Saturday, March 3, 2018

አንተ የደርግ ወታደር… ባክህ ይቅር በለኝ?! ስዩም ተሾመ Ethiopian Semay




አንተ የደርግ ወታደርባክህ ይቅር በለኝ?!
Ethio think thank Group
ስዩም ተሾመ
8 TPLf fighters getting in to the Palace in Addis murdering Ethiopian soldiers as Italian colonizers did to Ethiopians in the past with no  feeling of Ethiopianess
ላመንክበት ዓላማ፥ በቃልህ ፀንተህ ለሀገርህ ለወደቅከው የደርግ ወታደር፣እባክህ ይቅር በለኝ?! እርግጥ ነው፣ ከቤተ መንግስቱ ደጃፍ የወደቅከውለመንግስት ነውእንዳይባል ደርግ ከወደቀ ሰነባብቷል፣ለመንግስቱ ኃይለማሪያም ነውእንዳይባል ዚምባብዌ መግባቱን ሰምተሃል፣ማምለጫ ጠፍቶህ ነውእንዳይባል ያለኸው አራት ኪሎ ቤተ መንግስት ነው። ከህዝብና መንግስት የተጣለብህ ኃላፊነትየሚኒሊክን ቤተ መንግስትን መጠበቅ ነው አውቃለሁእንዲህ የወደቅከው ለደርግ ሳይሆን ለሀገርህ ነው፣ ከቁሳዊ ጥቅም ይልቅ ለቃልህ ነው።
አንተ በቃልህ ፀንተህ ላመንክበት የወደቅከው የደርግ ወታደር፣ እባክህ ይቅር በለኝ። አንተን ትቼ ገዳይህን ስላመንኩኝ ፀፀቱ ገደለኝ። ከሞት የተረፉት ጓደኞችሁ ልክ እንደ ወራሪ ጦር ሰራዊት ሲበተኑ ዝም አልኩኝ። በድህነት ሲሰቃዩ ግድየለሽ ነበርኩኝ። በርሃብ አለንጋ እና በሰው ዓይን ሲገረፉ ቸልተኛ ነበርኩኝ። ሃጢያቴ ተዘርዝሮ አያልቅም፣እባክህ ይቀር በለኝ!?  
የተዋደቁላት ኤርትራ ከአሰብ ወደብ ጋር እንደ ገጸ-በረከት ለሻዕቢያ ስትሰጥ በቁጭት ሲያለቅሱ ዝም አልኩኝ። ኤርትራ ኢትዮጲያን ስትወር ግን ከወደቁበት ትቢያ ተነስተው የሀገራቸውን ሉዓላዊነት አስከበሩ። የኤርትራ ጦር የተሸነፈው በእነሱ አስተዋፅዖ ሳይሆን ከትቢያ ላይ ጥሎ-ባነሳቸውበመለስ ዜናዊ የአመራር ብቃት ነውሲሉኝ አመንኩ። ሳይውል-ሳያድር ባድመን ለኤርትራ አሳልፎ መስጠቱን በሰማሁ ግዜ እጅግ ተፀፀትኩኝ። የኤርትራ ስደተኞች በአዲስ አበባ ከተማ እንዲህ በነፃነት የተቃውሞ ሰልፍ ሲያደርጉ ቀናሁኝ። የሀገሬ ልጆች መስቀል አደባባይ ላይ የተቃውሞ ሰልፍ ቢወጡ እንዲህ እንደ ጠላት በጭቃኔ ሲቀጠቀጡ ስመለከት ፀፀቱ ገደለኝ። 
  Not Ethiopian citizens, but Eritreans have the full rights in Ethiopia to protest against TPLF's refugee center maladministration or against Isayas Afewerki freely with no fear of arrest as they wish. Strange!!!
ላመንክበት ዓላማ፥ በቃልህ ፀንተህ ለሀገርህ ለወደቅከው የደርግ ወታደር፣እባክህ ይቅር በለኝ?! አንተን ችላ ብዬ ገዳይህን አመንኩኝ። አንተን የገደለህ እኔም ገደለኝ፣ ሀገር-አልባ አደረገኝ። በኢትዮጲያ ምድር ስደተኛ ሆንኩኝ። በአንተ ላይ የደረሰው በእኔ ላይ ደርሶብኝ ፀፀቱ ገደለኝ። አንተ የደርግ ወታደር፣ባክህ ይቅር በለኝ?
እጹብ ድንቅ ጽሑፍ! ኢትዮፕያን ሰማይ!