Sunday, May 19, 2019

የእነ በርሃኑ ነጋ ኢዜማ ፕሮግራም ስለ መገንጠል ያለው አቋም ከጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ አዘጋጅ Ethio semay)


በጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ባለቤትነት የተመዘገበችው ኢትዮጲስ ጋዜጣ ዋና ዘጋቢ ጋዜጠኛ ምስጋን ጌታቸዉ በፖሊስ ተደቦድቦ ታሰረ
May 22, 2019


የኢትዮጲስ ጋዜጣ ዘጋቢ በፖሊስ ተደቦድቦ ታሰረ፡፡ ዛሬ ጠዋት 4ኪሎ አካባቢ ቤታቸዉ ሲፈርስባቸዉ የነበሩትን የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ቅሬታ ሊዘግብ በሄደበት ወቅት ከቢሮ እንደወጣ በመንገድ ላይ ፖሊሶች ጠብቀዉ በመደብደብና በእጁ የነበረዉን ካሜራና ሌሎች እቃዎች ቀምተዉ ወደ ጣቢያ ወስደዉታል፡፡ጋዜጠኛ ምስጋን በአሁኑ ሰዐት አራዳ ፖሊስ ማዠዣ ጣቢያ ታስሮ የሚገኝ ሲሆን በድብደባ ጉዳት ያደረሰበትን ፖሊስ ለመክሰስ ምስክር ቢጠራም አይሆንም ተብሎ ሲደበድቡት ያዩ የአይን እማኞች ከግቢ እንዲወጡ ፖሊስ አድርጓል ሲል ስንታየሁ ቸኮል ያደረሰን ዘገባ አመልክቷል።

የእነ በርሃኑ ነጋ ኢዜማ ፕሮግራም ስለ መገንጠል ያለው አቋም
ከጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ አዘጋጅ Ethio semay)

ሰሞኑን እንደሰማችሁት ከተለያዩ የከሰሙ (?) የፖለቲካ ድርጅቶች/ፓርቲዎች/ ተወጣጥተው የመሰረቱት ኢዜማ የሚባል አዲስ ፓርቲ መመስረቱን ሰምታችሁ ይሆናል። ይህ ድርጅት የመሰረቱት ያው የሚታወቀው ባለፈው ሰሞን ትችቴ የተቸሁት ብርሃኑ ነጋ እና እንዲሁም ዛሬ ይህንን ዕድል ተጠቅሜ በትንሹ የማሳያችሁ የድሮ በወያኔ ፓርላማ/ምክር ቤት ተመራጭ የነበረው “መለስ ዜናዊ ሞቷል፤ የሞተን ሰው የሰራውን ሓጢያት እያነሳን ማውራት እናቁም” እያለ ሲቦተልክ የነበረ እና በቅርቡም የእስክንድር ነጋን ሕዝባዊ ጥያቄየማየው በጎሪጥ ነው” ብሎ ያለን እና እንዲሁም ትግሬዎች የበላይነት ከተንጸባረቀበት የኢትዮጵያ አየር መንገድ 12 አብራሪዎች እና 4 ቴክኒሻኖች (ብዙዎቹ አማራዎች) ሲባረሩ ወጣት ግርማ ሰይፉ በሚያስደነግጥ አነጋገር “ካፕቴን አበርሃም ጥበቡ” የተባለ በነገዴ/በዘሬ ምክንያት ብዙ ግፍ ደርሶብኛል ብሎ “ፓይለት ሆኖ ባርያ ከመሆን አርሶ አደር ሆኖ በነፃነት መኖር”  መሆን ይሻልል ብሎ አብራሪነቱን ትቶ ወደ አራሽ ገበሬነት የተለወጠው ግፍ የደረሰበት ዜጋችንን
“በማንነቴ ከሥራ ተባረርኩ ለሚል ዛሬ ጆሮ የለንም፣ ለምን ያኔ አላልክም? ብለን እንጠይቃለን። ፈርቼ፣ የት፣ ምናም ከሆነ መልሱ ፈሪ ከዚህም በላይ ይጠብቀዋል (የታረመ ፊደል)። ለፓይለትነት ከመውረድ በላይ የት እንዳያውርዱት ነው የሚፈራው። የት ሆኖ ልጅ ለማሳደግ ብለዋል ዶር ሀይሉ አርሃያ። ጎበዝ በብሄር ማንነት ተባረርኩ የፓይለቱን ከተቀበልኩ፣ የልደቱንም መቀበል ግድ ይለኛል። መውረድ አቃተኝ አልሞክረውም። "በመንጋ መንጫጫት እውነት አይፈጥርም። ፓይለቱ ወንድማችን በግብርናው ዘርፍ ምን አሰመዘገበ? ለአካባቢው አርሶ አደሮች ሞዴል ነበር? ወይስ ያው እንደ አነርሱ አራሽ ሆነ?" (አቶ ግርማ ሰይፉ ማሩ)

 በማለት ግፍ በደረሰበት ወገናችን ሲያሾፍ የነበረ እና የመሳሰሉ ሰዎች የመሰረቱት አዲስ ፓርቲ ነው “ኢዜማ” ማለት። ይህ ሰው የፓርላማ ተመራጭ ሆኖ የወያኔ አስተዳዳር በዘር የተዋቀረ ግፍ እንደሚፈጽም እያወቀ ግፍ በተፈጸመባቸው ዜጎች እንዲህ ያለ ጸያፍ ምላስ መሰንዘር ዛሬ በዚህ ፓርቲ ምን ብለው ሊሰብኩን እንደመጡ ግራ ገብቶኛል።

“ኢዜማ’ ብሎ የተጠራው ይህ ድርጅት ከትናንት በስቲያ በድርገጾች በለጠፈው ክፍል አንድ ባወጣው ፕሮግራሙ መፈታት ያለባቸው ባገራችን ውስጥ የተጫነብንን የጠላት ሴራ “በትምህርት ተቋማት፤ በዳንስ ቤቶች፤ እስከ ሚኒስቴር እና የሃይማኖት መሪዎች ድረስ እንደ እሳት ሰደድ የደረሰው የግብረ ሰዶም ወረርሺኝ እና ስለ ባሕር ወደቦቻችንም ሆነ ስለ ኤርትራን ጉዳይ አስመልክቶ” ምንም የተነፈሰው ነገር የለም”። ሌለው ሁላችንም የሚያሳስበንን ጣሊያኖች እና ኢትዮጵያውያን ግራ ክንፍ ፋሺስታዊ ማርክሲስቶች (በትግሬ ወያኔ በመለስ ዜናዊ እና በኦሮሞው ኦነግ መሪነት) የቀረጹልንን አገርን የማፍረስ ተልዕኮ ማለትም ‘ስለመገንጠል መብት መገደብ ወይንም መፍቀድ’ ያነሳው ነገር ምንም የለም። በሚገርም “የሕዝብ ውሳኔ” በሚል ኮድድ በሆነ “ምስጢራዊ አባባል” ግን ሕዝብ ከፈለገ በድምጽ መገንጠል ይችላል በሚል መልኩ አስቀምጦታል።

ትንሿ ትግራይን  ሲም-ካርድ’ (Sim Card ) ሰይሞ፤ ታላቋ ኢትዮጵያንግዑዝየቴሌፎን ቀፎ” አድርጎ የሳላትን የትግሬዎች ትምክሕት በሕግ የተደነገጉ 44 የጎሳ ባንዴራዎች አዘጋጅቶ፤ ለሚገነጠሉ ጎሳዎች አንቀጽ አዘጋጅቶ አገሪቱን ለማፍረስ እንደሰራ ይታወቃል። ኢዜማ በአገር ሰንደቃላማ ላይ ያለው አቋም ግልጽ ሲያደርግ “ስለ የጎሳ ባንዴራዎችም ሆነ ስለ መገንጠል” ምንም ያለው ነገር የለም። ኢዜማን እየመራ ያለው ብርሃኑ ነጋም ካሁን በፊት በግልጽ እንዳስቀመጠው “አንድ ጎሳ/ቤተሰብ… እገነጠላለሁ ካለ በጠምንጃ አንይዘውም በደምጽ መገንጠል ይችላል ብሏል” አሁን ያንን በውስጠ ሴራ ‘ኢዜማ’ ከዚህ በታች እንደሚከተለው አስቀምጦታል።

“1.1.3. ማንኛውም የፖለቲካ ጥያቄዎች በውይይት እና በዴሞክራሲያዊ ስርኣት እንዲፈቱ ይደረጋል፡፡ እንደ አስፈላጊነቱ ወሳኝ የሆኑ ጉዳዮች ወደ ህዝብ ውሣኔ እንዲሄዱ ስርዓት በማበጀት የህዝብን ውሣኔ ተግባራዊ ይደረጋል።” ይላል።

ይህ አባባል ወደ ጎረቤት አገሮች እንቀላቀላለን፤ወይንም እራሳችን አገር እንሆናለን (እንገነጠላለን) የሚሉ ነገዶች /አካባቢዎች/ወረዳዎች /አውራጃዎች/ ቤተሰቦች… ካሉ ”ወደ ህዝብ ውሣኔ እንዲሄዱ ስርዓት በማበጀት የህዝብን ውሣኔ ተግባራዊ ይደረጋል” ማለት ነው። የፍሬ ነገሩ ዋና ማጠንጠኛው እዚህ ላይ ያለቀ የደቀቀ ያደርገዋል። እነዚህ የበሰበሱ ደካማ ፖለቲከኞች በመሰረቱት አዲስ ፓርቲ ውስጥም የወያኔ ቀጥተኛ ቅጂ “ሕዝበ ውሳኔ” በሚል ሊሂቃን የሚፈበርኩትና የሚያቀጣጥሉት የተቆነጃጃ ማጃጃያ ቃላት ተጠቅመው አገር ለማፍረስ ወደ ላ እንደማይሉ የተረዳንበት አንቀጽ ነው። እንግዲህ ሕዝበ ውሳኔ የሚባለው ወሳኙ ብዙ ሳይሆን አንድ ሰው ነው

ለመሳሌ ሁለቱ ተቀናቃኝ ክፍሎች 50% ሌላኛው ደግሞ 50% ድምጽ ካገኙ ለመገንጠል የሚፈልገው ክፍል ማግኘት ያለበት ደምፅ 50%+1 ከሆነ በአንድ ሰው የካርድ ምርጫ ምክንያት አገር ይፈርሳል ማለት ነው። በቃ! ይህ ነው ሕዘበ ውሳኔ ማለት “ሕጋዊ አምባገነንነት” ማለት ነው። በሕዝብ ድምጽ ተንተርሰው የአንድ ሰው ካርድ “ወሳኝ ደምፅ” ሆኖ እንዲህ ያለ አገር በማፍረስ አሰራር ውስጥ ኢዜማም ገብቶበታል። ጠየተቀሩት ፌደራል ምናምን ምናም የሚሉ የተቀባዠሩ “ዲሞክራት ተቃዋሚ ፓርቲዎችም” ከዚህ ወረርሺኝ አልተላቀቁም።
ስለ ሰንደቃላማ ያወጣውን እንመለክት።
“2.6. የኢትዮጵያ ሠንደቅ ዓላማ አረንጓዴ፣ ቢጫ እና ቀይ ይሆናል፡፡ የመንግሥት ዓርማ የሚያስፈልገው ከሆነ በሕዝብ ይሁንታ የሚወሰን ይሆናል፡፡” ይላል።  (ይህም 50%+1 ማግኘት ማለት ነው)። እኔ ግራ የገባኝ “ለምንድነው የመንግሥት ዓርማ የሚያስፈልገው?” የኢትዮጵያ ሰንደቃላማ የመንግሥት ነው፡ አይደለም እንዴ? የኢትዮጵያ ሰንደቃላማ “አረንጓዴ፤ቢጫ እና ቀይ” ከሆነ  ሌላ የመንግሥት ዓርማ ለምን ያስፈልጋል? ሌላ  ዓርማ ማውለብለብ ምን ማለት ነው። ሌላ  ዓርማ እንዲያውለበልብ አይፈቀድለትም ብሎ እቅጩን ማሳወቅ ምንድ ነው ችግሩ?

“1.1.4. የኢ-ዜማ የፖለቲካ ፕሮግራም በማንኛውም ሁኔታ የዜጎችን የኤኮኖሚ ነፃነት፣ ማህበራዊ ፍትህ እንዲሁም የመኖሪያ ምድራችንን ከባቢ ሊጎዳ በሚችል መልኩ አይገረጽም።” ይላል

የመኖርያ ምድራችንን አካባቢ በሚጎዳ መልኩ እንዲቀረጽ እንፈልጋለን ብሎ አንዱ ክፍል ቢነሳ መፍትሔው ያው “የሕዝብ ውሳኔ” ሊሆን አይደለም ወይ? የሕዝብ ውሳኔ ገደቡ የት ነው? መንግሥት የሚባል ፈርጠም ብሎ መወሰን መብት የለውም? መገንጠል ትችላለህ ተብሎ ሁሉም በሕዘብ ውሳኔ የሚወሰን ከሆነ አካባቢየ በሚጎዳ መልኩ በፈለግኩት ልቅረጽ ቢል የሚያቆመው አካል ማን ነው?

“1.1.5. ዜጎች ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ሌሎችንም መብቶቻቸውንና ጥቅሞቻቸውን ለማስከበር በጋራ የመደራጀት፣ ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብታቸው ይከበራል።” ይላል።

ሃሳብን በነፃነት የመግለጽ መብት አከብራለሁ ካለ የሸሪዓ/የካሊፋ/ መንግሥት(እስላማዊ መንግሥት) ይመስረት ብለው አንገታቸውን ለጊዜው አቀርቅረው ውስጥ ለውስጥ በፖለቲካ ድርጅቶች ተሸሽገው ያሉት ነግር ግን በፓልቶክ እና በየ ዩቱብ ላይ በወጣቶች በተለይም በወጣት እስላም ሴቶች እህቶቻችን ሕሊና ውስጥ መርዝ የሚረጩት “የኢትዮጵያ ሙስሊም ብራዘር ሁድ” ዜጎች ስለሆንን “ተደራጅተን ሃሳባችንን እናሰራጭ” ቢሉ ኢዘማ በዚህ መልኩ በነፃነት መብት ሰበብ “የመደራጀት፤የመሰብሰብ፤የመስበክ እና የማወጅ ነፃነት መብታቸውን ሊያከብር ይሆን”? 

“1.1.6. የኢትዮጵያን የግዛት አንድነት ሊገሰስ የማይችልና የማይገሰስ መሆኑን፤ በኢትዮጵያ ሉአላዊ ግዛት ውስጥ የሚገኝ ማናቸውም የተፈጥሮ ሃብት የሃገሪቱ ዜጎች ሁሉ የጋራ ሃብት መሆኑን ኢ-ዜማ ያምናል።” ይልል።

በሕገ ወጥ የተነጠቅነውን ሉአላዊ ኤርትራ ውስጥ የሚገኝ ሃብቶቻችን ፤ገዳሞቻችን ወደቦቻችንን እና ሳይወዱ በግድ ለሁት የተከፈሉት ነገዶች እና ቤተሰቦች “ሉአላዊ ግዛትነት” ኢዜማ ምን አቋም አለው? ምንም! አስመራ ውስጥ ከኢሳያስ ጋር ሲሞዳሞድ የነበረው ከብርሃኑ ነጋ ይህንን የሚታሰብ አይደለም።ያኔ ስለ ባሕር ወደብ ያለውን አቋም ተጠይቆ እኛ ንቅናቄዎች ነን እለ ወደብ እና ኤርትራ ጉዳይ ለመወሰንም ሆነ አቋም ለማስያዝ መብት የለንም ሲል አሁንም አገራዊ ፓርቲ ብሎ አዲስና ‘ሕጋዊ ፓርቲ’ ሲመሰርትም ያንኑ አቋሙ እንደጠበቀ ነው!

“1.2.3. የየራሳቸው ሕግ አውጪ፣ ሕግ አስፈፃሚ እና ሕግ ተርጓሚ ይኖራቸዋል፡፡ የአካባቢ መስተዳድሮች የራሳቸው የወንጀል መቆጣጠሪያ የፖሊስ ተቋም ይኖራቸዋል።” ይላል።

ሁለት ነገሮችን ላንሳ። የአካባቢ ፖሊሶች ሲባል ምን ማለት ነው? የነገድ ፖሊሶች ናቸው? (ምክንያቱም በፕሮግራሙ ላይ ‘አንዳንድ ቦታ ውስጥ ቋንቋን ያማከለ መስተዳድር/አከላላል ይከተላል ይላል) እንዚህስ በምን ስም ነው የሚጠሩት (በቋንቃቸው ‘ኦሮሚያ ወዘተ ያ ወዘተ ያ… ወይስ ሌላ መጠሪያ ሊሰጣቸው ነው?)። ለምንድነው ካሁኑኑ የሚዋቀሩት አስተዳደራዊ አካባቢዎች ማን ከማን እንደሚዋሃድ ወይንም ብቻውን (ቋንቋ መሰረት አደርጎ) የሚተዳዳር/የሚቀረጽ አካባቢ/ነገድ/ በፕሮግራማቸው ግልጽ አድርገው ሊነግሩን ያልፈለጉት? ይህንን በተመለከተ በፕሮግራሙን ማውጣት አስፈላጊ ሆኖ አላገኙትም? ካልሆነ ፕሮግራማቸው ይህ ብቻ ከሆነ ይፕሮግራሙ ግልጽነት ጥያቄ ጭሮብኛል። 

ከምድሪቱ እትብት ተለይተው ብቻቸውን ርቀው የተጓዙት አራዊቶቹ የወያኔ መሪዎች በቅኝ ግዛት ያልተገዛው ይህ ኩሩን ሕዝብ የሚቀጠቅጡት የወታደሮቹ ማዕረግ ስም፣ ንግድ ቤቶቹ፣ ትምህርት ተቋማቱ፣ /ሀገሮቹ (ዞን) ጎዳናዎቹ በባዕድ ቋንቋ ተሰይመዋል። የወታደሮቻቸው “መታወቂያ” ባጅ/በደረታቸው የሚታይ ስማቸው/ የሚጻፈው በእንግሊዝኛ ነው፡ ማዕረጋቸውም ኮማንደር፣ ኮንስታብል፣ ኢንስፔክተር፣ ሱፐር ኢንስፔክተር፣ ሱፐር ኢንቴንዳንትነው።ሻምበል፣ ሻለቃ፣ መቶ አለቃ፣ ሃምሳ አለቃ፣ አሥር አለቃ…. የሚሉ አገር በቀል ወታደራዊ መጠሪያዎች የአማራዎች ነውና “በእንግሊዝ ቅኝ ግዛት እንደተገዙት  የኬኒያ እና የናይጄሪያ ፖሊሶች” ስያሜ ወስደን በላቲን ማዕረግ ሰይመናቸዋል ብለውናል። አማራና አማርኛን ለማጥፋት የተነሳንበት ዓላማ ነውና ስትፈልጉ አልቅሱ ይሉናል። በዚህ መልክ እያለቀስን 28 አመት ይኼየው ዛሬም ቀጥሏል።የቆየውን ይህ የቅኝ ገዢነት ወደ አገራዊ ስያሜ (ወደ ነበረበት) ለመመለስ ኢዜማም ሆነ ሌሎቹ ተቃዋሚ ፓርቲዎች በዚህ ላይ ምን ሃሳብ አላቸው? መልሱን እጠብቃለሁ።

መዝናኛ ስፍራዎች ንግድ ፤ትምሕርት ቤቶች የተሰየሙበት ላቲናዊ፤ዓረባዊ፤ጣሊያናዊ፤ቻይናዊ ስያሜ ያላቸው መጠሪያዎቻቸው “አገርኛ” በሆነ “የስም መጠሪያ” እንዲሆን በሕግ እንዲጸድቅ ኢዜማ ይሰራል ወይስ እንደ ድሮው ተቃዋሚዎቹ ተበባሪነታቸው/ቸልተኛነታቸውን ይቀጥሉበታል? 
አመሰግናለሁ - ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ)