ግንቦት 20 በትግራይ ፋሺስቶችና በኢትዮጵያ አርበኞች መሃል የተደረገው የማይረሳው
የሰንደቅ ዓላማው ግብግብ
ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay አዘጋጅ)
ጣታቸውን ቀስረው የሚታዩት ሻለቃ
አድማሴ ናቸው። ቀጥለው ያሉት ስማቸው ያልተጠቀሰ አርበኛ ኢትዮጵያዊ ናቸው።
ጸረ ኢትዮጵያው የህዝባዊ ወያነ ሓርነት
ትግራይ መሪ የነበረው ወደባችንን ለጠላት አስረክቦ፤ ኢትዮጵያን አፈራርሶ ወደ ግብአተ መሬቱ የገባው ባንዳው መለስ ዜናዊ
“……ድሮም ነበሩ፤ ዛሬም ቢሆን መንግሥታት አሉ። መንግሥት ምንድነው? እንዲያው ልብ
ብላችሁ አድምጡኝ። የሕዝቦችን መሞት ልነግራችሁ ነኝ። መንግሥት የክፉዎች ሁሉ ክፉ አውሬ ነው። ሲዋሽም እንዲያ ነው።
“መንግሥት ማለት ሕዝብ ማለት ነው።” የሚል ቅጥፈት ከአንደበቱ
አይጠፋም። በሕዝቡ ላይ ያዘጋጁትን ወጥመድ ነው መንግሥት የሚሉት። ልዩ ልዩ ሕዝቦች ይህንን ቋንቋ ይኖራቸዋል። ሕዝቦች ይህን
ቋንቋ መረዳት አይችሉም። መንግሥት ግን በሁሉም ቋንቋዎች የሚዋሽ አፍ ነው። የሚናገረው ሁሉ ውሸት ነው፤ ንብረቶቹ ሁሉ
የተሰረቁ ናቸው። የሚናከሰውም በተሰረቁ ጥርሶቹ ነው። ሆዱ እንኳ ሀሰተኛ ነው።
በየአገሩ እልፍ ኣእላፍ ሰዎች ይወለዳሉ። መንግሥት የተፈጠረው ለኒህ እልፍ ኣእላፍ
ሰዎች ነው። እንዴት እንደሚያባብላቸው ብቻ ተመልከቱልኝ። ሲያላምጣቸው፤መልሶ መላልሶ ሲያኝካቸው አያችሁልኝ? እልፍ ኣእላፍፎችን
ልብ ብላችሁ ተመልከቱ። የብልሆችን ሀብትና ፈጠራ ቀምተው ይወስዳሉ። የዘረፉትንም ባህል ነው ይላሉ። ሰው ሁሉ ቀስ በቀስ ራሱን
መግደል የያዘበት አገር ይሏል መንግሥት ነው። (1)
ከወራሪ ጣሊያን በከፋ መልኩ፤ በመንግሥትነት ስም ገብቶ፤ የአገራችን ኢትዮጵያን
አንድነትና ታሪክ እንዲሁም ልዓላዊነታችንን በሚጻረር መልኩ፤ በመለስ ዜናዊ የተመራው “ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ” የተባለው
ይህ የጎሳ ድርጅት፤ ግንቦት 20/ 1983 ዓ.ም ኢትዮጵያን ሲቆጣጠር፤ ባለፈበት ገጠርና ከተማ የኢትዮጵያን ሰንደቃላማ
አውርዶ፤ በምትኩ የወያኔን ሰንደቃላማ በመስቀሉ፤ ሕዝቡ በመቆጣቱ፤ በዚህ ፋሺስታዊ ድርጅት እና በኢትዮጵያ አገር ወዳድ
አርበኞች መካከል ስለ ሰንደቃላማ ጉዳይ ተነስቶ በጸረ ኢትዮጵያ ሃይሎችና በአገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን ጎራ ተለይቶ የታየው
ግብግብ፤ ታሪክ “ሀ“ ብሎ የዘገበው የመጀመሪያው የትግል ምዕራፍ የሰንደቃላማችን ጉዳይ ነበር ። (2)
የዛሬ ትችቴ በሁለት ክፍሎች የተከፈለ ነው፡
ከፍል -ሀ-
ባለፈው ሰሞኖች ወያኔ “የባንዴራ ቀን” እያለ ጣሊያን ባሰመረለት ዕቅድ ተጉዞ የአትዮጵያን
ሰንደቅ ዓላማ ህልውና እና ክብር ሲያረክስ ተመልክታችሁ ይሆናል። ይህ ለዓይን እና ለልቦና የሚሰቀጥጥ “ባንዳዊ/ቅጥረኛነት”
ስራ ምንም የማያውቁ ታዳጊ ወጣቶችን እና ሴራው በቅጡ ያልተረዱ ጀሌዎቹን አሰልፎ 44 ወያኔ ሰራሽ ባንዴዎችን እያውለበለበ
በኢትዮጵያ ሉአላዊ ክብር ሲያሾፍ በድረገጾቹ አማካይነት የለጠፋቸው ፎቶግራፎች አይታችሁ ይሆናል።
ይህ ቅጥረኛነት ሴራ የጀመረው ወያኔ ከትግራይ በረሃ ገስግሶ አዲስ አበባን ሲቆጣጠር የኢትዮጵያ
ብሔራዊ/አገራዊ ሰንደቃላማን ሳይሆን እንደ ባዕድ ወራሪ፤ ጣሊያን ይመስል የተለየ መልክና ቅርጽ ያየዘ የራሱን ባንዴራ
እያውለበለበ ነበር በግንቦት ወር ሴራው “ሃ” ብሎ የጀመረው። ሲኣይኤ መንግስቱ ሃይለማርያምን ወደ ዝምባብዌ በሰላም ካሸጋገረ፤
ከዚያች ወር ጀምሮ በስምምነቱ መሰረት ‘ወያኔዎች’ በሩ ክፍት ከተደረገላቸው በሗላ ኢትዮጵያን ‘በአፈሙዝ’ ተቆጣጥረው ትኩረታቸው
በሰንደቃላማ፤በተዋህዶ ርቶዶክስ ክርስትያን እና በአማራ ማሕበረሰብ ላይ ዘለፋቸውን ማነጣጠር ጀመሩ። ከዚያ ጊዜ ጀምሮ በየአመቱ
ግንቦት ወር ሥልጣናቸውን ለማስቀጠል ሴራቸውን የሚፈትሹበት ወር አድርገው ያዩታል። በተቀናጀ ዝርፊያም በምርጫ አሸነፍን ብለው
ሕሊናቸው ስተው በዕርዳታም ሆነ ከአገሩቱ የሚዝቁት የንግድ እና የተፈጥሮ ሃብት ከሚገኘው ገቢ በሺ የሚቆጠር ዶላር፤ ለዊስኪ እና ለቁርጥ ስጋ በየሸራተን
ሆቴል እና በዓለም ዙርያ ባሉ የወያኔ ዲፕሎማቲክ ጽ/ቤቶች ወጪ እየተደረገ በፈንጠዚያ ያበዱበት ጊዜም ነው። ሰሞኑ ደግሞ ስለ
ባንዳዊ ባንዴራዎቻቸው ሲለፍፉ ሰንብተዋል።
በሌላ ጎራ ደግሞ በህዝባዊ ግምባር ኤርትራ/ሻዕቢያ/ እና በውስጠ ሴረኞች መንግስታት
በገንዘብ የሚታገዘው፤ “የግንቦት 7 እና የሻዕቢያ ቱልቱላ” ብለው አገር ወዳዶች የሚጠሩት ራሱን “ኢሳት” ብሎ የሰየመ ራዲዮ እና ቴ/ቪዥን ጣቢያ፤ በሞሳድ፤በሲ አይ ኤና
በሻዕቢያ አፍቃሬ ግለሰቦችና በጸረ ኢትዮጵያ የታጀበ “ኤርትራዊ/ሻዕቢያዊ” አጀንዳ በማዘጋጀት ሻዕቢያዊው፤ ኢሳያስ አፈወርቅንና
ኤርትራን እንደ “አገር” ለማዳን ፕሮፓጋንዳ ሲሰራ መሰንበቱን የታዘባችሁ ይመስለኛል። ይህ ከብዙ አመት በፊት የጀመረው ካፈርኩ
ላልመለስ ባዩ እንደዛው እንደ “ይሁዳዊው” ካሳ ከበደ፤ ስለ ሻዕቢያ በጎነትና አጀንዳ ሽንጡን ገትሮ በየመድረኩ የሚቀደደው
በግንቦቱ ሰውየ “በንአምን ዘለቀ”፤በሻዕቢያ ካድሬዎች በእነ ሶፊያ ሃብተማርያም
ሲሰራበት የነበረና አሁንም እየቀጠለ ያለው ጸረ-ኢትዮጵያ
አጀንዳ በአዳዲስና ነባር እንሰሳዎች የወጣቱን ሕሊና የማጠብ
ዘመቻ ቀጥሏል። አጀንዳው አፍቃሬ ሻዕቢያ ኢትዮጵያዊያንን
(ከላይ በመጀመሪያ የሚታየው ፎቶግራፍ ይሁዳው ካሳ ከበደ ነው።ካሳ ከበደ፤ የሻዕቢያ የኢሳያስ አፈወቀርቂ ታሪክና ተክለ ሰውነት አሳማሪ ሆኖ የኢሳያስ ለኢትዮጵያ በጎ አሳቢነት መቆሙን ሽንጤን ገትሬ እከራከርለታለሁ በማለት
ሕዝባችን በወንጀል የሚከሰውን ባለ ብዙ ገበናው ለኢሳያስ አፈውርቂ ጥብቅና ለመቆም ሽንጡን የገተረ ሰው ነው። ከዚያ ቀጥለው ያሉት በየጊዜው ንግግራቸውን በማምታታት አድማጮቻቻውን ግራ በማጋባት
ከኦነግ ፤ ከኦብነግና ከሻዕቢያ ጋር ጭራቸውን በመቁላት የታወቁት አዲሶቹ የጠላት “ሳብቨርሲቭ” ዘመቻ አስፋፊዎች
ከቀኝ ወደ ግራ “ዶከተር ዜሮ/0/” በመባል የታወቀው “ኦነግ የመገንጠል ጥያቄ አቅረቦ አያውቅም” ብሎ ወጣቱን ለማሳሳት
የደሰኮረ ዶ/ር ጌታቸው በጋሻውና አንገቱን አጎምብሶ እየከተበ ያለው
የግንቦት 7 “ የሻዕቢያ አድናቂ’ “ታጋይ” ንአምን ዘለቀ ነው ።)
ያካተተ፤ በወያኔ እግር ለመተካት የተደረገ ሕቡዕ ሳይሆን ግልፅ የሆነ “የግንቦት 7’ ፤
የ ሲ አይ ኤ እና የሻዕቢያ ታላቁ ሴራ እውን ለማድረግ በኢትዮጵያ
ክብርና እና ሉዓላዊነት ለመቋመር “የዲሞራላይዘይሽን” ዘመቻቸው በሕዝባችን አስተሳሰብ ለውጥ እንዲኖር የውጭና
የውስጥ ያነፈነፉ ተውሳኮችን ወደ ሕዝባዊ መድረክ በመጋበዝ ተበራክተው ብቅ ያሉበት አጀንዳ ነው።
የመጀመሪያው የሕሊና አጣባው የጀመረው፤ “ኢሳያስን የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ወዳጅ
ተደርጎ እንዲታይ የተሰበከበት”፤ ሁሌም እንድትጠነቀቁበት የማስጠነቅቃችሁ “ሳብቨርሲቭ” ተብሎ የሚታወቀው “ያስተሳሰብ/የሃይማኖት/የባሕል/የአመጋገብ/የቋንቋና
ሉአላዊ የድምበር አዋሳኝ እሴቶች በሚጎዳ መልኩ ለውጥ እንዲኖር፤ ሕዝባችን ከያዘው ትክክለኛ አቅጣጫ ለቅቆ ለጠላቶች ሸብረክ
እንዲል” ፤ አዲስ የሚመስል ጠላቶች በሉአላዊነታችን የሚያነጣጥሩበት ነባር የማጥቃት ስልት ነው። ሰሞኑን “በሰላምና
በዲሞክራሲ ስም” በኢሳት/ግንቦት7 መሪነት የተዘጋጀው ‘ኮንፈረንስ’ ይህንኑ የሚያሳይ ነው።
ይህንን ስትመለከቱ፤ የአገሪቱ መጻኢ ሕልውና የሚፈታተኑ ዛሬም ከውስጣችን የተጐለጎሉ ብዙ
ያበዱ እንሰሳዎች መኖራቸውን መዘንጋት የለባችሁም። ትኩረታችን በወያኔም ሆነ በተቃዋሚ ውስጥ ያሉ የውጭና የውስጥ ተውሳኮች ላይ
ጭምር መሆን አለበት ብየ ካሁን በፊት ደጋግሜ የጻፍኳቸውና የተናገርኳቸው ቁም ነገሮችን፤ እንዲህ ያሉ ተከታታይ የአጥቂዎች
ዘመቻ እንደማይለዩን በማጤን ነው። በተቃዋሚው እና በተቃዋሚው፤ በወያኔ እና ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ችግር ሳይፈቱ የት የሌለ
ርቀት እየሄዱ አንዴ ምስራቅ አፍሪቃን አንድ ለማድረግ፤ አንዴ ኤርትራና ኢትዮጵያ ኮንፈረነስ እያሉ “የአገራቸውንን ታሪክና
ገመና” ለገበያ በማቅናት፤አገራችንን ለስውር በቀልተኞች በማጋለጥ ላይ ናቸው።
እንኳን ለኢትዮጵያ፤ለኤርትራ ሕዝብና
አብረው ለታገሉት ጓዶቹ ሳይቀር፤ ከነ ህፃናት ልጆቻቸው ያሰቃየ፤ ኢትዮጵያ ወታደራዊና ስቪላዊ ሙርኮኞች በባርነት
ቀንበር ይዞ አፍኖ የሚገኝ፤ “ተንኮል፤ ክፋት፤ ጭካኔና
በቀልተኛነት” እንጂ “እውነትና በጎነት” ከጎኑ ቆማ የማትታወቅ ኢሳያስ አፈወርቅ የተባለው “ጸረ ኢትዮጵያ ተውሳክ” አጀንዳውን የሚዘረጋው ፤ በበጎነት
የሚያወድሱት በእነዚህ በአበዱ ጦጣዎች በኩል እንደሆነ ከንግግራቸው ማወቅ ትችላላችሁ።
አንድ ነገር ብየ ወደ ርዕሴ ልገባ ነው ። በየፓልቶኩ ስጎበኝ “አማርኛ የሚናገሩ ‘አሚቼዎች’ እና ኢትዮጵያዊያን የግንቦት 7 ደጋፊዎችና
አባሎች” የሆኑ ንግግራቸው ሁሉ የኢሳያስንና የኤርትራን ክብር ከፍ እያደረጉ እያወደሱና እያጎሉ፤ የትግራይን ሕዝብ “አጋሜዎች”
በማለት ዘለፋና የዘር ማጥፋት ዛቻ በማስተጋባት፤ አብዛኛውን “የፓልቶክ ክፍል” አንዳለ በብዛት ተቆጣጥረውታል። ይህ አገር
በታኝ ዘመቻ የሆነ ዘረኛነት ቅስቀሳ በግልጽ እያሰራጩበት ይገኛሉ። ይህ አደገኛ የግንቦት 7፤ የሻዕቢያ፤ የኦብነግና የኦነጎች
“ሴራ” ሕዝብ ከዚህ አጥፊ ስራ እራሱን አንዲያጸዳ እጠይቃለሁ።
ይዋል ይደር እንጂ ተጠያቂነት ስለሚኖር፤ “አውዴዎች እየተቀዱ፤ ማንነታቸውንም ጭምር
እየተመዘገበ ስለሆነ” ካሁኑኑ ጥንቃቄ ብታደርጉ እመክራለሁ። ግራ ቀኙ ሳታስተውል በስሜት እየከነፍክ የምትገኝ ዜጋ ሁሉ፤ በሚደረደርልህ
የሻዕቢያ “በገና” ሕሊናሕ ከመታፈን ነፃ አውጣ። ከታፈንክበት ግማታም አየር ለመላቀቅ፤ መስኮቱን ሰብረህ ወደ ክፍቱ አየር
ብትወጣ፤ ላንተም ላገርህም ጤንነት ይበጃል።
ከፍል -ለ-
በዲያስፖራ ግንቦት 7 አባሎች የታየው ሻዕቢያን የማጎልበትና የኤርትራን ደህንነት
የማጉላት ዘመቻ ከላይ ተመለክተናል። ሰሞኑን ደግሞ በወያኔ በኩል ባለፈው ሰሞን በተጓዳኝ ተመሳሳይ ጸረ
አገራዊ ትዕይነቱና ጸረ ኢትዮጵያ ባንዴራዎቹን እያውለበለበ “ከጫካ ይዞት የመጣ ታላቁ የሳብቨርሲቭ” ዘመቻው ባለፈው
ሰሞን የጨፈረበትን ትዕይንቱን እንመለከታለን።
የወያነ ትግራይ መሪዎች፤ ገና ከጅምሩ ቀርጸው የተነሱበትን ጸረ ኢትዮጵያ አጀንዳቸውን
ለማካሄድና ሥልጣን ለመያዝ እንዲያመቻቸው፤ ወያኔዎች ለ24 አመት ኢትዮጵያን ከመቆጣጠራቸው በፊት፤ በአጥንት፤በደም በስጋ ዘመድ
አዝማድነትና በጋብቻ በቤተሰብነት እዛው በዛው መተሳሰራቸው ለሚቆጣጠሯት ኢትዮጵያ ቀላል እንደሚሆንላቸው በማሰብ የድሮ የትግራይ
መሳፍንትና ነገሥታት ሲጠቀሙበት የነበረውን አስተዳደራዊ ስልት በመከተል ነበር ይዘው ወደ አዲስ አበባ የገቡት። ዘጠኝ
“የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ” የፖሊት ቢሮ አባሎች እና ወደ ሰላሳ የሚሆኑ የድርጅቱ ማዕከላዊ
አባላት አብዛኛዎቹ በትዳር እና በዘመድ አዝማድ የተቆላለፉ ናቸው። ሌሎቹ በወያኔ ጥላ የተሰባሰቡ የብእዴን
እና የመሳሰሉ አሽከሮቻቸውም ልክ እንደ ወያኔዎች እርስ በርስ በጋብቻ ተጋብተው የመጡ ናቸው። አስተዳደሩ የከፋ ካደረገው አንዱ
የስርዐቱ መሪዎች እና አስፈጻሚ አሽከሮቻቸው፤ በዘመድና በጋብቻ ሐረግ ተጠናንገው ስለሰሩ፤ እነ መለስ ዜናዊ ይዘውት የመጡትን ጸረ
ኢትዮጵያ ፖሊሲ ለማስፈጸም እጅግ ቀለለላቸው።
ወያኔዎች በዚህ በተጠናናገ ቤተሰባዊ እና የጋብቻ ትስስር ትከሻ ለትከሻ ተያይዘው ወደ
አገሪቱ መሃል ለመግባት እንዲያመቻቸው፤ ግንቦት 20 በ ሲ አይ ኤ ተደግፈው ወደ አዲስ አበባ ገብተው ፓርላማውን ተቆጣጠሩት። በእነሱ
ስር የተደራጁም የአለቆቻቸውን ንግግርና ሴራ እየተከተሉ ፓርላማውን በቁጥጥራቸው አድርገው ሌላውን መፈናፈኛ አሳጡት። በዚህ ወቅት ወያኔዎች በመሰረቱት አዲሱ የሽግግር ፓርላማ፤ ሁለት ተቃራኒና
የተፋጠጡ ክፍሎች በመድረኩ ላይ ለሕዝብና ለታሪክ እይታ ብቅ አሉ።
አንደኛው ክፍል ከሰሜን ክፍለ ሃገራችን ከትግራይና ከመረብ ምላሽ/ኤርትራ ገስግሰው
የመጡ ባንዳዎች ሲሆኑ፤ በሌላው በኩል ደግሞ ከመላ ኢትዮጵያ የተወለዱ በፈታኝና በቁርጥ ቀን ብቅ ብለው ልሳናቸው በታሪክ
ማሕደር ለማስመዝገብ በተገኙ ኢትዮጵያዊያን መሃል ግብግቡ ተጀመረ።
በወቅቱ በግምባር ቀደም ወያኔን ፊት ለፊት ተጋፍጠው እስከ ሕልፈተ ሞታቸው ለኢትዮጵያ
የቆሙ እንደ እነ ፕሮፌሰር አስራትና እንደ እነ ዶ/ር ታዬ ወልደሰማያት የመሳሰሉ እንደነበሩ ባለፈው ጽሑፌ ላይ ያነበባችሁ
ታስታውሳላችሁ። ዛሬ ከፕሮፌሰር አስራት ባልተለየ መልኩ ወያኔን ከተጋፈጡት መሃል ሻለቃ አድማሱ እና ስማቸው ያልተጠቀሱ
ጥቂት አርበኞችም ነበሩ። አብዛኛው የዛሬ ወጣቶች የእነኚህ ሰዎች ግብግብ በብዛት አያስታውሰውም። እንኳን የእኚህ
ግለሰቦች ገድል ይቅርና፤ በአማራ ሕብረተሰብ ላይ የተነጣጠረው በሚሊዮኖች የጠፉበትና ካገራቸው እንዲባረሩ የተደረገው ጥቃት እንኳ
ምንም እውቀት የለውም።ይህ ደግሞ ሳንሆዜ ለስፖርት በዓል መጥተው ባነጋገርኳቸው ብዙዎቹ ወጣቶች የታዘብኩት ትዝብት ነበር። አማራ
ምን ደረሰበት? ሞረሽ ማለት ምን ማለት ነው? አማራን ከጨርሶ ጥፋት እንታደግ ማለት ምን ማለት ነው? ብለው የሚጠይቁ በርካታ
ወጣቶች ነበሩ (አሳፋሪ ምሁራን ነን ተብየዎችን፤ የምኒሊከን ጥቅሶችንና የአማራ ህፃናት መሬት ላይ ተኝተው ለረሃብና ለብርድ
የተጋለጡትን ፎቶ ግራፎችን በጎሪጥ እያዩ፤ የሞረሽን ድንኳን ያለፉትን እኔ የማውቃቸው ታዋቂ ሰዎችና የማላውቃቸው ስሜታቸው በሕዝብ
ሰቆቃ ሳይሆን በባዓሉ ዝግጅት ሜዳ ላይ በእስክስታ የተማረኩትን ሳላወሳ መለቴ ነው።
ግንቦት ወር የወያኔ ባንዴራ የተሰቀለበት ፤የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሰንደቃላማ የወረደበት
ወር ነው። ትንቅንቅ ካደረጉት አንደኛው ሻለቃ አድማሴ ይባላሉ። የዛሬ ወጣቶች አያውቋቸውም። ዛሬ እንዲያውቋቸው በግንቦት ወር
ወያኔዎች አዲስ አበባን ሲቆጣጠሩ፤ የኢትዮጵያን ወደብ ከነመርከቦች እና ጀልባዎች ለጅቡቲ እና ለኤርትራ በስጦታ መልክ ለጠላት
ያስረከቡበት፤ የኢትዮጵያን ሠራዊት በትነው በምትካቸው የትግሬ ወታደሮችን የተኩበትና፤ለማኝ እንዲሆን ያደረጉበት፤ ወያኔዎች የኢትዮጵያን
ብሔራዊ ሰንደቃላማ ያዋረዱበትና ብሔራዊ ሰንደቃላማችንን ዝቅ አድርገው በመመልከት፤ ያለፉትን ስርዐቶች፤ባሕል፤ሃይማኖትና ታሪክና
ገድል እያሳነሱ የወያኔ ገድል ከፍ አድርገው በሚያከብሩበት የባንዴራቸው ዓመታዊ በዓል ከመመልከታችን በፊት፤ ወያኔዎች ባዘጋጁት
የሽግግር መንግሥት በጉባኤው ላይ ተገኝተው፤ ሻለቃ አድማሱ እና ሌሎች አገር ወዳዶች በቪዲዮና በጽሑፍ አስደግፌ ከወያኔዎች ጋር
ያደረጉት ፍጥጫ ለታሪክ አስመስግበውልን የሁዱትን ትግላቸውን
ባንዳዎቹ “ዊስኪ ሲራጩ” እኛ ደግሞ የአርበኞች ኢትዮጵያዊያን ወላጆቻችንን “የኢትዮጵያዊነት ልሳን” እንደ ዊስኪ
እየጠጣን ሕሊናችንን በጠነከረ ኢትዮጵያዊነት ትግላችን እንዲቀጥል የማቀርብላችሁን ስዕለ ድምፅ/አውድዮ-ቪዲዮ እንድትመለከቱ
እጋብዛለሁ።
ከዚያ በፊት ግን በመለስ ዜናዊ እና በሦስት ቆራጥ ኢትዮጵያዊያን የተደረገው ፍጥጫ
ከንግግራቸው ያገኘሁት ለታሪክ ንባብ እንዲመች አቀርብላችሗለሁ፡
“ይህች ሰንደቃላማ አንድ ነጥብ ቢጨመርባት፤አንድ ነጥብ ቢቀነስባት የኢትዮጵያ ሕዝብ
ያዝናል። የሽግግሩ መንግሥት ሰንደቃላማውን በዘምባባ እና በወይራ ቅጠል ከሚያስተካክል ይልቅ፤ ባንድ አገር ሁለት አስተዳደር
አይመስርት!”
“እኩልነት ሲጠበቅ ማለት ደግሞ፤ ባንድ መንግሥት ሁለት አስተዳዳር ሳይኖር፤ የመንግሥት መ/ቤት ሁሉ ባንድ ብሔረሰብ ከጠራጊ ጀምሮ እስከ ሚኒስትሬ
ድረስ በአንድ ብሔረሰብ ሳይያዝ፤ላንዱ የተደረገለት ለሌላው ሲደረግለት፤ ይኼ፤ እውነተኛ ዲሞክራሲ ልንለውና አብሮ የመኖር ተስፋ
ያጠናክራል ልንል እንችላለን!”
“አንዱ ጎሳ በሌላው ላይ
መቀስቀስ፤ ተዋልዶ ተጋብቶ በሰላም የኖረውን፤ ‘ከመቶ አመት በፊት ጡት ቆርጠሃል’ ሲባል፤ ለምን ከመቶ አመት በፊት የነበረውና
የተቆረጠው ምላስ አብሮ አይነገርም? ለምን ጡት ብቻ? ምላስ ቢቆረጥ ምላስ ቢቆረጥ ልዩነቱ ምንድ ነው?”
“በሽግግሩ ወቅት ሻለቃ አድማሴ ከተናገሩት ንግግር ”
ስለ ሰንደቃላማ የተደረገው ውይይት፤
መለስ ዜናዊ፤
“ጨርቁ የፈለገው ሰው ሊያውለበልበው ይችላል። ጨርቁ ለኛ ኢሚንት ነው። እኛ ኢሕአዴግ
የራሳችን መለያ አርማ አለን።” (መለስ ዜናዊ፤ በሽግግር መንግሥት ወቅት
የተናገረው)
ጨርቅ እያለ ያለው የኢትዮጵያ ብሔራዊ አርማና የአገር መለያ ምልክታችንን ነው “ጨርቅ”
ሲል ያጣጣለው። ባንዳው መለስ በዚህ አላበቃም። ጋዜጠኛ የሚከተለው ይጠይቀዋል፡
የኢትዮጵያዊው ጋዜጠኛ ጥያቄ፦
ጥያቄ አለኝ!
“ኢሕአዴግ በደረሰባቸው የኢትዮጵያ አካባቢዎች በሙሉ የኢትዮጵያን ባንዲራ
ያወርዳል፡የሚባል ነገር አለ። እዚህ አዲስ አበባም እራሴ ባላይም፤ ከውጭ እንደሰማሁት፤ ሰላማዊ ሰልፍም ሲደረግ፤ የሰላማዊ
ሰልፉ አንዱ መነሻ፤ የኢሕአዴግ ሠራዊት አባላት የኢትዮጵያን ባንዴራ አውርደው የኢሕአዴግን ባንዴራ ስለሰቀሉ ነው፡ የሚባል
ነገር አለና፤የዚህ ድርጅት ግልፅ ያለ አቋም ስለ ኢትዮጵያ ባንዲራ በተመለከተ ምን ዓይነት አቋም እንደሆነ ቢገልፁልን?
የባንዳዎቹ መሪ መለስ ዜናዊ፤- መልስ፤--- ባንዴራው በተመለከተ፤ ከባንዴራው
በስተጀርባ ያለው አመለካከት ያለው መሰለኝ ወሳኙ። ጨርቁ የሚያመለክተው ነገር ይመስለኛል ወሳኙ፤ ከቀለሙ በላይ። አንዳንዶቹ
3000 አመት ዕድሜ ያለው ባንዴራ ነው እያሉ ሁሉ፤ ያልሆነ ነገር ተረት፤ተረት ሲናገሩ፤ ምናልባት ሰምታችሁ ይሆናል፤
ምናልባትም ያንኑ ዜና አሰራጭታችሁም ሊሆን ይችላል። ይህ ባንዴራ መቸ እንደተፈጠረ፤ በታሪክ ጸሐፊነት ስም፤ በምናምን ስም፤
ከአዝማሪነት ያላነሰ ስራ፡…… ከጨርቁ በስተጀርባ ያለው ምንድ ነው? “ነፃነት” ነው? እኩልነት ነው? ዲሞክራሲ ነው? የኢሕአዴግ ጠብ
ከበስተጀርባው ያለው አመለካከት ነው ጠቡ። በሚቀጥለው መድረክ (በሚቀጥለው መንግሥት/ስርዓት) የኢትዮጵያ ሕዝብ “ጨርቁ” የሚፈልገው
ከሆነ “የራሱ ጉዳይ ነው!!!!” የጨርቁ፤ የባንዴራው ጥያቄ ለኛ ትርጉም የለውም! ኢምንት ነው! “ጨርቁ” የፈለገው ሰው “ሊያውለበልበው”
ይችላል። ጨርቁ ለኛ ኢምንት ነው። ኢሕአዴግ የራሳችን መለያ አርማ አለን።”
“ምናልባት አንዳንድ የኢሕአዴግ አባላት በጨርቁ ላይ ቁጭታቸውን አውጥተው ሊሆኑ
ይችላል። ጨርቁ ሊውለበለብ ይችላል። የኢትዮጵያ ሕዝብ ይቀየር ካለ ጊዜው ጠብቆ ሊቀይረው ይችላል።
ከዚህ በታች በቪዲዮ የማቀርበው መለስ ዜናዊን የተቃወሙት በሰነዱ ሚታየው በጉባኤው ላይ
የነበሩ የመጀመሪያ ተናጋሪ ከነበሩት ሁለት ኢትዮጵያዊያን አርበኞች መካከል ስማቸው ማወቅ ያልቻልኩ (ምናልባት የኢድዩ ተወካይ
ሳይሆኑ አይቀሩም የሚል ግምት አለኝ። ስማቸው የምታውቋቸው ካላችሁ በኢመይል ጠቁሙኝ። ምክንያቱም በመጽሐፍ መልክም እያሰፈርኩት
ስለሆነ።) እና ከእሳቸውም ጋር አብረው የነበሩት ተናጋሪ ሻለቃ
አድማሴ ፤ ሁለቱ ተነጋሪዎች የሚከተለው መልስ ለመለስ ዜናዊ ከቁጭትና ከማስረጃ ጋር እንዲህ ሲሉ ኢትዮጵያዊ ኩራት በተመላበት ከተቀመጡበት
መንብር ተነስተው በድምፅ ማጉልያ መልስ ሰጥተውታል።
ስማቸው ያላወቅኩት ኢትዮጵያዊ አርበኛ ተነጋሪ፡-ከመቀመጫቸው ተነስተው ለመለስ ዜናዊ
የሰጡት መልስ እንዲህ በማለት ንግግራቸው ይጀምራሉ፤-
“የመጀመሪያ ተናጋሪ ወንድሜ የተጠቀመው ቃላት “ጨርቅ” የሚለውን የኢትዮጵያ ሕዝብ
የሚያውቀው በጨርቅነቱ ሳይሆን በክብርነቱ ነው። በወርቅ ፤ በልዕልና (በዘውድ) በከፍተኛ መዓረግ ነው
የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚያውቃት! ዘውድ ስል፤ የዘውድ መንግሥት ማለት አይደለም።ልክ እንደ ዘውድ፤ በልዕልና እንጂ፤ እንደ እንቁ
እንጂ፤ በጨርቅነት አይደለም! እኛ ታሪኩን፤ባሕሉን በየመድረኩ ሸፋፍነን ብንሄድ ታሪኩም የኢትዮጵያ ሕዝብ ታሪክ ስለሆነ፤ባሕሉን
የሚመሰክረው ነው። ሕዝቡ ያውቀዋል። ጥንቃቄ ብናደርግ ጥሩ ነው። ባሕር ወስጥ ነን ያለነው። ሕዝብ ባሕር ነው፤ እኛ ዓሳዎች
ነን። መልሶ ቢተፋን በምን ምክንያት እንደተተፋን መልሶ ማወቅ ተገቢ ይመስለኛል። ከሕዝቡ ወጥተን መራቁን ይህን ያህል ርቀን
መራቁን፤ይህን ያህል ርቀት መራመድ የሚያስኬድ አይመስለኝም። ስለዚህ የሕዝብ ፍላጎት ማወቅ አዋቂነት ይመስለናል።”
ሲሉ ተቃውሞአቸውን ገልጸዋል።
ሻለቃ አድማሴ፡ ደግሞ እንዲህ ሲሉ ከፊታቸው ከተናገሩት አርበኛ
ቀጥለው ንግግራቸውን እንዲህ ሲሉ ለመለስ ዜናዊ መልስ ሰጡ፦
ክቡራን ጌቶቼ!
እርግጥ ግፍ ተሰርቷል።አሁን ዘርዝሬ መናገር የማልችለው። ግን፤ግን፤ግን…ይህች
ሰንደቃላማ ደግሞ ብዙዎችን ነፃ አውጥታለች! ብዙዎችን የዲሞክራሲ መብት አጎናጽፋለች! አሁን የኢትዮጵያ ሕዝብ ቢጠየቅ፤ተራ
በተራ እያንዳንዱ ሰው ቢጠየቅ፤ ይህች ሰንደቃላማ፤ አባቶቻችን ለሷ ሲሉ ደም የተፋሰሱባት ነች። የወላይታ ንጉሥ የነበሩት፤
ምርጥ ጦር ልከው ዓድዋ ላይ የዘመተው የወላይታ ጦር ነው። የታሪክ መጽሀፍ አምጣ ከተባልኩ ማምጣት እችላለሁ፡ ታሪክ
መዝግቦታል። ይህችን ሰንደቃላማ ይዘው ነው፤ አባቶቻችን ከጠላት ጋር የተፋጁባት!
ክቡራን ጌቶቼ!
ስለ ዲሞክራሲ ብዙ ተናግራችሗል።
ዴሞክራሲ የሚኖረው፤ከሰንደቃላማ ምልክት ጋር ሳይሆን፤ ከአገዛዝ ከአስተዳደር ጋር ነው።
የብሔር ብሔረሰብ እኩልነት ሲጠበቅ ነው። ይህንን እደግመዋለሁ! የብሔር ብሔረሰብ እኩልነት ሲጠበቅ ነው። እኩልነት
ሲጠበቅ ማለት ደግሞ ‘በአንድ መንግሥት ሁለት አስተዳዳር ሳይኖር፤የመንግሥትን መሥርያቤት ሁሉ በአንድ ብሔረሰብ ከጠራጊ ጀምሮ
እስከ ሚኒስቴር ያለ ባንድ ብሔረሰብ ሳይያዝ፤ላንዱ የተደረገው ለሌላው ሲደረግ፤ይሄ እውነተኛ ዲሞክራሲ አለ፤ ተብሎ አብሮ
አውነተኛ የመኖር ተስፋ አለ ማለት ነው።
በወረቀት ላይ ቃላት ማስፈር ፤ በተግባር የማይተገበር የዲሞክራሲ ታሪክ ማብዛት ምን
ይጠቅማል?
አንዱ ጎሳ በሌላው ጎሳ እንዲነሳ መቀስቀስ፤ ተዋልዶ ፤ተጋብቶ፤በሰላም አብሮ
የተቀመጠውን ሕዝብ፤ እገሌ እንዲህ አድርጎሃል፤ከመቶ አመት በፊት ጡት ቆርጧል፤ ለምን ከዚያ በፊት ምላስ የተቆረጠውን አብሮ
አይነገርም? ለምን ጡት ብቻ? ምላስ ቢቆረጥ፤ምላስ ቢቆረጥ ልዩነቱ ምንድ ነው? ነውር ነው! አንዲህ ያለ መጥፎ ነገር አለ።
ጌቶቼ ሆይ!
ወደ ኤርትራም ስናተኩር ወደ ሰንደቃላማው ስንሄድ፤ ኤርትራው ተወካይ “አቶ አሊ አብዱ”
እዚህ እኛ ጋር ቁጭ ብለው አሉ፡ ዋሽተሃል እንዳልባል፤ ሊጠየቁ ይችላሉ፤ (ነጋሶ ጊዳዳ አቋርጠዋቸው “ይቅርታ ወደ ኤርትራ
አይሂዱ ስለ ባንዲራው ስለ ሰንደቃላማ ጉዳይ፤ ወደ ሌላ ጉዳይ አንዳይሄዱ፤…) እሺ! ኤርትራ የማነሳው ስለ ሰንደቃላማ ጉዳይ
በሚመለከት ነው። እዛም ቢሆን ተከብራ አንደኖረች ልናገር ፈልጌ ነው። እዚህ በመላ ኢትዮጵያ ሰንደቃላማ በሌለችበት ጊዜ፤
አስመራ ውስጥ ቅድስት ማርያም ቤተክርስትያን ኤርትራኖቹ ‘የኢትዮጵያ ሰንደቃላማ ይዘው እንደኖሩ ለማስረዳት ነው’።
“ይህች ሰንደቃላማ፤አንድ ነጥብ ቢጨመርባት፤ አንድ ነጥብ ቢቀነስባት፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ
ያዝናል! የሽግግሩ መንግሥት ሰንደቃላማውን በዘምባባና በወይራ ቅጠል ከማያስተካክል ይልቅ፤በአንድ አገር ሁለት አስተዳዳር
አይመስርት! ለአንድነታችን ትክክል የሚሆነው ይህ ሲሆን ነው።”
On
Record: When Meles vilified the Flag
ማጣቀሻዎች
(1)
Thus Spake Zarathustra ከሚል ልብ ወለድ ፍልስፍና መጽሐፍ የተገኘ። ደራሲ ከፍሬደሪክ ኒች/ ትርጉም
ነስሩ ዑመር። ከጀርመንኛ ወደ እንግሊዝኛ ትርጉም የተመለሰው መጽሐፉ አማዞን ውስጥ ብትገቡ ከ $4.00 00 በታች በርካሽ ዋጋ
ታገኙታላችሁ።)
(2)- (ጌታቸው ረዳ፤ ኢትዮጵያን ሰማይ ድረገጽ
አዘጋጅ፤ የትግሬ ልሂቃን በአማራ ላይ ያላቸው ጥላቻ ከምን የመነጨ ነው? ከሚል በመጽሐፍ መልክ በመሰራት ላይ ካለው የተወሰደ።)
አመሰግናለሁ
ጌታቸው ረዳ (Editor Ethiopian semay) getachre@aol.com