Monday, July 12, 2021

የትግራይ ታሊባኖች ጌታቸው ረዳ ኢትዮ ሰማይ Ethiopian Semay 7/12/2021

የትግራይ ታሊባኖች

ጌታቸው ረዳ

ኢትዮ ሰማይ

Ethiopian Semay

7/12/2021

አፍጋኒስታን እና ትግራይ ሁለቱም ተመሳሳይነት አላቸው። አፍጋኒስታን በሃይማኖት አክራሪዎች ሰበብ ትግራይም በአክራሪ የነገድ ፖለቲካ አራማጆች ምክንያት ሁለቱ በጨካኝ ገጸ ባሕሪያቸው የታወቁ ሆነው በታሪክ ተዘግበዋል።

የአፍጋን ታሊባኖች በተቃዋሚ አፍጋኖች ላይ እንደፈጸሙት ሁሉ፤ በወያነ ትግራይ የተመራው የነገድ ፖለቲካም በተመሳሳይ መልኩ “ታዋቂ ገዳዮችን” በማፍራት እጅግ ዘግናኝ የሆኑ ስቃዮች ፣ ጭፍጨፋዎች በጠቅላላ በእግዚኣብሔር ፍጡር ላይ ለማመን በሚያስቸግር የወንጀል ድርጊት በንፁሃን ኢትዮጵያዊያን አማራዎች እና ተቃዋሚ ትግሬዎች ላይ ፈጽመዋል፡፡

ትግራይ ውስጥ በ1967 ዓ.ም ደደቢት በተባለው የትግራይ ቆላማ በረሃ የተመሰረተው ተ.ሓ.ህ.ት. በሗላ ህ.ወ.ሓ.ት. የተባለ “በወርቃማ ዘር” ራሱን በማሞካሸት የተመሰረተ አክራሪ ድረጅት ከአፍጋን ታለባኖች የሚለይበት ባህሪ በጭካኔ አንድ ሲሆኑ ልዩነታቸው ታሊባኖች khimar ብለው የሚጠሩት የሻሽ ጨርቅ “ጭንቅላታቸው ላይ” ሲጠመጥሙት የትግራይ ወያኔዎች ደግሞ “ኩሹኽ” የሚባለው ስስ ጨርቅ በአንገታቸው ዙርያ በመጠምጠም ይለያሉ።

በነጮች አለም ውስጥ በነሱ ስነ ምግባር ያልተከተለ የነጭ ዘር “ዋይት ትራሽ” (የነጭ ጉድፍ) ብለው እንደሚጠሩዋቸው ሁሉ ታሊባኖችም “የጎደፈ እስላም” ብለው በሚሰይምዋቸው ተቃዋሚዎቻቸው ላይ “Hashshashin (ሓሻሺን) ብለው የሚጠርዋቸውን ነብሰገዳዮች በማሰማራት ግድያ ሲፈጽሙ የትግራይ ታሊባኖች ድግሞ “ሸዋውያን ተጋሩ” ብለው በሚሰይሙን የትግራይ ተወላጆች ላይ “ክርቢት” ወይንም “ፈዳይ” የሚባሉ ነብሰገዳዮች በማሰማራት “ንፁህ ትግራዋይ” ያልሆነውን የትግራይ ተወላጅ ለመማረክና ለመያዝ አስቸገሪ የሆነባቸውን ተቃዋሚያቸውን በመግደል፤ በህይወት የማረኩትንም አካላቱን በሰላ ቢላዋ ቆራርጠው ለጅብ ይጥሉታል።

በታሊባን ድርጅት ውስጥ በ 1990 ዎቹ ውስጥ “ሙላሕ ዳዱላህ” እና “ፒር አግሓን” የተባሉ የታሊባን ገራፊዎች እና የነብሰገዳይ እዝ አባሎች እጅግ ጨካኞች እንደሆኑ ሁሉ የወያኔ ገራፊዎች እና ነብሰገዳዮች ሰውን በእሳት እየለበለቡ ሲመረምሩ እና ሰውን ከአንገቱ በታች አመድ አልብሰው ‘አንገቱ ብቻ’ ከመሬት በላይ እንዲቀር ተደርጎ ሲጨነቅ ማየት ‘እርካታ የሚሰጣቸው’ የወያኔ በርካታ ገራፊዎች በሰለባዎቻቸው አንደበት በሚከተለው አገላለጽ ይገልጽዋቸዋል፡

 “ከላይ የሰው ቆዳ የለበሱ ከውስጥ አደገኛ የአራዊት ነብሳት የሚነድዋቸው አሰፈሪ ፍጡራን ናቸው” ብለው ይገለጽዋቸዋል።

የዘመናቱን ጭካኔና ወንጀላቸውን ብንተው ባለፉት ጥቂት ወራቶች ብቻ ብንመለከት ወያኔዎች የታሊባንን ጭካኔ የሚያስንቅ ወንጀል ፈጽመዋል። ሴቶችን ከመድፈር ጀምሮ ግድያ እና መንግሥታዊ ንብረትን በመዝረፍ፤ ከፍ ብሎም የአገራችንን የመከላከያ ተዋጊ ሰራዊት በተኙበት ከብበው 75% የሰው ሃይል እና ንብረት እንዳልነበረ አድርገዋል (ለዚህም ይመስላል የኤርትራ ድጋፍ ያስፈለገው) ። ከዚህ ባሻገር አማራ ላይ በማይካድራ እና በመሳሰሉት አካባቢዎች የዘር ማጥፋት ወንጀል ፈጽመዋል።

የባለፈው ወር የፈጸሙት አሰቃቂ ወንጀል ዜናው ሰምታችሁት ይሆናል። ትውልድ መንደሩ ከመቀሌ ትንሽ ወጣ ብላ ከምትገኘው “ዓዲ ጉዶም” ከምትባል ትንሽ መንደር የተወለደው  እምብዛ የተባለ በበይነ መረብ እውቀት የተመረቀ መሃንዲስ እና የሙዚቃ ባለሞያ፤ ትግራይ ውስጥ በነበረው ጦርነት ማሕበረሰቡን ለማረጋጋት ሲል በፈቃዱ በኢንቨስትመንት (ማእቶት/ልማት) የበኩሉን ለማገልገል ሲል ከሚኖርበት አዲስ አበባ ልጆቹና ባለቤቱን ጥሎ ወደ ትግራይ በመሄድ ጥቂት ወራት ከሰራ በሗላ፤ የትግራይ ሙዚቀኞች እና ባለሞያዎች ታሊባኖችን ተከትለው ወደ ትግራይ በረሃ ሲገርፉ ምስኪኑ “እንጂኔር እምብዛ” ግን አላማቸው ስላልወደደው፤ መንግሥት (?) ባሰማራለት የግል ሹፌሩ በተጠመደለት ሴራ ምክንያት ሹፌሩ ከወያኔዎች የህቡእ ግምባር አባላቾቻቸው በመመሳጠር ኢንጂነር እምብዛ ወደ አዲስ አበባ ለመሄድ ወደ መቀሌ አየር ማረፊያ ጣቢያ በመኪና ሲወስደው የወያኔ ነብሰገዳዮች ተጠልፎ ሰውነቱ በቢላዋ ተወጋግቶ እጆቹ እና አንገቱን ቆራርጠው ለጀብ ጥለውት መሄዳቸውን ዜናውን ከየኔታ ዩቱብ እና የመሳሰሉ የዜና ማሰራጫዎች ተነግሯል።

ሰለሞን የተባለው የኢንጀኔር አምብዛ የቅርብ ጓደኛ ሰሞኑን ‘የኔታ ዩቱብ’ ላይ ከወጣት ጋዜጠኛ መቅደስ ጋር ባደረገው ቆይታ ተጨማሪ መረጃ ሰጥቷል። ከጅብ የተረፈው የተቆራረጠው የእምብዛ ሰውነት ተለቅሞ “ገብርኤል ቤተክርስትያን” ተቀብሮ ነበር። ሆኖም የትግራይ ታሊባኖች አካሉን መቆራረጣቸው ሳያረካቸው ሲቀር የተቀበረው የእምብዛ ቁርጥራጭ “አካላቱ” ከመቃብሩ ቆፍረው እንደገና ለጅብ እንዲሰጥ በማድረጋቸውን የዓድዋው ተወላጅ የሆነው ጓደኛው ወጣት ሰለሞን ፤ በጓደኛው ሬሳ የተፈጸመው የወያኔዎች ወንጀል ‘ቁጭትና ሓዘን’ በተሞላበት ለኢትዮጵያ ሕዝብ በመግለጽ የወያኔ ትግራይ ጭካኔ ምንነት አጋልጧል።

ወያኔዎች ሌላም የጭካኔ ተግባር መፈጸማቸው ወጣት ሰለሞን ነግሮናል። ተምቤን ውስጥ ከመከላከያ አባል ጋር የፍቅር ግንኙነት የነበራት “ሴት አዳሪ” ከባዕድ ወታደር ጋር ግብረስጋ ፈጽመሻል በሚል አንድ እጇን ቆርጠዋታል።

በዛው ሰሞን አቶ ምዑዝ የተባሉ የአጋሜ አውራጃ ተወላጅ የሆኑ የኢድዩ አዋጊ ሆነው ወያኔን ለ17 አመት የተፋለሙ የትግራይ ተወላጅ ሰሞኑ በሌላ የዜና ማእከል ቀርበው ወያኔዎች የፈጸሙባቸው የጭካኔ ተግባር እንዲሁ ገልጸዋል። በእሳቸው ላይ የተፈጸመው የወያኔዎቸ ግፍ “ሆስፒታል ተኝተው እያሉ “ዓይናቸው ላይ በተጠና ሴራ” ዓይነ ብርሃናቸው የሚያጠፋ መርዝ በመውጋት እንዲታወሩ አድርገዋቸዋል። አቶ ምዑዝ በቃለ መጠይቁ ጥቁር መነጽር አድርገው ቃለመጠይቁ ሲናገሩ እጅግ ያሳዝናሉ።

በዚህ ሳያበቃ፤ ወያኔዎች “የገዛ ልጆቻቸውን” በወያኔ ፖለቲካ ካጠመቁዋቸው በሗላ፤ ልጆቹ በወላጅ አባታቸው ላይ በማሴር በወያኔ አፋኝ ነብሰ ገዳይ ቡድኖች ተይዘው እንዲገደሉ ወይንም እንዲታፈኑ ከፍተኛ ክሕደትና ሴራ በልጆቻቸው እንደደረሰባቸው ተናግረዋል።ወያኔዎች ልጆች ከወላጆቻቸው፤ ቤተሰብ ከቤተሰብ ተራርቀው እንዲገዳደሉ እና እንዲራራቁ በማድረግ የተካነበት ሴረኛ ቡድ ነው።

እዚህ ላይ ይህን ሳደምጥ ሂትለር ለጀርመን ወላጆች የተናገረውን “ልጆቻችሁ የናንተ ቢሆኑም አሁን የኔ ሆነዋል” ሲል ያነበብኩትን አስታወሰኝ።

ብዙዎቻችሁ የትግራይ ማሕበረስብ የወያኔ ጀሌ ነው ስንል በተለይ ብዙዎቻችሁ አማራዎች ስትቃወሙኝ አንዳንዶቻችሁም ስትሰድቡኝ እንደነበር ለታሪክ ያከማችሀዋቸው ሰነዶች ይመሰክራሉ። አሁን የትግራይ ሕዝብ በየትኛው ጎራ እንዳለ ጉልህ ስዕል እንደሰጣችሁ እርግጠኛ ነኝ።

በሚከተለው ጥያቄ ጽሑፌን ላጠቃልል፡

ለዚህ ጥያቄ ወጣት ሰለሞን በጋዜጠኛ መቅደስ ተጠይቆ ነበር፡

እንዲህ የሚል ጥያቄ፤

የትግራይ ሕዝብ ወያኔ በገዛ ፈቃዱ ወይም ደግሞ ለወያኔ ጥሩ አመለካከት አለው ብለህ ታምናለህ?

ሰለሞን፦

ሰው እየተገደለ ምን አገባኝ ብሎ አይቶ እንዳላየ የሚሄድ “ወያኔ በሚወስዳቸወ የጭካኔ እርምጃዎች  የተነሳ ምክንያት፤ የተሸማቀቀ ማሕበረሰብ ተከስቷል።

1) ወያኔ “ካሁን በፊት ታይቶ የማይታወቅ “ዘ-ሞስት ፈሪ ጀኔረሽን” ትውልድ ፈጥሯል”

2) ወያኔ “በታሪካችን አይተነው  የማናውቅ “ዘ-ሞስት ውሸታም” ጀኔረሽን/ትውልድ/ ፈጥሯል”

3)  ወያኔ “ዘ- ሞሰት ጨካኝ ጀኔረሽን እንዲፈጠር አድርጓል”                      

ሲል እውነታውን አስቀምጦታል።

እዚህ ላይ እኔም የማክልበት “ካሁን በፊት በትግራይ ታሪክ ውስጥ ታይቶ የማይታወቅ “የፋሺሰቶች ፖለቲካ” ተከታይ የሆነ “ወደ ሗሊት” ተመልካች ትውልድ ተፈጥሯል።

 በትምክሕት ጉራ የተወጠረ ፤ “በወርቃማ ዘርነት” የሚያምን ኢትዮጵያን እንደ ባዕድ አገር የሚያይ ፤ ጸረ አማራ ትውልድ ተፈጠራል።

ስናጠቃልል ፤ የትግራይ ታሊባኖች ከአፍጋን ታሊባኖች የሚለያቸው ታሊባኖቹ የእስልምና ሃይማኖት አክራሪዎች ሲሆኑ ፤ የወያኔ ትግራይ ታሊባኖች ደግሞ “ከወርቅ የዘር ሐረግ” የተወለድኩ ነኝ የሚል ፤ ማንኛውም የሚቃወመው ድርጅትም ሆነ ግለሰብ ከምድረገጽ በሃይል የሚያጠፋ አሸባሪ የሆነ አክራሪ የነገድ ድርጅት ነው።

እኛ ጥቂት የትግራይ ተወላጆች ድርሻችን ስንወጣ እናንተም ማሕደሮቻችንን “ሼር” በማድረግ ግዴታችሁን እንድትወጡ እየደጋገምን በመወትወት ላይ ነን።

ጌታቸው ረዳ

Ethiopian Semay