Sunday, April 15, 2018

አስገራሚ ፥ አስደናቂም ፥ አሳፋሪም ባጭር የተቀጨው የአታላዩ ጠቅላይ ምኒስትር የማታለለል ችሎታው ላያንሰራራ ላንዴም ለመጨረሻም መቀሌ ላይ ተቀብሯል! ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay)


አስገራሚ  አስደናቂም   አሳፋሪም ባጭር የተቀጨው የአታላዩ ጠቅላይ ምኒስትር የማታለለል ችሎታው ላያንሰራራ ላንዴም ለመጨረሻም መቀሌ ላይ ተቀብሯል!
ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay)

አብይ አህመድን በደምብ የገለጸው ተቺ እውቁ ብዕርተኛው ወዳጄ “አገሬ አዲስ” ነው። “ጎብላንድ አጭበርባሪው ጦጣ” በሚል የጻፈውን ኢትዮፓትርዮትስ ድረገጽ የተለጠፈውን ብታነቡ የብዙ ሰው ቀልብ የሳበው የአብይ አህምድ የአታላይነት ችሎታው በደምብ ገልጾታል። ድሮ አታላይነትን በብልጥነት ነበር የሚታወቀው።ብልጠት፤ ከተቀናቃኞችህ ላቅ በሎ መገኘት የሚል ትርጉም የተሰጠ ትርጉም ይመስለኛል። ጥሮ ግሮ ኑሮን ለማሸነፍ ይሁን በሌላ መልኩ ለጉራጌዎች ነበር ይህንን ችሎታ ሲሰጥ የነበረው።”ጉራጌ ይሉናል ግራ የገባቸው፤በቀዳዳ መርፌ እየታለልናቸው”። የሚል ግጥም እራሳቸው የገጠሙት ይሁን ወይንም ሌሎች የገጥሙላቸው፤ ብቻ ይህንን የብልጣብልጥነት ችሎታቸው ተገጥሞላቸው ነበር። ያ ብልጥነት ዘዴአቸው በብዙ መንገድ እንደየ ተርጓሚው ተለያይቶ በብዙ መንገድ ሊቸረቸር ይችላል።

        ወያኔዎች ከገቡ በላ፤ በ27 አመት ውስጥ “አየር ባየር” “ደላላ” “ብጻይ” “እህት ፓርቲ” “የኢንቨስተምነት አጋሮች” ወዘተ…በሚባሉ በሦስት ክፍሎች የመጡ ወገኖች የጉራጌዎቹን ቦታ የተኩት አደሬዎች፤ትግሬዎች፤ሶማሌዎች እንደሆኑ ይነገራል። በወያኔዎች ግፍ የተማረረው የኢትዮጵያ ሕዝብ “ሳንፈልጋቸው 27 አመታቸው!” ብሎ የወያኔን የደም ሥር ለማድረቅ ሲሞከር በዘዴ የገቡት የዛሬዎቹ ኦሮሞዎች ደግሞ ለየት ባለ ስልት በቀዳዳ መርፌ ሾልከው የሕዝቡን ቀልብ በመሳብ አብይ አህመድ የተባለ “ጎብላንድ አጭበርባሪው ጦጣ” ተክተው ሳናስበው አስጨበጨቡን። ይህ አታላይነት በአገራችን አዲስ ባይሆንም  ይህ አታላይነት ከሌሎቹ የሥልጣን አታላዮች ልዩ እና አዲስ የሚያደርገው  በሥርዓቱ ዘንድ ‘በሞት እና እስር’ የሚያስቀጡ  ያልተለመዱ ንግግሮችንና ለገደልናቸው ዜጎች ይቅርታ እንጠይቃለን ብሎ ዜጎች መግደሉን በይፋ አምኖ ይቅርታ በመጠየቁ ሕዝብ በማታለሉ ልዩ ያደርገዋል።

ይህ በሥርዓቱ የተወለደ ያደገ ከሥርዓቱ የወጣ የሥርዓቱ ወታደር የነበረ ሰው ባልተጠበቀው ንግግሩ ሕዝብን ተስፋ ያስሰጠው የጠቅላይ ሚኒስትርነቱን ቦታ ከያዘ በላ፤ ያ ሁሉ ኢትዮጵያዊነት በተናገረበት ለዛው ከአፉ ሳይደርቅ በሁለተኛው ሳምንቱ ውስጥ እነኚህ ከላይ የተዘረዘሩት ሕዝብን ያስጨበጨቡና ተስፋ ያስሰጡ (ያጃጃሉ) ኢትዮጵያዊ ንግግሮች የተናገርን ዜጎች ሁሉ ሲገድለንና እና ከአገር ሲያባርረን የነበረውን፤ በኢትዮጵያ አምላክ ፍርድ ተፈርዶበት በሰይፍ ተሰይፎ ከዚህ አለም የተሰናበተው “ኢትዮጵያን የወጋየጥላቻ አባት” የተባለው የወያኔው መሪ መለስ ዜናዊን “በጀግንነት” ዘከረው።

ይቀጥል እና እሱ ሲመራቸው የነበሩት የኢትዮጵያ ሠራዊትን “ወራሪ” “አማራ” እያሉ በባሰ መልኩ ኢትዮጵያዊውን ሠራዊት እንደ ‘ጣሊያን ጦር’ በመቁጠር በጠላትነት የፈረጁትን፡ በትግራይ በኤርትራ በምፅዋበአልጌና…  ‘ኢትዮጵያውያንን የወጉ’  ለኤርትራ ወንበዴዎች እና አረቦች የወገኑ” የወያኔ ሽምቅ ተዋጊ ሃይሎችን “ጀግኖች” ብሎ በመሰየም የአባባ ጉንጉን ሲያስቀምጥ ወታደራዊ ሰላምታውና ወገንተኛነቱ ለማን እንደወገነ ግልጽ አድርጎልናል።

ይህ የጥላቻ ሃውልት የሚያመላክተን ነገር አማራውን ከወልቃይት ጀምሮ ሲያፍኑና ሲያሳድዱ ኢትዮጵያን ሲወጉ ለነበሩት የትግራይን ልዕልና እንጂ ለኢትዮጵያ ልዕልና ያልተሰው  የወያኔ እንጂ የኢትዮጵያ ሰንደቃላማን እያውለበለቡ ያልተሰው የኢትዮጵያ ሰንደቃላማ በጠላትነት ፈርጀው ከተሰቀለቺባቸው ግድግዳዎችቤተክርስትያናትት/ቤቶች እና መንግሥታዊ መ/ቤቶች ሲያወርዱዋት ለነበሩት በጸረ ሸዋነትናበፀረ ምኒልክነት መተከል ተነስተው ለተሰው ተዋጊ ሃይሎችን በቆመ ሃውልት ሥር አበባ ሲያኖርና ‘በጀግነነት’ ሲያሞግሳቸውእነሱንም ወርቅ ባለበት አፉ ውስጥ አንዲት ሐረግአንዲት ቃል እንኳ ዳር ድምበር ለማስጠበቅ ሲሉ በትግራይም ሆነ በኤርትራ ምድር፤ ከወርቅ ልጆች ጋር ለተዋጉም ሆነ በባድሜ ለተሰተው በሺዎች የሚቆጠሩ ወያኔ ሲገባ ያባረራቸው ብቃት ያላቸው ወታደሮችና ወታደራዊ አዛዦች እንዲሁም ተዋጊ አይሮፕላን አብራሪዎች ፤ ግንቦት 1990ዓ.ም  ትግሬን ለማዳን ጥሪ ተደርጎላቸው ግማሹ ተለምነው ወደ ሠራዊቱ የገቡ በሺዎቹ ያለቁት የድሮ የሰራዊት አባላት የባድሜ ጦርነት ፍልምያ የሚዝክር አንዲት የምስጋናም ሆነ የጸሎት ቃል ከመናገር ይልቅ ፤ ምን ታመጡ ብሎ “ትግሬዎችና መሪያቸውን (ከኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ከሚሉ ጦረኞች ከሸዌዎች ከሚኒልካውያኖች ከባንዴራው በስተጀርባ ካሉት አማራዎችና ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን ጋር ስትገጥሙ) በጦርነቱ ጊዜ “ወርቅነታችሁን” ያስመሰከራችሁ “ወርቆች” ሲል ለወያኔ አሽከርነት ሲመለመል፤ ት/ቤት ውስጥ አለቃው መለስ ዜናዊ ያስተማረውን ሐረግ እየጠቀሰ "የአማርን የወንድ ዘር በመቀጥቀጥ፤ የአማራ ውብ ሴት ወጣቶችን እራቁታቸውን እያስወለቀ ሰክሮ በየእስር በቱ የሚመረቅነው ወረበላ የወያኔ ምልምል ገራፊና ግበረሰዶማዊ እና ደም የጠማው ሱሰኛ ሁሉ ” በወርቅነትና ሞተርነት”
   ሲያሽሞነሙናቸው ማድመጥ እጅግ ፤እጅግ ይዘገንናል። 

ባጣም አድርጎ ያማል። ይህ ሰው አታላይነት የተላበሰ ቢሆንም አታላይነቱ ግብዝነቱንም ጭምር የተላበሰ ነው። ባንድ አፍ ሁለት ምላስ የበቀለበት ጉደኛ ሰው ነው። 

የድሮ ጦር ተዋጊ ሃይሎች ከወያኔ ተዋጊዎች ጋር ሆነው በግንቦተ 4/1990 ዓ.ም ምን እንደተደረገ አብይ ስቶት ነው? እስኪ ኢትዮፎረም ድረገጽ የወጣው አንባቢዎቼን ላስታውሳችሁ፤-

የኢትዮጵያ ሰራዊት በምዕራብ ትግራይ በኩል ተሰኔን አልፎ በረንቱ ከተማ በመግባት ሃይኮታን አልፎ አስመራን ለመግባት በጉጉት ይጠባበቅ ጀመር።በመካከለኛ ግንባር ሻምበቆ በማለፍ ፆሮና ገብቶ አይቀሬው 95 /ሜትርን አልፋ የምተገኘውን አስመራን በርቀት ማየት ጀመረ። በምስራቕ ትግራይ በኩል ዛላምበሳ ከተማን አልፎ ሰንዓፈ ከተማ በመቆጣጠር እምባሴራ ተራራ ላይ ሆኖ አዲ ቀይሕና የአስመራ በር የሆነችሁ ደቀምሓሬን በርቀት እየተመለከተ መጣን መጣን ይላል…።
በአፈር ክልል ባዳን አልፎ እንዳልጌዳ፣ ዓውዳ አልፎ የአሰብን መስመር ለመቁረጥ እየተፋለመ ይገኛል። በቡሬ ግንባርም የኢትዮጵያ ሰራዊት ከፍተኛ መስዋእትነት በመክፈል አይሞከር ምሽግን ደርምሶ የአሰብ ጨው ፋብሪካ ጋር ተጠግቶ የባህር በራችን ለመመለስ በስሜት እየተዋጋ ነበር።
በወቅቱ ከሻዕቢያ ከተማረኩት አንዱ ያለውንዓስብ የነበረው /ጦር ሁሉ ተነስቶ በዓፋር መሬት እንዳይቆረጥ ምፅዋዕ ላይ ተቀያሪ ምሽግ ሰርቶ ገብቷል። እዚህ ዓሰብ የቀረው አንድ ብርጌድ ነው። ይሀውም እኔ አንዱ የዛ ብርጌድ አባል ነኝ።የሚል ቃሉን የሰማ ሰራዊታች ሺዎች ጓዶችን ወድቀው እያየ የነሱን መስዋት ከዳር ለማድረስ በደስታ ወኔውን ተነሳሳ።

ይህ ሁሉ ሲሆን የሻዕቢያ መሪዎች በሬድዮና ቴሌቪዥን ላይ የድሮ የሳህልና የናቅፋ ዘፈኖች ለሕዝቡ እንዲታዮ በማድረግ የነበራቸውን ትጥቅና ንብረት ወደ ናቅፍና ሳህል መጫን ላይ ነበሩ::" ምንጭ (Ethiopian Media Forum- ያልተፈታው የሰኔ ቋጠሮ! (የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ያልተሰሙ እዉነታዎች2006/2014)"

ይህ ሁሉ ጀግንነት ሊታይ የተቻለበት ምክንያት ያለ የድሮ ጦር ተዋጊና አዛዥ እንዲሁም በችሎታቸው የታወቁት የድሮ ተዋጊ አይሮፕላን አብራሪዎች ሱታፌ የወያኔ ሽምቅ ተዋጊ ብቻውን ከቶ በምንም ታምር፤ ሻዕቢያን ማስወጣት እንዳልቻለ በሁለት አመት የሻዕቢያ 1000 ኪ/ሜ ተዘፍቆ መቆየት ማስረጃ ነው። (ምክንያቱም ሻዕቢያ ለ10 አመት ወታደራዊ ስልጠና እና ምልመላ ሲያካሂድ ወያኔ የራሱንም የድሮ ሠራዊትንም ሠራዊት ሲበትን ነበር-! ሆን ተብሎ በእነ መለስ ዜናዊ እና ስብሐት ነጋ…ወዘተ አሻጥር!)። ታዲያ አብይ ስለ እነዚህ ጸሎት አደረገ? ለምን? ምክንያቱም ‘የወያኔ ድርጅትን የሚቆጣጠሩት’ አለቆቹ አሁንም ኤርትራኖችና ለኤርትራ ልባቸው የለሰለሰ ትግሬ ባንዳዎች ስለሚቆጣጠሩት ነው። ከውግያው በላ የተባረሩት ሠራዊቶችን አስታውሱ፧ ለምን ተባረሩ? እራሱ የቻለ ሌላ ርዕስ ነው።

ይህ ከታች የሚታየው አሳዛኝ ፍጻሜ የሚያሳ ፎቶ ከወርቆቹ ጋር መመደብ ያሳፍራል? ከወያኔዎች ጉሮሮ ለጉሮሮ ተናንቀው ሳሕልና ምጽዋ ሲዋጉ እኮ እነ በዛብህ ጴጥሮስ የድሮ ሠራዊት አባሎች ነበሩ። ‘የአታላዩ ተጋዳላይ’ ወርቆቹና ሞተሮቹ እያወዳደራቸው ያለው እኮ ከሌሎች ነገዶች የተገኙ ኢትዮጵያውንን አሁን ካለችበት ጭለማ እንዳትገባ ለማዳን የተዋጉ፤ እራሱ አብይንም ‘የወርቆቹ’ አሽከር እንዳይሆን ከወላይታ፤ ኦሮሞ፤ አማራ፤ ኤርትራ፤ ትግሬ…..ወዘተ… የተውጣጣ ሠራዊትን እኮ ነበር። አብይ “መዳቦች” እና “ዝቅተኛ ዋጋ የሚያወጡ” በሚል የግምገማ ነጥብ እየመደባቸው ያለው እኮ እነ በዛብህን ነው። 

ሳይደራደሩላቸው በዛው ቀልጠው ቀርተው፤ ቤተሰቦቻቸው ለዝንተ ዓለሙ በሐዘን ተውጠው ሲቀሩ እነ ደብረጽዮን በየቻይና ና ኤሺያ “ፖርኖ አዳራሾች” እየተዘዋወሩ የኢስያ ሴቶች … እየላሱ ሲመረቅኑ ይውላሉ። ስተአስበው አውነትም አስገራሚ ወርቆች ናቸው! የሚገርም ነው! ሌላው ሕዝብ ተሻካሚ ዕቃ፤ ሆኖ ትግሬው ‘አንቀሳቃሽ ሞተር’ አድረጎ የመሳል ቅዠቱ በማን ግፍት እንዲያ እንዲል እንደተገፋፋ ሊገባኝ አልቻለም።እርግጥ ጹሑፉ ያረቀቁለት ወያኔዎች ናቸው። ቢያንስ የወረቀቱ አርታኢዎች ወያኔዎች እንደሆኑ እርግጠኛ ነኝ። ለአብይ እንዴት እንዳጎመዠው አላውቅም እንጂ ፤እኔ ትግሬነቴን እንዴት እንደጠላሁት አብይ ባወቀልኝ ጥሩ ነበር! ጥሎ አይጥሉት ነገር የዘር ነገር! ጂኔን -ትውልዴን ወዴት አሽቀንጥሬ ልጣለው? ተፈጥሮ ሆነ!!
ይህ ፎቶ እውቁ ተዋጊ አይሮፕላን ጦር አብራሪው የኮሎኔል በዛብህ ጴጥሮስ ነው። በዛብህ ዝቅ ብሎ ሲበርር በጥይት ተምትቶ ተከስክሶ ሲወድቅ ለኢሳያስ ያደሩ ካፍንጫቸው ርቀው ማሰብ የተሳናቸው የኢሳያስ አሽከሮች ወደ መግረፊያ ሲወስዱት ነው።እነሱም በታረቸው፤እሽክርና ሲመራቸውና “የውሸት ነፃነት ስካራቸው ሲበርድላቸው” መጠየቅ ሲጀምሩ ወደ መግረፊያ ተወስደው ግማሹ ወደ በዘብህ አገር ወደ እምየ ኢትዮጵያ አገር ሸሽተው በስደት እየኖሩ ነው። “አታላዩ ተጋዳላይ” እነዚህን ጀግኖች ያውቃቸዋል? ለመሆኑ የወርቅ ልጆቹ እነዚህ “መዳቦች” በባድሜ ጦርነት ጊዜ ለምን ፈለጋቸው? ለመሆኑ ወርቅ ብቻውን መጋፈጥ ይችላል? ወይስ ስብሓት ነጋ እንደተናገረው “ወርቅ ከአፈር ጋር አብሮ አይኖርም? መኖር የለበትም” ነው? ወርቅ ብቻውን መኖር ከቻለ አፈር ጋር ምን ያስጠጋዋል?

ልደምደም፡
ይህ ሰው ሁሉንም አታሏል። ‘ኢትዮጵያና ፤ ኢትዮጵያዊነት ሲያነሳ ተገንጣዮችን አስደነበረ ተስፋ አስቆረጣቸው ፥ ለአጭር ጊዜም ቢሆን ቀበቶአቸውን አስፈትቶ ‘ኢትዮጵያ’ እንዲሉ ሳይወዱ እንዲያመነዥኩት አደረጋቸው፤ በሞላጫ ምላሱ በዛው አላቆመም፡ “ኢትዮጵያውያኖችንም በእምየ ኢትዮጵያ ጓዳ ዞሮ በመግባት በስሜት ስካር ጠመደን! ደንግጠው፤ የልብ በሽታ ሊይዛቸው የተቃረቡት እና እንቅልፍ አጥተው የነበሩትን ‘ድንጉጦቹን’ የህወሓት ጀሌዎችንም ሁለተኛ እፎይታ ሰጣቸው። ይህ አስገራሚም ፤ አስደናቂም አሳፋሪም ባጭር የተቀጨው የአታላዩ ጠቅላይ ምኒስትር የማታለለል ችሎታው ላያንሰራራ ላንዴም ለመጨረሻም መቀሌ ላይ ተቀብሯል። እኔ እንቆቁልሽ የሆነብኝ፤ መለስ ከሞተ በላ የምን ወርቅና ሞተርነት ነው እንደገና እየሰማን ያለነው? ሰውየው ሰክሮ ነበር ልበል? ተቃዋሚን እስሮ የወንድን ዘር ብልትን መቀጥቀጥ ወርቅነት ነው? የሴት ልጅ ጥፍር በቢንሳ መንቀልና እርቃንዋን እያዩ ማዋረድና መመርቀን ወርቅነት ነው? የፖለቲካ እስረኛን  ቅስም ለመስበር በግብረሰዶማውያን ማስደፈር ወርቅነት ነው? የምን ወርቅነት ነው እየቃዠብን ያለው?
ክፍል ሁለት ይቀጥላል….።
ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay)