Monday, October 30, 2023

አንቺ ምን አገባሽ ሁለት አባት አለሽ አንዱ ቢሞትብሽ ባንዱ ትምያለሽ! ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay ድረገጽ አዘጋጅ 10/30/23

 

አንቺ ምን አገባሽ ሁለት አባት አለሽ

አንዱ ቢሞትብሽ ባንዱ ትምያለሽ!

ጌታቸው ረዳ

Ethiopian Semay ድረገጽ አዘጋጅ

10/30/23

 

ጽሑፉ አንዳንድ የፊደል ስሕተቶች ስለነበሩት ታርሟል።   

በመጀሪያ ለርዕዮት ሚዲያ አዘጋጅ ለቴድሮስ ፀጋዬ ከፍ ያለ ምስጋና እና ይቅርታ እጠይቃለሁ። ይቅርታ የጠየቅኩበት ምክንያት ቪዲዮውን በቅጂ ወደ ፌስቡኬ እንዲለጠፍ በማድረጌ። ይህንን ያደርግኩበት ምክንያት ስላለ ማለት ነው።

ከዚህ በተጨማሪ በዚህ ቃለ መጠይቅ የምታደምጥዋቸው  ዶ/ር ያዕቆብ ኃይለማርያም ስለ አብይ አድናቆት የቸሩት ገና አብይ ወደ ሥልጣን ብቅ ብሎ ሕዝብ ባጃጃለበት ወቅት ስለነበር፤ የያኔ የወቅቱ ጉዳይ ስለነበር በዚያ ተመለክቱት።

በተቀረ ስለ ከሃዲውና ባንዳው ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም የተቸረው አድናቆት ያው ብዙውን ጊዜ ዶ/ር ያዕቆብ ኃይለማርያም ወያኔ ወደ ሥልጣን ሲገባም “የብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች” የሚለው የፋሺሰቶች ታምቡር ሲደልቁ ከነበሩት ግምባር ቀደም አንዱ ስለነበር ከዚያም አለፍ እያለ ወያኔን ተቃውሞ የታሰረ ቢሆንም እንደ ጉንፋን በሽታ የወያኔ ፍቅር አለፍ ያለ እያገረሸበት መኖሩን እና እኔም ስቃወመው እና ሳደንቀውም እንደነበር ሳልጠቅስ ስለማላልፍ ስለ ከሃዲው የፋሺሰት ፓርቲ የወያኔ አመራር አባል ደ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ማመስገኑም ከዚያ ተያያዥነት ስላለው  በዚህ እለፉት።

ደ/ር ያዕቆብ ስለ ወደብ ታሪክ አንስቶ የሰጠው ምሁራው የሕግ ትንተና ቁምነገር ስላለበት ስለ ቀይ ባሕርና የወደብ ጉዳይ ሲነሳ በማሾፍና ተውኔት እየሰሩ ከኤርትራኖች ጋር የሚጠያሽቃብጡ ጸረ ኢትዮጵያ የሆኑ የሻዕቢያ ኤርትራኖችን እየጋበዙ (ልክ የግንቦት 7 እንደነ ንአምን ዘለቀ ሲያደርጉት እንደነበር) ቃለ መጠይቅ እየሰጡ ለሚያጎለብትዋቸው ለምሳሌ እንደ <<አንድ አማራ ሚዲያ>> አይነቶቹ የሻዕቢ አሽቃባጮች ማድመጥ ባይፈልጉምና ጥያቄውን በፌዝና በማሽቃበጥ ሊገድሉት ለሚፈልጉ አስመሳዮች ተቀባይነት ባይኖሮውም ፤ ሕሊና ላላቸው ዜጎች ጥያቄው እንዳይሞትና ችግኙን ውሃ እያጠጣን አገር ወዳድና ወላዋይ ያልሆነ መሪ እስኪገኝ ድረስ አዳዲስ የሻዕቢያ አስቃባጮችና ባንዳዎች እንደበፊቱ እንዳይደፍኑት ህያው እንዲሆን ለሚፈልጉ እንዲያደምጡት እነሆ። 

በመጨረሻ ዶ/ር ያዕቆብን አመሰግናለሁ። በሚቀጥለው የተው የዶ/ር ተኮላ ወ/ሓጎስ አስደናቂ የባድመና የቀይባሕር ወደቦች ጥያቄ  ትንታኔ ጉዳይ ማንም ምሁር እንዲያ ያለ ትንታኔና ሙግት ስላላቀረበ ሰፊ ገባ ስለሆነ ፌስቡከምረ እንድያ ያለ ሰፊ ዶክዩመንት ለማስተናገድ ቅም ስለሌለው እንዴት አሳጥሬ እንደማቀርበው እያሰብኩ ነው። ተከታተሉኝ። አቀርባለሁ። 

ባድሜ፤ ዛላምበሳ፤ ኢሮብ ወዘተ… ዛሬም በአብይ ደደብነትና ትብብር በጦርነቱ ወቅት በአመጽ ሻዕቢያ ወስዶታል። ያ ትግል ዛሬም ህያው እናደርገዋለን። ተከታተሉኝ።

ባንዳዎችና አሽቃባጮች ሁሌም ሁለት ቤትና የሚሸሹበት መጠለያ አላቸው። ለዚህ ነው <<አንቺ ምን አገባሽ ሁለት አባት አለሽ አንዱ ቢሞትብሽ ባንዱ ትምያለሽ!>> የተባለው። 

Ethiopia: Interview with Dr. Yacob Hailemariam on Assab || ከዶ/ ያዕቆብ ኃይለማሪያም ጋር የተደረገ ቃለ ምልልስ

https://youtu.be/yHpF1pVALeg?si=sodMs5lHfayUiJVe

ጌታቸው ረዳ    

ጌታቸው ረዳ