትግል እንቅስቃሴና “አገራዊ ፍቅር” ያልታጠቁ መሪዎች ፖለቲካውን” ሲያራምዱ የሚከሰት አደጋ ነው። ጊዜያዊ ጥገና እና እርካታ የሚያመጣው ጠንቅ በጣም የከፋና ረዢም ቀውስን ያስከትላል።

አንድ ምሳሌ ልስጣችሁ። ‘መላው ህይወቱ ሰውን በመግደል ያሳለፈው ‘የኮራፕት ክሪሚናል’ ኢሳያስ አፈወርቂን ተክለሰውነት ለመገንባት ሲዳክር የነበረው ‘አስቃባጩ’ የግንቦት 7 መሪው በአንዳርጋቸው ጽጌና በአገር ወዳዱ የመቶአለቃ አያልነው ደሴ መካካል በኢሳት ቲ/ቪ ስለ ተቃዋሚዎች አብሮ መስራት በሚመለከት የተደረገው ውይይት ተመልሳችሁ ብታደምጡ፤ “አንዳርጋቸው ጽጌ” ሉዓላዊ የአገር\ ሶቨርኒቲ/ አንድትን፤ዳር ድምርንና ሰንደቃላማን “እንደ ቅድመ ሁኔታ” መቀመጥ የለባቸውም የሚለውን ድረጅቱ በጽሑፍ የበተነውን መስምር፤ እውይይቱም ላይ ከመድገሙ አልፎ፤ “ግንቦት7” የሚከተለው “ፕሮግራምና መርህ” እንደሌለው “ለሥልጣንም” እንደማይታገል፡ የተከራከረበትን ስታደምጡ፤ ከላይ የተከሰቱ የወደፊት አደጋና ግርግር አፍላቂ ምክንያቶች የሚሆኑት ምንጮች እንደዚህ ያለ ‘መርሃ ቢስ’ ‘የጠላት አሰላለፍ ግንዛቤና’ ‘የአገር እንድነት መርህ’ የማያስቀምጥ ትግል፤ “ከጎኔ ጋር ቆሞ ወያኔን ለመጣል እየታገለ ያለው ጠላት” የሚባለው “ምንም አይጎዳኝም/ ሥልጣን ሲገኝ በሗላ የምናየው ጉዳይ ነው” በሚል ‘መርህአልባ’ ‘በይደር’ ያስቀመትከው ጠላት የባሰ ግርርግርና መርዝ አሰራጪዎች የሚሆኑት እነሱ ናቸው።

ለምሳሌ ወያኔ ይኼውላችሁ እንደ “ፍጥምጥማችሁ ተፈጣጠሙ” ብሎ ወደ ክልሉ ወደ ትግሬ ሪፑብሊክ ቢሄድ፤ አገር ገንጣዮቹ ሕዝብን በመፍጀት፤ ሁሉንም ለመጥረግ ወደ ሗላ የማይሉ የመጀመሪያ ግርግግር ፈጣሪዎች እነሱ አንደሚሆኑና፤ “ምንም አያደርጉም” የተባሉ የሁቱና የቱሲ ዓይነት “ሞንሰተሮች”እንደሚሆኑ እወቁ። ችግሩ ሲባባስ ከኦሮሞ እና ኦጋዴን የሚባረሩት፤አገር ውስጥ ያሉ “ኢትዮጵያ” የሚሉ ተቃዋሚዎችና፤ “የእነ ግንቦት7 ምሰኪን ጀሌዎች” እንጂ ‘‘መሪዎቹ” ውጭ አገርም ሆኑ፤ እዛው አገር የሚኖሩም ቢሆን ነገሩን ለመብረድና ለመከላከል፤ ወደ ክልሉ ብቅ እንደማይሉ ሳይታለም የተፈታ ነው። እነ ግንቦት 7 እንኳ ገና ለገና፤ ካሁኑኑ “የእነ ሰሚራ ቡና እና ዕጣን ‘ሽታ’ እንጂ የጦርነት ባሩድ” ሳያሸቱ “የመጀመሪያው ፊሽካ ነፋን” ባሉበት በሳልስቱ ወደ አሜሪካቸው መመለስ ጀምረዋል። ንዓሻ በሎ! ይላል ትግሬ “ሞኝህን ፈልግ!” ጥሩ አባባል ነው።
  
አስኳሉ ሲፈስስ፤ በተለይም የታጠቁ ክፍሎች ከሆኑ! የሚያመጡት ትርምስ ብዙ ነው። “ግድየለም” እየተባለ በቸልተኝነት በወዳጅነት እያየህ ቆይተህ፤ “ማአከሉ ሲናጋ”፤ የሚቆጣጠሩትም ሆነ ግርግር የሚፈጥሩት እነዚህ ክፍሎች ናቸው የምለውም ለዚህ ነው። የእገሌ ድርጅት መሪ ከታጠቁ ተግንጣዮች ጋር አብሮ እየሰራ ነው! እያመጣቸው ነው፤ ወደ መሃል እየጎተታቸው ነው፤ ጎበዝ ድረጅት ነው የሚል የሰነፎች ሙገሳ እየተቸረው፤ ተገንጣይንና በተለይ በዘር ማጥፋት ወንጀል የተሳተፉትን ‘በወዳጅነት መመልከቱ” ባሕሪያቸውን አለማወቁ ከፍተኛ ጠንቅ እንዳለው መገንዘብ ያስፈልጋል።

ወንጀለኞቹም፤ ከወንጀላቸው ለመሸሸግ የማያደርጉት ሙከራ የለም። ውንጀላቸው ያለፈ ወንጀል ነው፤ ያነን ማንሳት ሰላም አያመጣም፤ “ወላጆቻችን ፤ዘመዶቻችን ገድለውብናል፤ እንፋረዳቸዋለን የሚሉ ስም እየተለጠፈባቸው *ጠብ ጫሪዎች* *ለብጥብጥ የሚጋብዙ” ክፍሎች ብቻ ናቸው የሚቃወሟቸው” የሚሉ “ግብዞች አሉ”። እንዲህ ከሚሉ አንዱ “መረራ ጉዲና” ነበር። ባለፈው ሁለት አመት ውስጥ ‘ይመሰልኛል’ (ድምፁ ቀድቼዋለሁ) ‘በአዲስ ደምፅ ራዲዮ’ መረራ ጉዲና የተለመደው ቧልቱ “ሲቦተልክ” አድምጬዋለሁ (ዛሬ ኦሮሞዎች ሲገደሉ ግን ጮክ ብሎ ገዳዮች በሕግ ይጠየቁ ባዩ ቀዳሚው እሱ ነው) ።

አስገራሚው ግን ፖለቲከኞቹ የሚነግሩን “ወንጀለኛው እና ሽብር የሚፈጽመው “ወያኔ” ብቻ እንጂ ሌላ ሽብርተኛ የለም፡ እያሉ ወንጀለኛ ድርጅቶችን ሽፋን እየሰጡ ነው። ሕዝቡንም በዛው በተሳሳተው ጎዳና እንዲመላለስ እያደረጉት ነው። ይህ ሴራ በጥብቅ ማወቁ አስተዋይነትን ይጠይቃል። ወንጀላቸውን እየሸፈንክ “ወንጀል” ሰሪው “ወያኔ’ ብቻ ነው ብሎ በሕዝብ ፊት በሚዲያ በቂ ሽፋን መለገስ “ተባባሪነት” ብቻ ሳይሆን መጻኢ ጊዜ “ተአማኒትን” ያሳጣል። ተጎጂዎችንም አጥቂዎቻቸውና ገዳያቸው እንዳያውቁና በሕግ እንዳይፈረዷቸው ማድረግ  ነው።

እንዲህ ያለ አገራዊ መሰረት ለማናጋት የተሰለፉ የውስጥም የውጭም ጠላቶች በጥንቃቄ ካልተከታተልካቸው፤ በቸለተኝነትና “ወያኔ” ብቻ ይውደቅ እንጂ የሚል “ጊዜያዊ ጥገና” temporary fixation የሁለት ክፍሎች ጥምረት ማለትም “የሰነፎች ወይንም ተንኮለኛ” ፖለቲከኞች የሚከተሉት ስልት ነው። አጃቢዎቻቸውም በዛው ግንዛቤ በጎደለው አስተሳሰብ እየተከተሉ መርህ አልባ ሆነው፤ ዳግም ለሌላ ዙር “ግርግር” ይጋለጣሉ። አሁን እየተጓዝን ያለበት ሁኔታ ያንን ያመላክታል።

የዛሬው ኦሮሞ ወጣት ተማሪዎች እየተከተሉት ያለው እንቅስቃሴ “ባይተዋርነት” ያመነጨው የፖለቲካ ቀውስ ነው። ቀውሱ “ኪሳራ” ነው። ተቃዋሚዎቹም በዛው አክሳሪ እንቅስቃሴ በመጓዝ፤ “ወያኔ ይውደቅ እንጂ” በሚል ሂሳብ እየጓጉ ‘አክሳሪ ፖለቲካ” እየተጓዙ ያሉትን ‘ግንዘቤ የጎደላቸው ኦሮሞ ተማሪዎችና ከሗላ ሆነው እየገፏቸው ያሉት “ፋሺስታዊ ተገንጣይ ክፍሎች” በሚዲያና በይፋ እያበረታቱ፤ የተገንጣዮቹ ፕሮፓጋንዳ በሚዲያዎቻቸው ሰፊ ሽፋን በመስጠት የኪሳራ ፖለቲካ እየተጓዙ እያየናቸው ነው።

ይህ የኪሳራ ጉዞ በቅርብ ለምናውቃቸው አዲስ ክስተት አይደለም። ተቃዋሚ ድርጅቶች ብቻ ሳይሆኑ የተገንጣይ ፋሺሰት ፕሮፓጋንዳዎችና አገራዊ አንድነትን የሚጻረሩ አፍራሽ “የተገንጣይ ድርጅቶች መግለጫዎች” በየሚዲያው በስፋት ሲለጥፉላቸው ዓመታት አልፏል። ዛሬም ያንኑ እየደገሙት ነው። ኢትዮ-ሚዲያ በሚባለው “አፍቃሬ ኦሮሞ ተገንጣዮችና ፤ጠባብ ትግራዋይነት” የሚያጠቃው ይህ ሚዲያ የነዚህን ክፍሎች ፕሮፓጋንዳ ሲለጥፍ፤ሲያስተጋባ፤ሲክብ፤የፎቶግራፍና የቪዲዮ ስራዎች በስፋት እያሰራጨ ነው።

እሱ ብቻ ሳይሆን “ዘ-ሐበሻ” የተባለው ከተስፋዬ ገበረአብ ጀምሮ፤ በኢትዮጵያ ምድር ውስጥ የተፈለፈሉ “አፍራሽ ተገንጣይ የሆኑ ፋሺስት ድርጅቶች” መግለጫዎችና የፕሮፓጋንዳ ስራዎች እንዲሁም ሰንደቃላማዎቻቸውና አርማዎቻቸው በሙሉ በሕዝብ ሕሊና እንዲቀረጹ ከፍተኛ የጠላት/የሳብቨርዥን ስራ ሲሰራ ብዙ አመታት አልፎታል።

በቅርቡም ‘እንደ አቅሚቲ’  “አረብ እንጂ ሶማሌ/አፍሪካ” አይደለንም በሚል (ካሁን በፊት ቃለ መጠይቁ በማስረጃ አቅርቤላችሁ ነበር፤ያንን አስታውሱ) መሪ የሚመራው ኦጋዴን ነፃ አውጪ የተባለው “ጸረ ኢትዮጵያ ደርጅት” ያደራጃቸው “ኦጋዴን ወጣት ተማሪዎች ሕብርት” OYSU: በእንግሊዝኛ የተጻፈ መግለጫ ስታነቡ “ The Ogaden and Oromo people share a common struggle,…..” የጋራ ትግላችን “መገንጠልን ነው” የሚለው ጸረ ኢትዮጵያ ፕሮፓጋንዳና እንዲሁም ድረገጹ በቪዲዮና በፎቶግራፍ ያጣበበው፤ የባይተዋሮቹ ኦሮሞ ተማሪዎች ቅንቅስቃሴ ፕሮፓጋንዳ ስራ ለዓለም እያስተጋባ ነው።

ይህ ክስተት ‘ኪሳራ’ ውስጥ የሚዋኝ “መርህቢስ” የሆነ ተቃዋሚና የሚዲያ ደካማነትን ያመላክታል። ጥያቀው የሚከተለው ነው። ለኢትዮጵያን አንድነት “እቆማለሁ” እያልክ “የኢትዮጵያ አንድንትን” የሚጻረሩ “የተግንጣዮች መግለጫና፤ የሚዲያ ሽፋን ከሰጠህ፤ ምኑ አገራዊ ተባልከው?” ሚዲያ እጅግ ወሳኝ መሆኑን የታወቀ ነው። ተገንጣዮቹ  የሚዲያ ሽፋን ጠቃሚነቱን ስለሚያውቁና በዚህ ብልጦች ስለሆኑ እነዚያ ግብዝ የሚዲያ ተቋማትን እየተጠቀሙባቸው ነው። የተገንጣይ ሚዲያዎች የሚያካሂዷቸው ፕሮፓግንዳቸውን የሚያስፋፉ እንደ እነ ደ/ር ዜሮ (ጌታቸው በጋሻው) የመሳሰሉ አሳፋሪ ግለሰቦች፤ የነሱን ዓላማ እና ፕሪንስፕል በይፋ የማይጻረሩ ካልሆኑ በቀር፤የነሱን መሰሪ ወንጀልና የነቀዘ የፖለቲካ ትግል የሚተነትን ጽሁፍ ብትልክላቸው “ከቶውንም፤ አያትሙትም”።

በቅርቡ ኢሳት የተባለው “አፍቃሬ ኢሳያስና፤ ኦነግ የሰየማቸው የከተማዎችን ስም ተቀብሎ የሚያስተጋባ የባንዳዎች ስብስብ” በተደጋጋሚ ለበርካታ አመታት እና በቅርቡም “ጃዋርን የሚያክል” አደገኛ ሰውና ጸረ ኢትዮጵያ ወጣት፤ ወደ ሚዲያው ጠርቶ ፕሮፓጋንዳውን ለኢትዮጵያ ኦሮሞ ወጣቶች የፕሮፓጋንዳ ሽፋን በመስጠት እያሞጋገሱ “ሲያስተላልፍለት” እንደነበረ የምታውቁት ነው።ከዚህ ወዲያ ጸረ ኢትዮጵያነት ፍፁም ሊኖር አይችልም። ፕሮፓጋንዳ የጦርነት ግማሽ ሃይል ነውና “ግማሹን ጦርነት” ተቃዋሚዎች “ለኢትዮጵያ ተጻራሪ” ሃይሎች እየሰሩ ይገኛሉ።

ተቃዋሚው “ከፋሺት ተገንጣይ ቡድኖች ጋር በመተሻሸትና በኢሳያስ አፈወርቂ የፕሮፓጋንዳ ካድሬዎች ድጋፍና ወታደራዊ ስልጠና” ኢትዮጵያ ውስጥ ለውጥ ማምጣት ይቻላል የሚለው እንቅስቃሴ የሚያጎላው ለምንድነው? የሚለው ጥያቄ ሰፊ ዝርዘር ውስጥ  ያስገባናል። ባጭሩ ግን፤ዞሮ ዞሮ፤ የሚያመላክተው መርህ አልባ ከመሆናቸው (ዋናው ይህ ቢሆንም) ሌላ፤ አልፍ ብሎም “ትግሉን” የሚመሩት አገር ውስጥ ያሉ መሪዎች ጭራሽ ፈሪዎችና፤ ለመስዋእትነት ያልተዘጋጁ፤ ‘ተምበርካኪዎች’ ስለሆኑ፤ እነሱ የማይመሩት ማንኛውም “ቦግ” የሚል ወያኔን የሚጋፈጥ ሕዝባዊ እንቅስቃሴ ሲከሰት “መርህ ይኑሮው አይኑሮው” ድጋፋቸውን ቶሎ ይሰጣሉ። ምክንያቱም እነሱ በመሪነት ፊት ለፊት ተሰልፈው የሚጋፈጡበት ወላፈን ባለመሆኑ (ልክ ዲአስፖራ ያለው ‘ግፋ በለው’ የሚለው ‘መርህ-ቢስ’ የሆነው “የግንቦት7 የፓልቶክ ተቃዋሚ ጀሌው” ዓይነት)_፤ ድጋፋቸውን መስጠት ብቻ ሳይሆን ማንኛውም ቦግ የሚል እንቅስቃሴው ሰብአዊነትን፤የመብት ጥያቄንና አገራዊነትን ያላብሱታል”። ይህ በሽታ ተሎ ወደ ሚዲያዎች ይተላለፍና ከሚዲያዎች ወደ ፓልቶክ ዞሮ “የእንቅስቃሴው ምንነት ሳይመረመር” የመብት ጥያቄ ተብሎ ይደመደማል። ሆ ሆታው ዓለም ያዳርሳል። ከአስመራ “እንዳ ሰሚራ ቡና ቤት፤ አመርቂ ቡና እየተፋላ” የተነፋው የፊሽካው ደወል “ሆ ሆታ” የትኩሳት “ግለት” እንደጦፎውና ባንዴ “አንደቀዘቀዘው” ዓይነት ክስተት!  ያሁኑ ኦሮሞዎቹ የባይተዋርነት ቀንቅስቃሴም ተቃዋሚዎች ያላቸው እውቀት “አሳዛኝ ግንዛቤ” ነው የምለው ለዚህ ነው።

 ታማኝ በየነ የተባለው የኢሳትና የግንቦት 7 “አራጋቢ” ስለ ኦሮሞ ተማሪዎች የተናገረውን ስናስታውስ ከላይ የጠቀስኩት የግንዛቤ ቢስነቱን ያንጸባርቃል። ምንም ይሁን ምንም የተማሪዎቹ እንቅስቃሴ የመገንጠል ነው ተብሎ  አንዳንዶቹ የመገንጠል እንቅስቃሴ ፍላጎት ነው ቢሉም፤ “የመገንጠል ጥያቄ ባልደግፈውም፤ መብታቸው ነውና አከብርላቸዋለሁ”፤ ዲሞክራሲ ማለት የመብት ጥያቄ ነው ብሎናል።

ዲሞክራሲና አገር ምን መሆኑንም ብዙ ዜጎች አልገባቸውም። ተማርን የሚሉ ክፍሎችም ዲሚክራሲ ከአገር ማፍረስና ያለማፍረስ ያያይዙታል። ዲሞክራሲ ባለፉት ቃለ መጠይቆቼ እንደገለጽኩት አገር ማፍረሻም፤ሂትለሮችና ፋሺስቶች ወደ ሥልጣን መወጣጫ የሚገለገሉበት ዘዴ ነው (የሂትለር አማጣጥና እድገት፤ ወደ ሥልጣን የመጣበትን መሳልል አስታውሱ)። ዲሞክራሲ፤ ከአገር አንድነትና ደህንነት ጋር ተያያዥነትና ወሳን ሚና እንዳለው የሚገልጹ ተቃዋሚዎች የተበራከቱበት አገር ቢኖር “ኢትዮጵያ ምድር” ውስጥ ብቻ ነው። ትምህርቱ ከየት አንዳገኙት አለውቅም።

በተለይ “ሪፈረንደም” የሚል ሂደት እንዲተገበር የሚጥሩ “ኢምፔሪያሊስቶች’ መሆናቸው ታሪክ ይነግረናል። ለምን እንደሆነም የምናውቀው ነው። ሙልጭልጭ እያሉ ፤ አልገዛም እያሉ የሚያስቸግሩ ‘ዲግኒፋይድ//ኩሩ’ አገሮች፤ለማንበርከክ የአገሮች ቀላላል “የአይጥ መያዣ”/ ትራፕ / አይነት መሆኑ ነው። “ራስን በራስ ማስተዳዳር/ሪፈረንደም” እጅግ አድርገው ፋሺስቶች/ጎጠኞችና ኢምፔሪያሊስቶች አጥብቀው እንዲተገበር ይጥራሉ። ሆኖም ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዝናል። ሱዳንም፤ፓኪስታንም፤ሶማሊም፤ኤርትራም…… መወጣጫ አጥተው፤ ራስን በራስ ማስተዳዳር የተባለው “ሬፈረንደም” ወደ ራስን በራስ መገዳዳልና ወደ ጦፈ ስደትና የጭቅጭቅ አዙሪት፤ተለውጦ መውጫ መንገድ አጥተው “የተቀረቀቡበት” ወጥመድ እንደማለት!

ዲሞክራሲ ሞንስተሮች የሚከተሉት በእራሱ ሂደት በየጊዜው እያበጃጀ እንደገና እራሱን የሚያቃጥልና የሚጻረር፤ ብዙሃን በአናሳ ወይንም በግለሰቦች መብት ላይ አመጽ የሚያስነሳ “ሞብ-ሩል” የሚያሰፍን ስርዓት የመሆኑንም ጭምር አይነግሩንም። ያንን ይሸፍኑታል። አሜሪካን አይነት “የባንክ ባለሃብቶች” የሚቆጣጠሩት ‘የኦሊጋርኪ’ ስርዓት በዲሞክራሲ የሚጎናጸፉበትን ስልጣን እና ቁማር ተመልከቱት። ዲሞክራሲ ነው። ዲሞክራሲ፤ እንኳን አገርን ለማቆየት፤ እራሱንም በተመሰረተበት ሕግ ለመቆየት ዋስትና የለውም። ማንም የታጠቀ ዱርዬ የሚጠልፈው፤ የሚፈርስ፤የሚተካ ነው።ለዚህም ክስተት ስንት ህይወት ተገብሮበታል።መጨረሻው ገዢና የበላይ አስተዳዳሪ የሚሆነው “ራስ በራስ ማስተዳዳር ሳይሆን”  “ጥቂቶች” ወደ ምቾት ዓለም አንደላቅቆ፤ ሌላ አዙሪት ውስጥ የሚያስገባ፤ በንትርክ የተከበበ ስርዓት ነው።

ግለሰቦች ሳይሆኑ ብዙሃን/ማጆሪቲ የሕግ ባለቤቶችና የበላይ የሚያደርግ አግላይ ስርዓት መሆኑንም ሳንደብቅ እንጋጋርበት።አናርኪ፤ሶስያሊስት፤ፋሺሰት፤ናዚዎች፤ኮሚኒስት፤ካፒታሊሰት፤ዲሞክራትስ፤ሪፓብሊካን፤ ሞናርክ እና ልኡላን፤ሼኮችና ሙላሆች…….በበላይነት የሚመሩት የብዙሃን ደምፅ በጥቂቶች ህይወት ላይ የሚወስን ዘዴ በመጠቀም ነው!

 ዲሞክራሲ የነዚህ ሁሉ “ኦሊጋርክ” ክፍሎች የመጫወቻ ስልት ነው። ጥቁር `እንደ ሰው ሳይሆን 1/3ኛ የሰው ቅርጽ ያለው እንሰሳ ነው፡ስለሆነም እንደ እንሰሳ በንብረትነት መመዝገብ አለበት ብለው ብዙሃን ድምፅ አሳልፈው አሜሪካኖች “በድምፅ ብልጫ” ውሳኔ በማሳለፍ የተጠቀሙበትን ስርዓት ስትመለከቱ የዲሞክራሲ ስልት ነው። ጥቂቶች ተቃወሙት፤ ሆኖም በብዙሃን ተሸነፉና ብዙሃኑ የጥቂቶቹን ድምፅ ረግጠው፤ ባርያዎች “እቃ የመሆን ሕግ ተደነገገ።

ዲሞክራሲ አስፈሪ የሞንስተር ገጽታው “ብዙሃን በጥቂቶች ላይ የሚጭኑበት ዲክታተርሺፕ’ ነው የምለውም ለዚህ ነው። ስለሆነም ዲሞክራሲ እና የአገር ሉአላዊ “ልዕልና” አንድ ሊሆኑ አይችሉም/አይገናኙም። ኦሮሞዎችና ኦጋዴኖች እየጠየቁት ያለው ይህንኑ “የነገድ/ጎሳ ወይንም “ራስን በራስ ማስተዳደር መብት” ነው። በተለይ ደግሞ ዝቅ ሲል ‘ነገድ ተሞርኩዞ’ ራስን በራስ ለማስተዳደር የሚፈቅድ ዲሞክራሲ “አመጸኞች/ዱርዬዎች” እነሱን በማይመስሉ ነገዶችና ዜጎች ላይ የመብት መዳፈርን የሚያጎናጽፍ ሰርዓት ነው። አሳዛኙ ደግሞ፤- “ልገንጠል” ያለ ቡድን (ሕዝብ እየተባለ ነው በሕዝብ ስም የሚነገደው) በጉልበት መያዝ አይቻልም፤ በዲሞክራሲ ረፈረንደም መብት ይሰጠውና ይለይለት፤ ሕዝቡ  እንተማመንበታለን (ኢትዮጵያዊነቱን አጥብቆ ያከብራል) ፤ “ራስን በራስ ለማስተዳዳር እንዲመች፤ የአካባቢው ሰዎች በሚመረጡ ሰዎች ብቻ እንዲተዳዳር “የፌደራል” መብታቸው ካስከበርክ ሰላም ይመጣል”; የሚሉ ደካሞችና “እንዝህላልነት ያጠቃቸው ታላላቅ የውጭ አገር ሰዎችና ታላላቅ “የአፍሪቃ ደራሲያን” እና “ኖብል ተሸላሚዎች” ሲናገሩ አድምጬአለሁ።

መገንጠል ማለት አገርን ሰውን ቤተሰብን በሁለት በሦሰት ከፋፍሎ፤ ታሪክን ሰላምን መግደል ማለት ነው። ተገንጣይ ግንጠላውን ብትፈቅድለት ሌላ ጦርነት ከፍቶ (ኤርትራና ፓኪስታንን አስተውሱ) እንደገና ሰላም መንሳቱ አይቀሬ ነው (የራሱ እትብት ስለሌለው፤ በግድ የተቆረጠ ስለሆነ)። ‘በራስ ሰው’ መተዳዳር ከዜግነትም፤ከሥልጣኔም አኳያ “ሌሎችን ነገዶችና ዜጎችን ፍጹም አግላይ ነው”። ያ ብቻ ሳይሆን፤ መገንጠል ከጀመረ፤ የመገንጠል ፍላጎትና የብጥብጥ “ሱስ” በተለያዩ የክልሉ “የነቀዙ/ኮንታሚነትድ የሆኑ” ሊሂቃኖች ምክንያት ሌላ መነታረኪያ ርዕስ እየፈጠረ “ግንጠላው ሌላን ግንጠላ እያራባ”፤ እየተከፋፋለ “የት አንደሚቆም” ሳይታወቅ ይቀጥላል ፤ማቆሚያ ድምበርም የለውም (ኤርትራ ውስጥ ዛሬ የግንጠላ/ብሔር ጥያቄ ያነገቡ ብዛት አላቸው)። እስከ……ወዲያኛው እየተገነጣጠለ እራሱ በራሱ እያቃጠለ እያፈረሰ ሁከትን የሚያራባ “የዱር ሕሊና” የተሸከሙ ሰዎች “ፋንታሲ ዓለም” ሆኖ ከንቱ የሚሆነውም ለዚህ ነው።

“ኢማጂነሪ ጠላት/ እየፈጠረ ሰላም በማደፍረስ ፓኪሰታን/ምስራቅ/ምዕራብ ቤንጋሊ/ አፍጋኒስታን ከሕንድ ሲገነጠሉ ያጋጠማቸውና አሁንም ያላባራ መከራ የዚህ ውጤት ነው። ባጭሩ ግንጠላም ሆነ የነገድ ዲሞክራሲ፤ “ሽብር፤ግርግር” ማለት ነው። ሽብር መብት አይደለም። እነዚህ ክፍሎች በሽብር ወንጀል የምንከሳቸው የአማራን ሕዝብ ሰቆቃና ህይወት ያጠፉ ወንጀለኞች የሚመሩት እንቅስቃሴና የቀየሱት ትግል ነውና “ከመብት ጥያቄ ጋር አይገናኝም”።

ተቃዋሚዎችና ሚዲያዎች በሰሞኑ የኦሮሞ ተማሪዎች እንቅስቃሴ ያላቸው አሳዛኙ ግንዛቤ ስል ምን ማለቴ ነው?

ኦሮሞ ተማሪዎች “ባይተዋሮች ናቸው፤ የሰሞኑ የኦሮሞ ተማሪዎች ‘ባይተዋርነት’ ያመጣው እንቅስቃሴ ነው። እንዲህ ስልስ ምን ማለቴ ነው? ሰሞኑ አንድ ምሁር ወዳጄ እሱን ከመሰለ ምሁር ወዳጁ በሰሞኑ ኦሮሞዎች እንቅስቃሴ ያደረጉትን የወዳጅነት ሃሳብ ልውውጥ ግንዛቤዬን እንዲጎለብት ብሎ የተነጋገሩበትን አንዳንዳንድ ውይይቶችን አጫወቶኝ ነበር። ሙሁሩ እንዲህ ይላሉ፦

መቼም fantasy የኢትዮጵያ ልሂቃን መለዮ ነው።” (አሜሪካ ሜኔሶታ ውስጥ የሚኖር)ፕሮፌሰር እስቄል ገቢሳ ሰሞኑን በኦሮሞ ሚዲያ ኔትወርክ ቀርቦ፤ ይህ የኦሮሞ ተማሪዎች ንቅናቄ መሪ የለውም፣ ምክንያቱ እና መፍትሄው ምን ይመስሎታል?” ተብሎ ተጠየቀ። ህልመኛው የተደናገረውፕሮፌሰርአንገቱን በኩራት አቅንቶ የምሁርነት ማመላከቻ መነጥሩን ሽቅብ ገፍቶ ተናገረ፤

በታሪኩ ኦሮሞ የአንድ መሪ መሀበረሰብ አይደለም፤ ጥንትም ሆነ ዛሬ የኦሮሞ አብዮት የጋርዮሽ አብዮት ነው፡፡ መሪ አያስፈልገውም፡፡እንደውም የኦሮሞ ህብረተሰብ ነቅቶ መጠበቅ ያለበት አንድ መሪ እንዳይነሳ ነው፡፡ የገዳ ስርዓት በኦሮሞ ህዝብ ደም ስላለ አንድ መሪ አያስፈልገውምመሪው በደሙ ያለው የገዳ ስርዓት ነው፡፡” … ሲል ለተጠየቀው መለስ ሰጠ።

እስቄል እንደሚያልመውም ይህ አብዮትም ኦሮሚያን በመገንጠል በስኬት ሲጠናቀቅ ከሀያ አምስት አመታት በላይ የአሜሪካን ሊበራል ዲሞክራሲ ካጣጣመበት አመሪካ ከሌሎች ሌሎች ጓዶቹ ጋር በመሆን የአዲሲቷን ኦሮሚያየቦኩን” በትረስልጣን በመጨበጥ ይህንን መሪ አልባ መሀበረሰብ ለመምራት ነው፤ ወደ ተስፋይቱ አለም፡፡ እንደ እውነቱ ከሆነ ግን በአለም ዙሪያአብዮት” ያለመሪ” እናጥርት ብሎ ባልተደነገገ አላማ” ተደርጎ አያውቅም፡፡ በአመራሩ፣ በአላማውና በአስተዳደራዊ መዋቅሩ ያልተቀናጀ ንቅናቄግርግርእንጂአብዮትአይባልም። የገዳ ስርዓት በኦሮሞ ህዝብ ውስጥ በተግባር የለም፡፡ ያለው በሊህቃኑ ምናባዊ rhetoric ውስጥ ነው፡፡

እንዲህ ያለም ንቅናቄ ውጤት አይኖረውም፡ ይህፕሮፌሰርምንድን ሚቃዣው፤ የኦሮሞን ህዝብንስ በተግባር ምን ያህል ያውቀዋል? እኔ መቼም አያቴ እንኳን ይህንን ደንባራ ዘመን ሳያዩ ሞቱ ነው ያልኩት። እንደ እውነቱ የኦሮሞ ወጣት እንዲሁም የኦሮሞ ማህበረሰብ በጠቅላላው በገዛ ሀገሩ ባእድ ከተደረገ እና በሀገሩ ባይተዋር መሆን ከጀመረ አሁን ሐያ አምስ ዓመትተ ሆኖታል፡፡ እኔ ይህንን ከስተዋልኩ ቆይቻለሁ። ሐረማያ በሰራሁበት ዘመን የኦሮሚያ ተማሪዎች ሁሉን እርግፍ አድርገውየባዕድ ኑሮ” ሲገፉ አይቻለሁ፡፡ ከግሩፕ ስራ አስተባባሪነት እስከ ትልልቅ ዩንቨርሲቲ አቀፍ የክበብ እንቅስቃሴዎች በተሳታፊነት እንኳንየሉበትም”፡፡በአመራር መሳተፍ” እማ አይታሰብም፡፡ በዩንቨርሲቲ የተጓዳኝ የትምህርት እንቅስቃሴ ያልዳበረ የአመራር ችሎታ በኋላ ከወዴት ሊመጣ ይቻለዋል? ከየክልሉ ከሚመጡ ተማሪዎች ጋር ያላቸውመሀበራዊ ተራክቦ” እጅግ ዝቅተኛ ነው።

 ይሄ ነገር ውሎ አድሮ ሀገር ይጎዳል፡፡ የኦሮሞ ተማሪዎች በተጓዳኝ ክበባት ተሳታፊ ለመሆን የማይፈቅዱበት፣በባይተዋርነት ከመሀበራዊ ተሳትፎ እራሳቸውን ያገለሉበት ምክንያት ተጠንቶ ከወዲሁ መፍትሄ ካልተበጀለት ተተኪ የአመራር ችግር ይከሰታል በማለት ለባልደረቦቼ አማክሬ ያተረፍኩት የፌዝ መሳለቂያነትን ብቻ ነበር። አሁን ውጤቱ መታየት ጀመረ። እስቄል ግን አልገባውምገዳ ምናምን ይላል፡፡

የገዳ ስርዓትየጦርነት ግዜ ስርዓት” ስለመሆኑ እና ከዚህምጠባዩ” የተነሳ ዛሬዲሞክራሲከምንለው ፅንሰ ሀሳብ ጋር ምንም ተፈጥሮአዊ ቁርኝት ወይ ተመጋጋቢ-ተግባቢነት የለውም።  የዚህ የኦሮሞ ማህበረሰብ በሀገሩ ባይተዋር የሆነበት ምክንያት ጥልቅ የባህል እና የታሪክ መሰረት ያለው ሆኖ እናገኘዋለን። በሚሶዮንያን ሴራ በብሄረሰብ የፖለቲካ አደረጃጀት ስም የኦሮሞኛ ቋንቋበላትን ፊደላት” እንዲፃፍ ሲደረግ ሰፊው የኦሮሞ ህዝብ ለዘመናት በፍቅርም ይሁን በጠብ ከተቀረው የኢትዮጵያ ህዝብ ጋራካዳበረው የባህል መሰረት ተነጠለ”። በዚህም ሳይበቃ የሰሜን ኢትዮጵያን ህዝብ ከደቡብ በዘርና በፖለቲካድልድይ” ሆኖ ለዘመናት ያገናኘው የሸዋ ህዝብና መኳንንቱ በታሪክ ፊትበወራዳነት” እንዲቀርቡ ሲደረግአኩሪ ታሪኩን” አጣ። ብሽሽታቸው እስኪላጥ ፈረስ ጋልበው ዘመናዊ ኢትዮጵያን የመሰረቱት የሸዋ የኦሮሞ መኳንንትአሸብረቂ ታሪክ” ተሰርዞበባንዳነት” ተዋርደው ቀረቡ። በህወሓትሴራ” የሸዋ ግዛትከስድስት ክልሎች” ባላይእንዲከፈል” ተደረገ። ከዚህም የተነሳ የደቡቡና/በተለይ የኦሮሞና/ የሰሜኑ የኢትዮጵያታሪካዊ ቁርኝት” ተበጠሰ።

በድምሩ በተለይ የኦሮሞ ወጣትበሀገሩ ባይተዋርነትን” አተረፈ፡፡ ሀገራዊ ራዕዩም ተኮላሸ፡፡ ከተማዬ ሚለው አዲስ አበባአለ አግባብ” በኦሮሚያተስፋፋ” በማለትግንባሩን ለጥይት ሲሰጥ”፤ አባቶቹ የሞቱለትየሀገሩ ዳር ድንበር” ሲቆረስ እናለሱዳን ሲሰጥ” ብምን አገባኝነት ቆሞተመልካች” ሆነ።ለመደምደም ያህል የኦሮሞ ሊህቃን እንደሌሎቹ የኢትዮጵያ ልሂቃን በነበረው እየሞላ፤ የነበረውን እያዳበሩ ከመሄድ ይልቅ አፍርሰው ጀማሪዎች ሆኑ። እሰካሁን እንከዋን የክልሉ ህገ መንግስትሁለቴ” ለውጠዋል፡፡ ባነድራውንም ግዜው ሲደርስሊለውጡት” ተዘጋጅተዋል፡፡ ቢመርም እውነቱ ይህ ነው፡፡"……

 ይላሉ ምሁሩ ከወዳጄ ጋር ያደረጉት ስለ ሰሞኑ የኦሮሞ ተማሪዎች እንቅስቃሴ ውይይት።
አውነትም፤ fantasy የኢትዮጵያ ልሂቃን መለዮ ነው”። ያሉት ምሁሩ፤ተገንጣዮቹ ኢትዮጵያዊያን አይደለንም ቢሉም፤ “ክሕደቱን አኑሮው” በጨዋ ሞራል መናገራቸው ነው እና በኢትዮጵያ ሊሂቃን መለዮ ነው ሲሉ “ኦሮሞ” ነን የሚሉትንም ለመጨመር ነው። እኔ ደግሞ የምጨምረው “ፋንታሲው/fantasy” በሊሂቃኖቹ ብቻ ሳይወሰን በሚዲያ ባለቤቶችም ጭምር ነው።

አንድ ምሳሌ ልስጣችሁና ልደምድም”። ወዳጄ ዶከተር አሰፋ ነጋሽና ፕሮፌሰር ጌታቸው ሃይሌ “ኢትዮሚዲያ” በተባለው ሚዲያ “ጠንከር” ያሉ “ለውይይት የሚጋብዙ” ምሁራዊ ትንታኔአቸው ለሕዝብቻን እንዳይተላለፍ የታገዱ ጸሐፊዎች ናቸው። የዚህ ሚዲያ አዘጋጅና ተባባሪዎቹ፤ እንዲሁም የመሳሰሉ ሚዲያዎች ‘ሥልጣን’ ላይ ቢወጡ ምን ያህል “ጨቋኝ” ይሆኑ እንደነበር ከወዲሁ ማየት ትችላላችሁ። ካሁኑኑ የመጻፍ መብት ሲያግዱ፤ መጪዋ የአገራችን ዕድል፤ ምን እንደምትመስል ግንዛቤ ካጠራቸው ከነዚህ “የሚዲያ ታይራንት” ግለሰቦች  ይሰውራት የምለውም ለዚህ ነው።

ታሪኩ እንደዚህ ነው፦
ዶክተር አሰፋ ነጋሽ ብቃት ያለው የፖለቲካ ተንታኝና የሕክምና ምሁር ነው። ደ/ር አሰፋ ነጋሽ፤ የኔው ብጤ ነው። “የፖለቲካ ኮረክትነስ/ድብብቆሽ/አድርባይነት/አይቶ እንዳላዩ…” ሆኖ ማለፍ የማይወድ ሰው ነው።  ለሚዲያዎችም ሆነ ለተገንጣዮች “በእሱና በእነሱ መካከል” በሕዝብ ፊት ዲቤት/ውይይት/ እንዲደረግ ብዙ ጊዜ በይፋ “ጥሪ” አድርጎላቸው፤ ሊገጥሙት አልፈለጉም። “አጀንዳቸው” ዋጋ ቢስ መሆኑን የማጋለጥ በቂ እውቀትና ብርቱ ትንተና ማድረግ እንደሚችል ስለሚያውቁ ፤ እንዲሁም ወያኔዎች/ኦነጎች/ኦብነግ፤ በፓርቲ ስም፤በሕዝብ ስም….ወዘተ….ብዙ ወንጀል እንደሰሩና incredibly corrupt and  visionless/እጅግ የነቀዙ፤ራዕዬ-ቢስ/ መሆናቸው ማሕደራቸው በሚገባ ስለሚያውቅ፤ እስካሁን ድረስ ደፍረው “ግብዣው” ለመቀበል አልደፈሩም። ታዲያ የሕክምና ሊቅ እና የፖለቲካ ተንታኝ ዶ/ር አሰፋ ነጋሽ “Why Have the Amaras Once Again Become Victims of Ethnic Cleansing by TPLF? By Assefa Negash, M.D. 18th of April 2012 የሚል በ5 ክፍል የቀረበ ጽሑፍ፤ ለሕዝባችን እንዲዳረስ ‘ለኢትዮ-ሚዲያ’ አዘጋጅ ልኮለት፤ሕዝብ የራሱን ግንዛቤ እንዳይወስድ ሲያግድ ለተገንጣይ ቡድኖችና፤ አማራ ይቅርታ ይጠይቅ እያሉ ጥላቻን የሚዘሩ “የነገድ አቀንቃኝ ፖለቲከኞች” ግን ፕሮፓጋንዳቸውንና ፎቶግራፋቸውንም ጭምር ሳይሰለች ለብዙ አመታት እስከዚቺው ደቂቃ ድረስ እየዘረጋላቸው ይገኛል። ኢትዮ ሚዲያ ብትጎበኙ የምታዩት የተገንጣዮችና ጠባብ ጎሰኞች ፎቶግራፍና የፕሮፓጋንዳ ቅስቀሳ ጹሁፎችን ነው።
ደ/ር አሰፋ ነጋሽ ዘገባ እንዲህ ይጀምራል፤
“A pregnant woman who only gave birth to a child during the night was thrown out on the street the following morning along with her mattress and child who is just a few hours old (neonate). Pregnant Amara women have been forced to flee their homes. Many children as young as 8 months of age have been locked up in prison along with their lactating mothers and they have nothing to eat or drink thereby suffering from hunger. ……”
 እያለ በ5 ክፍል ተዘጋጅቶ ከአገር ባማርኛ የተዘገበውን ወደ እንግሊዝኛ ተርጉሞ የዘገበው የአማራ ሕብረተሰብ ሰቆቃ እንዲለጥፈው የላከለት ጽሁፍ “አቶ አብርሃ በላይ” አላትምም ሲሉ እምቢ አለ። በዚህ አብርሃ እና ደ/ር አሰፋ ነጓሽ የደብዳቤ ምልልሳቸው እንዲህ ይነበባል። (ካሁን በፊት ለጥፌላችሁ እንደነበር ትዝ ይለኛል)
Greetings from Holland. I am sending you an article which has been broken down into five parts. Please post it on your website. You may not like all the content of the article, but I trust that you would accept the right of contributors like me to hold different opinions. I fully take responsibility for any opinion I express in this article and as I have stated clearly at the end of my article, I am ready to accommodate any perspective that challenges my views. So let me know whether you post it or not.
 With best regards,
 Assefa Negash

የአቶ አብርሃ በላይ አምቢታ የእምቢታ መለስ እንዲህ ይነበባል፦
From: Editor <editor@ethiomedia.com>
Date: 19 april 2012 08:44:30 CEST

Dear Dr Assefa Negash,
 My apologies for my delayed response!
To begin with, this short reponse shouldn't in anyway be mistaken for an invitation to engage you in a dialogue over the differences you and I've over the situation in Ethiopia.

For instance, a sentence from your piece reads: "In present-day Ethiopia the only people who are not adversely affected by this rule are the Tigreans who as members of the ruling Tigrean regime have every right to settle in every part of Ethiopia and prosper even at the expense of others."

We are worlds apart, brother.

For you, TPLF means the Tigrai people and vice versa.

Though I wrote for years to persuade fellow compatriots like you that the ruling class is strictly an anti-Ethiopia mercenary class, such literature has fallen on deaf ears because brothers like you have made up their minds that Tigrians are in power and the people of Tigrai are beneficiaries of the 'Tigrian regime.'

That is the whole point in a nutshell.

But again, you are entitled to your opinion as I'm to mine. I'm not going to post your article because I believe - with all due respect - your article is not only wrong but also misleading, and detrimental to the unity of the Ethiopian people.

I'm writing this as an Ethiopian journalist, and not because I was born into a Tigrian family. I would have rejected (and I've done it several times in the past) if I were asked to post an article that in anyway tarnishes the image of the Amhara, Oromo etc people. For instance, a few days ago, an article written by Prof Getachew Haile about the Oromo people was removed from our website shortly after it was posted because there were lines that cast our Oromo people as 'invaders' and much worse.
 I hope such denial of service wouldn't in any way strain our friendship.
 Warmest regards,
Abraha Belai, Editor

የአማራ ሕብረተሰብ ሰቆቃ ለመላ ዓለምና ለሕዝባችን ለመንገር በመረጃ የተዘጋጀ እንዳይሰራጭ ያገደበት ምክንያት መልስ ሲሰጥ የሰጠው ምክንያት በራሱ ቃል “brothers like you have made up their minds that Tigrians are in power and the people of Tigrai are beneficiaries of the 'Tigrian regime.' ይላል። ስለሆነም ትግሬዎች ሥልጣን ላይ ሳይወጡ ሥልጣኑን ተቆጣጥረውታል ማለትህና፤ትግሬዎች በዚህ ሥርዓት ተጠቃሚ ሳይሆን ተጠቃሚ ነው…” የሚል እምነት ስለያዝክ “አልለጥፍልህም!” ሲል ማጠቃለያ ምክንያቱ ይህ ብቻ መሆኑን ገልጾለታል። That is the whole point in a nutshell. ሲል በግልጽ አምቢታው ግልጽ አድርጛል። ትግሬዎች ሥልጣኑን ተቆጣጥረውታል ለማለት “አማራን ሰቆቃ” ምክንያት አድርገህ በሽፋን የመጣኸው ‘በወያኔ ዘመን ትግሬዎች ተጠቃሚዎች ናቸው፤ ትግሬዎች ሥልጣን ላይ ናቸው” ለማት ስለፈለግክ ነው” ሲል ጽሑፉን ላለማተም አብርሃ  የሰጠው ምክንያት ያ ነበር።

ተቃዋሚዎች ነን እያሉ እነዚህ ውጭ አገር የሚኖሩ “ሚዲያዎች” ኢትዮጵያዊያን አርበኞች የሚጽፉትን አስተያየት አናስተላልፍም እያሉ፤ ተገንጣዮች ግን “በቀጣይ” የሽፋን መብት፤ከነሰንደቃላማቸው በቪዲዮ እየተቀረጸ ሽፋን ሲያደርግላቸው አይተናል። እነዚህ በተቃዋሚነት የቆሙ “ነፃ ሚዲያ ነን የሚሉ ነፃነት የሚያፍኑ ሚዲያዎች” ግማሾቹ  ከጠባብ ጎሰኛነት ስሜት አጥር መውጣት ያቃታቸው ሲሆኑ፤ አንዳንዶቹ ደግሞ “በፖለቲካ ድርጅት ፍቅር” የተተበተቡ “ድርጅት ሙርኮኞች” ናቸው። ወደ “ታች የሚንሸራተቱ” ትናንሽ ሕሊና ያለቸው መሆኑን ብቻ ሳይሆን፤ የፖለቲካው ግንዛቤአቸውም እጅግ የጫጫ መሆኑን ነው የሚያሳየን።

የአብርሃ ክርክር ከስሜት የማያልፍ ፤ጭብጥ የሌለው መከላከያ ነው እየሞገተ ያለው። ሌላው ዝርዝር የጥናት ድጋፍ ያላቸው መረጃዎችን እንተወውና “ጥልቅ ምርምር” የማይጠይቀውን የወልቃይት ሕዝብ መሬት በትግሬዎች የመነጠቁ እውነታ/ ’ሄጂመኒ/ አነክሴሽን’፤ ትግሬው ሰፍሮበት በዓይኑ እያዬ (መነጋጋር ጀምርን በነበረበት ጊዜ ይህን መረጃ ለአብርሃ በላይ በስልክ ነግሬው ነበር)፤ ‘ትግሬ አልተጠቀመም፤ስልጣን ላይ አይደለም’ ፤ ብሎ መካድ የግንዛቤ እጥረት ብቻ ሳይሆን፤ አብርሃና መሰል የትግሬ ሊሂቃን ለራሳቸው ግልጽ በሆነ፤ እነሱ በሚያውቁት ምክንያት ለኛ ግልጽ ባልሆነ መከራከያ “ትግሬ አልተጠቀመም፤ሥልጣን አልያዘም” እያሉ ይክዳሉ። ይህ ደግሞ “እስር ውስጥ  ያለው “አብርሃ ደስታም” ጭምር ሲያካሂደው የነበረ መስመር ነው።

የመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ፖለቲካ ሳይንስ መምህር የነበረው ታሳሪው አብርሃ ደስታ “ወያኔ ዘረኛ አይደለም፤ ወያኔ በግለሰብ እንጂ በማሕበረሰብ ላይ፤ማለትም በአማራ ላይ ዘረኛነት አላካሄደም።” “የግለሰብ አፓርታይድ ግን አካሂዶ ሊሆን ይችላል።” “ወያኔ አፓርታይድ አይደለም”፤ “ትግሬ ስልጣን ላይ የለም፤ትግሬ አልተጠቀመም”፡ “ጃዋር መሐመድ ፖለቲካ ይመቸኛል”….ወዘተ….ወዘተ….ሲል ይከራከር እንደነበር የሚታወስ ነው። የወያኔ ፖሊሲ “በአማራ ሕብረተሰብ” ላይ የጻፈው “ቁልጭ ብሎ” እየተነበበ ያለው የወያኔ የትግል መነሾ፤ “አብርሃ ደስታ” ሙልጭ አድርጎ ሊያሞኘን ይፈልጋል።

ሚዲያዎችም በዚህ ዓይነት “ስካርና ክሕደት” አልፎም “አጉል የፖለቲካ ጊዜያዊ ድጋፍ ለማግኘት በእወደድ ባይነት” አብረው አየነጐዱ ናቸው። እንዲህ ያለ ጉድ ተሸክመውም ቢሆን ዛሬም ለጠባቦችና ለገንጣዮች እነዚህ ሚዲያዎች ክፍት አድርገው እያገለገሉዋቸው ነው።

ባይተዋር ኦሮሞ ተማሪዎችም፤ “ማይምነትን” ያለበሷቸው የኦሮሞ “ፋሺስታዊ ምሁራን” ከመቃወም ይልቅ አገራቸው ኢትዮጵያን በመካድ፤ በጠባብ ክልል ተከልለው “ወደ ፋሺዝም” እያመሩ “ግራ በመጋባት ላይ ናቸው”። ወዴት እያመሩ እንደሆነም በቅጡ ይወቁት እንጂ ምን አንደሚገጥማቸው አላወቁትም። መፈክራቸውና ንግግራቸው የሚደመጠው ኦሮምኛ ስለሆነ፤ የተቀረው ኢትዮጵያ ህዝብ ምን እያሉ እንደሆነ ማወቅ አልቻለም። እየተገለሉ ባይተዋርነት እያጠቃቸው ነው የምልብትም ነጥብ ለዚህ ነው።

ሕዝቡ ምናቸው ተረድቶ ይደግፋቸው? አገራዊ የመገናኛ ቋንቋችን አማርኛ እንዳይናገሩና እንዳይማሩ በላቲን ፋሺስታዊ ሊሂቃን ፖሊሲ ታግደው ወደ ድቅድቁ የድንቁርና “ጭለማ” ተገፍትረው ሙሉ በሙሉ ባሳዛኝ ሁኔታ ተፈርዶባቸው እስከወዲያኛው በማይምነት ሰንሰለት ታስረው ገበተዋል።ሕዝባችን በምናቸው ይረዳቸው?

ኦሮምኛ እንኳን መላው አገሪቱን በ24 አመት ለማስተዋወቅ ቀርቶ፤ ካሁን ወዲያ በ700 አመት ውስጥም ሕዝቡ እንደ አማርኛ ተሎ አገራዊ መገናኛ አያደርገውም። ምክንያቱም ቋንቋ ለመስፋፋት “የራሱ ልዩ ሂደቶችና ሕጎችን” ተከትሎ በገበያና በመሳሰሉት ያደገ እንጂ በተጽእኖ አይመጣም።  ያም ቢሆን እጅግ ለዘመናት ዕድሜ ይፈጃል። ኦሮሞዎች ደግሞ የተከተሉት “ላቲን” ነው። ከተቀረው ሕዝብ ጋርም እንዳይገበያዩ እና እየተዘዋወሩ እንዳይሰሩ “በክልል ቋንቋቸው ታስረው፤ እራሰቸው ባይተዋር ዓለም ገብተው፤ ወኪሎቻቸው ሳይቀር “በሚዲያና በፓርላማ ሲነጋገሩና ሲጠይቁ” ባስተርጓሚ ነው መልክቶቻቸው የሚያስተላልፉት። አሳዛኙ ክስተት ይኼ ነው። በገዛ አገራቸው “ኬኒያዎች” ሆነዋል።

የሊህቃኑ ደካማነት ቢያስቅም፤በወጣቱ ላይ የቋንቋ ጥላቻ እንዲያድርበትና፤አገራዊ የመረዳጃ “ቋንቋ” አማርኛን “የመማር እገዳ” የጫኑበት ወንጀል ግን እጅግ አሳዛኝ ነው። ውሎ አድሮ ይህ በራስ ባይተዋርነት ችግር እንደሚመጣ እናውቀው ነበርና፤ ዛሬ ያልነውን ነገር ጊዜው ደርሶ፤ ተማሪዎቹ ሲሰለፉ፤መልእክት ሲያስተላልፉም ሆነ መፈክር ሲያስተጋቡ፤ ምን እያሉ እንደሆነ “የኢትዮጵያ ሕዝብ ሊገባው አልቻለም”። ስለሆነም፤ ሕዝቡም እንደ ዩክረይን እና ዓረብ ሰልፈኞችች የሚሉትን ሳይገባው በቴ/ቪዥን እያያቸው፤ ምን እንደሚሉና አንደፈለጉ ሳይገባው “አግራሞቱ” በታዛቢነት እየቀጠለ ነው።

በሌላ በኩል አስተርጓሚ ሆነው ሚቀርቡት (የኦሮሞ እንቅስቃሴ መረጃ ለሕዝባችን የሚነግሩት) ደግሞ ተቃዋሚ የሚባሉት እነ ጠባብ ብሔረተኛ አቀንቃኙ መራራ ጉዲና እና ተምበርካኪው ጸረ አማራው “የሰማያዊው ፓርቲ መሪ” ተብየው ይልቃል ጌትነትና መሰል ተቃዋሚዎች በኩል ነው። አስተርጓሚዎቹ እነዚህ ባይኖሩ ሕዝቡ በምናቸው እንደሚገባው እግዚሔር ይወቀው። እኛም ባስተርጓሚ ነው የምንረዳቸው እንጂ ምን እንደሚሉ “እኔ ራሴ” አይገባኝም።

የእነዚህ ደላላ አስተርጓሚ ተቃዋሚዎች፤ ትክለሰውነት እየተቀባበሉ ሳይሰለቻቻው ለ15 ቀመት “የፕሮፓጋንዳ ሽፋን” የሚሰጡዋቸው ደግሞ በበኩላቸው “ተቃወሚ ሚዲያዎች” ናቸው።  ሆን ብለው የነዚህ ተምበርካኪ ሰዎች ተክለሰውነት እያሞገሱ በድምሩ ካንዳንዶቹ ጋር ለ24 አመት አብረው ዘልቀዋል። አስገራሚው ግን፤ እያደር ቃርያ የመሆናቸው ትዕይንት ሕዝቡ ቀስ በቀስ የገባው ይመስላል (ዲአስፖራ ጀሌዎችን ትተተን ማለት ነው)።

ሕዝቡ ቆራጥ መሪ አጥቶ፤ ወያኔ ለ24 አመት ለምን በብልግና እየተጨማለቀ እንደቆየ የሚዲያዎችና የተቃዋሚዎች “ደላላነት፤ተባባሪነት፤ አታላይነትና እከከኝ ልከክልህ” ባሕሪ መሆኑን አውቆታል።ሕዝባችን እነዚህ “ሚዲዮክር” (ዕርባና ቢስ) ተቃዋሚዎችና ሚዲያዎች፤በአፈጮሌነት እየተነዱ እስከዚህ ድረስ ደርሰዋል። ትናንት እንዳልረቡዋችሁ ሁሉ ዛሬም ሆነ ነገ እንደማይረቡዋችሁ እወቁት።

የኦሮሞ ተማሪዎችም ይህ ሁሉ የኦሮሞ ወጣት በወያኔዎች ጥይት ሲረሸን፤ እውጭ አገር ተቀምጠው ምቾት የከበበው ኑሮ የሚመሩ እነ “ኢብሳ ጉተማና እነ ጃዋር፤ እነ እዝቄልና እነ መገርሳ…… ም ሆኑ የታወቁ የኦነግ ጀሌ ሙዚቀኞች” “ግፋ በለው” “አሮሚያ ኬኛ” ከማለት አልፈው ወደ “ኦሮሚያ ኬኛ” ጠመንጃ ማንገትም ሆነ ወደ ሰልፉ ወላፈን “እራሳቸውና ልጆቻቸው ልከው ለመቀላቀል” እንደማይደፍሩ “ አገር ውስጥ ያሉት ተማሪዎቹ፤ከልባቸው ይህንን የሊሂቃን አታላይነት “ከመኔሶታ አዳራሽ መፈክር ማስተጋባትና በቲቪ/ራዲዮ መለፍለፍ አልፈው፤ እራሳቸውንና ወጣት ልጆቻቸውን መስዋእት ለመሆን ወደ ኢትዮጵያ/ኦሮሚያ ወደ እሚሉት ክልል ትግሉን ለመምራት ዝግጁ አንዳልሆኑ” ተማሪዎቹ ቀስ በቀስ እንደሚረዱት ያውቃሉ። ከዛው ማሃምነትና ባይተዋርነት ለመላቀቅ የጊዜ ጉዳይ እንጂ “የምንሰማው ጉድ” ሩቅ አይሆንም።  

እነዚህ ግፋ በለው ተገንጣይ አቀንቃኞች፤ እንኳን ወደ ኢትዮጵያ መጓዝ ቀርቶ ፤ጠመንጃ እንካችሁ ወደ እሚላቸው ወደ ኤርትራ ሄደው የሚዋሹላትን “ኦሮሚያ” የምትባል “ነፃ” ለማውጣት ለመሄድ አልከጀሉም። የፒዛ “ሱስ” ሃይለኛ ነውና፤ የሚያድርጉት አታላይ ባህሪያቸውን ምን እንደሚመስል እራሳቸው ያወቁታል።ምስኪን የኦሮሞ ገበሬ ልጅ ግን ባይተዋር ሆኖ፤ የፖለቲካቸው ሰለባቸው የመሆኑን ክስተት እጅግ ያሳዝናል።    

ለማጠቃለል
 እየታየ ያለው የኦሮሞ ተማሪዎች እንቅስቃሴ ክልላዊ የነገድ ጥቅም አስከባሪ ከመሆን አልፎ፤ የመገንጠል ጥያቄን እና ባይተዋርነትን የሚያጎለብት “ኢትዮጵያዊ ግንዛቤ የሌለው” ሥር ነቀል የስርዓት ለውጥ የማያመጣ፤የአገሪቱን አስኳል አናግቶ “መሪ የሌለው ወደ አናርኮ ፋሺዝም” የሚመራ፤ “ራእዬ ቢስ” የተገንጣዬች አብዮት ስለሆነ ጥንቃቄ ያስፈልገዋል።  ፓኪስታን/ኤርትራ/ሶማሊ/….የመሳሰሉ በጭቆና፤በወረበሎች፤ በነገድና በሃይማኖት ግጭት እየታመሱ በመዋለል፤ ለቀውስ የዳረጋቸው ምክንያት የዛው አካባቢ ምሁራኖች “የነቀዘ ሕሊና” ስራ ላይ በመዋሉ ነው።  ኢትዮጵያ ውስጥም “በወንጀል የተጨማለቁና የተሳተፉ ነብሰገዳዮችና ፋሺስት ርዕዮት ያነገቡ ድርጅቶች ስለሆኑ” እገዳ አካልተደረገላቸው፤ እጣ ፈንታው የነ ፓኪስታንና የነ ደቡብ ሱዳን “ግርግር” ትክክልኛ ቅጂ በአገራችንም ውስጥ ይደገማል።

ወደዚያውም እያመሩ እንደሆነ ተከታዮቻቸው በጥንቃቄ ሊያዩት ይገባል። ቴምፐራሪ ፊክስ “ጊዜያዊ ምርቃና እንጂ” ዘላቂ “ኢፎርያ” የተላበሰ “እፎይታን” አያመጣም።ይቀጥላል…….አመሰግናለሁ- ጌታቸው ረዳ (Editor Ethiopian Semay) getachre@aol.com