አዕምሮአዊና አካላዊ ግርፋት በዘመነ ኦሮሙማ አፓርታድ
ጌታቸው ረዳ
ኢትዮ ሰማይ አዘጋጅ
(Ethio Semay)
11/12/2021
በምርመራ ውስጥ ከአካላዊ ጫና ይልቅ ስነ ልቦናዊ ጫናን መጠቀም እና ኑዛዜን ማግኘት ለዘመናት ሲሰራ ቆይቷል። ተጠርጣሪን ማሰቃየት ብዙ መንገዶች ቢኖሩም፤ ዋናዎቹ በሁለት ዓይነቶች የማሰቃየት ሰልት ሊከፈል ይችላል።
የመጀመሪያው የስነ-ልቦና ማሰቃያ
መሳሪያ ፍርሃት ነው። የማሰቃያው ውጤት ተፈላጊነቱ ተማርማሪው ቢያንስ ፤ ቢያንስ ተመርማሪው አካላዊ ድብደባ እንዳይደርስብኝ በሚል
ከአካላዊ ድብደባ ለመሸሽ ሲል ተመርማሪው በጭንቅ ምጥ ውስጥ ኑዛዜ ለመስጠት ስለሚገደድ መርማሪዎች ሕሊናን የመስጨነቅ ስልት ይጠቀማሉ።
አንድ ምሳሌ ልስጣችሁ። ስለ
ዶስቶይቭስኪ ያነበባችሁ ሰዎች ይህ ታሪክ ታውቁት ይሆናል የሚል እምነት አለኝ። ዶስቶይቭስኪ ሩሲያዊ ልብ ወለድ ደራሲ ነበር። ዶስቶየቭስኪ
በዋነኝነት የሚታወሱ አምስት ገናና ምጽሐፍት አሉት። “ከመሬት በታች
ማስታወሻ፣ ወንጀል እና ቅጣት፣ The Idiot (ደደቡ)፣ Demons እና ካራማዞቭ ወብድማማቾች” የሚባሉ ጽፏል።
ታዲያ እ.ኤ.አ. ታኅሣሥ 22 ቀን 1849 ጥዋት የሩሲያ ደራሲ ፊዮዶር ዶስቶይቭስኪ
ከሌሎች 20 እስረኞች ጋር በአመፅ ጥፋተኛ ናችሁ ተብለው በሞስኮ ከተማ ሴሜኖቭስኪ ወደ ተባለው ሕዝብ የሚሰበሰብበት የባዓል መሰብሰቢያ
አደባባይ ላይ እንዲረሸኑ ተፈርዶባቸው ተወሰዱ። እንዲረሸኑ ውሳኔው መተላለፉን ለማሳወቅ በአንድ ወታደራዊ ጄኔራል የፍርዱ ውሳኔ በአስጨናቂ ዝግታ ተነበበ። ልክ የተኩስ ቡድኑ እንዲተኩስ ትዕዛዝ ሲሰጠው፣
አቅጣቻው እንዲስት በሚያስደነግጥ አስፈሪ በሆነ ተከታታይ የእሩምታ
ቶከስ ተለቀቀ ። ወዲያውኑ የጀነራሉ አንድ ረዳት “ከዛር ኒኮላስ ቀዳማዊ” የታሸገ ወረቀት ይዞ መጣ። ጄኔራሉ በመቻኮል ከፈቶ ይዘቱን አስታወቀ፡ የመረሸኑ
ቅጣት ተሽሮ ወደ ሳይቤሪያ ማሰርያ ቦታ በእስራት እንደተቀየረላቸው ተነገረ። የትዕይነቱ ትወና ሆን ተብሎ የተቀነባበረው
በዛሩ (በንጉሡ) ነበር። እነ ዶስቶይቭስኪ የእሩምታ ጥይቶች በጆሮአቸው ሲያንዣብብ ሲተኮስ ሰምተዋል፡ ደንግጠው ነበርና ‘ቀስ በቀስ’ ሕሊናቸው ሲመለስ “በህይወት እንዳሉ ተገነዘቡ”።
ሆኖም ድንጋጤው ዕድሜ ልክ የሚቆይ እየባነኑ የአእምሮ ጉዳትን ለመፍጠር
የታቀደ የማሰቃያ ስልት ነበር ።
ይህ ከላይ ያየነው በወያኔ
ዘመንም የተደረገ ተመሳሳይ ድርጊት ነበር። በዓብይ አሕመድ ጊዜም ተደርጓል። ደዴሳ ጫካ ተወስደው በድብዳባ እና በተመሳሳይ ሙከራ
የተፈጸመባቸው ሳጅን ደሳለኝ የተባሉ ታሪካቸው ቀርቦ ሁላችንም አንብበን እኔ ፌስ ቡክ እና ድረገጽ ላይ ይገኛል። ሌሎች በኦሮሞ
አካባቢዎች እንዲሁ ተፈጽሟል።
ሌላው የስነልቦና ማሰቃያ መሳሪያ
ተጠርጣሪን “ግራ መጋባት” ነው። ይህ በተለያዩ መንገዶች ሊደረግ ይችላል. የእስራት ሁኔታ ተጠርጣሪው በታሰረበት ክፍል ሆን ተብሎ ‘እርጥብ ፣ ቀዝቃዛ (ወይም አንዳንድ ጊዜ ሆን ተብሎ የተጋነነ
ሙቀት) እስርቤት ክፍሎች ላይ መልቀቅ ፣ ወይንም ብዙ ጊዜ የቀን
ብርሃን መከልከል’። ብርሃን ሳያገኝ ሲቆይ ተመርማሪው ጭለማ ውስጥ ብቻው ወይንም በቡድን ሲዘጋባቸው ፤ እስረኛው “ጊዜው” ረዢም
ስለሚሆንበት በትክክል ለማሰብ በጣም ከባድ ያደርገዋል። በዚህ ላይ ምግብና መጠጥ ከተከለከሉ ወይም በየተወሰነ
ጊዜ ወጣ ገባ በሚል የምግብ አቅርቦት ሲደረግ እስረኞች የበለጠ ‘ግራ’ ይጋባሉ እና ከጊዜ በኋላ በራሳቸው ስብዕና ላይ ሙሉ እምነት
ያጡና “ያለደረጉት ወንጀል አድርጌአለሁ እንዲሉ ይገደዳሉ”።
ይህ በሁለተኛ ደረጃ የጠቀስኩት
የማሰቃያ ስልት በወያኔ ዘመን እና ዛሬ በአብይ አሕመድ “ኦሮሙማ መንግሥት” ተግባራዊ ሆኖ ወንድሜ እና ዘመዶቼ በዚህ ሕሊናን የማስጨነቅ
የምርማራ ስቃይ እያለፉ ነው። ለዚህ ስቃይ የዳረጋቸው የኢንተርሃሙዌው ቡድን ከፍተኛ ተጠያቂ ነው።
ይህ ሁሉ እውን ሆኖ እያለ
ትናንት የወያኔ እልፍኝ አስከልካይ የነበረው ዛሬ ደግሞ የአብይ አሕመድ
“ኩሊ” የሆነው “ወንጀለኛውና በውሸቱ የታወቀው” ዛሬ “የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲኤታ አምባሳደር” ነኝ የሚለው ስልጤው “ሬድዋን
ሁሴን” “በመዲናዋ ሰዎች በማንነታቸው እየታሰሩ ነው በሚል የሚናፈሰው ወሬ ሃሰተኛ ነው” በማለት ወንድሞቻችን እና ዘመዶቻችን ምንም
ወንጀል ሳይገኝባቸው “ትግሬ በመሆናቸው ብቻ” እየተለቀሙ ወደ ማጎርያ እየታጨቁ ከላይ የገልጽኳቸው የህሊና የማሰቃያ ስልት ገብተው
ሲሳቃዩ እያወቅን በነገዱ የታሰረ የለም ሲል “ለዓለም/ ለአልጀዚራ
ሚዲያ ሲዋሽ” ሰምተናል።
ሌላ ቀርቶ ይህ በነገድ ማሰር
የተጀመረው ሁለት ሳምንት በፊት ሳይሆን እስክንድር ነጋ እና በጓደኞቹ
ላይ የተፈጸመ ነው። በዚህ ጥርጥር የለኝም።ብዙዎቹ “አማራ፤ኦርቶዶክስ” ናቸው ተብለው ነው የታሰሩት። ባለፈው ሁለት ሳምንት “ቤቲ”
ከተባለች የኦነግና የጃዋር ተከታይ” ባደረገችለት ቃለ መጠይቅ ዘረኛው እና ዋሾው የአብይ አሕመድ የግል አማካሪና በሳወዲ አምባሳደር የሆነው ኦነጉ “አሚን ጃንዳይ” ይህንኑ ውሸቱን ነበር
ሲዋሽ የሰማችሁት። ስለ አደገኛው ዘረኛ ስለ “አሚን ጃንዳይ የጻፍኳቸው ለላፉት 20 ምናምን አመት ያደረግኩት የማጋለጥ ሰነድ በድረገጼ ማየት ወይንም በሌሎች የለጠፉልኝ ሚዲያዎች በብዛት ታገኛላችሁ። ሰለ አሚን ብዙ ስለጻፍኩ ስለ እርሱ አልተችም::
ዋሾውና በወንጀል ድርጊት ለ27 አመት ሲካፈል የነበረ የመለስ ዜናዊ ተለላኪው
ሬድዋን፡ ግን ዛሬም ሲዋሽ አላፈረም
1) “ሰዎች በማንነታቸው ለእስር ተዳርገዋል የሚል እምነት የለኝም።”
2) “ይህ ተፈጽሞ ከሆነ ግን
በህግ የሚያስጠይቅ ነው።”በማለት ለፕሮፓጋንዳ ፍጆታ
ሲዋሽ ትንሽ ስቅጥጥ አላለም።
በ1ኛ ደረጃ የተጠቀሰው በማንነታቸው
ወንድሞቻችን ታስረዋል። ህ ሃቅ ነው። “ባሕርዳር ውስጥ” ሬድዋን
ለምን ሄዶ አያጣራም? ለምን ይዋሻል?
በ2ኛ ደረጃ የተጠቀሰው የዋሸው
አስመሳይ ውሸት ደግሞ ‘በሕግ የሚያስጠይቅ ነው” ካለ ለምን እኛ
የምንጽፈው ተመለክቶ ወንድሜና ቤተሰቦቼ ወደ ታጎሩበት እስር ቤት ሄዶ፤ የታሰሩትን ፈትቶ፤ ከተፈናቀሉት የቀድሞ ሥራቸው እንዲቀጠሩ በማድረግ ካሳ ከፍሎ፤ አሳሪዎቹን በወንጀል ለምን አልጠየቀም?
ነው ወይስ የውሸት ሱሱ ስላስቸገረው?
ይህንን ተመልከቱልኝ፤
3) “ፖሊስ ከወቅታዊ ሁኔታ
ጋር በተያያዘ የተጠረጠሩ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር እንደሚያውልና ተጠርጣሪዎቹ ጉዳያቸው ተጣርቶ እጃቸው ከሌለበት እንደሚለቀቁም
አስረድተዋል።
ተጠርጣሪዎቹ እጃቸው ከሌለበት መጀሪያውኑ በምን ምክንያት ለረዢም ወራት ታስረው ማስረጃ ስላልተገኘላቸው በዋስ ተፈትተው አንደገና ከተፈቱ ሳምንት ሳይሞላቸው በዚህ የሰሞኑ የዘር ማጽዳት ጥቃት “ታፍሰው” እስር ተወርውራዋል። በምን ማስረጃ ነው ሊታሰሩ የበቁት? የዚህ ኩሊ አለቃው “ማስረጃ ሳንይዝ ሳናጣራ አናስርም” የሚለው ውሸቱ “ምን በላው”?
4) ሬድዋን ሁሴን አያይዞም
አገሪቱ ግጭት ላይ መሆኗን ተከትሎ የአሸባሪዎቹን ቡድን አባላት እና ተላላኪዎችን የፀጥታ አካላት በቁጥጥር ስር እያዋሉ መሆኑን
ይገልጻል።
5) ንጹሃን ወንድሞቻችን እና ዘመዶቻችን ምንም ባልዋሉበት “ትግሬዎች” ብቻ ስለሆነ እንደ “ጃፓን አሜሪካዊያን” እየታፈሱ መታሰራቸውን ንጹሃንን እያንገላቱ፤ ከሥራቸው እንዲፈናቀሉ ሆን ተብሎ የተደረገ “ሴራ” የፀጥታ አካላት ብሎ የጠራቸው “የጎስታፖ አካላትን” በዚህ የናዚ ተግባር በመሳተፋቸው አመስግኖአቸዋል።
ነገ አይነጋ መስሏት ወፍጮ
ላይ ትጸዳዳለች “ የሚለው የትግርኛ አነጋገር፤ አለ፡ ነገ ይነጋል፤ ሬድዋን እና መሰል ስብእናቸው የሸጡ ትንንሽ ሰዎች ለፍርድ
ይቀርባሉ። እስከዚያው ድረስ የደርግ ዕጣ እስኪደርሳችው ድረስ “ማላገጥ” ችለውበታል።
ካፍንጫቸው ርቀት ማሰላሰል
የተሳናቸው በደመነብስ የሚጓዙ ኢንተርሃሙዌው ደጋፊዎች እና “corrupted mind” የሆኑብቹየዎቻቸውም አብረው “መቀለድ፤ መጨፈርና
መደሰት” ችለውበታል። “ቡችየዎቹም” የንፁሃን ዜጎችን ግፍ ቁቡልነቱን እየደገፉ “ሰው” መሆናቸውን አቁመዋል። አንድ ሰው በዚህ
ድጋፍ ከገባ በኋላ የህሊና ጤና የለውም። ፍርሃትን ለማሸሽ ሲሉ “የዜጎችን ግፍ የሚደግፉ” ሰዎች ቀስ ብለህ ሕሊናቸውን ብትኮረኩረው፣
ከቆዳቸው ሥር ፍርሃት ተቀምጦ ታገኛለህ።ወለጋና ባሌ አርሲና ደብረዘይት የአማራ እናት በልጅዋ ሬሳ ጎን ተቀምጣ የመንግሥት ያለህ
እያለች ስትጣራ ሳይሰማቸው በተፈጥሮ የተሰመረው ከአጽናፍ እስከ አጽናፍ የተዘረጋው “ሰብአዊ መስመር”ጥሰው በመግባት “በሽተኛው
የኦሮሙማው አፓርታይድ” አለቃቸውን ንጸሃን ትግሬዎች በገፍ እያፈሰ ስላሰራቸው ተቃውሞ ስለደረሰበት እርሱን ለመከላከል “ሲቀባጥሩ”
የሚያሳዩት ትዕይንት እጅግ የሚገርም ነው። ምሕረት ያውርድ!
ጌታቸው ረዳ
ኢትዮ ሰማይ አዘጋጅ
(Ethio Semay)