Wednesday, January 5, 2022

ወደ አራዊትነት የተለወጠው የትግራይ ተዋጊ ሃይል የዓለም አቀፍ ሴት ደፋሪዎችን ሬከርድ ሰብሯል! ከጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ)

 

 

ወደ አራዊትነት የተለወጠው የትግራይ ተዋጊ ሃይል የዓለም አቀፍ ሴት ደፋሪዎችን ሬከርድ ሰብሯል!

ከጌታቸው ረዳ

(ኢትዮ ሰማይ)

Ethiopian Semay

1/5/2022

እናት አገር አልቅሺ! ያለው ደቡብ አፍሪካዊውአላን ፓተንላለቀሰላት እናት አገር ዛሬእናት አገር ኢትዮጵያአልቅሺ ለተባለላት ደቡብ አፍሪካ በባሰ መልኩ እናት ኢትዮጵያበጥላቻእና Toxic masculinity “መርዛማ ወንድነትበተሰማቸው የትግራይ ተዋጊዎች 85 ዕድሜ ያላቸው መነኩሴና 13 አመት ዕድሜ ያላቸውእግር የተከሉ ህጻናት ሴቶችንእስከ መድፈር ደርሰዋል።

የትግራይ ሕዝብ ወደ አማራ አገር ዝመቱ ብሎ መርቆያዘመታቸው ልጆቹክልልተብሎ በተከለለውአማራ ክልልበገባባቸው መንደሮች፤ገጠሮችና ከተሞች ሁሉሴቶች፤ የቆረቡ የሰገዱ ባለ ትዳሮች፤ህጻናት፤መነኮሳት እና በምርኩዝ የሚራመዱ አያት እናቶች እገሌ ከእገሌ ሳይለዩየተዘጉ መኖርያ በሮችንበሌሊት እየሰበሩ በቡድን ሆነው ጠመንጃ ደግነው ጾታዊ አመጽ ሲፈጽሙ እንደከረሙ ሰለባዎቹ በእምባ ታጅበው የደረሰባቸው ግፍ እየገለጹ ይገኛሉ።

ወንዶች ያውምአረጋዊያንእያለቀሱ ነው። እፊታቸው በጥይት ገድለውባቸውሴትየዋ ልጆቼን አደራእያለች ሽማግሌ ባልየዋን ተሰናብታ ስታሸልብ ያዩ እኝህ አረጋዊ ደሴ ከተማ ለተሰበሰበው አደራሽ ሕዝብእያለቅሱሚስታቸው በግፍ እንዴት እንደተገደሉባቸው እየገለጹበቪዲዮአይቻለሁ። ወንድ የሚያለቅስባት አገርእርይ በይ አገሬ!” ሲያንስ ነው።

ለሕዝብ የተለቀቁ ሁሉንም ቃለ መጠይቆችና ስዕለ ድምጾች (ቪዲዮዎች) ሰብስቤ ባንድ ሌሊት ልጨርሳቸው አልቻልኩም። የጾታዊ ጥቃቱ አፈጻጸም አንዱ ካንዱ የበለጠ አሰቃቂ እና አስለቃሽ ሆኖብኝ እየተረበሽኩ ሁሉንም ማየት አልቻልኩም። ዕንቅልፍ ሁሉ ነስቶኛል።

እውጭ አገር የሞኖሩና አገር ውስጥ የሚኖሩየትግራይ ምሁራንና የትግራይ ሕዝብያለ ምንምየውግያ ደምብና የሞራል ግዴታ ሳይማሩበዘፈንና በጭፈራ በስሜት ብቻ እየገፋፉየትግራይን ወጣት ቀጥል ዝመትእያሉዋቸው ከሰውነት ወደ አራዊትንት የተለወጡት የትግራይ ተዋጊዎች የፈጸሙት የተዘጉ ስቆች፤ ሆስፒታሎች፤ ክሊኒኮች፤ የእህል መደብሮች፤ የልብስና የዕቃ መጋዝኖች እየሰበሩ፤ የሚዘረፍ ዘርፈው በመኪና ወደ ትግራይ እየጫኑ፤ መሸከም ያልቻሉትንም ሰባብረው ገነጣጥለው፤ ተቋማትን እንዳልሆኑ አድርገው ፤ድልድዮችን መኪኖችን እያጋዩ በመጨረሻ ሕዝቡ ብሎሲነሳባቸው ወደ ሗላ አፈግፍገዋል።

ይህ ሁሉ ግፍ ስመለክትእናት አገር አልቅሺየሚለ፤ው ቃል አልበቃ ሲለኝ እነዚህን አራዊቶች የምገልጽበት ቃል ፍለጋ ስኳትት ሰነብቼ ምንም አላገኘሁም።  ብትግርኛሓኽሊ ድሙየምንለው ቤት አልባ ራስ አደር” (ሆምለስ) ድመትበተከፈተ ቀዳዳ የሰው መዝጊያ ሾልኮ በመግባትለቤተሰብ የተሰራ ዶሮ ወጥ ወይም ሥጋ ወጥ የያዘ ድሰትበልቶና ደፍቶት የሚሰወር፤  በየሰው ጣራ ወጥቶጦር አውረድእያለጣራውን በመቧጨርባለ ማቋረጥ ሃይለኛ ድምጽ በማስሰማትበወድቅት ሌሊትየተኘውን ሰላማዊ ሰውዕንቅልፍየሚነሳውወረበላው ድመትወያኔዎችን ለመግለጽ ይስማማ ይሆን ብየ አንዱን ወዳጄ ይህ ዓይነት ድመት በአማርኛ ምን ይባላል ብየ ጠየቅኩት።

ሸለመጥማጥ የሚባል አለ፤ ግን እርሱ ግን ረዢም ጭራ ያለው ድመት የሚመስል የቤት ድመት ሳይሆን ደሮን በመንጠቅ የታወቀ የዱር/የበረሃ/ ድመት አለ። ይህም ዕወቁ የቃላት ምሁር አቶ ተሰማ ሀብተሚካል ያዘጋጁትከሣቴ ብርሃን ተሰማ የአማርኛ መዝገበ ቃላትገጽ 302 ገልጸውታል -- ሆኖም  አንተ ከምትለው አመጸኛው የቤት ድመት ጋር አይመሳሰልም። ይመስለኛል አንተ የምትለው ድመት ኦሮምኛዲገላብለው የሚጠሩት ይሆን? ብሎ ሃሳብ ሰጠኝ። ለመሆኑ ለምን ፈለግከው? አለኝ። ለጽሑፌ ርዕስ ልጠቀምበት ነበር ብየ ታርኩን ስነግረው ይህንን መለሰልኝ

“Nothing in our language can adequately convey the diabolic deeds of Weyane's. Today I heard on a radio how they killed va two weeks old baby whose mother could not run away. After killing the child they stood on its corpse. The poor mother had to witness all this. This happened in Northern Wello (Wag region). They sexually abused 85 years old nun who begged them to spare her. Even wild beasts do not describe the evil deeds of Weyanes' I am afraid you have to coin a new word that has not been in use.” አለኝ።                                                                                                                    

ትርጉም፡

““በእኛ ቋንቋ የወያኔን ዲያብሎሳዊ ተግባራት በበቂ ሁኔታ ማስተላለፍ የሚችል ቃል የለም። በተከታታይ እየተሰሙ ያሉት አስደንጋጭ ወያኔ የፈጸማቸው አስነዋሪ ወንጀሎች እየተሰሙ ነው። ዛሬ አዲስ ዜና የሰማሁት አለ። እናቱ መሸሽ የማትችለውን የሁለት ሳምንት ህፃን እንዴት እንደገደሉ ዛሬ በሬዲዮ ሰማሁ። ልጁን ከገደሉ በኋላ በሬሳው ላይ ቆሙ፤ ምስኪኗ እናት ይህንን ሁሉ ማየት ነበረባት። ይህ የሆነው በሰሜን ወሎ (ዋግ ክልል) ነው። 85 ዓመቷን መነኩሲት እንዳይደፍሯቸው በፈጠራቸው አምላክ እየተማጸኑ ቢለምኗቸውም ወያኔዎቹ በዚች መነኩሲት ላይ የፆታ ግንኙነት ፈጸሙ።ወያኔዎችን ለመግለጽአውሬየሚለው አይገልጽም አውሬ የሚለው እንኳን የወያኔን እኩይ ተግባር አይገልጸውም። እስካሁን ድረስ ስራ ላይ ያልዋለ አዲስ ቃል ካልፈጠርክ። የነዚህእኩያንሰዎች ምንነት ለመግለጽ ቃል ታገኛለህ ብየ አልደፍርም።አለኝ።

የወያኔ ጋኔሎችን የሚገልጽ መዝገበ ቃላት ለመፈለግ ያልገነጠልኩት መጽሐፍ የለም። ሰይጣናዊ ተግባራት የሚገልጹ ልብ ወለድም ይሁን እውነተኛ ታሪክ ቃላት ፍለጋ ወደ ዩኒቨርሲቲ ላብሬሪ ሁሉ ሄጃለሁ። የዳሰስኳቸው የግዕዝም ይሁን አማርኛ እና እንግሊዝኛ መዝገበቃላትም ይሁኑ መጽሐፍቶችያነሱና ለስላሶች ስለሆኑ የኢትዮጰያን እናቶችና 13 ዕድሜ ያላቸውእግር ተከልህጻናት ለመድፈር ከገሃነመ ሰማይ ወደ ምድራችን የተላኩየትግራይ ተዋጊ ጋኔሎችተስማሚ ቃላት ፈልጌ ላገኝ አልቻልኩምና አንባቢዎቼ አግዙኝ።

የሚገርመው ደግሞ ኢትዮጵያ አይደለንም ብለው ወደ ትግሬነት ዜጋ የተለወጡት ትግሬዎቹ እነ አብርሃ በላይም ሆነ እነ ርዕዮት ሚዲያ (ቴድሮስ ፀጋዬ) “ጨፍጫፊ ሴት ደፋሪ የአብይ አሕመድ ወታደር ምንም ጊዜም ቢሆን እንደ ወታደርነት መቀጠል የለበትም ጠቅላላ ከታች እስከላይ መፍረስ፤ አለበትእያሉ ሲያናፉ በተጻራሪው ግንነፃ አውጪያችንብለው ኤፍእያሉ እየቆለጳጰሱ የሚጠሩትወረበሌው ህጻናትና መነኮሳትን ደፋሪው የትግራይ መከላከያ የሚባለውፋሺስታዊው የወያኔ ወራሪ ጦር ግንመፍረስ አለበትሲሉ አልሰማናቸውም። ይልቁንስትግራይ ትዕወትእያሉ በወንጀል የተጨማለቁትን (ባለ ሪከርዶቹ) “የእነ ጻድቃንፎቶ ግራፍ በፌስቡካቸው (በአብርሃ በላይ ፌስቡክ) ማድመቂያ አድርገውት እያየናቸው ነው።

ለነዚህ ሰነፎች የምለው ነገር ካለኝ መጽሐፈ ምሳሌን ጥቅስ ነው።

 “መጽሐፈ ምሳሌ 2611 ውሻ ወደ ትፋቱ እንደሚመለስ እንዲሁ ሰነፎች ስንፍናቸውን ይደግማሉ።

አሁን ወደ አብይ አሕመድ እንመልከት

 ይህ ሁሉ ውርደት እንዴት እንደመጣ የወያኔ የአፈጣጠር በሕርይ መሆኑን ከታች የምገልጸው ቢሆንም፤ ቀንደኛ ተጠያቂው ግን አብይ አሕመድ ነው።በአብይ አሕመድ ሕጻናዊ የአገር ደህንነት አመራርና የብቃት ማነስወያኔዎችደፍረውናል። ሱዳኖች ደፍረውናል።ሱዳኖች የደፈሩት ሉዓላዊ መሬታችንም ለምን ደፈራችሁ ተብለው ሲጠየቁ  “እራሱ አብይ ውሰዱት ስላለን ገብተን ወስደናልምን ታመጡ! ብለውናል።

 ዕድሜው ሙሉ ያገለገለው ለአፓርታይድ ስርዓት ካለው ፍቅር የተነሳ ወለም ዘለም እያለ ከወያኔዎች ጋርአንገት ላንገት ተቃቅፎእስከ ሑመራ  እስከ አክሱም ድረስ ሲተሻሽ ከርሞ አጅሬዎችህጻንነቱንስላወቁበት በገንዘብም፤ በመሳሪያም በመረጃም በደምብ ሲዘጋጁእርሱ ግንላንድ ሰው ብለን ጦርነት አንከፍትምእያለ ሲያሾፍያለ ምድቡ ፓርክ አሳማሪ ሆኖሲዝንዘላዘል ቆየ። ይባስ በሎ ከየክልሉበፋሺስት ልዑላኖችትዕዛዝኢትዮጵያዊያን ከየክልሉ እየተፈናቀሉ የትም ሜዳ ፈስሰው ያለ-መጠለያ ሲሰቃዩ አርሱ ግን ንግሥነቱን ለማጠናከርጎርፍ መጣባችሁ ብሎ እንደ ሳወዲዎቹ ንገሥታትለጋሽ ንጉሥሆኖለሱዳኖች የገንዘብ እርዳታ ሲረጭከረመ። በመጨረሻ አጅሬዎች ወያኔና ሱዳኖች የህጻኑን ትንሽ ህሊና ገምተውኢትዮጵያን ወረሩዋት፤ ደፈሩዋት

 “ንግሥነቴን መርቁልኝእያለ አመት ከቆየ በሗላ ወያኔዎችእስኪሸድኑድረስ (ቃሉ ትግርኛ ነው- ማን ይግጠመኝ የሚል አጠገቡ በሰለም የቆመ በሬን ሳይቀር ሁሉንም እየዘለለ የሚዋጋ በሬ) ጎርምሰው እርሱ ሲንዘላዘል ከርሞ መጨረሻ እየሆነ ያለውን ጉድ ሊደርስብን በቃ።

መጨረሻ ምስጢሩ በማይገባን ሁኔታ ወያኔዎች ከትግራይ ተነስተው እስከ ደብረብርሃን በር ድረስ ሕዝብ እየደፈሩ እየዘረፉ፤ከብቶች እያረዱ፤እየገደሉ ሲገሰግሱ፤አብይ አሕመድናየኢሳቱ "ካቡጋ" መሳይ መኮንንየመሳሰሉየዘር ማጽዳት ቀስቃሽ ወንጀለኞች” “ክበበው፤ አስገባው፤ አፍነውእያሉ ከትግራይ ውጭ ያለ በመላ አገሪቷ ያለ የትግራይ ተወላጅ "ፖለቲካ ያለውም የሌለውም" “ወያኔ ነው፡ተብሎበኢንትርሃሙዌው ቡድንእንደ ናዚ ወደማጎርያ እስር ቤትና በየድልድዩ ሥር ጭምርታስሮ ንብረቱ እየተዘረፈ፤ ሥራው እየተፈናቀለ፤ የሞተ የታመመ፤ የታረዘኮነስንትረሺን ካምፕውስጥ ታጉሮ ይገኛል።

ይህ ደግሞ  ሆን ተብሎ ጦርነቱን እንዲቀጥል አገር አገር እንዳይሆንበጀነሳይድ ላይ ሌላ ጀኔሳይድአብይ አሕመድ ምንም በሌላቸው ንጸሃን በወንድሞቻችን እስካሁን ድረስ (የራሴን ዘመዶች ነው እየተናገርኩ ያለሁት) ንጹሃን ላይ ግፍ እየፈፀመ ነው። በዚህ ምክንያት ቤተሰቦቼ በመታጎራቸው ብናደድም ወደ ወያኔ አልተቀለቃልኩም። ግን ብዙ ትግሬዎች በንዴትና በእልህ ወደ ወያኔ ድጋፍ ተቀላቅለዋል። ጦርነቱ የከበደ ያደረገው አንዱ ይህ የመበቀል ቁጣም ነው። አብይ አገር መምራት አይችልም የምለው ለዚህ ነው።

አብ አሕመድ እራሱ 32 ወታደሮቼ የትግራይ ሴቶችን በመድፈራቸው በቁጥጥር ስር አድረጌአለሁ ብሎ ይናገር እንጂ ፍርዱ በይፋ አልታየም። ትግራይ ውስጥ ወታደሮች የጦር ወንጀል ሲፈጽሙ በቪዲዮ አይተናቸዋል። የጦር መሪ ነውና አብይ በዘር ማጽዳት ወንጀል መከሰስ አለበት።

መደምደሚያ

ወያኔዎች በአማራ ላይ ያላቸው ጥላቻ ከላይ የተጠቀሰው ወንጀል እንዲፈጽሙ መነሻ ሆኗቸዋል። ከዚህ መነሻ በተጨማሪ የሚከተሉት የፖለቲካ ፍልስፍና ደግሞ ዋናው የአራዊታዊ ባህሪያቸው ምንጭ መሆኑን የሕክምና / እና የአእምሮ ሓኪም የሆነው ሆላንድ-አምስተርዳም ኗሪ የሆነው ወዳጄ / አሰፋ ነጋሽ ወያኔዎች ስለሚከተሉትየፋሺስቶች-ፍልስፍናበተከታይ አባላቶቹስነ ልቦናየሚያደርሰው ጫና  በእንግሊዝኛ የጻፈው ወደ አማርኛ ተርጉሜ ቀንጭቤ ላስነብባችሁ እና ልሰናበት።

እንዲህ ይላል፦

የፋሺዝም/ ናዚዝም የማዕዘን ድንጋይ የሆነው Ultra-Nationalism (አክራሪ ብሔረተኛነት) ጤነኛ አእምሮ ያለው ግለሰብ ወደ-ምክንያታዊሰውነት ይለውጠዋል። ይህን የሚያደርገው ህሊናውንበማገድነው። ኅሊናውን ወይምየሞራል ኮምፓስን/የሞራል መመርመሪያውበአልትራ ብሔርተኝነት ተጽዕኖ ሥር ያስወረረ ግለሰብ ሕዝባዊ ንቅናቄውን (መንጋውን) በመቀላቀል የግለሰባዊ ማንነቱን በመጣል የፋሽስት መሪዎቹን ትእዛዝ በባርነት ይሠራል። በሂትለር ዘመን በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ጀርመኖች እና በሚሊዮኖች በሚቆጠሩ ጣሊያኖች በሙሶሎኒ ጊዜ የደረሰው ይህ ነው።

የሙሶሎኒ ፋሺስታዊ መፈክር ወይምመፈክር ተከታዮቹሊከተሉት የሚገባ እና በሃይማኖታዊ ቁርጠኝነት በተግባር ላይ ለማዋልእመኑ፣ ታዘዙ እና ተዋጉየሚል ነበር። ዛሬ በህወሓት ስር ያሉ ትግሬዎች የሚያደርጉት ይህንኑ ነው። የጣሊያን ፋሺዝም እና የመስፋፋት ፖሊሲው በጥቅምት 1935 ኢትዮጵያን መውረር አስከትሏል።ይህ ወረራ 1935-1941 መካከል ብቻ 730000 ኢትዮጵያውያን ላይ አሰቃቂ ግድያ አስከትሏል። ይህ እልቂት እስከ ዛሬ ድረስ የታፈነ ዕውቅና ነው። በጣሊያን ፋሽስታዊ መካሪዎቻቸው ተብራርተው የፋሺስታዊ አስተሳሰብን የጫኑት የትግሬ ፋሽስቶች ባለፉት 30 ዓመታት ውስጥ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንን ለሞትና መፈናቀል ምክንያት በማድረግ ከጣሊያን ፋሺስት መካሪዎቻቸው በልጠው የጣሊያን ፋሺስቶች በኢትዮጵያ የወሰዱትን እርምጃ ትልቅ ትርጉም ያለው አድርጎታል።አሰፋ ነጋሽ (/)

ወደ አራዊትነት የተለወጠው የትግራይ ተዋጊ ሃይል የዓለም አቀፍ ሴት ደፋሪዎችን ሬከርድ ሊሰብር የቻለበት ምክንያት ከላይ የተጠቀሰው የሚከተለው የፖለቲካ ፍልስፍና ምክንያት ነው።

 እኛ ድርሻችንን እያነሳን ነው፤ አንባቢዎች ደግሞ ሕዝቡን ለማስተማር ጽሑፉን ተቀባበሉት።

አመሰግናለሁ

ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ) 1/5/2022 Ethiopian Semay