Wednesday, September 7, 2022

ኩኩሉ አልነጋም ገና ነው ሌሊቱ! ጥያቄየ ለፋኖዎቹ መሪ ለዘመነ ካሴ ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay 9/7/22

ኩኩሉ አልነጋም ገና ነው ሌሊቱ!

ጥያቄየ ለፋኖዎቹ መሪ ለዘመነ ካሴ

ጌታቸው ረዳ

Ethiopian Semay

9/7/22

ብዙውን ጊዜ ነገሮች ከመሻሻላቸው በፊት በጣም የከፉ ይሆናሉ። ለንጋቱ አበሳሪ ኩኩሉ ባዩ የዶሮ ጪኸት ነው። ደሮ ከኩሉ ካላለ ‘አልነጋም ገና ነው! ሌሊቱ አሁንም ሌሊት ነው፤ ጨለማው እንደተጋገረ ነው ያለው ማለት ነው።

በጽሑፌ ርዕስ የተጠቀምኩት “ኩኩሉ አልነጋም ገና ነው ሌሊቱ” በሻምበል ዮሃንስ አፈወርቅ ተገጥሞ ብዙነነሽ በቀለ የተዜመ በንጉሡ ዘመን ከፍተኛ የፖለቲካ መልዕክት ያስተላለፈ ሙዚቃ ነው።

ዛሬ በዘመነ ዳግማዊ ግራይ አሕመድ እየተመራ ኢትዮጵያን በተለይ ደግሞ አማራውን ለቅስፈት እየዳረገው ያለው ጅማ ያደገው ኦሮሞ ሳይሆን ከኦሮሙማዎቹ በላይ የኦሮሙማ አቀንቃኝ በመሆን የሚንደፋደፈው ኤርትራዊው አበይ አሕመድ ሥልጣን ላይ ወጥቶ የኦሮሙማ ዕቅድ እያሟላ አገሪቷ የወደቀች አገር አድርጓታል። ጥያቄው አማራው ዛሬስ ራሱን ለመከላከል ምን እያደረገ ነው የሚለው መልስ አላገኘም? በኔ ግምግማ ራሱን እንዲከላከልበት ከመቸውም በላይ የታጠቀው ጠመንጃ ተሸክሞ እያደረገበት ነው ያለው ምንድነው ብትሉኝ “ምንም!!!”

ከ16ኘው ክ/ዘመን ሕሊና መውጣት ያልቻሉት ወደ ሰውነት ያላደጉ “እንሰሳ” የሆኑ አረመኔዎቹ አማራዎችን እያረዱ እየበሉና እያባረሩዋቸው ናቸው። ከሞት የተረፉት ከወለጋ የተባረሩት አማራዊት እናት ጥሪ ትዝ ይላችሗል? “እባካችሁ አማራን አድኑ! እባካችሁ አማራን አድኑ!” ትዝ የላችሗል ይህ ድምጽ? ቀላ ያሉ ሻሽ የጠመጠሙ ውብ ቀጭን እናት ናቸው፤ ይህንን ያሉት። ዘንግታችሁት ከሆነ ‘ቪዲዮውን’ ዛሬም ይኼው ለጥፌዋለሁ።

የእኚህ እናት መልዕክት ለማን ነው? ለትግሬው፤ ለኦሮሞው ወይስ ለማን? ለናንተው ለአማራ ወጣቶች ነበር። ታዲያ ምን አደረጋችሁ? ምንም። ይህ ጥያቄ የጠየቅኩት በግምት 30 አመት በላይ ሆኖታል። ዛሬን መልስ አልአገኘም። መልስ ሰጪዎቹ ተብለው የምንጠብቃቸው የአማራ ወጣቶች “ዩ ትዩብ” መድረክ ላይ ሆነው ሲያቅራሩ ፤ አማርኛ ሲያሳምሩ ፤አንዳንዱም የእስክስታ ችሎታቸው ሲያሳዩን እንጂ ፤ወደ አገር ቤት ገብተው ጫካም ሆነ ተራራ ላይ ወጥተው የጥንት የፋኖነት ተግባር በመከተል ‘ወላጆቻቸውና እህቶቻቸውን’ ከሞት ለመታደግ መስዋዕ ለመሆን ዝግጁነታቸውን አላሳዩም። የሚገርመው ደግሞ “እጅግ ጠቃሚ የሆኑ ቀስቃሽ ዶክዩመንቶች/ሰነዶች ሲለጠፉ “ሼር” ማድረግ እንኳ ዳተኞች ናቸው። በጣም የገበዙ ዳተኞች ናቸው። ወደ እኛው ዘመን ልውሰዳችሁ፡ በወጣትነታችን ጠምንጃ ታጥቀን ዛሬ አገሪቷን እየበጠበቷት ባሉት ጠላቶች ላይ ተኩሰናል፤ እሱም እኛ ላይ ተኩሶብናል። የተምቤን ተራሮች የትግራይ በረሃዎች ሥር ምሽግ ቆፍረን ተዋግተነዋል። በጣም የጦፈ፤ ወንድነትን የሚፈታታን ጦርነት ላይ ተካፍያለሁ።ራሴን እያመሰገንኩ አሁንም እኮራለሁ። የዛሬ ወጣቶች ምን ዋጣችሁ?

አገርቤት ስላለው ወጣት ደግሞ እንመልከት፤

ከ30 አመት በላይ ግብረሰዶም እንዲለማመድ የተደረገው ወጣት፤ ከሰው እጅ እና ኪስ ስልክ መንጥቆ የሚሮጥ ፤ የተከበሩ ጀግኖችን ሃውልት የሚያፈርስ፤ ህጻናትን በቢላዋ የሚያርደው፤ ሰው ገድሎ ባደባባይ እንደ ፍየል ዛፍ ላይ ገልብጦ በመስቀል የሚጨፍር “የአራዊቶቹ መንጋ” የሆነው ወጣቱን ኣይደለም እያነሳሁት ያለሁ። ትኩረቴ አብን የሚባለው የፌዘኞች ሰላቢና አስጠቂ የሆነ አማራዊ ድርጅትን አይደለም ። ትኩረቴ ፋኖዎች ላይ ነው።

አማራው ወጣት ምን እያደረገ ነው? በፋኖ መደራጀቱን አውቀናል። ይህ ደግሞ ነብሱን ይማርና ጀ/አሳምነው ጽጌ ያደራጀው ታጣቂ ሃይል ነው። ሰንት ፈተና አልፏል፡ ታስሯል፤ ተገድሏል። ሲገድል ፤ ሲያስር ግን አላየንም። ለምን አፍኖ አያስርም፤ ለምን የብልጽግና አሽከሮችን ገድሎ አያስሸብራቸውም?? ችግሩ ምንድነው ? ጠምንጃ? መሳሪያ እማ ታጥቃችሁታል።

ዘመን ካሴ ፤ ዘመኔ ካሴ እየተባለ ስንት ወራት አለፈው? በመሪነት ተሰይሞ የት ተሰውሮ እንዳለ አይታወቅም። የተስፋ ብርሃን እና ርችት ይተኩሳል ሲባል ስንት ወራት አልፎታል። ዘመኑ እንኳን ጠመንጃ የመታጠቅ ዕድል ገጥሞህ ሳትታጠቅም በቀላሉ የሚያስታጥቅህ ዘመን ነው። የብልግናው ፓርቲ በጠየቀው ቋንቋ ካላነጋገራችሁት ምኑን ታጠቃችሁት?

እንኳን ጫካ ውስጥ በሽምቅ ጠላትን ማስሸበር ቀርቶ ከተማ ውስጥ እንኳ በመንግሥት ተብየው ላይ ሽብር መፍጠር የሚያስችል ሁኔታ በጣም ክፍት ነው። ያውምእንደዛሬው መቸም አመቹ ወቅት የለም። ተራ ሌባው አይደል “መሳርያ ታጥቆ ያዲስ አባባ ከተማን እያስጨነቀ ያለው?” ታዲያ ዘመነ ካሴ ምን ዋጠው?

ለዚህ ጽሑፍ መነሻ የሆነኝ የሚከተለው አስገራሚ አቤቱታ ነው።

ጎንደር ላይ የፋኖ አባሎች ወያኔን ለመውጋት የይለፍ ፈቃድ እንዲሰጣቸው የኦሮሙማው ብልጽግና ለሆነው ወኪል ሲጠይቁት፤ “አይሰጣችሁም፤ አይፈቀድላችሁም” ተብለው ተከለከሉ። እንግዲህ ሕዝባችንን ከሞት እንከላከል ስላሉ የኦሮሙማው መንግሥት ፀረ አማራው “ብአዴን” ወያኔን መውጋት አይፈቀድላችሁም ካላቸው፤ ምርጫው ምን መሆን ነበረበት? ምርጫቸው እምቢ ያላቸውን አካል “በጥይት መድፋት” ነበር መሆን የነበረበት። እነሱ ግን ምን አደረጉ እንደገና ወደ ባሕርዳር ”አቤት” አሉ። እዛም ተከለከሉ።ከዚህ ወዲየስ ወዴት?!!?

እነዚህ ሰዎች ለምን ጫካ ግበተው ፈቃድ ከልካዩ የቅንጦት መኪናውን ይዞ በየገጠሩና አስፋልቱ ሲተላለፍ የደፈጣ ውግያ ከፍቶ በጥይት እንዳይተላለፍ ማድረግና መኪናውን መንጠቅ አንዴት ያቅታቸዋል። ጎዳና ላይ አድፍጠው “አፍነው” በመውሰድ የታሳሪ ልውውጥ ማድረግ አዲስ ትግል መጀመር እንዴት አልተቻላቸውም? እሱ የይልፍ ፈቃድ ከከለከለ ፤ጫካ ገብቶ መንገድ ዘግቶ የይለፍ ፈቃድ አፋኖ እንዲያገኝ ማድረግ እንዴት ያቅታል? አርበኛ መሳፍንት የተባሉት የፋኖ አዛውንት ከወያኔ ጋር 27 አመት ሲታገሉ አሸበሩት አንጂ አላሻበራቸውም። ዛሬ የወልቃይት፤ የጎንደር፤ የወሎ፤ የጎጃምና የሸዋ ወጣት ፋኖዎች ምን ዋጣቸው?

የሽምቅ ርችት ይተኩስ ይሆናል የተባለለት ዘመነ ካሴ “ጫካ” ውስጥ ነው ያለው ተብሏል (እርግጠኛ አይደለሁም) ጫካ ውስጥ ነው እየተባለለት የለው ዘመነ ካሴ ምንም የረባ ስራ ካልሰራ ከተማ ያሉት ፋኖዎች ምን ያድርጉ? ይህ አማራ የሚባለው ምን አዚም ነው የተደገመበት? እንዴት አንድ ወንድ ይታጣ? በታሪክ ለመጻፍም እኮ በጣም የሚያሳፍር ሪኮርድ ነው። ኦሮሞዎቹ ባሕርዳር ድረስ መጥተው አሳምነውን እና ሌሎቹን ሲገድሉና ከዚያም ሲያፍኑ ወጣቶችና ፋኖው ካልተነሳ መቸ ሊነሳ ይችላል?

ከተማ ውስጥ የሚንደፋደፉት የፖሊስ አዛዦች፤ በየፍረድቤቶች የተቀመጡ አስቸጋሪ ዳኞች እና እስር ቤት ሰውን የሚገርፉ ገራፊዎች በየመኖርያ ቤቶቻቸው እና መጠጥ ቤቶች የሚረግጧትን መሬት ማመን አስክያቅታቸው ካላሸበራችኋቸው፡ ያ ካልቻላችሁም ጫካ ገብታችሁ፤ የብአዴን ብልጽግና ተብየው ቡድን በሚተላለፍባቸው የበረሃ መንገዶችና ድልድዮች ስምሪት በማድረግ እንዳይተላለፍ አድርጎ እየፈኑ ማስጨነቅ ካልቻላችሁ ሌላ ምርጫ ምን ይምጥላችሁ? ያውም ጫካ ገብቶም ሆነ ከታማ ውስጥ ለመሸፈት ተቆጣጣሪ የሌለበት አናርኪ የሆነ በጣም ምቹ ጌዜ እኮ ነው? ዘመነ ካሴ ለመሆኑ የት ነው ያለኸው? ሴትዮዋ “እባካችሁ አማራን አድኑ!”” ሲሉ ጠመንጃ ተሸክሞ መሰወርን አይደለም እየጠየቁ ያሉት። እሳቸው የጠየቁት እየገደለን ያለውን መንግሥትና ተላላኪዎቹን ግደሉልን ከዚያ ሌላውን በተራው አሽሸብሩት፡ ነው ዋናው የውቢቷ እናት ለናንተ አማራ ወጣቶች ያቀረቡት የጭንቅ እና ዕንባ አቤቱታ። እንኳን ልትታደጓቸው እናንተንም ራሳችሁ ማትረፍ ሳትችሉ አዲስ አበባ አትገቡም ተብላችሁ፤ ወያኔንም አትወጉም ተብላችሁ እስርቤቶች በአማራ ነገድ ተሞልቷል።

ካገሩ የወጣ ካገሩ እስኪመለስ

ቢጭኑት አህያ ቢጋልቡት ፈረስ

የሚባለው አማራው ከወለጋ ፤ ከሐረር ፤ ከጂማ ፤ ከአርሲ አገርህ አይደለም ተብሎ ቢጭኑት አህያ ቢጋልቡት ፈረስ ሆኖ ቆየ፤ ዛሬ አገሩ በገዛ መንደሩ ውስጥ የሚኖር ጎንደር ፤ጎጃም፤ ሸዋ እና ወሎ ያለው አማራ እንዴት እንዴት ሲሆን “ቢጭኑት አህያ ቢጋልቡት ፈረስ ሆኖ ተገኘ?”

 Ethiopian Semay