Tuesday, February 2, 2010

The Font Traders

www.Ethiopiansemay.blogspot.com የፊደል ነጋዴዎች የፖለቲካ ወስላቶቹ ካደረሱብን ኪሳራ አይለዩም ጌታቸዉ ረዳ

የማከብራችሁ ክቡራን የኢትዮጵያ ሰማይ አንባቢዎች በእናንተ ድጋፍ እና የዋሸራን ፊደል አዘጋጆች እርዳታ ምክንያት በኢትዮጵያ ቁዋንቁዋ ለመጠቀም ይሄዉና ችያለሁ።ሆኖም ካሁን በፊት ስጠቀምበት ከነበረዉ የግእዝ ዩኒኮድ አጠቃቀም ስልት ለየት ስለሚል ከምታዩት አንዳንድ ያጠቃቀም ስልት ስህተት (የኔዉ) ማየት ትችላላችሁ። ከዚህ ሌላ አጠቃቀሙ እስክለምደዉ ጊዜ እንደሚፈጅቢኝ እርግጠኛ ነኝና እንደ «ኤሊ» እየተሳብኩም ቢሆን ጹሁፎቼን አቀርባለሁ። ይህቺኛዋ ማሳሰብያ ለመጻፍ ከአንድ ሰዓት ተኩል በላይ ፈጅቶብኛል። እንዲህ ዓይነት ችግር ሊከሰት የቻለበት ምክንያት አስቀድሜ እንደገለጽኩት የተለያዩ የፊደል ነጋዴዎች በፈጠሩብን ተጽእኖ ነዉ። ለማንኛዉም ባገሪቱ የዘመናዊ ቃንቁዋ (ስህተቴን ተመልከቱ) መጠቀሚያ /መገልገያ መሳርያዎች ሂደት ጉዳቱ ምን ያህል እንደሆነ ፍርዱን ለናንተዉ ልተዉ። ለማንኛዉም ለተባበራቺሁኝ ሁሉ አመሰግናለሁ። ብዙ ወገኖች እንደጣፉልኝ ከሆነ ፥ባማርኛ ማንበብ አስቸጋሪ እየሆ ስለመጣ ወደ እንግሊዚኛዉ እንዳዘነበሉ ገልጠዉልኛል። ለዚህ ሁሉ ሰበቡ «የተለያዩ የፊደል መሃንዲሶቻቺን እንደፖለቲካዉ መድረክ ሁሉ በዘፈቀደ እየቀረጹ ለንግድም ለችሎታ ማሳያም በማድረግ «ኣንድ ወጥ» የሆነ የጋራ አጠቃቀም ዘይቤ ስላልተከተሉ ነዉ። ይህንን ችግር እንዳይቀጥል ምሁራን እና የኔ ብጤ ዜጎች ሁሉ ቃንቁዋቺንን ለምርምር ዝና እና ለገንዘብ መጠቀሚያ በሚያደርጉት ላይ ስሞታቺንን በቀጣይነት ማስሰማት እና ማዉገዝ ይኖርብናል እያልኩኝ አደራየን አስተላልፋሁ። ማንነታቺን ለንግድ ችርቻሮ እና ለምርምር ዝና አናዘጋጀዉ። ለዚህ ለዚህ እኛነታቺንን ለማዉደም እና እርስ በርስ ላለመግባባት እየተጠቀሙብን ያሉትን የፖለቲካ ድርጅቶች ይበቁናል እና በጽሁፍ ልሳናችን ላይ እየደረሰ ያለዉ ዉዥምብር አንድ እልባት ይኑረዉ። ዋሸራ ከ4,0 ወደ 4,1 አዲስ ህትመት ስለቀየረዉ በዊንደዉ 7 መጠቀም ችያለሁ። በኒያላ እና በሌሎቹ ግን አስቸጋሪ ሆኖብኛል። በተለይ GEEZ UNICODE በእዲስ ህትምት ቢመጣ ደስ ይለኝ ነበር፤፤ የድሮዉ GEEZ UNICODE ግን በ«ቫይረስ» ስለተጠቃ ብትጠነቀቁ ጡሩ ነዉ። ለተባበራቺሁኝ ሁሉ አመሰግናለሁ ለገንዘብ ትርፍ ሲባል የሃገር መሬት መሸጥ እና ቃንቁዋቺንን በሚያዳክም ስልት መጠቀም ብሄራዊ ወንጀል ነዉ። ኢትዮጵያ ለዘላም ትኖራለች!!!!!!!
ጌታቸዉ ረዳ