Friday, October 2, 2009

ባርናባስ ገብረአብ እና በጋምቤላ ዘር የማጽዳት ዘመቻ

ባርናባስ ገብረአብ እና በጋምቤላ ዘር የማጽዳት ዘመቻ (ከወያኔ ገበና ማሕደር) ጌታቸዉ ረዳ www.Ethiopiansemay.blogspot.com
በጋምቤላ ዉስጥ የዘር ግጭት ሲካሄድ የወያኔ የፌዴራል ምክትል ሚኒስትር የነበረዉ ዶ/ር በርናባስ ገብረአብ ለአሜሪካ ድምፅ ራዲዬ የትግርኛዉ ክፍል ባልደረባ የሆነዉ በትረሥልጣን በወቅቱ ባርናባስን አነጋግሮ ነበር፣፣ ባርናባስ በቃለ መጠይቁ እንዳመነዉ በግጭቱ ለተከተለዉ ጉዳት “የፖለቲካ ተጠያቂዎች ነን” ፣ “ከፖለቲካ ተጠያቂነት ማምለጥ እንዴት ይቻለናል” በማለት “የሕግ ተጠያቂዎች” ባንሆንም በፖለቲካችን ምክንያት ለተከተለዉ እልቂት ተጠያቂዎች ነን ያለበትን ቃለ መጠይቅ ስታነብቡ፣ የርናባስ “ሂፕክርት” (ዞር አሉ አልሸሹም) የፖለቲካ እና የሕግ ተጠያቂነት ለያይቶ ማየቱ ፍርዱ የሕግ ባለሞያዎች እና ለእናንተ ለአንባቢዎች በመተዉ ቃለ ሙሉዊን ቃለ መጠይቁ ከትግርኛ ወደ አማርኛ የተረጎምኩላችሁ “የመልካም አስተዳደር እና በልማት ወደ ሗላ መቅረት “ለዘር ግጭት” ሰበብ እንደሚጋለጥ እና እንዲሁም ‘ግጭቱ ፍንጭ ሲያሳይ የፌደራል ባለሥልጣኖች “ፈጠን ብለን መልስ አልሰጠንበትም” ያለበትን፣ እና እልቂቱ ከተፈጸመ በሗላ እራሱ እስፍራዉ ድረስ በመሄድ “ሕዝቡን ሰብስቦ ይቅርታ እንደጠየቀ” ያመነበትን ቃለ መጠይቅ እነሆ፣- አሜሪካ ድምጽ ራዲዬ፣- ደ/ር በርናባስ ገብረብ ጥርያችንን አክብረዉ ስለመጡ አመሰግናለሁ፣፣ ደ/ር በርናባስ በቅርቡ በጋምቤላ የተከሰተዉ የሕዝብ ግጭት መነሻዉ ምን እንደሆነ እና ሁኔታዉ እምን ደረጃ ላይ እንዳለ ቢገልጹልኝ? ደ/ር በርናባስ ገብረአብ - በዚህ በታሕሳስ ወር በጣም አስከፊ የሆነ ግጭት አጋጥሞ ነበር፣፣ ብዙ ሰዉ ሞቷል እስከ 74 የሚሆኑ ቁስለኞችም አሉ፣፣ (ተጎጂዎቹም) ከአኙዋ የተባሉ ብሔረስብ ተወላጆች ናቸዉ፣፣ አጥቂዎቹ ደግሞ በክልሉ ዉስጥ የሚኖሩ የደጋ (Highlanders) ሰዎች ናቸዉ፣፣ ሃቁ ይሄ ነዉ፣፣ ሁኔታዉ ይሄ ነዉ፣፣ ነገር ግን ሁኔታዉ እንዴት ብለን ለማየት ብንሞክር “ይቺኛዋ ለብቻዋ”ተነጥላ መታየት የለባትም፣፣ በክልሉ በአንዋር እና በአኙዋ (ክ) ብሔረሰብ ግጭቶች ነበሩ፣፣ በዚህ ምክንያት ሰፋ ያለ መድረክ ከፍተን ጠለቅ ያሉ ዉይይቶች እንዲካሄዱ አድርገን ሁኔታዉ እንዲበርድ አደርገን ነበር፣፣ በወቅቱ በዉጤቱ ያገኛናት (የታየዉ) ሰላም ተጠቅመን ክልሉን ወደ ልማት እንዲሸጋገር አላደረግንም፣፣ ዋነኛዉ ለግጭቱ መነሻ የሆነዉ ምክንያት፣ በአንድ በኩል “መልካም አስተዳደር” ያለ መኖር ያመጣዉ የሗላ ቀርነት ችግር ነዉ የመሰረቱ የግጭቱ ምክንያት፣፣ ነገር ግን የታየዉ “ጊዜያዊ” ግጭት መነሻዉ ግን የትምክህት ስሜት ባደረባቸዉ በደገኛዉ ትምክህተኛ እና በንፁሃን የአኝዋኮች ኗሪዎች መካከል ነበር የታየዉ የግጭቱ መነሻ፣፣ ጥያቄ፣- እነኚያ “ደገኞች” እያሏዋቸዉ ያሉት እነማን ናቸዉ?
ባርናባስ፣- ከክልልዩ ብሔረሰብ ተወላጅ ዉጭ የሆነዉ ክፍል ማለት ነዉ፣፣ ከኦሮሚያ እንዲሁም ከትግራይ ሁሉ ሳይቀር በሰፈራ ወደ እዛዉ ክልል ተሰድደዉ ሄደዉ የሚኖሩ ሞልቷል፣፣ ወደ ክልሉ በስራ ምክንያት ተቀጥረዉ የሚሰሩ “ሲቪል ሰርቪስ”-ሰራተኞች ሞልቷል፣፣ሆን ብለዉ ፕሮቮከሺን/የግጭት ቁስቆሳ እንዲነሳ ጥረዋል፣፣ በግድያዉ ተሳተፉ የክልሉ ፖሊሶች ሁሉ ሳይቀር፣ ምመህራን ሁሉ አሉበት፣፣ እንዲሁም የከተማዉ ዱርየዎችና የቀን ተቀን የጉልበት ሰራተኞች ሳይቀሩ እነዚህ ሁሉ የተሳተፉበት ስብስብ ነዉ፣፣ “ክብሪት”-በመያዝ የኗሪዎችን ቤቶች በእሳት እያቃጠሉ ሰዉ ሲገድሉ ነዉ የዋሉት፣፣ ጥያቄ፣-
በዚህ ዓመት በተደጋጋሚ የሕዝብ ግጭት የታየበት ሁኔታ ታይቷል፣፣ በዚህ ተደጋጋሚ ግጭት ለ
ምሳሌ አይሪን የተባለዉ የዜና ስርጭት ስለጉዳዩ አስመልክቶ ሲተነትን ባለፈዉ ጊዜ ግጭትን የሚያስነሱ ክስተተቶች ታይተዉ እንደነበርና የኢትዬጵያ መንግሥትም ይህንን ተገንዝቦ በወቅቱ ሁኔታዉን ተከታትሎ በወቅቱ ፈጠን ብሎ እንዲታገስ ባለማድረጉ አሁን (በታሕሳስ ወር) ለታየዉ አስከፊ ግጭት እንዲከሰት ሆኗል፣ ስለሆነም መንግስት ለአካባቢዉ ሕዝብ ይቅርታ ጠይቋል የሚል ዜና አለ፣- እዉነት ነዉ? ባርናባስ፣- እነኛ ምልክቶች ነበሩ ወይ? አዎ፣፣ ሃቅ ነዉ፣፣ የተወሰኑ በክልሉ ዉስጥ ለደርግ ሲያገለግሉ የነበሩ የክልሉ የአኙዋክ ብሔረሰብ ተወላጆች፣ ከፖሊስ ከአየር ሃይል የተባረሩ “የጠባብ ቡድኖች” አባሎች አሉ፣፣ እነኚህ ሆን ብለዉ በደገኛዉ እና በክልሉ ተወላጅ ብሔረሰቦች መካከል ጠብ እንዲፈጠር በማለም የኮንስተራክሽን ሰራተኞች፣ የህክምና ባለሞያተኞች ሳይቀር “ገድለዋል”፣፣ ሆን ብለዉ ግጭት እንዲነሳ ያደረጉት ጉዳይ እንደነበር እናዉቃለን፣፣ እንግዲህ “ምልክት ታይቶ”ነበር እየተባለዉ ያለዉ “ያቺዉ”ናት፣፣ ፌደራል መንግሥትም ሁኔታዉ ሲታይ ፈጠን ብሎ መልስ አልሰጠበትም፣፣ እኔዉ ራሴ ሄጄ (በድርጊቱ)የተጠቁትን ሰዎች ሰብስቤ “ይቅርታ ጠይቄአቸዋለሁ”፣፣ ጥያቄ፣- ይቅርታ ጠይቀናል ማለት “ተጠያቂዎች ነን” ማለት ነዉ? ባርናባስ፣- ፖለቲካሊ?
ጠያቂ፣- አዎ፣
ባርናባስ፣-
አዎ፣ ግጭቱ አስቀድመን ብንገታዉ ኖሮ መልካም ነበር፣፣ ነግር ግን (አላደረግንም)፣ ስለዚህ ማንኛዉም ዓይነት የህዝብ ችግር ሲያጋጥም ከተጠያቂነት እንዴት ነፃ እንሆናለን? ጥያቄ፣- ይህ ማለት፣-ለጠፋዉ ንብረትም ይሁን የሰዉ ሕይወት ለተጠቃዉ ሕብረተሰብ የገንዘብ ካሳ ሊከፍል ነዉ ማለት ነዉ? ባርናባስ፣- የፖለቲካ ተጠያቂነት አለ (በፖለቲካዉ ያስጠይቀናል)፣፣ይህ ማለትም፣ ማንኛዉም የልማት ፣የመልካም አስተዳደር ጉድሎቶችን በሚመለከከት እኛ እሥልጣን ላይ ያለነዉ ስልጣን የተሰጠን ሰዎች ፣ ባለሥልጣኖች ሃላፊነት እንወስዳለን ማለት ፖለቲካዊ ተጠያቂነት አለን ማለት ነዉ፣፣ ይሄ ፖለቲካዊ ተጠያቂነት ይባላል፣፣ ነግር ግን ሰዉ ሲገድሉ የዋሉት እና የኗሪዎችን መኖርያ ቤቶችን በእሳት ሲያጋዩ የዋሉት ደግሞ በሕግ ተይዘዉ ወደ ፍርድ ቤት ሊቀርቡ ነዉ፣፣ እኛ እያልን ያለነዉ “መልካም አስተዳደር እና ልማት” ለማጠናከር የቆምን ሰዎች ላለፉት 12 ዓመታት ለአካባቢዉ ትርጉም ያለዉ የአስተዳደር ለዉጥ ስላላመጣን ከተጠያቂነት እንዴት ነጻ መዉጣት እንችላለን? ጥያቄ፣- ዶ/ር ባርናባስ (እርስዎ) ሲገልጹ (በግጭቱ) 60 ሰዎች እንደተገደሉ ነዉ የገለጹልኝ፣፣ ሆኖም በተባበሩት መንግሥታት የዜና ማዕከል አስተላለፈዉ ዘገባ ግን እስከ ሁለት መቶ ሰዎች እንደተገደሉ ነዉ የገለጸዉ፣፣ የትኛዉ ቁጥር ነዉ ትክክለኛዉ? ባርናባስ፣- መንግሥት እና እኛም አባሎች በተገኘንበት ከተጠቂዎቹ ጠይቆ አረጋግጦ ያጣራዉ 56-ሰዎች ብቻ ናቸዉ የተገደሉት፣፣ ነገር ግን …-ተሳስተናል እንበል እና ወደ 60 ሰዎች ተገድለዋል እንበል፣ ነገር ግን “ሁለት መቶ”-ብቻ ሳይሆን እዚህ አገር ዉስጥም ቢሆን “ሦስት መቶ”ሰዎች ናቸዉ የተገደሉት ብለዉ አደል የዘገቡት?!ያ ግን ዝም ብሎ ከጭብጥ የተናሳ ዘገባ ሳይሆን እንዲሁ ነዉ፣፣ ለምን ዓላማ እንደተዘገበም አይገባንም፣ ዓላማዉ የኢትዬጵያ መንግሥት ለመወንጀል እና ስም ለማጥፋት የተደረገ ነዉ፣፣ ጥያቄ.- በቅርቡ በአሜሪካ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያወጣዉ መግለጫ የኢትዬጵያ ሠራዊት ግጭቱ ዉስጥ እጁ አስገብቷል የሚል…… ባርናባስ ፣- ልክ አይደለም! ምክንያቱም እኛ ይህ አሉባልታ እንደሰማን ሕዝብ ሰብስበን በተለይም ተጠቂዉን ክፍል አነጋግረናል፣፣ ሕዝቡ የነገረን ሠራዊት ባይኖር ኖሮማ ከተማዋ እንዳለች ትቃጠል ነበር፣ በከተማዉ ዉስጥም ቆሞ የሚሄድ ፍጡር ባልተገኘ ነበር፣፣ የርዋንዳዉን ዓይነት ሁኔታም ይከሰት ነበር፣፣ስለዚህ ሠራዊት ነዉ ያቆመዉ፣፣ ሌላዉ “የኢትዬጵያ ሠራዊት የሚባል”ነገር የፌደራል ፖሊስ እንጂ የፌደራል መከላከያ እዛ አካባቢ አልነበረም፣፣ ፖሊስ ግን በተለይ “ደገኛዉ ፖሊስ” በግድያ የተሰማሩ ነበሩ፣፣ ሕዝቡ እከሌ እነ እከሌ ሰዉ ሲገድሉ ነበሩ ብለዉ ጠቁመዉ ያስያዟቸዉ የተያዙ ፖሊሶች አሉ፣፣ ጥያቄ፣- የፀጥታ ስጋት በአካባቢዉ እንዳለ እና በተለይም የነዳጅ ፍለጋ በሚካሄድበት አካባቢ ይህ ግጭት አሁንም እንደቀጠለ እና እንዳላቆመ ይነገራል፣፣ ሠራዊት ሰላም ለማስከበር ወደ አካባቢዉ ተሰማርቷል ካሉኝ አሁን ያለዉ የግጭት እንዴት ነዉ የቀጣይነት ክፍተት ዕድል ሊያገኝ የቻለዉ? ባርናባስ፣- አይደለም፣፣ እንዴት መሰለህ፣-ነዳጅ ፍለጋ ሚካሄድበት አካባቢ የግጭት አካባቢ አይደለም፣፣ ያዉም በማነጻጸር “የተረጋጋ” አካባቢ ነዉ፣፣ የታጠቁ ሰዎች አሉ ብየህ ነበር፣- እነኚህ የታተቁ ክፍሎች በአካባቢዉ አሉ፣፣ በአካባቢዉ ዉር ዉር የሚል ጥቂት የታጠቀ ጥቂት የሽፍታ ቡድን ይኖራል፣ በረሃ ስለሆነም ለማስወገድ “ዕንቅፋት”አይሆንም፣፣ እሱ ደግሞ ይጠረጋል /ይመታል፣፣ ሰረዊቱ ስራዉን ባጭር ጊዜ አጠናቅቆ ሰላም እንደሚያሰፍን ተስፋ እናደርጋለን፣፣ ጥያቄ፣- ፀረ መንግሥት የሚንቀሳቀሱ የታጠቁ ሽፍቶች አሉ ነዉ የሚሉኝ? ባርናባስ፣- የኛ ሳይሆኑ የወጭ ሃይላት በአካባቢዉ እንዳሉ ታዉቃለህ፣፣ ስማቸዉ ሳንጠቅስ ማለት ነዉ፣፣ ጠያቂ፣- የለም ስማቸዉ ቢገልጹልኝ ደስ ይለኛል፣፣ ባርናባስ፣- ያዉ የታወቁ ናቸዉ እኮ! የደቡብ ሱዳን ታጣቂ ክፍሎች ለምሳሌ አሉ፣፣ በተለያዩ ከተሞች የግድያ ተግባር ያከናዉን ነበር ብየ ያልኩህ አስቀድሜ- እዚያዉ አለ፣፣ያ ካልተወገደ ስጋት እያልክ የጠቀስከዉ ሊኖር ነዉ፣፣ እሱ አለ፣፣ ከጋምቤላ ወደ ታች ወደ ደቡብ ህዝቦች እስከ 300 ኪ.ሜ. አካባቢ ደርሼ መጥቻለሁ፣፣ ግን ዲማ ዲሎ ፣ አቆቦ፣ ዶር የሚባሉ በረሃዎች አሉ፣፣ በዛ በረሃ “ተሸሰሽጎ” አዩኝ አላዩኝ እያለ በስጋት የሚሽሎኮሎክ ቡድን አይታጣም፣፣ እሱም ደግሞ ትንሽ የጥፊ ዓይነት ግራ ቀኝ አጠናግረህ “መታ-መታ” አድርገህ መቆጣጠር ይቻልል፣፣ ጥየቄ፣- ጋምቤለ ባሁኑ ሁኔታ ጸጥታዋ በእንዴት ዓይነት ሁኔታ ይገኛል? ባርናባስ፣- ሙሉ በሙሉ መረጋጋት አለ ልልህ አልችልም፣፣ አስተማማኝ ሰላም እንዲሰፍን ግን ቀጣይ የሆነ ሰራዎች ተዘጋጅተዋል፣፣ ጥያቄ፣- ሌሎች ማለትም ከአካባቢዉ ኗሪዎች ሌሎች ማለትም እንደ ትግርኛ እና አማርኛ ቋንቋ ተናጋሪ ሕብረተሰቦች ሲኖሩበት ከነበረዉ አከባቢ እየተገደዱ በግድ እየተባረሩ እንደሆነ ምንጮች ይገልጻሉ፣፣ የእነዚህ ዜጎች ደህንነት ለማረጋገጥ መንግሥት ምን እርምጃ እየወሰደ ነዉ? ባርናባስ፣- አቀስቀድሜ የጠቀሰኩት የሽፍቶች ቡድን በእነዚህ ክፍሎች አይደል ታርጌቱ (ንጥጥሩ)?፣- እንግዲህ በአቦቦ አካባቢ “ፍኝዶ” የምትባል አንዲት መንደርም አቃጥሏል፣፣ ትግሬዎች እና አማራዎች ብቻ ሳይሆን ማንም ኢትዬጵያዊ ዜጋ ጋምቤላ ያልሆነዉን ሁሉ ነዉ ጥቃቱን ያነጣጠረዉ፣፣ አሁን ሁኔታዉ ተረጋግቶ ኗሪዎቹ ወደ እየ ሰፈራቸዉ መመለስ ጀምረዋል፣፣ እኔ ከጋምቤላ ከተመለስኩ ሳምንት ሆኖኛል፣፣ በየቀኑም ኢንፎርመሺን (መረጃዎች) ይነግሩኛል፣፣ ጥያቄ፣- በሺዎቹ የሚቆጠሩ አኝዋኮች ድምበር ተሻግረዉ ወደ ሱዳን እንደተጠለሉ ነዉ እየተነገረ ያለዉ፣፣ ደቡብ ሱዳን እንደሚባለዉ የተረጋጋ አይደለም፣ - ሆኖም ከኢትዮጵያ የተሻለ ደህንነት ስለሚሰማቸዉ ሆኖ ነዉ ወደ ሱዳን ለመጠለል የፈለጉት? እነኚህ ሰዎች በስደት ሊኖሩ ነዉ ወይስ የኢትዬጵያ መንግሥት ሊደርስላቸዉ ነዉ? ባርናባስ፣- ቢሺዎቹ እየተባሉ የሚጠሩት ስደተኞች ሚዲያዎች እንዳሸኛቸዉ አደል ቁጥሩን ከፍ ዝቅ የሚያደርጉት?! እንግዲህ ቁጥሩን በሚመለከት “በሱዳን በኬኒያ” በኩል መረጃዎች አግኝተን ነበር እኛ በአካል ሄደን አልቆጠርናቸዉም - ሆኖም ቢቢሰ 6000 በሏቸዋል በጭብጥ ከቦታዉ ሄደዉ ያረጋገጡ ደግሞ 5000 ናቸዉ፣፣ ያም ቢሆን ቀላል ቁጥር አይደልም፣፣ የምናደርግላቸዉ ነገር እኛ የተሻለ ሰላም እና መረጋገት ፈጥረን ወደ ልማቱ ወደ ሀገሩ እንዲመለስ ነዉ ፍላጎታችን እንጂ እዛ ይኑር አንልም፣፣ ግን መጀመርያ አስተማማኝ ሰላም በአካባቢዉ ማምስፈን ይኖርብናል የሚል እምነት ነዉ ያለኝ፣፣ ጠያቂ’ አመሰግናለሁ ደ/ር ባርናባስ ገብረአብ ገብረአብ፣ እኔም አመሰግናለሁ፣፣ ከኢትዬጵያ ሰማይ- አዘጋጅ -/-ለጋምቤላ ሕዝበ ቆመናል የምትሉ የሕግ ባለሞያዎች፣ ጉዳዩን አስመልክቶ ወቅቱ ጠብቆ ወሳኝ የሕግ ክርክር ማሕደር ሲከፈት ለዘር ማጥፋት ተጠያቂዎች የሚከሰሱ ባለስልጣኖች ስለሚኖሩ ባለሥልታኖቹ ከሚሰጡት እና ከሚጽፏቸዉ ደብዳቤዎች እና ዉሳኔዎች እንዲሁም ለሚዲያ ከሚሰጡት ቃለ መጠይቅ ለክህደታቸዉም ሆነ ለእምነት የመረጃ ምንጮች ስለሚሆኑ የሰብአዊ መብት ተንከባካቢ ተሟጋች ክፍሎች ከዚህ ቃለ መጠይቅ ጠቃሚ መረጃ ስላምታገኙበት ለመጪዉ ጊዜ ለፍረድ ክርክር እንዲጠቅማችሁ መዝግቡት፣፣ ሰነድ ሳይያዝ አፍ አሞርሙሮ ብዕር አሹሎ መጮህ ለተጠቂዉ ክፍል አይፈይድም፣፣ “የወያኔ ገባና ማሕደር” ዝግጅታችን የሚዘግባቸዉ የወያኔ ገበናዎች በየግል ማስታወሻችሁ በመያዝ ተጠቀሙበት፣፣ ፍትሕ ይዘገይ እንደሆን እንጂ መከሰቱ አይቀሬ ነዉና ሁሉም ዜጋ በየግሉ የዘገበዉን እና አነበበዉን እንዲሁም በግል የሚያዉቀዉን የወያኔ ወንጀል እየዘገበ ለታሪክ ማሕደር ማስተላለፍ ይጠበቅበታል እያልን በሚቀጥለዉ ዝግጅት እሰክንገናኝ አማን እንሰንብት፣፣ // http://www.ethiopiansemay.blogspot.com/