Monday, June 8, 2009

ጣሊያን ሊጥላት የታገላትን ሰንደቅ ዛሬም በወያነ ትግራይ ተደገመ!

ጣሊያን ሊጥላት የታገላትን ሰንደቅ ዛሬም በወያነ ትግራይ ተደገመ! ጌታቸዉ ረዳ www.Ethiopiansemay.blogspot.com
ይህ ጽሁፍ ለማጸፍ ዓላማ አልነበረኝም፣፣ይህ አስቸኳይጽሁፍ ለመጻፍ የገፋፋኝ ምክንያት በwww.Ethiopianpatriots.com የህዋ ሰሌዳ ላይ AEUP and the Issue of the National Flag in Tigray በሚል ቪኦኤ ከትግራይ ያስተላለፈዉን ዘገባ ሳደምጥ በኢንጅኔር ሃይሉ ሻዉል ሊቀመንበርንት የሚመራ የመኢአድ ኢትዮጵአዊ ድርጅት በትግራይ ክፍልሃገር ዉስጥ በአላማጣ ከተማ ዉስጥ የከፈተዉ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሰቅሎት የነበረዉን አያሌ ኢትዮጵያዊያን ከዘመነ ንጉሥ አምደጽዮን እና ከዚያም በፊት የምትታወቀዉ ባለ ሦስት ሕብረ ቀለም ያላት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሰንደቅዓላማ (አረንጓዴ፣ቢጫ እና ቀይ)፣ ‘የትግራይ ሕዝብ ነፃ አዊጪ ግምባር’ብሎ ራሱን የሚጠራ “እጆቹን በደም የታጠበዉ ይህ ጸረ ኢትዮጵያ ድርጅትና- ሕገ ወጥ መንግሥት” በሾመዉ የከተማዉ ከንቲባዉ በኩል “የወያኔ ትግራይ ‘ሁለተኛዉ ባንዴራ’ የሆነዉ ከማሃሉ ሰማያዊ ቀለም የለበሰ የአይሁዶች ምልክት ያለበት ባለ ጨረር ኮከብ ባንዴራ” ካልሰቀላችሁ ሰቅላችሁት ያላችሁትን “ሕጋዊ ሰንደቃላማ የኢትዮጵያ ሰንደቃላማ አይደለም” {ህወሓት አያዉቀዉም!!} በማለት ጽ/ቤቱ ህንጻ ላይ ተሰቅሎ የነበረዉ ይህ ለዘመናት የተከበረና - ህወሓት ብሎ ራሱን የሚጠራ ይህ “የሻዕቢያ ቅሪት/ቁሻሻ”ገና በዚህ ዓለም ሳይፈጠር፣ “ብሔራዊ ሰንደቃላማ” ሆና በትግራይ ሕዝብና በብዙ ነገስታቶቿ የተከበረቺዉ “ሰንደቃላማቺን” በጠመንጃ አፈሙዝ ተጠቅሞ በጉልበት አስፈራርቶ እንዲወረድ ካስደረገ በሗላ የመኢአድ ጽ/ቤትም እንዲዘጋ አድርጛል የሚል የዜና ዘገባ ሳዳምጥ ንዴቱ አላስችል ብሎኝ እንቅልፍ ሳልተኛ ይህንን ቁጭቴን ጽፌ አንድ ሳዓት ሳልተኛ ወደ ስራ መሄድ ነበረበኝና-ኢትዮጵያ በአደገኛ መንገድ ላይ እንዳለች ሁለቻሁም እንድታዉቁት ደጋግመን እያሳሰብን ነዉ፣፣ እንደምታዉቁት ወያኔ ሲፈጠር የማያዉቁት የዋህ ተከታዮቻቸዉ በሞኝነታቸዉ ብንስቅባቸዉም፣ባለማወቅ እየተከተሏቸዉ-ያሉት የመሃል አገርና የደቡብ/የምስራቅ ኢትዮጵያ አካባቢ ተወላጆች ወያኔን በማመገስ አድርጉ የሚላቸዉ የጥፋት ተልዕኮአቸዉ እየፈጻሙ ስለምናዳምጣቸዉ አገሪቱን እነሱንም ጭምር ይዛ ወደ ገደል እየተጓዘች መሆኗን ሳልገልጽ አላልፍም፣፣ ወያኔ ከነ እሱ ይልቅ ተጀምሮ አስኪያልቅ እኟ የትግራይ ተወላጆች በደምብ ስለምናዉቃት እኛ የምንሰጣቸዉን መረጃ ሳይንቁ ይህ “የሻዕቢያ ጥራጊ ጭፍራ”ከመደገፍ እንዲያቆሙ ዛሬም በድጋሜ እናሳስባለን፣፣ ይህ የሻዕቢያና የጀብሃዎች “ኩሩሩ-ቡችላ”የትግራይን ህዝብ ወዶ ሳይወድ እየተገደደ በቁመናቸዉ ከነህይወታቸዉ ሳይሞቱ ብዙ የተከበሩ አዛዉንቶች በእሳት እያሰቃየ ዛሬ ወዳለበት ደረጃ ከመድረሱ በፊት። ደርግ በቀይ ሽብር የከተማዉን ወጣት ሲጠርግ ፤ የሻዕቢያ ቅጥረኛ የሆነዉ ወየኔም፤ ትግራይ ዉስጥ በገጠሩ፤ ኢትዮጵያዊነቱን ያልካደና እምነታቸዉን ያላመነ ገበሬዉንና ወዛደሩን <ኮራኹር አምሐሩ፤ ሽዋዉያን ተጋሩ> (ያማራ ቡችሎች- የሸዋ ትግሬዎች) እያለች የ “ኢዲህ” ታጋይ ቤተሰብ ዘመድና አዝማድ የተባለ ሁሉ በጠቅላላ፤በሬና ላሙን፤በግ አና ፍየሉን፤ አህያዉን በቅሎዉን፤ ደሮዉንና ጎተራ እህሉን፤ ማርና ቅቤዉን፤እየወረሰች ለወሬ ነጋሪ ሳይቀር ፤ ለሐማሴኖች መደሰቻ ተብሎ፤ላሻዕቢያ ያልሰገደ’ምስኪን የትግራይ አራሽ ገበሬ፤ “ዘር ማንዘሩ”ከምድር እነዲጠፋ እየረሸነች፤ ለሌሎች መቀጣጫ ተብሎም በወጉ በቤተዘመድና በጎረቤት እንዳይቀበር፤ለንቃተ ህሊና ትምህርት ወደ በረሃ ተልኳል እየተባለ፤ ሳይመለስ የቀረዉ የቤትና ጎረቤት ሰዉ ታዝቢ ይቁጠረዉ። በማለት “አሞራዉ”ደራሲ ወንድሜ አቶ ግደይ ባሕሪሹም ያሰሰቡትን ዛሬም ለነዚህ የዋህ ተከታዮቻቸዉ ወያነ ትግራይ ማንነት ለማስታወስ እገደዳለሁ፣፣ ሻዕቢያ የተባለዉ የኤርትራዉ ድርጅት፤ በግማሽ ትግራይ ተወላጅ የሆኑትን ዘመዶቹን፤ ወየኔ ትግራይ ድርጅት “ቁንጮ”ላይ አስቀምጦ፤በንጹህ የትግራይ ዘርና ትዉልድ ላይ ግፍ የፈጸመበት “በሃያኛዉ ክፍለ ዘመን መጨረሻ ጊዜ” እነደነበር፤ ለተተኪዉ የትግራይ ትዉልድ ታሪክ መጥቀስና ማዉረስ የተቆርቋሪ ወገን ግዴታ ነዉ። ትግርኛ በመናገራቸዉና ወላጆቻቸዉ ትግራይ ዉስጥ ተወልደዉ የትግራይን መሬት ፍሬና እህል በልተዉ በማደጋቸዉ፤ትግሬዎች ነን በማለት፤ትግራይን ህዝብ-"ለነጻነትህ ብርሃን ነዉ"-እያሉ፤ በዘር ወገናቸዉ ለሆነዉ ለሻዕቢያ በተንኮል ተወክለዉ፤የትግራይን ሕዝብ የወገኑ የመሃል አገር ያማራና የኦሮሞ ወዳጅ ለዘላለም እንዳይኖረዉ ፤በኤርትራዊያን ተጨቁኖ፤ በአማራዉም ተጠልቶና ተራርቆ እንዲኖር፤ በተንኮል ወደ ገሃነም ጨለማ መሩት። ዉጠቱም ይሄዉና “ጣሊአኖችና የኮሚኒስት ፋሺስቶች” “ብሄር ቤረስብ” እያሉ ኢትዮጵያን አንድነት በዘዴ ለመበታተን ባቀዱት የተንኮል ዘዴ ዛሬ በወያኔ አማካይኝነት በስራ ላይ ዉሎ ያልነበረ ታሪክና ሰንደቃላማዎች እንደ አሸን ፈልቶ እርስ በርሱ ወደ ጨለማ እና መበታተን ወደ ገደል እያዘገመ እንደሆነ በዓይን እያየን ነዉ፣፣ የኢትዮጵያ ሰንደቃላማ አናዉቅም ሲል ወያኔበቀሪዉ ያገራችን ሕዝብ -"ባንዳ አስገንጣይ ተገንጣይ ታሪክ ሻጭ"እየተባልን እኛ የትግራይ ተወላጆች እንድንወቀስ፤ ታሪክ ዘላለም እንዲከሰስና በታሪክ እነዲኮነን አደረጉን። በሻዕቢያ መሠረተ ዓላማ የተጠመቁ “ግማሽ ትዉልዳቸዉ ከሃማሴኖች/ሰራየ እና ትግራይ የተወለዱ”፤ የትግራይ ሕዝብ በመሀል አገር ህዝብ እና በተቀረዉ ያገቱ አካባቢ ሕዝብ እንዲሞገስና እነዲመሰገን አይፈልጉም። ይልቁንም እንዳቀዱትና ዘፈናቸዉና ፕሮግራማቸዉ ደጋግሜ እንዳቀረብኩላችሁ በትግሬዉና በአማራዉ መካከል የከረረ ጠብ ተፈጥሮ በዚህ ባገሪቱ ሰንደቃላማ እና ታሪኳ እንዲሁም ያገሪቱን ብሔራዊ ቋንቋ እንዲጠፋ እን በጣለትነት እንዲታይ በመሞከር ምክንያት የትግራይ ሕዝብ ከአማራዉ የኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር እየተጋጨና ተቀያይሞ እንዲኖር ጥረዋል፣፣ ብሔራዊ ያገሪቱ ቋንቋ በላቲን ቋንቋ ተተክቶ መጪዉ ትዉልድ አፍሪካነቱን እንዲጥል እርስ በርሱ እንዳይገበያይበት እና እንዳይነጋገርበት ከፍተኛ ዘመቻ ሲያደርግ ከቆየ በሗላ - በዚህ በቅርብ ወራት ደግሞ በ1988ዓ.ም እና በ1928 ዓ.ም ጣሊያን ሊጥላት ሞክሮ ታግሎ ያቃተዉን ያገራችን ብቸኛ እና ብሄራዊ ሰንደቃላማችንን “የአፓርታይዱንና የእስከ መገንጠሉን ፖሊሲዉ” የሚቃወሙትን በየተቃዋሚ ጽ/ቤቶቻቸዉ ድረስ ጠብመንጃ የያዙ ሎሌዎቹን አስከትሎ በመሄድ “ኢትዮጵያዊነት መለያቸዉ የሆነቺዉ ወላጆቻችን የሞቱላት የተሰዉላት፣ በዱር ሸንተረሩ የተንከራተቱላትና የተጋዙላትን ባለ ሦስት ቀለም ሰንደቃላማችንን” ወደ መሬት በመጣል ሕልዉናዋን ለማጥፋት ለመጨረሻ ጊዜ እየታገላት መሆኑን መረጃዉ ቁልጭ ብሎ ይታያል፣፣ በኔዉ አገላለጽ- ወያነ ትግራይ ብሎ ራሱን የሰየመ ይህ ወራዳ “የሻዕቢያ ቅሪት- (EPLF Artifact”) በወያኔዉ በአስገደ ገብረስላሴ አገላለጽ “የሻዕያ ጊላ” (የሻዕቢያ - (ባርያ) የለየለት የአፓርታይድ ስርዓት እያካሄደ መሆኑን ለሚጠራጠር ሰዉ ካለ አሁኑኑ ቢያዉቀዉ የተሻለ ነዉ እላለሁ፣፣ ይህንን አስመልከቶ አንድ እውቅ የአገራችን ጸሃፊ ብዕር ያሰመሩበትን እንደገና ዛሬም ላስታዉሳችሁ እፈልጋለሁ፣፣ ወያኔ ከቋንቋ እስከ በዘር ማስተዳደር የጀመረዉ -ዛሬ ደግሞ የህወሓትእንጂ የኢትዮጵያ ሰንደቃላማን አላዉቃትም ሲለን -ወያነ ትግራይ የጣሊያን ዲቃላ (ግልባጭ) የሆነ ፕሮፖጋንዳዉ ስራ ላይ እያዋለዉ መሆኑን በግልጽ ሲነገረን፣ እዉነት እላችሗለሁ-ከየዓለማቱ በጥራጊ መልክ ወደ ኢትዮጵያ የመጣዉ አፓርታይድና ፋሽዝም ይፋ ሆኖ ለጎብኚዎች የሚነበብ ነጋሪት (ማስታወቂያ) ገና አልወጣም አንጂ፤አሁን ከሚሰራዉ የጣሊያኖች ግልባጭ ስራ ከስራዉ ጋር አብሮ ማስታወቂያዉ ቢወጣ ኖሮ የጦቢያዉ ጸሃፊ አቶ ጸጋየ ገ/መድህን አርአያ ያስቀመጡትን ዓይነት ማስታወቂያ በምድሪቱ ለይ መለጠፍ ነበረበት የሚል እምነት አለኝ። ልጥቀስና በዛዉ ልሰናበት፦ "የሰላምሐዋርያት ወደ ሚኮነኑባት ዓለም አንኳን ደህና መጡ! ነቢያት ዛሬም ወደ ሚወገሩበት መዲና ጥሩ እግር ጥለዎታል። ከዓለም አካባቢ በጥራጊ መልክ የወጣዉ አፓርታይድና ፋሺዝም ሥር እየሰደዱ በሚገኙበት አሮጌ አገር አዳዲስ ጋንግስተሮችን ያገኛሉ። ማስታወሻ ደብተርዎን ይቆጥቡ።ብዙ የሚያስጽፍ ድርጊት አለና!ለማንኛዉም እንኳን ወደማፊያዎች አገር መጡ!ስለሕግና ስለሕጋዊነት ብዙ ይሰማሉ! እንኳን ደህና መጡ ብቻ!"….. "ስለንግድና እንቅስቃሴ የሚያስተምረዉን ሥነ ኣእምሮ አወቃለሁ ባልልም ቱሪስት ድርጅት (እሱም ስሙን ቀይሮ ካልሆነ)የተነሳሁበትን ዓይነት ማስታወቂያ ገና ከቦሌ እላይ እና ቀጥሎም የአራዳነት ማእከል በሆነዉ ከጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ወረድ ብሎ ቢለጠፍ-ከ24-ዓለም ድንቅ ነገሮች አንደኛዉ አንደሚሆን እገምታለሁ።" (ጸጋየ ገ/መድህን አርአያ ጦቢያ ቁጥር 10/1993) የአገሪቱ ታሪክ፣ አንደነት፣ ቅርስ ማንነት ብሄራዊ ቋንቋ ዛረ ደግሞ በጥበብ ለማጥፋት የተሞከረዉ የቆየዉ ያገሪቱ ብሄራዊ ሰንደቃላማ የማጥፋት ዘመቻ “ግልጽ- አካላዊ የጥቃት” ዘመቻ የተከፍተባት መሆኑን እና ያገሪቱን ሰንደቅ መለኳ እና ክብሯን ለመጠበቅ ያመች ዘንድ ማንኛችንም ልዩነታችንን ወደ ጎን ትተን የተቃዉሞ ሰላማዊ ሰልፍ አንዲዘጋጅ ባገሪቱና በዉጭ ላሉት ለፖለቲካ እና ሲቪክ ማሕበራት መሪዎች መልእክቴን አስተላልፋለሁ፣፣
ጌታቸዉ-ረዳ-(ሳንሆዘ-ካሊፎርኒያ-አሜሪካ) www.Ethiopiansemay.blogspot.com