Thursday, April 9, 2020

ከድጡ ወደ ማጡ የወየኔ ተቃዋሚ ትግሬዎች የተጣዱበት ምርጫ ከጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ Ethio Semay)


ከድጡ ወደ ማጡ የወየኔ ተቃዋሚ ትግሬዎች የተጣዱበት ምርጫ
ከጌታቸው ረዳ
(ኢትዮ ሰማይ Ethio Semay)
ከድጡ ወደ ማጡ የወየኔ ተቃዋሚ ትግሬዎች የተጣዱበት ምርጫ
ከጌታቸው ረዳ
(ኢትዮ ሰማይ Ethio Semay)
ለብዙ አመታት በፖለቲካው መድረክ የቆያችሁ ዜጎች ስለ የወያኔ ተቃዋሚ ትግሬዎችም ሆነ ስለ ጠቅላላ የትግራይ ብሔረተኞች የፖለተካ አቋማቸው በሚመለከት በርካታ መፅሕፍቶች ማሳተሜን የምታውቁት ነው። ጥቂት የትግራይ ተወላጆችን ሳይመለከት በብዙዎቹ የትግራይ ሊሂቃን ባህሪ የታዘብኩት ነገር ቢኖር አክራሪ ትግራዋይ ጎሰኝነታቸው ሲነጻጸር የዛሬ ኦሮሞ አክራሪ ሃይሎች በቃልም በተግባርም እኩል መሆኖቻውን ነው።

ሁለተኛው የሚያመሳስላቸው ደግሞ-“ ጠላታችን የሚሉት ክፍል ወይንም ገዢ ሃይል ይወገድልን እንጂ ከዚያ የሚብስ ስለማይመጣ የመጣውን እንደግፍ የሚሉየጠሉትን ስርዓት ለማብሸቅ ብቻ በእልህ ተነሳሽነት ተነስተው፤ የጥንት ወላጆቻችንከጥዱ ወደ ማጡየሚሉትን አነጋጋር የሚገልጻቸው ሆነው አግኝቻቸዋለሁ።

በዚህ ወር ውስጥ ገንኖ የሚጠራው በየሚዲያው ብቅ፤ብቅ ማለት የጀመረውጸረ ምኒሊከነቱራሱ የሚያወድስና ከፍ ሲልምወልቃይት የትግራይ መሬት ነው ስለሆነም ወልቃይትን የሚነጥቅጦርነት እንገባለን፤ ታጠቅ ተወደብ/ተደራጅበሚለው መፈክሩ የሚታወቀውየዓረናው አብርሃ ደስታቦታ የወሰደውብልጽግናየተባለው አዲሱ የኦሮሞ ፋሽቶች ፓርቲ የትግራይ ወኪል ሆኖአብይ የተናገረው ትምክሕታዊ ንግግርም ሆነ በሥሩ የሚደረግ የሰብኣዊ ነክ ጭካኔዎችንመልስ እንዲሰጥበት ሲጠየቅ የአብይን ወንጀል በጀሮው እያደመጠና በዓይኑም በየሚዲያውእናቶች፤ አባቶችም ወጣቶችም ምሁራኖችም የፖለቲካ እስረኞችምየሚያስሰሙትእሮሮእያየ አላወቅኩም አልሰማሁም ወይንምየአብይ የባሌ ኦሮሞ ትምክሕታዊ ንግግሩ ትክክል ነው፤ እምንበታለሁ፡የሚለንነብዩ ስሑል ሚካልየተባለው አዲሱ የፋሺሰቶች አቀንቃኝ የትግሬ ሊሂቃን ጉዞ ስመለከትዛሬምከድጡ ወደ ማጡ እየተጓዙ መሆናቸው እየተመለከትን ነው።

ልጁ ዕድሜው ወጣት ሆኖ በትምህርት የበሰለ ነው። በዚህ ሰሞን የኔ ቤተሰብ የሆነ የቅርብ ዘመድ የነብዩን መጽሐፉ እንዳነብብ በፖስታ ልኮልኝ እየጠበቅኩ ነው። አንዳንዶቹ እንደሚሉት ልጁ ከዓድዋዎቹና ከአክሱሞቹ የወያኔ ፖለቲከኞች ጋር በታርክ ንግሥነት እልክ በመጋባትየዕንደርታዎችን ጉልታዊ/ንጉሳዊ/ የበላይነት ታሪክበፉክክር ለማንፀባረቅ እንደጻፈው ይናገራሉ። ለማንኛውም እስካነብበው ድረስ በዚህ ልቆጠብና ወደ ፖለቲካው እናምራ።

በተለያዩ መድረኮች የምታይዋቸው ከትግራይ የተገኙ የአብይ አሕመድ አዳዲስፈረሶችብዙዎቹ ወያኔን ሲቃወሙ የነበሩ ናቸው። እነዚህ ልጆች ማየት ያልቻሉት ምንድነው? ለምንስጎምበስ ያለው የወያኔ ስርዓትና አሁን ሥርዓቱን በዘዴ ተቆጣጥሮ በውጭ ሃይላት የተደገፈው የኢትዮጵያን እናቶችና ወጣት ሴቶችን ለዋይታና ለግድያ የዳረገ በአብይ አሕመድ የሚመራው የኦሮሞ መንግሥት ድሮ ወያኔ ሲቃወሙ የነበሩት እነ ነብዩ ስሑል ሚካልም ሆኔ እነ አብርሃ ደስታና (አብርሃ እንኳ የወያኔ ተቃዋሚ አልለውም) እና አንዳንድ የኔ የቅርብ ወዳጆቼም ጭምር በጣም በሚያስገርም ከስተት እና ፍጥነትየዚህ ሥርዓትደጋፊዎች ብቻ ሳይሆኑእየተሰራ ያለው ወንጀል ጭምር ሽምጥጥ አርገው በመካድእውር ድጋፍሊሰጡ እንዴት ቻሉ የሚለው ጥያቄ በርካታ የስነ ልቦና ምርምር ይፈልጋል።

አንዳንዶቹ በደርግም ሆነ በወያኔ ሥርዓት ሰቆቃ (ግርፍያን/እስራትን) የቀመሱ ናቸው። አብይ አሕመድ ከመጣ ጀምሮ በሥርዓቱ ወታደሮችና ከንቲባዎች ብዙ ሰዎች ታስረው፤ ተፈናቅለው፤ ተደብድበው፤ደብዛቸው የጠፉ ለመሆናቸው በሺዎች የተሰነዱ የሰነድና በቪዲዮ ማስረጃ የተደገፈ ሃቅ ነው። ታዲያ እነዚህ የድሮ የወያኔ ተቃወሚ ትግሬዎች አሁን ደርሰው (ያዛሬው ጭካኔ እና ሕግ አልባ ሥርዓት) የሰዎችን ሰቆቃ እና እምባ ለምን አልታይ አላቸው? የሚለው ሁላችንም ልንነጋገርበት የሚገባ አስገራሚ ክስተት ነው።

እነዚህ ሰዎች ካሁን በፊት በወያኔ የተሰቃዩ ስለመሆናቸው ብያወቁም ለምንከሁለት ሥነ ምግባር የጎደላቸው ሥርዓቶች ውስጥ አናሳውን ሰይጣን ሊመርጡ ደፈሩ? ሥርዓት ሲመረጥ በግለሰባዊ ቅራኔ ወይንም ጥላቻ ሳይሆን በመርህ እንደሆነ እነዚህ አሁን አብይን በመደገፍ ላይ የሚገኙ የትግራይ ሊሂቃን ይህ መሠረታዊ መርህ አያውቁም ማለት አይቻልም። ለድጋፋቸው መነሾ የሚሰጡት ምክንያትእንኳን ወያኔ ተወገደ እንጂ የፈለገው ሰው ይግዛኝየሚል ነው። ይህምደርግ ይወገድ እንጂ ሰይጣንም ቢሆን ይግዛኝሲሉ ከነበሩት እና የባሰ ሰይጣን በምትኩ እንደተተካ የምናወቀው የቅርብ ታሪክ ነው።

ምርጫቸውከመጥበሻው ምድጃ ውስጥ ወደ እሳቱ መዝለልከሚለው ጋር ተመሳሳይ ነው። እንዲህ ያለ ምርጫ በወያኔ ተቃዋሚ ትግሬ ሊሂቃን ብቻ አልተወሰነም። እነ ፕሮፌሰር መስፍን /ማርያምአማራ ሶማሌውን ሽርጣም ሶማሌ ይለው ነበርእያሉ ጸብ ለማስነሳት ድሮ ጥንት የጻፉትን መጽሐፍ ረስተው ዛሬአማራ የሚባል የለምብለው ሲከራከሩአማራ የሚባለው ሶማሌውን ሲሰድብ ከየትኛው ጠፈር የመጣ አማራ ነበር አማራ እያሉ የጻፉት?” ብለን ስንጠይቃቸው መልስ የማይሰጡ ዛሬአብይን ከነ ምናምኑ ካልደገፍነው ለአውሬዎች እንጋለጣለንእያሉአውሬን በአውሬየመተካት ትምህርት የሚያስተምሩ ምሁራንም ተበራክተዋል።

ይህ ገልቱነት የሚገርም ነው።ውሻን ማሳደግ ፈልገህ ቁንጫውን ጠልተህየሚባለው አሜሪካዊ የሞኞች አነጋገር ለዚህ ምሳሌ ነው። ውሻውን ስትፈልግ ቁንጫውን ማራጋፍ እና እንዲጸዳ ማድረግም እኮ ይቻላል። ችግሩ ግን ቁንጫውን ለማጽዳት ሲሞከር ቁንጫዎቹን ከነቆሻሻው መነካካት ውሻው ይጮህና የነክስሃል የሚሉ የገልቱዎች መከራከሪያ ነው የጨነቀ ነገር (ልክ የነ ብርሃኑ ፤ልክ የነ መስፍን /ማርያም፤ ልክ የነ አንዱአለም አራጌ፤የሺዋስ አሰፋ፤ / ዳኛቸው ተሾመ፤ተማኝ በየነ እና አል ማርያምወዘተ መከራከሪያ) የሚገርም ነው።  

የሚገርመው አብይን ለመቃወም ከወያኔ ያልተናነሰ ያውም ባንዳንድ ድርጊቶች የከፋ ወንጀል ተፈጽሟል። ይህ ሰው አሸጋጋሪውእኔ እና እኔው ብቻ ነኝየሚል የድረዉ የኡጋንዳውኢዲ አሚን ዳዳየሚመስል ባሕሪ የተላበሰሰው በጭፍን ያለመቃወምመደገፍስንመለከት የምንጠይቀው ጥያቄከወያኔና ከጀረመን ናዚ ደጋፊዎች ብምን ይለያል?

አዲስ አበባ በሚዲያ ላይ ያለ ምንም ሰቀቀን በድፍረት ወጥተው 3000 አመት እንገዛችኋለን የሚሉን (እነ ሌንጮ ባቲ) የአብይ የፖለቲካ አማካሪና አዲስ አባባ የኦሮሞዎች ናት ብሎ በኬኛ ፖለቲካ መግለጫ የለጠፈው የአብይ አሕመድ ፓርቲ (“የኦሮሞ መንግሥትን”) መቃወም ወደ ከፋ ሁኔታ እንገባለን እያሉ፡አያ ጅቦን አትነካኩየሚሉ የፋሺዝም ደጋፊዎችዛሬ ሁለት አመት ሙሉ እናቶች ሲያለቅሱ ወንዶች ብልታቸው በገመድ ታስረው የኋሊት ሲጎተቱ እያለቀሱ ለሕዝብ ሲገልጹ ያለመቃወም ከሞራልም ከሕግም ተቀባይነት የለውም።

ይሁን እንጂ አሁን አብይን በመደገፍ ላይ የምናያቸው ትግሬዎች ከወያኔ ጥላቻቸው ውጭ አብይን በሞራልም በሕግም የሚደግፉበት ነጥብ የለም።

አብይ ማለት መለስ ዜናዊ ነው፤ መለስ ዜናዊ ማለት አብይ ነው፤ወያኔ ማለት ኦሕዴድ/ኦዴፓ/ ማለት ነው። የትግራይ ተወላጆች ወያኔን ስትደግፉ 27 አመት ኢትዮጵያን ለመከራ ያጋለጣችሁት እንዳይበቃ፤ ዛሬ ደግሞ በወየኔ ደጋፊዎች እግር የተተኩየኦሮሞ ፋሺስታዊና አፓርታይዳዊ መንግሥትደጋፊዎች የሆናችሁ የትግሬ ሊሂቃኖች እባካችሁ ለሁለተኛ ዙርፋሺስዝምና አፓርታይዳዊ ሥርዓትእንዳታነግሱብን ዛሬም ጥሪ አቀርባለሁ።
አመሰግናለሁ
ከጌታቸው ረዳ
(
ኢትዮ ሰማይ Ethio Semay)