Saturday, March 7, 2015

“በዘሐበሻ ድረግጽ” አዘጋጅ ላይ የተቃውሞ ጥያቄ ዝግጅት
“ታርሞ የቀረበ” “በዘሐበሻ ድረግጽ” አዘጋጅ ላይ የተቃውሞ ጥያቄ ዝግጅት
ከጌታቸው ረዳ (የ Ethiopian Semay አዘጋጅ)
(Friday, March, 09, 2015)

ለመላ ኢትዮጵያዊያን አርበኞች እና አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን ሁሉ!
መጀመሪያ ሰላምታዬ ይድረሳችሁ።
 


ባለፉት ቀናቶች በስሕተት ያልታረመ ግርድፍ ጽሑፍ በኢንተርኔት አንዲለጠፍ ልኬ ተለጥፎ ነበር። ይህ በምትኩ የቀረበ ሰፋ ያለ ሐሳብ የያዘ ጽሑፍ ነው።


 ለብዙ አመታት በኢትዮጵያ ሥም ተጠልለው እኛን መስለው የኢትዮጵያን ስም እንደ ኦነግ እና ኦብነግ “ሐበሻ” (ዘሐበሻ) በሚል መጠሪያ እየተጠቀሙ እና ሰንደቃላማችንን በሎጎ/መለያ በድረገፆች እየለጠፉ እኛን ለማጃጃል ድረገፆችን አዘጋጅተው የሚንቀሳቀሱ አዘጋጆች የታዘብናቸው ጥቂቶች አሉ።ከነዚሁ አንዱ ለኦነግ ልቡ የሚደማ “የኦሮሞ” ጎሳ ነው ተብሎ የሚነገርለት  ወጣት “ሔኖክ አለማዮህ” የተባለው የዘሐበሻ ድረገጽ አዘጋጅ አንደኛው እና ቀንደኛው የጸረ ኢትዮጵያ ፕሮፓጋንዳ ጽሑፎች/ባንዴራዎች/የስብሰባ ማስታወቂያዎች.. አሰራጭ ድረገጽ በመሆን፤ “የሳብቨርሲቭ/የጠላት ማጥቂያ ዘመቻ” ተዋናይ በመሆን በግምባር ቀደም የሚጠቀስ የድረገጽ አዘጋጅ ነው። ለምሳሌ ትናንት March, 5, 2015 Oromiaya-The Executive Committee (EC) of the Oromo Liberation Front (OLF) - See more at: http://www.zehabesha.com/#sthash.BjdFevvG.dpuf በሚል ርዕስ ኦነግ ያወጣውን አፍራሽ ጥሪ ለጥፎላቸዋል።

ይህ ፎቶ የዘሐበሻ ድረገጽ ዋና አዘጋጁ ሔኖክ ኣለማዮህ ነው።
አንዲህ ያሉ ጸረ ኢትዮጵያ የሆኑ የጸረ ኢትዮጵያ ሃይላት ቅስቀሳ እና ማስታወቂያዎች በዚህ ድረገጽ ለብዙ አመታት ሲለጠፉ መኖራቸው ይታወቃል። ካሁን በፊት በቃለ መጠይቆቼም ድረገጹን በሚመለከት አደገኛነቱ እና ብዙ ሰዎች የተጃጃሉ መሆናቸውን አሳውቄአለሁ። አሁንም እያስጠነቀቅኩኝ ነው።

ዩዲጄ የተባለ ፓርቲ፤ በወያኔ “የዲሞክራሲ ካሲኖ” በመቋመር “ዲሞክራሲ” አመጣለሁ ብሎ እራሱን አጃጅሎ ድርጅቱን የእምቧይ ካብ አንዲሆን ያዳረገ የተቃዋሚ ድርጅት፤ በውጭ አገር በግምባር ቀደም ሲደግፉት የነበሩትም አንዱ ይኼው የዚህ የዘሐበሻ ድረገጽ አዘጋጅ አንዱ ነው። ለጣለት ፕሮፓጋንዳ ከማስራጨቱ አኳያ ሲገመገም፤ ዩዲጄን ለምን ሥራ ይደግፋቸው አንደነበር ለወደፊቱ እንደ እነ ጃዋር መሐመድ “ታረክ” የሚገልጸው ይመስለኛል። ልጁ በወያኔ እፈለግ ስለነበር በሊቢያ በሰሓራ በረሃ አድርጌ ለመሰደድ በቅቻለሁ፡ ብሎ ላሜሪካ ድምፅ ቃለ መጠይቅ የሰጠ ቢሆንም፤ ይህ ወጣት ጥቂት አመታት ሚኔሶታ ከኖረ በሗላ ተመልሶ ወደ ኢትዮጵያ ገብቶ አንደገና በሰላም መመለሱ በራሱ ኢመይል ያደረገልኝ መሆኑን እሱም አይክደውም። በዚህ ውዥምብራም የታሪክ ጊዜ ማን እና ምን እንደሆነ ማወቅ አስቸጋሪ ሆኖ አግኝቸዋለሁ። ታሪክ ለወደፊቱ ይገልጸው ይሆናለል የምለውም ለዚህ ነው።

ብቻ እሱ እና መሳይ ጓደኞቹ፤ እውጭ አገር ሆነው እዛ ላለው ዩዲጄ  ሲባል ለነበረው የተቃዋሚ ድርጅት፤ ቡድን ለይተው፤ ሲላቸውም ወጣቱ እንጂ “ሽማግሌ” መምራት የለበትም እያሉ በኢንጅነር ግዛቸው እና በተቃራኒ የቆሙ ሰዎችን በማናከስ ድርጅቱ ተበጣብጦ ለዚያ አስገራሚ ውርደት እንዲበቃ ከፍተኛ የፕሮፓጋንዳ ሥራ ሲያሰራጩ ከነበሩ ድረገፆች ይኼው አንዱ ነው። በወጣት እና በሽማግሌ የፖለቲካ አመራር ጨዋታ ገብተው “ሥልጣን ሳይያዝ፡ በዛ ቁማር ፤ የወያኔ ጭዳ ሆነው ተቃጥለው ተበታተኑ። በግርማ እና በግዛቸው በኩል ነበረው ውዝግብ እንደ ጀብዱ ተቆጥሮ ንትርካቸውን በአውዲዮ ቪዲዮ የተቀዳውን በየድረገጹ እንዲለጠፍ አድርገው አድምጠነዋል። ያ ደግሞ የነዚህ ወጣቶች ነን ባዮች ሥራ ነው። አስጋራሚ! 

ለዚህ የወጣት እና የሽማግሌ ይምራ መፈክር ተዋናዮች እነ ሄኖክ እና የካናዳው (ብርቱካን ቃሌ ዋና ተቆጣጣሪ) ታዬ “ማይጨው” የተባሉ ናቸው። እነሱን የመሳሰሉ ወጣቶች ካሁን በፊት ብርቱካን መዲቅሳና ብርሃኑ ነጋ… በቦዲ ጋርድ ታጅበው ከለመዚን ሲወርዱ “የእጅ ቦርሳዎቻቸው እና ጃንጥላ አበባዎቻቸውን” እየተቀበሉ ከሰማይ የወረዱ መላእክት አስመስለዋቸው ከሗሊቷ ‘ኩት፤ኩት‘ እያሉ አስቂኝ ፖለቲካ እየሰሩ ወጣቱ ብርሃኑ ነጋ፤አንዳርጋቸው ጽጌ፤ እና ወጣትዋ ብርቱካን መዲቅሳ እንጂ “ሽማግሌው” ሃይሉ ሻውል ወይንም “ሽማግሌ ፖለቲከኞች’ ጊዜያቸውን አብቅተዋል እና ፖለቲካውን አይምሩት፡ እያሉ ቅንጅት እንዲፈርስ የተጫወቱት ሚና የሚዘከር ነው። የዛሬ ወጣቶች የተባሉት ዬዩዲጄ ወጣት አመራሮች ደግሞ ገና ምርጫው ሳይደርስ ለወያኔ ጅቦች ተመቻችተው ከደጃፍ በራቸው ሳይወጡ ተበሉ። 

የዘሓበሻ ድረገጽ አዘጋጅ ዛሬም ሆነ ትናንት ኢትዮጵያን ለማፍረስ ያልተኛው ኦነግ የተባለው የእስልምና አክራሪ እና የናዚ ርዕዮት የተቀላቀለበት እምነት የሚያራምዱ ግለሰዎች ሰዎች ያሉበት ድርጅት፤ ካሁን በፊት “ኦነግ” የአማራ ህጻናት እና ሽማግሌዎች፤ነብሰ ጡሮችን እና ዓይነሰውራን በቢላዋ አንግታቸውን ያረደ፤ ከነ ነብሳቸው ወደ ገደል ገፍትሮ ኢትዮጵያዊያንን (ኦሮሞዎችም ሳይቀሩ የገደለ) የጨፈጨፈ፤ የአገራችን ሕዝብ ለማበጣበጥ፤የሌላውን ማሕበረሰብ ሳይጨምር ከወያኔ ጋር ሆኖ የፋሺሰት ክልል ካርታዎችን አዘጋጅቶ ሰፈፊ መሬቶችንና ወንዞችን ወደ ኦሮሞ አጠቃልሎ የሕዝባችን ሕይወት “እንደ የሩዋንዳ ሕዝብ” ለማናጋት ፤ቢያንስ ከ42 አመት በላይ አገራችንን ለማፍረስ ያልፈነቀለው ድንጋይ የለም። 

ሆኖም፤ በጠምንጃ ተደስቆ፤ ተዋርዶ፤አፍሮ እና  አፈር-ልሶ፤ በቦሌ አይሮፕላን ጣቢያ ተሳፍሮ የቀረቺውን ብጥቅጣቂ ድርጅቱን ለማትረፍ ከአገር ሸሽቶ መኖሪያው በኤርትራ፤ በአውሮጳ ፤ በአሜሪካ፤ እንዲሁም ዓረብ አገሮች በማድረግ እየተመጸወተ፤ ያልነቁ ኦሮሞዎችን በጎሳ አደራጅቶ በማሞኘት “ሰንካላ ዓለማውን” ለማሳካት ለበርካታ ዓመታት ጥሯል። ያንኑ ለማሳካትም በተመሳሳይ በኢትዮጵያዊያን የተቃዋሚ  ድርጅቶች ውስጥ ሰርጾ ለመግባት ሞክሮአል። ካሁን በፊትም “ኤ ኤፍ ዲ” የተባለ በሻዕቢያው “የማነ ማንኪ” እና በኦነግ መሪነት የተዋቀረ ድርጅት (ኦነግ፤ኦብነግ እና ቅንጅ ማለትም የአንዳርጋቸው ጽጌ “ቅንጅትን” የወከለ። በወቅቱ አንዳርጋቸው “ኤስ ቢ ሲ” ከተባለ ራዲዮ ጋር የሰጠው አስገራሚ ቃለ መጠይቅ ሌላ ቀን አስነብባችሗለሁ) ያልጣረው ነገር አልነበረም። 

በቅርቡም እኛን ለማጃጃል  አንዳንድ የተቃዋሚ መሪዎች እና ምሁራን ተብየዎች ለምሳሌ፤- ብርሃኑ ነጋ እና ዶ/ር ጌታቸው በጋሻው…. የመሳሰሉት “አፈቀላጤዎች” በማድረግ ተከልሎ ኢትዮጵያዊያን ማሕበረሰቦችን በመጥራት በየአገሩ ብዙ የፕሮፓጋንዳ ሥራው ለመንዛት ችሎ እንደነበር የቅርብ ትዝታ እና በቪዲዮ የተዘገበ መረጃ አለ።ያ ሴራ በከፍተኛ ጥረት አጋልጠን  አክሽፈነዋል።
ዛሬ ደግሞ የሚኔሶታ /አሜሪካ ኗሪ የኦሮሞው ጎሳ ነው እየተባለ የሚነገርለት የዘሐበሻ ድረገጽና ጋዜጣ ባለቤት የሆነው ሔኖክ ዓለማዮሁ-የተባለው-“ሳብቨርሰር/የጠላት-ተባባሪ” የሻዕቢያ፤የኦነግ፤የኦጋዴን…ፕሮፓጋንዳ፤ምሰሎች፤መዝሙሮች፤ስብሰባዎች፤በዓሎች፤ ዘፋኞቻቸው እና የፖለቲካ መሪዎቻቸው (በፕሮፓጋንዳ አዳራሽ አዘጋጅ በመሆን) እና ቦታ በመስጠት፤ጠላቶቻችን ከጠበቁት በላይ ከፍተኛ የሆነ ቅስቀሳ በድረገፁ እንዲያሰራጩ እየተባበራቸው ለብዙ አመታት ቆይቷል። ዛሬም ያለ ምንም ይሉኝታ የፕሮፓጋንዳቸው የሴራቸው አሰራጭ ሆኖ ቀጥሎበታል። 

ዛሬ ይህ የሳብቨርሲቭ/ኢትዮጵያን-የማጥቃት ዘመቻ እና ቅንብር ለማስቆም እና ለመቃወም፤ በሜኔሶታ ኗሪዎች የሆናችሁ ኢትዮጵያዊያን በዘሐበሻ ድረገጽ እና ጋዜጣ በሚዘጋጅበት ቦታ ሄዳችሁ ሰላማዊ ሆነ ተቃውሞ አንድታሰሙ፤ካልሆነ የተቃውሞ ደብዳቤ አንድትጽፉለት ጥሪዬን አቀርባለሁ። ጠላት ምንም ቢሆን ጠላት ነው፤ ዋናው ጠላት ግን አሾክሻኪው እና ተባባሪው ቀንደኛ ጠላት መሆኑን ልብ ማለት አለባችሁ። ስንት ጊዜ ለመሞኘት ዝግጁ ናችሁ? አንድ ጊዜ ? አንድ በቂ ነው። ሁለት?  ሞኞቹ  እኛ እንጂ የጠላቶቻችን አሾክሻኪው ሊሆን አይችልም። ለነገሩ ወያኔ እና ኦነግ ልዩነት አላቸው? ልዩነት ከሌላቸው ዘሐበሻ ድረገጽ ለምን ታዲያ የወያኔ ፕሮፓጋንዳ አይለጥፍም? ሄኖክ ኦነግ እና ወያኔን የሚያያቸው፤ አንደኛው ጠላት አንደኛው ወዳጅ አድርጐ ስለፈረጃቸው ነው። ለኛ ሁለቱም የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታ ናቸው። ሁለቱም በብሔራዊ እና ሰብአዊ ወንጀል ሊጠየቁ የሚገባቸው ጸረ ሕዝብ ናቸው።

ኢትዮጵያዊያን እስኪ አንድ ጥያቄ ልጠይቃችሁ! የኢትዮጵያዊያን ተብሎ የተሰየመ ድረገጽ የወያኔ ፕሮፓጋንዳ ቢለጥፍ የሚሰማችሁ ስሜት ልትገልጹልኝ ትችላላችሁ? ሄኖክ አለማዮህ ኦነግ እና ወያኔ ልዩነት አላቸው የሚል አምነት ካላሳደረ በቀር ‘ሁለቱም” እኩል ጸረ ኢትዮጵያ ሃይላት ናቸው የሚል ከሆነ፤ ለምን የወያኔ ማስታወቂያዎች አብሮ ሲለጥፍ እና ሲያሰራጭ አላየነውም? አንዱ ጠላት አንዱ ወዳጅ እያሉ ሕዝብን ለማጃጃል የሚደረግ ሻጥር/ተንኰል ነቅታችሁ ማወቅ አለባችሁ። ተላላኪዎች የሚገቡበት ዋነኛ የተልዕኮ ሴራቸው ሁለቱም ጠላቶቻችን ሆነው እያሉ፤ አንዱን በወዳጅ አንዱን በጣለት ፈርጀው፤ ኦነግን በሕዝብ ልብ አንደ ገራገር ድርጅት ተደርጎ አንዲወሰድ የማድረግ “የማታለል ሥራ” አንደኛው የተካኑበት “የሳብቨርሲቭ/የማጥቃት” ጥበብ አንዱ ነው።

 ባለፈው ሦሰት ሳምንታትም ሆነ አንዳርጋቸው ከተያዘበት ቀን ጀምሮ፤ ኤርትራኖች ስለ አንዳርጋቸው ጥብቅነና ቆመው “ኢትዮጵያን ናሺናሊሰት” አፋችሁን ያዙ እያሉ በዚሁ ድረገጽ ሲሰድቡን ነው የከረሙት። ይህ ድረገጽ ሁሉም አደብ ግዛ አንዲለው ጥሪዬን አቀርባለሁ።

አመሰግናለሁ።
ኢትዮጵያ በጥቂት በልጆቿ ጠንካራ ትግል አንደገና ተቆማለች
የኢትዮጵያን ሰማይ ብሎግ አዘጋጅ ጌታቸው ረዳ getachre@aol.com