ታላቁን ምስጢር
ላፈነዳው
ነው!
ወደ አዲስ አበባ የገቡት የአብይ ሸኔዎች!
ክፍል 2
ጌታቸው ረዳ
12/8/24 Ethiopian Seamy
አዎ የኦነግ ታጣቂዎች እጃቸውን በሰላመ ሰጡ እየተባለ አብይ
አሕመድ በለመደው አጭበርባሪ ባሕሪው ሊያጭበረብር ሞክሯል። እውነታው ግን እነኚህ ኦነግ የተባሉ “ታጣቂዎች” በአብይ አሕመድና በለማ
መገርሳ ድጋፍ ሰጪነትና መስራጭነት የተመሰረቱ አምሐራን ሲያርዱ የነበሩ የአብይ አሕመድ ታጣቂዎች ናቸው።ማስረጃው ከታች አቀርባለሁ።
ብዙ ሰዎች “ምንድነው ይህ ሁሉ ክብርና ማስጎብኘት ማሽሞንሞን”
እያሉ ሲገረሙ አንብቤአለሁ። ሰዎቹ ብዙ መረጃ ስላልተከታተሉ ስለሚሆን እንጂ ታጣቂዎቹ የራሱ የአብይ አሕመድ ልጆች ናቸው።
ይህንን የአብይ አሕመድ ምስጢር ያጋለጠው ማስረጃ ላቅርብ።
የሰነዱ ርዕስ እንዲህ ይላል፡
<<ታላቁን ምስጢር ላፈነዳው ነው!>>
ይላል
ይህንን ምስጢር ያጋለጠው “አፈንዲ ሙተቂ” ይባላል። አፈንዲ
ጥሩ ተንታኝ (ፀሐፊ፤ ጋዜጠኛ) እና የምሥራቅ ኢትዮጵያ “አክራሪ” ነው። በትምህርቱ ከላይ እራሱ እንዳስቀመጠው
“Ethnographic Researcher and Author” ነው።
ታላቁን ምስጢር ላፈነዳው ነው! (አፈንዲ ሙተቂ)
በሚል ምስጢሩን እንዲህ ሲል ያፈነዳዋል።
ኦነግ
የኦነግ መሥራቾች
እነ ኤሌሞ ቂልጡ ፤ ሁንዴ (አህመድ ተቂ)
በቂላ ቡሌ ፡ ብክር ገሎ ፤ ባሮ ቱምሳ ፤ ሙሄ አብዶ
ሌንጮ ለታ፤ ዲማ ኖጎ ፤ መገርሳ በሪ፤ ዳውድ ኢብሳ
፤ ገላሳ ዲልቦ፤ ገዳ ገመዳ ፤ ኦቦማ ምትኩ ፤ ...ወዘተ ነበሩ።
ይልና ፤
ከዚያም የኦነግ ተረከዝ የተከተለው የአብይ አሕመድ ስሪት
የሆነው የአምሐራን ሕዝብ ለማረድና ለማሳደድ የተደራጀው አብይ አሕመድ ወደ ሥልጣን ከመጣ ወዲህ ሥሙን የገነነው “ኦነግ ሸኔ” የተባለ
“አራጅ ድርጅት” መሥራች አባላት ስም ዝርዝር እንዲህ ያቀርበዋል፡
ኦነግ ሸኔ
የኦነግ ሸኔ” መስራቾች ድገሞ
እኔ አፍንዲ ሙተቂ፤ ጃዋር መሐመድ፤
ኩምሳ ድሪባ (ጃል መሮ)
ያያ በሺር፤ ህዝቄል ገቢሳ፤ ሀምዛ ቦረና ፤ ግርማ ጉተማ፤ ሰለሞን ኡንጋሼ፤ ጋዲሳ
ሆማ፤ ነጃት ሀምዛ ነን።
ለምሥረታው የሚያስፈልጉ ግብአቶችን የሚያሟሉልን ደግሞ ዶክተር አብይ እና ለማ መገርሳ ነበሩ።
ድርጅቱን የመሰረትንበት ቃለ ጉባም በእጄ ይገኛል።
>>
በማለት ከመስራች አባል አንዱ የሆነው “አፍንዲ ሙተቂ”
ለኢትዮጵያ ሕዝብ የተደበቀውበን ምስጢር ይፋ አድርጎልናል። ይህንን ሰነድ ይዤው ነበር ፤አሁን ወቅቱን ጠብቆ አስፈላጊነቱን ስላየሁት
እነሆ ምስጢሩን ለረሳችሁት ወይንም ለማታውቁት እንድታውቁት ጋብዣለሁ።
በዚህ አጋጣሚ <<ህዝቄል ገቢሳ>>
የተባለው በዝርዝሩ ላይ ስሙን የተጠቀሰው የኦነግ ሸኔ መስራችና የግንጠላ ፕሮፐጋንዲስት አንድ ነገር ልበልና ልደምድም። ታስታውሱ እንደሆን የበረራ ቀዳሚት አዲስ አበባ
ደራሲ የታሪክ ምሁርና አስተማሪ ‘’ፕሮፌሰር ሀብታሙ ተገኘ” ባለፉት ወራት ልደቱ አያሌውን በመተቸት << አምሐራ
ነኝ የሚል ሰው እንዴት ህዝቄል ገቢሳ ከመሳሰሉ ሰዎች ጋር ሄዶ ስብሰባ ያደርጋል? ለመሆኑ ከዚህ ሰው ጋር ምክክር የሚያደርግ አምሐራ
ምን የሚሉት አምሐራ ሊሆን ይችላል?>> የሚል ጥያቄ በማቅረብ ልደቱን እንደወረፈው ታስታውሳላችሁ? አዎ ፕሮፌሰር ሀብታሙ
ትክክል ነበር። ህዝቄል ማለት ወሎ የኦሮሞ መሬት ነው እያለ አገር
ቤት ገብቶ እስከ ወሎ ድረስ በመሄድ የስልቀጣ ፕሮፓጋንዳ ሲያካሂድ የነበረ “ጸረ አምሐራና ጸረ ኢትዮጵያ” የሆነው “የኦነግ ሸኔ
ድርጅት መስራችና በብዙ መንገድ “መወገዝ” ያለበት ነውና ፕሮፌሰር ሀብታሙ ስህተት አልነበረውም።
ህዝቄልን እዚህ ላነሳው የፈለግኩት አጋጣሚውን ለመጠቀም
ነው። አንዳንድ ውዥምብራሞች እንደ ሁነኛ ፖለቲከኛ አድርገው ቆጥረው
ለሚዲያ አቅርበውት እንደ አጋጣሚ አንዳንድ ሚዲያዎች ስጎበኝ “እኔ የማንም ድርጅት አባል ሆኜም አላውቅም፤ አይደለሁምም፡ ሰዎች
አንዴ ፋኖ ይሉኛል፤ አንዴ ኦነግ ይሉኛል” ሲል ሲናገር ሰሞኑን ሰምቸው ገረመኝ። ሁለት ሦሰት ሚደያ ሳደምጥ (ሁለቱ አፍቃሬ ወያኔዎች ሲሆኑ) አንዱ ድግሞ እንደ አብይ አሕመድ ሁሉንም የሚደምር “መላ ቅጡ” የማይታወቅ የሚዲያና የሕግ
ተማሪ የሆነው አውስትርያ ኗሪ የሆነው <<አራጆች የሚል ቃል ባንጠቀም ጥሩ ነው ፡ እኔ ሰው ስለመታረዱ አላውቅም>>
በማለት በሌላ አነጋገር << አራጆቹን
(ኦነግ - ቅጽል ስም “ኦነግ ሸኔ”) የታረዱት “ሰው” (አምሐራዎች) ስለመታረዳቸው
አላውቅም>> ፡ የሚል “የሃሳብ ገበታ” አዘጋጅ “ሞገስ ዘውዱ ተሾመ”
ሚዲያው ላይ ህዝቄል ገቢሳን ጋብዞት ህዝቄል “የማንም ድርጅት አባል እንዳልሆነ ወዘተረፈ..” ሲበጠረቅ ሰማሁትና
፤ ይህ ሰው ስንቴ ሊያሞኘን ሊሞክር ነው? አልኩኝ። ሃቁ ግን ህዘቄል ገቢሳ ኦነግ ሸኔ/ኦነግ/ መስራች አባል ነው።
እንዲህ ያሉት ሰዎች ናቸው በየ ኢትዮጵያ ሚዲያዎች እየተጋበዙ
የኦነግ ፖለቲካና ኦነጋውያን ባሕሪ የማያውቅን አድማጭ ሲያሞኙት የሚውሉት።
አብይ አሕመድ ስንቱን ወንጀልህን እንቁጠር?
ጌታቸው ረዳ (ETHIO SEMAY)