Tuesday, October 28, 2008

ጉልቡጥ ፖለቲካ


ጉልቡጥ ፖለቲካ
ጌታቸዉ ረዳ
ወንድሜ አቶ በልጂግ “እኔም ትግሬ ነኝ” በሚል ርዕስ የጻፉትን አንብቤዉ እጅግ ደስ አለኝ።
ቢሆንም ትናንትና አንዱን ሰሌዳ ላይ ስጎበኝ EEDN በሚባል ዝግ የዉይይት መድረክ ላይ ርዕሱን በሚመለከት ሁለት ጸሃፍት የተቹትን ቀና ትችት ያሰፈሩትን እና አንድ በክዳት ዓለም የዋኘ ግንፍል ሰዉ ያቶ በልጂግ አሊን ማሳሰቢያ አነበብኩ።የEEDN(ኑ) አንደኛዉ ተቺ ገንቢ ሆኖ ባገኘዉም መታረም ያለበት ብለዉ የተቹበት የአቶ በልጂግ አሊን “እኔም ትግሬ ነኝ” በ“እኔም ኢትዮጵያዊ ነኝ” የመተካት ርዕስ፡ ፈረንጆቹ hypcrit የሚሉት አተቻቸት ሆኖ አግንቸዋለሁ።
ጸሃፊዉ አቶ በልጂግ አሊ “እኔም ትግሬ ነኝ” ያሉበት ምክንያት የEEDN-(ኑ)ተቺ የገባቸዉ አልመሰለኝም። ብዙ ተቺዎች እንደሚስማሙት ብዝዎቻችን የኢትዮጵያ ቅድስና ክብር እየሸሸን ወያኔዎቹም ሲወርድ ሲዋረድ የተላለፈልንን የየአንድነት ጸጋችንን እየገፈፉት መሄዳቸዉ ለዓመታት ተተችቶበታል። የአንድነት ስሜታችን፤ ኢትዮጵያዊነታችን እየፈረሰ እኛ ኢትዮጵያዊያን ወደ ሃድያ ፤ትግሬ ፤አማራ ዓፋር አኝዋክ……..ሆነናል። ይሄ መሆን አላስጣልም፡ ነገር ግን ኢትዮጵያዊነታችን እያስጣሉን እንደመጡ ግልጽ ነዉ(የጣልያኖቹ ፖለቲካን ያጤነዋል)። የማንነተቻን የአንድነታችን ክር ወደ ዉድመቱ እያቀና ያም መሆኑን ስላየን ነበር ሁላችነን በትግሉ ተሰልፈን ዛሬ እየጮህን ያለነዉ። ያለ በለዚያማ የሚያስጮኸን ምክንያትም አልነበረንም።
የአማራ ገበሬ ኦሮሞዎች በሚኖሩበት አካባቢ ለዘመናት ከኖሩበት ቀዮአቸዉና መንደሮቻቸዉ በዘረኞች/ በኢትዮጵያ ናዚዎች በእሳት ጋይተዉ በሺዎቹ ተገድለዋል። ህጻናት በትምርተ ገበታቸዉ እንዳሉ የ ኦነግ ባንዲራ አወለብልበዉ በመጡ የኦነግ እና የእስልምና አክራሪዎች ተዋጊ ሠራዊቶች (ጦሩን የመሩት ስም ዝርዝራቸዉ ካሁን በፊት ተገልጿል) ያገሪቱን ብሄራዊ ሰንደቃላማ አዉርደዉ በምትኩ የነሱን ሰቅለዉ ህጻናቱ ክክፍላቸዉ ዉስጥ ዘግተዉ እሳት ለቅቀዉ እንደፈጅዋቸዉ የተዘገበ ነዉ። ወንጀሉ ዛሬም እየጮኸ ፍት የፍትህ ያለህ ይላል። ኢትዮጵያዊያን ምሁራንና ጠበቃዎቹ “ከእጅ አይሻል ዶማ” ስለሆኑ የንጹሃኑ ደም ዛሬም ከኢትዮጵያ ሰማይ ሆኖ ወደ ምድሪቱ ይጮሃል። የወንጀሉ ገጽታ “ናዚዎች ባይሁዶች” ላይ “አስራኤሎች በፍልሰቲኖች” ላይ ያደረሱት ጭካኔ አይተናነስም። ዛሬም “ትግሬዉንና የአማራዉን ቆዳ ገፍፈን የዉሃ ስልቻ/መያዣ እናደርገዋለን” የሚሉ ድምጻቹ በየፓል ቶኩ ተቀድተዉ “በ ኢትዮ-ላዮን ዳት ካም” ሰሌዳ ላይ ተለጥፎ ለሕዝብ ተላልፋል። ዛሬም “ኢትዮጵያን ካረንት አፈይርስ ዲስካሽን ፎረም" እያለ ራሱን የሚጠራ ጸረ ትገሬዎች የተሰበሰቡበት ጋጠወጦች የሚፈለፈሉበት የፓል ቶክ መድረክ” ጸረ ትገሬ ፕሮፖጋንዳ ፤ስድበ እና ክርክር እየተካሄደ መሆኑን እየተከታተልነዉ እና ቅጁም ካሁን በፊት ይፋ ለሕዝብ እንደተላለፈ ይታወሳል።
ካሁን በፊት በበደኖ፤ በአርሲ ወዘተ… የተደረጉ የዘረኝነት የጭካኔ ክስተቶችና ባሕሪዎች ከናዚዎችና የአይሁዶች ጭካኔነት “ፓራለል” (ንጽጽር) ማድረግ አይቻልም እያሉ የጸጉር ስንጠቃ አካዳሚ ጨዋታ ትችታቸዉን ለብዙዎች ኢትዮጵያዊን “ሂፕከሪቶች” እያዩ የታወሩ እያነበቡ የማያነብቡ ዕዉራን ናቸዉና ሁኔታዉ አልታያቸዉም። ለዚህም ነበር የ“ኢኢዲኤኑ” ተቺዎች 5 ሚሊዮን አይሁዶች በናዚዎች ስለተገደሉ ኢትዮጵያ ዉስጥ ያን ያህል ቁጥር የለም አይሞትም እያሉ የቁጥር አንጂ የጭካነዉ የጥላቻዉ መረን “ወደዛዉ ወደ ናዚዎቹ እና ወደ ሩዋንዳዉ ቅትለት ሊያመራ እንደሚችል” የተጠቆመዉን የአቶ በልጂግ አሊ ትምርታዊ “ማስጠንቀቅያ” ማናናቅ ብቻ ሳይሆን ጭራሽኑ አንዳንዱማ ለኛ “ግልጽ” በሆነ ምክንያት ላንዳዶቻችሁ ላይገባችሁ ይችል ይሆናል፦በሚከተለዉ የመከላከሉ ሽፋን (ዲናያል)-መልዕክቱ እንደሚከተለዉ አንድ አስገራሚ ፍጡር አንዲህ ሲል በዛዉ በኢኢዲ ኤን” መድረክ ለሃጩን ሲአዝረከርክ ይሄዉ፦
“if he/she can tell me the difference between the Meles Zenawi “ Interhamway” and the “ Enem Tigre Negn” messages. To me both messengers have one thing in common which is to fabricate things and also to divide people as they have been doing for so long”. ከዚህ አጻጻፍ ማንነቱን መገመት በጣም ቀላል ነዉ። ከየትኛዉ ፓል ቶክ እና ከየትኛዉ የፖለቲካ ቁርኝት እንዳለዉ ያጣችሁት አይመስለኝም።የአቶ በልጂግ አሊን ምክር እና መስጠንቀቂያ ከመለስ ጋር ማነጻጸር ወይንም ጭራሽኑ ቢገትሪ/ጸረ ትግሬነት ዘመቻ አያደገ አልሄደም “ፈጠራ ነዉ”-የሚለን ወንድማችን “ግልቡጦሽ” የሚባል የኛ የትግሬዎች ጨዋታ እተጫወተ ይመስለኛል። ጭንቅላትህ መሬት ላይ ተክለህ አግርህ ሽቅብ ሲመለከት ዓይንህ የሚያየዉ የማየት ሃይልን የሚፈትን ጨዋታ ላይ ሆኖ ነዉ የጫዋታዉ ጽሁፍ የጻፈዉ። ወንድማችን “ከግልብጦቹ” አንዱ” ነዉና አቶ በልጂግ አሊን ያያቸዉ በዛዉ “በጉልቡጥ ዓይኑ” ነበር። ግልቡጥየዉ ከጉልብጦቹ ጋር አቆይተን፡ ወደ ሌላዉ ቀናዉ ትችት ነገር ግን “ሂፕክሪት” ወደ ሆነዉ “እኔም ትግሬ ነኝ” ወደ “አኔም ኢትዮጵያዊ ኘኝ” ቢሆን ኖሮ ሸጋ ነበር ሚሉትን ወደ ሌሎች አቃቂረኞች እንመልከት።
ካዘ በፊት ግን አንድ ነገር ልበል።ሁሌም የማከብራቸዉ ወንድሜ አቶ አበራ ሲሳይ አቶ በልጂግ አሊን በመደገፍ “ትግሬዎችን ጥላቻ እያደገ መሄድ “የፈጠራ ጽሁፍ” በማለት አቶ በልጂግ አሊን ከመለስ ዜናዊ ጋር የጨመራቸዉ ከላይ ያየነዉ “ጉልቡጥ” ጸሃፊዉን በጥሩ እንግሊዝናቸዉ አንዲህ ሲሉ ማጠናገራቸዉ ደስ አለኝ። ልጥቀስ ‘Targeting a certain group or organization for political gain is not new but a standard practice to Ethiopian politics. That is what the writer mainly concerned with. The writer supported his case with objective facts. It is up to you to disprove it. Your problem, I surmise is rather the author not the essence of the article. በጅ! አደረጉልኝ የጥንቱ የጥዋቱ ወንድሜ አቶ አበራ ሲሳይ።
አሁን ወደ ሌላኛዉ ተቺት እናምራ። “እኔ “ኢትዮጵያዊ ነኝ” መሆን ነበረበት ያሉት ተቺ- ከ “እኔም ትግሬ ነኝ” የሚለየዉ ትግሬዎች ላልሆኑ ኢትዮጵአዊያን የተላለፈዉን መልክት የተምታታባቸዉ መሰለኝ። እነዲህ ይላሉ “The author has forgotten the development of seventeen years of self isolations of ‘ Tigrewoch’ in the Diaspora. Let us face the truth and place the blames where they belong. The ‘ Tigrewoch’ left the Ethiopian Halls in every city around the world and established their own ‘ Tigrewoch’ halls and effectively separated themselves from the rest of the Ethiopians. They minded their own businesses and their existences separate from the others. They developed their own issues and concerns, and initiated new development different from the rest of the Ethiopians. Their ideas about democracy and development in Ethiopia became different from the rest of Ethiopians. They participated in no human rights issues and other national issues along with the Ethiopians. They invented different perspectives about democracy and how government should be formed democratically in Ethiopia different from the rest of the Ethiopians. The blame must not be against those innocent ‘ Tigrewoch’ but those few leaders who led the good Ethiopians in that direction. Those who orchestrate the rejection of ‘ Tigrewoch’ from the rest of their fellow Ethiopians must be condemned and crashed. They are no less destructive than TPLF. The innocent ‘ Tigrewoch’ must not be blamed, but they must be guided by the principles and philosophy that made Ethiopians one people and one indivisible nation. Ethiopians individually or in groups must think of uniting the Ethiopians where ever they are and reestablish its land and inhabitants the way they have been for centuries. The author should begin to fight by joining the forces that would bring down to the ground the notion and the system of ‘ KILIL’ . The author should also teach and show his fellow country people that self-isolation is destructive and must advocate and encourage people to rejoin the halls of Ethiopians every where in every city around the world. He should rewrite ‘ enem Tigre negn’ to read ‘ enem Ethiopiawi negn’ .“እኔም ኢትዮጵያ ነኝ” ማለት የነበረባቸዉ ራሳቸዉን ላገለሉ “ትግሬዎች” መሆን ነበረበት ይላሉ ከተቺዉ እንደተረዳሁት ።
ሁለቱም አባባል በጣም ይለያሉ። አቶ በልጂግ አሊን ያሳሰባቸዉ የኔን ኢትዮጵያዊነት መካድ አለመካድ ሳይሆን ወይንም ራሳቸዉን ያገለሉ ኢትዮጵአዊን/ት ትግሬዎች ወደ ኢትዮጵያዊነት የመምጣቱ ጉዳይ ሳይሆን እየተቹት ያሉ፡ የመልዕክታቸዉ ዋና “ስጋት“በ ኢትዮጵያዊነት ስም”-ባንዳንድ ጋጠወጥ የሞሉበት ፓል-ቶክ መድረኮች የሚፎክሩት ፎካሪዎች- ከትግራይ ሕዝብ ይልቅ ልዩ የላቀ ኢትዮጵያነት ያላቸዉ የመሰላቸዉ ተቆርቋሪ ኢትዮጵያዊያን/ት ነን ባዮች ሌሎች (ከትግሬዎች ዉጭ የሆኑ) ኢትዮጵአዊያን “የትግራይ ሕዝብን”-እደግመዋለሁ “የትግራይ ሕዝብን”ለመጨፍጨፍ፤ለማሳለቅ፤ለማሸነፍ፤ለማንበርከክ፤ ለማሳደድ፤ “ንምጽናት” (ትግርኛ ትርጉሙ ethnic cleansing) ዘርን ለማጥፋት ግድያ ለመፈጸም፤ቤቶች እና ንበረቶቻቸዉ ለማቃጠል፤ ከሚኖሩበት አካባቢዎች ወደ ትግራይ አንዲጋዙ/እንዲባረሩ የቀሰቀሱ በየፓል ቶኩ ካሁን በፊት ተደምጧል እና (ከሞላ ጎደል አንዳንድ ክስተቶች በግበርም ተደርጓል እና 1991-1992 እና በ1997) ዛሬም “ኢትዮጵያን ካረንት አፈይርስ ዲስካሽን ፎረም እና ባንዳንድ ፓል-ቶኮችም - ጋጠ ወጦች የሕዝብን ክብር ቅዱስና የማያዉቁ ይህንን የዘረኝነት የተላበሰ ዛቻ እና ዘለፋ በትግራይ ህዝብ ላይ እያሰሙ እያደመጥን ስለሆነ፤ ጋጠዎጦቹ በትግራይ ሕዝብ ላይ የሚደረግ ዛቻ እና ዘረኛ ዘለፋ ሁላችንም “ጎረቤትህ ሲታማ ለኔ ብለህ ስማ” ኑዉና እኛም ኢትዮጵያዊያን ስለሆንን ትግሬዎችም (ምንም የማያዉቀዉን የትግራይ ገበሬ አዛዉንት፤ሴቶች ህጻናት ..) ኢትዮጵያዊን የደም አጥንታችን ቁራጮች ስለሆኑ “ጋጠዎጦቹ ልቅ ተለቅቀዉ በየፓልቶኩ ዘረኝነት እንዲረጩ ሲለቀቁ ዛቻዉ እኛኑም ጭምር ስለሚነካ “አኔም ትግሬ ነኝ” ብለን ኩሩዉ የትግራይ የኢትዮጵያ የሃይማኖታችን የፊደላችን ትምርት ፈልሳፊና መሰረት የሆነዉ የትግራይ ሕዝብ ሲነካ በአንድነት ቆመን መከላከል ኢትዮጵያዊ ግዴታ አለብን! ነበር የአቶ በልጂግ አሊ የማያሻማ መልዕክት ያስተላለፉት።ሆኖም አብዛኛዎቹ የአገራችን ሙሁራን “በሂፕክርት ሱስ ናላቸዉ አናዉዞታልና” ይህንን የማያሻማ መልከትና ማስጠንቀቅያ ትግሬዎቹስ ለምን “እኔም ኢትዮጵአዊ ነኝ’-ለምን አይሉም ተብሎ መቀየር ነበረበት ወደ ሚለዉ “ዉዥምብርነት”-መግባቱ በበኩሌ አልወደድኩትም።
የመልክቱ መነጽር ለማየት የታለመዉ ኢላማ ያወላግደዋልና አልወደድኩትም። መልዕክቱ ለትግዎች ሳይሆን አፋቸዉን ዘግተዉ በቸልተኝነት ለሚያዳምጡ ወይንም የፓል-ቶክ ሰሌዳዎች/መድረኮች ለ“ ኢትዮጵያ “ስኪን-ሄዶች” እና “ኩሉክስ- ክላኖች” ደቀመዛሙርት ያለ ሴነሰር-ሺፕ ያለ ቁጥጥር በስመ “ዲሞክራሲ” ለሚለቁዋቸዉና ለተቀሩት አፋቻዉ ዘግተዉ ጀሮአቸዉ ከፍተዉ ለሚያዳምጡ ኢትዮጵአዊያን “ደጎች”ን ነዉ።ኢትዮጵያ ከቶዉንም እንደሩዋንዳ አንደ ጀርመን አትሆንም የሚሉን “ሂፒክሪቶች” የማሰተላልፍላቸዉ መልክት ቢኖር የ1991-1992 የዘር ማጥፋት ታሪክ ዕሪታዉ፤ ቶክሱ እሳቱ ሽብሩ በምድሪቱ የወረዱ እምባዎች የፈሰሱ ደሞች “ብልታቸዉ በሰላ ተቆርጦ ተገድለዉ በሞቱት ዓይነስዉራን በሬሳቸዉ አፍ ላይ ተጎርሶ እንዲታይ የተደረጉት “የትኢትዮጵያዊያን ናዚዎች” ስራ በኢትዮጵያ የታሪክ ማህደር የተመዘገበ ነዉ። ያዉም ትናንትና!ማህደሮቹን ገላብጡ። የስሜት እሩጫ የትም አላደረሰንም። ታሪክን መርምሩ። እያልኩ የትግርኛዉ ምሳሌ “ትማሊ ትማሊ ከይወረደ ጻሕሊ” (የወጡ ሽታ ዛሬም እየሸተተን፤ ያዉም የትናቱ፤ ገና ከምጣዱ ሳይወርድ)ልጥቀስላችሁ።
የዋሃኑ ያገሬ ሰዎች፤ አስከመቸዉ “ነገር”-እየረሳችሁ ልብ ሳትገዙ ትኖሩ ይሆን? መጪዉን አስተዉሉ። ቁስላችን ዘወትር ለማስፋት የሚከጅሉ “ጋጠወጦችን”-በብርቱ ተከታተሉ። እያደጉ እየተበራከቱ አዳዲስ ወጣት “ናዚ ኢትዮጵያዊያን/ት” ወደ ፖለቲካዉ መድረክ ብቅ እያሉ ዛሬም እንዳሉ ካሁኑኑ እየመከርን ነዉ። የናዚ አስተሳሰብ መጸሃፍ ጽፈዉ ለሕትመት እና ለንባብ ያበቁ “ኢትዮያዊያን ናዚዎች” በቅስቀሳቸዉ “ዛሬም የሚኮሩበት”-ተቃዋሚ የፓሎቲካ ድርጅቶችን እየመሩ ናቸዉ።በነሱ ዱካ የሚራመዱ ተናዳፊ ንቦቻቸዉ ደግሞ በየፓልቶኩ የምተዳምጡት አፋቸዉ ምን እያወራ እንደሆነ መታዘብ ነዉ። ይሄን ማን ይረሳዋል? ዴቪድ ድዩኮች አሉን። “ድዩክ’ ለፕረዚዳንትነት ምርጫ ሲቀርብ የክሉክስ ክላን እምነቴን ጥየዋለሁ እያለ በመንገድ ላይ ትንንሽ ህጻናት ተማሪዎች እያስቆመ ግምባራቸዉን እያሻሸ ሲያነጋግር በዘመቻዉ ፕሮፖጋንዳ ማስታወቂያ ቀርቦ እንደነበረ ታስታዉሳላችሁ።
ዛሬም የኛዎቹ ናዚዎች ትልልቁን መድረክ ይዘዋል።የሻዕቢያ እና የወያኔ ትግራይ የጥላቻ የጎሳ ፖለቲካ እኛኑን በምንናዉ ዓይነት የጦርነት/የሞኞች የመተላለቅ እልቂት አስገብቶ ከ70,000 ከሰባ ሺህ በላይ ሕይወት እንደበላ መጻህፈትና ጋዜጦች ስለ ህዝቦች ምን ይሳደቡ እንደነበር፤ ድረ ገጾች በጦሩነቱ ጊዜ ምን ይሉ እነደነበር፤ የኢሳያስ አይሮፕላን መቀሌ ላይ በህጻናት ላይ የፈጸመዉ የናዚ የፋሺስቶች ስራ ከመቸዉ ተረሳ እና ነዉ በኛም አገር አይደረግም ተብሎ ክርክር ዉስጥ የተገባዉ?-ከመቼዉ ረሳችሁት?-ከናዚዎች ባሕሪ የተሻልነዉን የዛሬዉ ምልክታችን በምንኛችን ነዉ? የኦርቶዶክስ ሃይማኖት የሕዝበብ ጠላት ነዉ እያሉ የሞሶሎኒ ቅስቀሳ የሚያካሂዱ የሚጽፉ የሚናገሩ የዘረኞች ድርጅት መሪዎች በሰላም አየር ጥላቻን ሲነዙ በምንሰማበት ምድር? አይፈጸምም! ብሎ ምክርን ማጥላላት “ደግነት” ይመስለኛል።
በመጨረሻም በዛዉ በኢትየጵያን ካረንት አፌይርስ በተባለዉ የጋጠወጦች እና ጸረ ትግሬ ፕሮፖጋንዳ በሚለቀቅበት ልቅ መድረክ ላይ ታዋቂዉ ጋዜጠኛዉና የጋዜጠኞች ማህበር ተጠሪ “አቶ ክፍሌ ሙላት” ለቃለ መጠይቅ ይቀርባሉ ተብሎ እየተወራ ስላላ አቶ ክፍሌ ሙላት በዚህ አጋጣሚ የጋጠወጦችንና የጸረ ትግሬ መድረኮችን የመኮነን ሃለፊነት አለባቸዉና መድረኩን ላለማክበር “ቦይኮት” እንዲያደርጉ ጥሪየን አቀርባለሁ። አምላክ ኢትዮጵያን ይጠብቅ www.ethiopiansemay.blogspot.com