Sunday, December 6, 2020

አብይ አሕመድ እና የወያኔ መሪዎች የአፓርታይድ ስርዓት ለማስቀጥል በውጭ አገሮች የተቀጠሩ ሰላዮች ናቸው! ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay) December 6/ 2020

 

አብይ አሕመድ እና የወያኔ መሪዎች የአፓርታይድ ስርዓት ለማስቀጥል በውጭ አገሮች የተቀጠሩ ሰላዮች ናቸው!

ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay)

December 6/ 2020

በመጀሚያ ይህንን ልበልና ወደ ርዕሴ ልግባ። እብሪተኛው ፋሺታዊው ወያኔ በጫረው እሳት እራሱን አቃጥሎ እንደ ዝንጀሮ በፈርሃት ቆፈን ዋሻ ለዋሻ ተደብቆ እየተመታ ተበታትኖ ሲሸሽ ማየቴ ደስታየ ወደር የለውም። እራሱ በለኮሰው እሳት ለመቃጠሉ ተጠያቂው እራሱ እንጂ ማንም እንዳልሆነ ብቀብልም፤ እዚህ ድረስ ጠግቦ ብዙ ኪሳራ እስኪያመጣ ድረስ የታገሰው ልፍስፍሱ አብይ አሕመድም እንደ መንግሥት መሪ ሆኖ ባለመገኘቱ ለኪሳራው ተጠያቂ ነው። ይህ ካልኩ ዘንድ ወደ ርዕሴ ልግባ።

አሜሪካኖችና ሶቭየቶች እንዲሁም ቻይናዎች ዓለምን ለመግዛት ባላቸው ጉልበትና ፍልስፍና በቀጥታም በተዘዋዋሪም ሲፋለሙ፤ ይህ ተፋላሚ ሃይል በውስጥ ከቀጠርዋቸው ሰላዮቻቸው በኩል በ1960ዎቹ ወደ አገራችን በመግባት እንደተቀረው ኢትዮጵያን በምስራቅ እና በምዕራብ ፍልስፍና ተወጥራ እንደ ወተት ስትናጥ የኛ ሊህቅ ተማሪዎች መሪ ተዋናዮች ነበሩ። ከተዋናዮቹ መካከል የዛሬዎቹ የዳግማይ ወያኔ መሪዎች አንደኞቹ ነበሩ። በሚቀፍፍ ሁኔታ ኢሕአፓም፤ መኢሶን፤ ወያኔም፤ ሻዕቢያም ከውጭም ከውስጥም ሆነው በተሰበኩበትና ባነበቡት የባእድ ፍልስፍናዎች ፍቅር ተጠምደው የአገራችን ‘ባሕልና ወግ’ በማፍረስ በአፍሪካ ውስጥ በጣም አጥፊ ተግባራት በመፈጸም አገራችን አሁን ላለችው ክስተት ዳረግዋት።

በዓለም ላይ ሁሉ ፣ በምስራቅም በሰሜንም በደቡብም፣ያደገም፤ያላደገም አገር ሁሉ አሜሪካኖች በሚመሩት ዓለም አቀፍ የባንክ እና የስለላ ኮርፖሬሽን በተዘረጋው አዲስ አብዮት (ኒው ወርልድ ኦርደር) ምክንያት ‘ሶቭየት ሕብረት’ ብትንትንዋ እንድትወጣ በማድረግ የአሜሪካ የኮርፖሬት ካፒታሊዝም የበላይነቱን ተቀዳጀ፡፡ በዚህ መልክ አጋጣሚውን በመጠቀም የኮርፖሬት ካፒታሊዝም የበላይነቱን ሲይዝ በአፍሪካ ውስጥ በጣም አጥፊ ተጽዕኖዎችን ማድረግ ጀመረ። ዓለም አቀፍ ካፒታሊዝም “የአፍሪካን ዳግም ቅኝ ግዛት” በመባል በሚታወቀው በቀጥታም ሆነ በእጅ አዙር የጀመረው በሌሎች አፍሪካ አገሮች ቢሆንም አገር በሚያፈርስ መልኩ ዘመናዊ ባሮችን በመግዛትና በማዟዟር እንዲሁም ሕዝባችን በጎሳ እንዲሸነሽን በመርዳት ኢትዮጵያ ውስጥ የተለየ መሰሪ ተከትሏል።

 

እ.ኤ.አ. ከ 1990 ዎቹ መጀመሪያ ጀምሮ አፍሪካዊው ማንነት እየተደመሰሰ በተለይም በኢትዮጵያ በምዕራባዊያን የባህል ወረራ መስፋፋትን ቀዳሚ ስፍራ መያዝዋን ሁላችሁም የምታውቁት ነው። ወያኔዎች በእነ ፖል ሔንዝ እና በእነ ሐርማን ኮኸን ተደግፈው ኢትዮጵያን ተቆጣጠሩ። ኤርትራም እንዲሁ በ ሲ አይ ኤው ምልምል በኢሳያስ መሪነት “ባሕረ ነጋሽ” ተገነጠለች። በመላ አፍሪካ እርስ በርስ የመዋጋት ባሕል ተከሰተ። ዛየር ፣ ሴራሊዮን ፣ ላይቤሪያ ፣ አንጎላ ፣ ሩዋንዳ ፣ቡሩንዲ፤ አይቮሪ ኮስት፤ የሶማሊያ የጦር ቀጠና ሆኑ። በእነዚህ ሁሉ የአፍሪካ ሀገሮች የተቋቋመው መንግስት ሲወድም ሕዝቦች አልቀዋል፡ ተቁዋማት ወድሟል። ለውድመቱ ምክንያት ደግሞ ከውስጥ "ኤሊት" ተብሎ በሚጠራው በ kleptocratic ማፊያ በሚመሩ "የጎሳ" ግንባሮች ፍልሚያ ውስጥ እጁን በማስገባት በሁለቱም ተፋላሚ ግምባሮች “የኮርፖሬት ካፒታሊስት የስለላው መረብ” ሁሉንም ዓይነት ሠራዊቶች በገንዘብም በሃሳብም በመደገፉ ነው።

ዓለም አቀፍ ሕጎችን በመጣስ በተፋለሚ ወገኖች በቀጥታ ጣልቃ በመግባት ተጠያቂነት የሌለባቸው ተፋላሚ ወንጀለኞች ያሻቸው እንዲያደርጉ የተቻለውን አደረገ። በዚህ ፍልሚያ አደራጅ ሆኖ የታየው የስለላው መረብ እስራኤልና አሜሪካ እንዲሁም ጂሃዳዊው እስላም ከመካከለኛው ምስራቅ ቱጃሮች በመቀናጀት ኢትዮጵያ ውስጥ ሉአላዊ ድንበሮችዋን በሚጻረር መልኩ “ጎሳዊ” ግንባሮችን በመፍጠርና በመደገፍ ኢትዮጵያ እንደትፈርስ ከተፈረጁት አገሮች አንድዋ ሆና አሁን ላለንበት እልቂትና የዘር ፍጅት ተዳርጋለች።

የአይሁዶቹ የሞሳድ ድርጅት የውስጥ ሰላዮችን በማደራጀት የአይሁድ ሃይማኖት ተከታዮች የሆኑትን በተለምዶ “ፈላሻ” የሚባሉትን ኢትዮጵያዊያንን አገራቸው እንዲክዱ በማድረግ በምስጢር የዘረጉትን መዋቅር ስብከት ፈላሻዎቹም ኢትዮጵያ አገራችን አይደለችም በሚል ፖለቲካዊና ሃይማኖታዊ ሰበካ ተቀብለው፤  በሺዎች የሚቆጠሩ ትግርኛ፤ አማርኛና አገው ተናጋሪ ኢትዮጵያዊያን ወደ እስራል በማስገባት ዛሬም ነተኛሁ ሰላዮቹን በመላክ ባለፈው ሰሞን ተጨማሪ ፈላሻዎች በገፍ ጭነው በመውሰድ የሰው ሃይል እየበዘበዘች ነች። ቻይንም ሕንድም ሆነች አሜሪካ እንዲሁም አረቦች ግብርናውና ማአድኑን አንድ ባንድ ተንሰራፍተው ተቀራምተውታል።

እንዲህ ያለው ዘረፋ በአገራችን ብቻ ሳይሆን በመላ አፍሪካ እና እስከ ኢራቅ፤ሶርያ እና ሊቢያ ድረስ ጣልቃ ገብተው ሀብቶቻቸው ሁሉ ተቆጣጥረው አገሮቹ እንዲፈርሱ ሆነዋል። ኢትዮጵያ አሁን ላለችበት የጦርነት ፍልሚያ በሁለቱ ወገኖች የሥልጣን ሽሚያ እና በውጭ የታቀደ ዕርዳታና ሴራ ውጤቱ የሰው እልቂትን እያስከተለ ነው። ኢትዮጵያ “ፌይልድ ስቴት” (የተንኮታኮተች አገር) ተብላ ከተመዘገበች ቆይታለች። ብያንስ በኔ እና በመሳሉ ጓደቼ በኩል ይህንን እናምናለን።

ወያኔና ኦነግ ተንከባክበው ባሳደጉት ተማሪያቸው “በአብይ አሕመድ” መካከል እየተካሄደ ያለው ጦርነትና ውግያ አፍሪከ ውስጥ በዓይነቱ ለየት የሚያደርገው ነገር፤  አገር በሚያፈርሱና የጎሳ የበላይነት በሚፎካከሩ ሁለት የጎሳ መሪዎች የሚካሂዱት  መሆኑን ጎልቶ የሚታይ ጉዳይ ነው። አብይ አሕመድ አገር አትፈርስም የሚለው እርሱ በጎሳ ስርዓት ኢትዮጵያን እስከተቆጣጠራት ድረስ ሲሆንወያኔ ደግሞ ያጣሁት ሥልጣን መልሼ ካልያዝኩ ትግራይ ትግርኚን እመሰርታለሁ በሚል ቅዠት ምሲኪን ሕዝብ እንዲታረድ ባመድረግ ሁለቱም በመንግሥታዊ ስርዓት አያያዝ ጉድለትና ወንጀል ተጠያቂዎች ናቸው።

ሁሉም ዓይነት ዱርዬዎች እየተከሰቱባት ያለቺው ኢትዮጵያ ሁለቱም ግምባሮች በሚከተሉት መንግሥታዊ ስርዓት መሆኑን መታወቅ ይኖርበታል። በውጭ አገር የተደገፈው “የጎሳ ስርዓት” ተወግዶ አዲስ መሪ ካልመጣ የሁሉም አይነት ዱርየዎች መናሃሪያ የሆነቺው ኢትዮጵያ ወደ ከፋ ጭለማ መገፍተርዋ መጠራጥር የለባችሁም።

አላመን ካልሆ በቀር እውነታው በሁሉም አቅጣጫዎች አገራችን በሁሉም ዓይነት የግልና የጎሳ ታጣቂዎች ወደ ገደል እየተጎተተች ያለቺው አገራችን  አዲስ መፍትሄ ያሻታል። በእነዚህ ታጣቂ ዱርየዎች ላይ እንደ አብይ አሕመድ እና ወያኔ የመሰሉ በውጪ የተመለመሉት የባዕድ አገልጋዮች የሚከተሉት ፓለቲካ ስንመለከት፤ ያውም እንደ እነ እስክንድር እና ልደቱ እንዲሁም አስቴርና ብዙ ጀግና እመቤቶች በሽብርተኛነት ወንጅሎ የሚያስር መሪ ኢትዮጵያዊ ነው በሎ መቀበል እጅግ ያስቸግራል።

ይህ ግለሰብ የሚመራው ስርዓት እጅግ የሚያማምሩ ገበርዲኖች ለብሰው ሰው የሚመስሉ በወንጀል ሥራ የተሳተፉ ኢትዮጵያ እና አማራ የሚሉ ቃላቶች ሲደመጡ የሚባንኑ ፤ በቤቶችና በገንዘብ ዘረፋ የሚሳተፉ መንግሥታዊ ዱርየዎች የተከማቸበት መንግሥት የምትመራ  ኢትዮጵያ አገር ሆና ትድናለች ብለን ካልን ከፈጣሪ በስተቀር “እስካሁን ድረስ ፍትሕ ያልፈተሻቸው ዱርየዎቹ”  መፍትሄ ናቸው ተብሎ እንደመንግሥት መቁጠር ተራ ጅልነት ነው።

 

ወዳጄ እና መምህሬ የነበሩት ፕሮፌሰር ዓለሜ እሸቴ ባንድ ወቅት በጻፉልኝ ደብዳቤ እንዲህ ብለው ጽፈውልኝ ነበር፤ “…the Mafia robbery going on in each "tribal state" (or Kelel) with Weyane kleptocrats being the greatest of all the robbers.” ከወያነ ክሊፕቶክራቱ ትልቁ ዘራፊ በተጨማሪ በእያንዳንዱ “የጎሳ ግዛት” ውስጥ ማፊያዊ ዘረፋ  እንደቀጠለ ነው።” (ፕሮፌሰር ዓለሜ እሸቴ) ብለው ነበር።

ሌላ ቀርቶ እስከ አሁንዋ ድረስ እየገረመኝ ያለው ሁኔታ “የጎሳ ነጻ አውጪዎች” ሴራ እንዳይበቃ በላዩ ላይ “ጎሳዊ” የፖለቲካ ፓርቲዎች ህጋዊ ሆነው ሲደመሩበት አገሪቷ 30 አመት ሙሉ ምን ያህል የቆረቆዘ “ሚዘራብል” (ደደብ አሳዘኝ) ምሁር ጫንቃዋ ላይ እንዴት አስችሏት እንዳዘለቻቸው ሳስበው ይገርመኛል።

ምሁሩ ብቻ ሳይሆን የአብይ አሽቃባጮችም ሌሎቹ ጉዶች ይገርሙኛል። አብይ አሕመድ የሚመራው ስርዓት “ወድዶ ሳይሆን ተገድዶ” ወያኔን አሳድዶ በመቅጣቱ ደስታቸውን ከመግለጽ ይልቅ፤ ይህንን የጦርነት ድል አስታክከው “ከወያኔ ያልተሻለው የጎሳ ሕገ መንግሥት ጠበቃው ጸረ አማራው አፓርታይዱ አብይ አሕመድ “መሪዬ ነህ” እያሉ እንደ ሜዳ ፍየል ሜዳው አልበቃ ያላቸው “የፖለቲካ ማሃይሞችንም” ላግራሞቴ ተጨማሪዎች ናቸው።

በዘም ወረደ በዚህ አብይ አሕመድ ከኦነግና ከሻዕቢያ፤ የወያኔ መሪዎች ደግሞ በነበሩበት የበረሃ ትግላቸው የውጭ አገር ቅጥረኛነታቸው ያየነው ሲሆን፤ ወያኔ ወደ መንግሥነት ከገባም በሗላ አብይ አሕመድና መሰል የወያኔ የስለላ ሰራተኞች በነበራቸው የመንግሥት ሥልጣን እና ቦታዎችአውቅና ተጠቅመው በሞሳድና በአሜሪካ እንዲሁም በእንግሊዝ የስለላ ድርጅት የተቀጠሩ የተለከፉ ሰላዮች መሆናቸው መጠራጠር የለባችሁም። የግሎባል ካፒታሊዝም ልዕለ ሃያሉ አገር እነዚህን እንዴት እንደሚጠልፋቸው ለማወቅ ለፈለገ ሰው ”By way of deception” የሚል የሞሳድ ሰራተኛ የነበረው ካናዳዊ አይሁድ መመልከት ነው። ለማንኛው “ኢትዮጵያ ታበጽህ ኢደዊሃ ሃበ እግዚአብሔር!”

ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay)