Friday, September 3, 2010

አረጋሽ አዳነ፤ሐስን ሽፋ፤ቢተው በላይ “የዝጉልኝ ቤታቸው” ታሪካና እና የትግራይ ገበሬ “የማጎርያ ቤት” ወንጀላቸው

ይድረስ ለጎጠኛው መምህር (አማርኛ) እና ሓይካማ (ትግርኛ) መጽሐፌን ለመግዛት ዕድሉን ያላገኛሁ ካላችሁ በሚከተለው አድራሻ ደውላችሁ ማግኘት ትችላላችሁ Telephone (408) 561 4836 begin_of_the_skype_highlighting (408) 561 4836 end_of_the_skype_highlighting አረጋሽ አዳነ፤ሐስን ሽፋ፤ቢተው በላይ “የዝጉልኝ ቤታቸው” ታሪካና እና የትግራይ ገበሬ “የማጎርያ ቤት” ወንጀላቸው ከየወያኔ ገበና ማህደር (ጌታቸው ረዳ) Septemebere 6/2010 www.ethiopiansemay.blogspot.com getachre@aol.com

ለቅዱስ ዮሐንስ የማስነብባችሁ የወያኔ ገበና ማሕደር የሚከተለው ነው።ይህ ታሪክ የተገኘው ከጋህዲ ቁጥር 3 የትግርኛ መጽሐፍ ውስጥ ወያኔን ከመሠረቱት 11 ሰዎች አንዱ ከሆነው በአቶ አስገደ ገብረስላሴ ከጻፈው መጽሐፍ ነው። ታሪኩ የሚተነትነው ”ስታራተጂ መጥቃዕቲ” ተብሎ በሚታወቀው ወያነ ትግራይ በደርግ ሥርዓት ላይ ለመጨረሻ ጊዜ ያወጣው ወሳኝ ወታደራዊ የጥቃት/የፍልሚያ (ዕቅድ) ለማጠናከር ሲባል ወያነ ትግራይ በትግራይ አርሶ አደር ሕይወት ላይ ያደረሰው አሳዛኝ ታሪክ ነው። ታሪኩ ረዢም በመሆኑ አሳጥሬ በማቅረብ ትግርኛ ለማታነቡ ዜጎች ሁኔታውን ባጭሩ እንድትረዱት ይረዳ ዘንድ አሳጥሬ በመተርጎም ለዛሬ የወያኔ ገበና ማህደር ዓምዳችን ወያኔዋ አረጋሽ አዳነ ዓረና ትግራይ ለፍትሕ ፤ለዲሞክራሲና ለሉኣላዊነት በሚል መጠርያ ድርጅት መስርታ ብቅ ስትል ፀረ መለስ ዜናዊ ነችና መለስን ታስወግድልናለች ብለው ብዙ የዋሃን ዜጎች ሲሰብኩን አንዳንድ ”አቃጣሪ/ደላላ” ጋዜጠኞችና ዌብሳይት ባለቤቶች ድንቅ ታጋይነቷንና ለፍትሕ ለሰብአዊነት ህይወቷ በሙሉ እንደቆመች አስመስለው ውሸትን ሲለቀልቁና ሊያስተዋውቁንና (ሲያቃጥሩ) እንደንደነበር ይታወሳል (አሁንም ይሰብኩናል)። ይግረም ብሎም ከወደ ካናዳ በኩል የሚደመጡ መለስ ዜናዊን እንቃወማለን ገብሩና አረጋሽ እናከብራለን/እንከተላለን የሚሉ እንዳንድ የፖለቲካ ኩታራዎች፡ ሥልጣን ውስጥ በነበረችበትና በረሃም እያለች ስትፈጽማቸው የነበረው የሥልጣን ብልግናዋን ስናጋልጥ በየዜናው ማሰራጫ የምትዋሸንን ስብዕናዋን ለማጋለጥ የምናደርገው ጥረት እየተከላከሉ እና እያሾፉብን ”ሳትጠራቸው አቤት ሳትላከቸው ወዴት” የሚሉላት ቡችሎቿ መለስ ዜናዊን የምትጥልልን ታጋይ ነፃ አውጪያችን ነችና (ለድርጅቷ ለዓረና ትግራይ) ዕርዳታ ገንዘብ እናዋጣላት እያሉ ታሪክ ምን ይለናል ሳይሉ ቡቹላነታቸው ለማስመዝገብ በገንዘብና በሞራል ፍቅራቸውን እንደገለጹላት ውጭ አገር የተመሠረቱት የተቃዋሚዎች ዌብሳይት የምታነቡ ሁሉ የታሪክ ምስክሮች ናችሁ። ጉዷን የሚያውቁ የዓይን ምስክሮች ግን የፍትሕ ረጋጭ እና በስልጣን የባለገች በከርሰ መቃብር ውስጥ ሆነው የፍትሕ ያለህ እያሉ በእርሷ ምክንያት ሕይወታቸው ያጡ፤የተፈናቀሉ፤ንብረታቸው ተበትኖ የትም የቀረ፤ከቤተሰቦቻቸው የተለያዩ በጠቅላላ ለፈፀመቺው ወንጀልና ዲክታተርያላዊ ጸባይዋ/ትዕቢቷ በሠራቺው ግፍ ሳትቆጭ የተገላቢጦሽ ዛሬም ስትኩራራ አድምጠናል።

የመለስ ዜናዊ ተቃዋሚ ነን የሚሉ የትግራይን ገበሬ/ኗሪ ስቃይ ከእሚንት የማይቆጥሩት “ሳትጠራቸው አቤት -ሳትልካቸው ወዴት” የሚሏት አዳዲስ ጀሌዎችዋ በግፍ የቆረፈደው የታሪክ ዕድፏን አጥበው ውድነቷን እያብራሩ ወደ ፖለቲካው ገበያ ሊሸጡልን ቢሞክሩም፤ “የዘንድሮ” ደላላ “ጋዜጠኞችም” ከመለስ ዜናዊ በምን ትሸልያለሽ ሲሏት “Because people know what I have been through, what I have given up for the truth. They know that power had not corrupted me. (Welcome to Ethiopia's election 2010: The case of Adwa By Eskinder Nega April 2, 2010) ብትለንም ”የምሯ፤ከልቧ ነው የምትናገረው” እያሉ ወደ ኮከብነት /ወደ ጣይቱነት በመለወጥ ለውሸቷ ሽፋን የሚሰጧት አለቅላቂ ጋዜጠኞችም የለበሰቺውን የታሪክ እድፍ ሲያደንቁላት አይተናል። እነ አረጋሽ እነ ስየ እነ ገብሩ እነ ተወልደ እነ ዓለምሰገድ እነ ቢተው እነ አውዓሎም… በየዱሩ በየጉድጓዱ ውስጥ ጥለውት የመጡት የገበሬው፤የከተማው፤የምሁሩ ኗሪ ሕይወት ፍትሕ በማጣት ወደኛ ጮኾ ስሞታውን ስንመዘግበለት ውጭ አገር የሚገኙት አንዳንድ የተቃዋሚ ሚዲያዎችና የፖለቲካ ድርጅቶች ለሙታኖች በመቆምችን ለምን ይጠሉናል? ምናቸው ስለሚነካቸው ነው የሙታንና የተገፉ ዜጎች ስሞታ ስንመዘግብ እየጎረበጣቸው የሚገኘው? እውን አረጋሽ አዳነ “they (voters) know that power had never corrupted me” “ስልጣን አላበላሸኝም” ስትል እውነት ከልቧ ነው እያሉ የታሪክ እድፏን የሚጠራርጉላት ደላላ ጋዜጠኞች አስገደ ገብረስላሴ እያጋለጠው ያለው የነ አረጋሽ እና የወያነ ትግራይ መሪዎች ምስጢር ከማጋለጥ ለምን ወደ ሗላ አሉ? የአስገደ ገብረስላሴ፤የገብረመድህን አርአያን ፈለግ አንከተልም ብለው ያደፈጡ የተደበቁ ሚስጢሮች እንዳይጋለጡ የሚጥሩ ወንጀለኞችና ተባባሪዎቻቸው ለጊዜው ከቅጣት ቢያመልጡም ከታሪክ ተጠያቂነት ግን አያመልጡም። አስገደን ከልብ አመሰግናለሁ። ወደ አስገደ ሰነድ ከመግባቴ በፊት ከዚህ በታች የሚቀርበው ሰነድ ”ስትራተጂካዊ መጥቃዕቲ” የሚል በተከታታይ ስለምታገኙ ስትራተጂካዊ መጥቃዕቲ ምን እንደሆነ ልግለጽና በቀጥታ ወደ ሰነዱ እንገባለን። ስትራተጂካዊ መጥቃዕቲ ለወሳኝ ምዕራፍ የሚያደርስ የመጨረሻ የውግያ ዝግጅት ነው። ”ስትራተጂካዊ መጥቃዕቲ” ተብሎ የሚታቀው የወያነ ትግራይ የጦርነት ዕቅድ ብዙ ሃላፊዎችን በየዘርፉ ያካተተ ሲሆን ሰዎቹ በተለያዩ የሥራ ዘርፎች ሃላፊነት ወስደዋል።ስንቅ፤ነዳጅ፤መጓጓዧ፤ትጥቅ፤ሕክምና የመሳሰሉት በተቀናጀ አሰራር እንዲቀነባበር የተደረገ ጥናት ነው። በዚህ ዘመቻ ወሳኝ ሆኖ የተገኘው ደግሞ የተዋጊው ሃይል ቁጥር በብዛት መኖር ወሳኝነት ስለነበረው፤በወቅቱ ወያነ ትግራይ የሻዕቢያ ባርያ ስለነበረ ጌታውን ሻዕቢያን ከኢትዮጵያ ሠራዊት ለማዳን ሲል በብዙ ሺሕ ትግራይ ታጋዮች ወደ ኤርትራ በመላክ እንዲያልቁ በማድረጉ፤ ”ስተራተጂካዊ መጥቃዕቲ” ስለተባለው ዝግጅት ከመደረጉ በፊት ከቀረው እጅግ አድካሚ እና ወሳኝ ፍልሚያ ሲነፃፀር በሰው ሃይል እጅግ ቀንሶ እና ተመናምኖ ነበር። ለዚህ አንድ ሁለት ምክንያቶች ነበሩት። አንዱ ቀደም ብየ እንደገለጽኩት ወደ ኤርተራ እንዲሄድ ተደርጎ በሺዎች ተሰውተዋል።ሌላው ታጋዮቹ ከደርግ ሰራዊት ይዘት ትግራይን ነፃ እንዳወጡ ወዲያውኑ እንዲተገብረው የተማረው ጠባብነት በተግባር በማዋል ”ትግራይን ነፃ አውጥተናል፤ አማራው ነፃ ለመውጣት ከፈለገ እራሱ ነፃ ያውጣ፤ እኛ ላማራዎች ስንል የምንሰዋበት ምክንያት የለንም፤ ስለዚህ ከአለውሃ ምላሽ ወዲያ እንዲሁም ከደብረታቦር ወዲያ አናልፍም በማለት ከነ ትጥቃቸው ምሽጋቸውን እየለቀቁ ወደየ መንደራቸው ስለሄዱ የወያኔ ታጋይ በቁጥር የተመናመነ ስለነበር የግድ እሱን ለመተካት ሲል የትግራይ ገበሬ ወጣት በግድ ወደ ማስልጠኛ ጣቢያ በመትመም ወታደራዊ ስልጠና ተገድዶ እንዲወስድ ተደርጓል። ከየመንደሩ በገፍ እየታፈሰ ሲሄድ እምቢ ያለ ደግሞ ከዚህ በታች ያለውን ድርጊት ተፈጽሞበታል። ባንድ ወቅት በግድ እየተገፋ አፅቢ በተባለው ማሰልጠኛ ውስጥ 79 ሺህ አዲስ ምልምል ታጋዮች እንደነበር አስገደ ይገልፃል።ይኸ አሃዝ እንድ ቦታ የነበረ እንጂ በየገጠሩ ማስለጠኛ የያዘዘቸው ብዛቶች በርካታ ናቸው።ከዚህ ቀጥሎ የምታነቡት አስገደ የዘገበው ታሪክ አምቢ አልታገልም ያለ ሰው በአሳዛኝ ሁኔታ የትግራይ ገበሬ እና የከተማ ኗሪ ሕዝብ በወያነ ክፍሊ ሕዝቢ (ካድሬዎች/የህዝብ ግንኙነት ሓለፊዎች) እየተጎተተ ወደ ማጎርያ (ኮንሰንትረሺን ካምፕ) እስርቤቶቸ ተወስዶ የደረሰበት ስቃይ ትመለከታላችሁ። ወደ ታሪኩ ልውሰዳችሁ። አስፈገደ ገ/ሥላሴ እንዲህ ይላል። ”የአዲስ ምልምሎች ሥልጠና ጉዳይ በበላይነት የሚመሩ ከማዕከላዊ የደጀን አስተዳደር ክፍል የህወሓት ፖሊት ቢሮ አባላት ስምዝርዝር የሚከተሉት ናቸው። 1 ገብሩ አስራት 2 አረጋሽ አዳነ 3 ተወልደ ወልደማርያም 4 ቢተው በላይ የምልመላው የህዝብ ግንኙነት (ክፍሊ ሕዝቢ 08)ሃላፊው ተወልደ ወልደማርያም ሲሆን ከተወልደ ሥር በትግራይ ውስጥ በየአውራጃው ለምሳሌ በወልቃይት፤ፀገደ፤አርማጭሆ፤ፀለምቲ፤ላሬ፤በየዳ፤ጃን አሞራ፤በለሳ ሰቆጣ፤ወሎ ሰሜን ሸዋ 500 የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ነበሩ። በስትራተጂካዊ የማጥቃት ዘመቻ ዕቅድ ለማሳካት አዲስ ሰልጣኝ ለማብዛት ሁለቱም ማለትም የሕዝብ ግንኙነትና የደጀን አስተዳደር ክፍል ከፍተኛ ሓለፊነት ተጥሎባታፀቸዋል። ምክንያቱም ተመልማይ ብብዛትና በወቅቱ ሰልጥነው ወደ ጦር ግምባሩ ካልዘመቱ ስትራተጂካዊ መጥቃዕቲ ሚባለው ወሳኝ ፍልሚያ ግቡ አይመታም። የታሰበው ግብ ካልመታ ”ሙሽራ ሳይዙ ሚዜ ፍለጋ ዓይነት” እንዳይሆንበት በማሰብ ካሁን በፊት በግድም ሆነ በውዴታ ልጆቹን ወደ ጦር ሜዳ አስልኮ አታግሎ የነበረ ወላጅ ወይንም ቤተሰብ ልጆቻቸውን ወደ ታጋይ ምልመላ ያልላኩ ቤተሰቦች/ጎረቤቶች ካሉ ልጆቻቸው እንዲያታግሉ ”ዛሬ ያልከተተ በቁሙ የበከተ” የሚል መፈክር እንዲያሰሙዋቸው በመገፋፋት በሁለቱም ላይ ቅራኔ እንዲፈጠር አድርገው ለጆቻቸው ያልላኩ ሰዎች በግድ እንዲሄዱ በመጫን በርካታ ምልምሎች ወደ ማሰልጠኛ ቦታ ጎረፉ። በተለይም በ1981 ዓ.ም ደርግ የለቀቃቸው በሗላ ነፃ የወጡ ቦታዎች ያልተነካ ወጣት ስለነበር መጀመርያው ዙር ላይ 30,000 ወጣት በግድ ተመልምሎ ሰልጥኖ ታጋይ ሆነ። ያ በ1982 ዓ.ም በጠባብነት ስሜት (ፀረ ኢትዮጵያዊነት /ፀረ አማራነት) የተማረውን ትምህርት ተግባራዊ ለማድረግ ምሽጉን እየጣለ ወደ የቤቱ የሄደው ታጋይ ከነ ብረቱ ተመልሶ ወደ ጦር ሜዳ መመለስ ጀመረ። የመጀመርያው ዙር በእንዲህ ቢከናወንም የተጠበቀው ቁጥር ከተገመተው በታች ስለሆነ እና የመታገል ስሜት ስለቀዘቀዘ ሰሜቱን ለማነሳሳት የኪነት ቡድኖች እነ እያሱ በርሐ እና እነ ገብረመድህን ስቡሕ (ጠርጣራው) ወደየ ገጠሩ ወደየ አውራጃው ተሠማሩ። የኪነት ትርዒት ባሳዩ ቁጥር ባንድ መድረክ ውስጥ ወደ 300 ሰዎች ለትግል ዝግጁነታቸው ይገልፁ ነበር። ያም ሆኖ አሁንም የተፈለገው ሃይል ማግኘት አልተቻለም። በቂ የታጋይ ቁጥር ስላልተገኘ የሚከተለው ውሳኔ ተላለፈ። ወደ ትግል ለመሄድ ዝግጁነቱ ያላሳየ ሁሉ በታጋዮችና በሚሊሺያ ወያኔዎች እየተጎተተ ወደ ማሰልጠኛ ጣቢያ እንዲወሰድ። አልታገልም ብሎ አሻፈረኝ ያለ ወጣት ደግሞ ሚሰቱ፤ወላጆቹ፤እህት ወንድም ዘመድ አዝማድ እየተገደዱ እስር ቤት እንዲገቡ፤ንበረታቸው፤በግ፤ፍየል ላም በሬ ደሮ እንሰሳት በሙሉ ተወርሰው ለድርጅቱ ገቢና ጥቅማጥቅም ይውላል። በነፃ በወጡት ገጠሮችም ሆነ ከተማዎች እምቢ እያሉ የሚያንገራግሩ፤የሚያውኩ፤የሚሰብኩ በማንቁርታቸው እያታነቁ ወደ 06 እስር ቤት ተወርውረው እንዲቀጡ። ቅጣቱም ወደ አፅቢ ማሰልጠኛ ቦታ በመሄድ ሠልጣኙ የሚወስንላቸው የቅጣት ውሳኔ ተግባራዊ እንዲሆን ሙሉ ስልጣን ተሰጣቸው። የዚህ ምልመላ ቅጣት ውሳኔ አመንጪዎች፤ፈፃሚዎችና አስፈፃሚ አካላት ሥም ዝርዝር የሚከተሉት ናቸው። ተወልደ ወልደማርያም የሕዝብ ግንኙነት አስተዳደር ሐላፊና አደራጅ ገብሩ አስራት የትግራይ ደጀን አስተዳዳሪ አረጋሽ አዳነ ትግራይ ደጀን ምክትል አስተዳዳሪት ቢተው በላይ ሕዝብ ድርጅትና አስተዳደር (ምክትል) ሃለቃ ፀጋይ በርሀ ሕዝብ ግንኙነት ሃላፊ ሐሰን ሽፋ ደጀን ትግራይ የፀጥታ ጉዳይ ሐላፊ ቁዱሳን ነጋ የምዕራብ ትግራይ የሕዝብ ጉዳይ ሐላፊ ትርፉ ኪዳነ የትገራይ ማዕከላዊ አስተዳደር የሕዝብ ክፍል አደራጅ ሓላፊት አብርሃ ማንጁስ የድርጅት ጉዳይ ፀሐፊ ዘርአይ አስገዶም መቀሌ የሕዝብ ጉዳይ ሐላፊ ዓለምሰገድ ውረታ ውቅሮ የህዝብ ጉዳይ ሃላፊ እና የውቅሮ አስተዳዳሪ ምሩፅ የዛላምበሳ እና አካባቢዋ ሕዝብ ጉዳይ ሓላፊ ሃረያ ስባጋድስ ዓድዋ የሕዝብ ጉዳይ ሓለፊት (ልጅቷ በህይወት የለችም፡ የተወልደ ወ/ማ ባለቤት የነበረች ነች (ከተርጓሚው) አቶ ሙሉ ሰንደቕ የህዝብ ጉዳይ ሸዊት ገብረክርስቶስ የሕዝብ ጉዳይ ዓባዲ ወልዱ የሕዝብ ጉዳይ ካሕሳይ ቆራይ የእስርቤቶች (06) ጉዳይ ሓላፊ እና በመቶዎች የሚቆጠሩ እነዚህና እነዚህን የመሳሰሉ የሕዝብ ጉዳይ ሓላፊዎችና ካድሬዎች ሲካሄድ በነበረው የሕዝብ ዓፈና ተጠያቂዎች ብቻ ሳይሆኑ ዓፈናውን በግምባር ቀደምትንት ፈፃሚዎችና አስፈፃሚዎች የነበሩ ናቸው። ለዛ ዓፋኝ እና አስገዳጅ የምልመላ መርሃ ግብርና ዓፈናውንም ግብር ላይ መዋሉን የሚከታተል ፖሊት ቢሮ ማአከላዊ አባላት ሲሆን በተለይም ደግሞ የማአከላዊው አመራር ኣባል (ሰንትራል ኮማንድ)በቀጥታ ምልመላውን በምን ሁኔታ መካሄድ እንዳለበት ይቆጣጠረው ነበር። ከላይ ተጠቀሱት ሰዎች ምድብ ሥራቸው ተሰማርተው ዓፈናውን ማጧጧፍ ከጀመሩ በሗላ በጣም በርካታ የከተማና የገጠር ወጣቶች ካአፈናው ለማምለጥ ሲሉ ወደ ሱዳን (ጂዛን) እና ወደ ደርግ መሸሽ ጀመሩ። በተላለፈው መመርያ መሠረት ከዚያ በሗላ የሸሹትን ወጣቶች ቤተሰቦች ንብረታቸው እየተቀሙ/እየተወረሰ ሚሰት፤ባለቤት፤አባት፤እናት፤ወንድም፤አጎት....ሁሉ እየተለቀሙ ፅዳት በጎደላቸው፤ምግብ በሌለበት፤ሕክምና በሌለበት ትናንሽ እስር ቤቶች እና የእስረኛ ማጎርያ ስፍራዎች ታጉረው እንዲሰቃዩ በመደረጉ ለታይፎይድና ልዩ ልዩ ለተላላፊ በሽታዎች እና ለተቅማጥ በሽታ ተጋለጡ። ከገጠር የተወረሰ የቤተሰብ እህልም ወደ ከተማ እየተጫነ የአሳሪዎቻቸው ባለሥልጣኖች መሽሞንሞንያ ሆነ። ክፍሊ ህዝቢ (የሕዝብ ጉዳይ) የሚሉዋቸው እነዚህ ክፍሎች ባለ ሙሉ ሥልጣን ሆነው ያለ ተቆጣጣሪ ሕዝቡን አበሻቀጡት። 17 ዓመት ሸሽጎ፤ አዝሎ ወደ ሰሜን ሸዋ ያሸጋገረን እሽርሩ ብሎ ተንከባክቦ ያሳደገን ሕዝብ ካሳው/ወረታው ዓፈና ሆነ! አሳዛኝ! በአስገዳጅ እየታፈነ ወደ ህወሓት ትግል እንዲገባ የተደረገው ይህ አሳዛኝ ድርጊትና ግፍ ለማስረጃ እንድትሆናችሁ እኔ የማውቀው በዓይኔ ያየሁዋት አንዲት ማስረጃ በማቅረብ ልመስክር። ሐቁን ገልጬ ለናንተው ለፍረድ ልተወው። በወቅቱ ምድብ የሥራ ቦታየ ሽሬ ውስጥ ነበር። አዲስ መመርያ ስለሚተላለፍ ወደ ሃገረሰላምና (ተምቤን) ባስቸኳይ እንድትመጣ ተብየ ትዛዝ ተላልፎልኝ በመመርያው መሠረት ከሽሬ ተንቀሳቅሼ መንገድ ስጀምር መውጫ በር ላይ በሺሕ የሚቆጠሩ ፍየሎች፤ በጎች፤ላሞች፤በቅሎና ደሮዎች በወያኔ ታጋዮችና ሚሊሽያዎች እየተገሩ ወደ ከተማው ሲገቡ አገኘሗቸው። ግራዝማች በላይ ሃይሉ የተባሉ አንድ አዛውንት አባት ከከብቶቹ ሗላ ሗላ በአዝግሞት ሩጫ እየተከተሉ ንብረቴ ዘረፉኝ እያሉ እየጮኹ ሰማሗቸው። እንዴ! ምን ጉድ ነው ብየ፤ ምን የሆኑ አባት ናቸው? ብየ ታጋዮቹን ስጠይቅ ”አይ ተዋቸው ሕሊናቸው ተቃውሶባቸው ነው” አሉኝ። አብረውኝ ከኔው ጋር በመኪና ሲጓዙ የነበሩ 8 ታጋዮች ነበሩኝ። መኪናዋን አስቁመን ”አቦ! (አባባ) ምንድነው ችግሩ? ብለን ጠየቅናቸው። ”ንብረቴ ተወረርኩኝ! ወያኔ ፀባይዋ ቀይራለች! አዲስ ጠባይ አምጥታለች!” አሉን። እኚህ አባት ታጋይ ዘነበ በላይ የሚባል ልጃቸው በ1968 ዓ.ም ተጋይ ሆኖ እስከ የሃይል መሪነት እና አዋጊ ሆኖ ውጊያ ላይ ተሰውቷል።ሌሎች ሁለት ልጆቻቸውም እንደዚሁ ታጋዮች ሆነው በክብር ተሰውተዋባቸዋል። ይህ ሁሉ አስተዋፅኦ አድርገው ልጆቻቸውን ያጡ አዛውንት አባት መሆናቸውን እየታወቀ አንድ የቀራቸው ልጃቸውን ታገል ተብሎ አልታገልም ብሎ ስለተሰወረ፡ የኚህ አባት ንብረት የሆነ 30 ፍየሎች 42 ከብቶች አንድ በቅሎ6 አህዮች 10 ኩንታል እህል ወረሷቸው። እኛም ታሪካቸውን ሰምተን በማዘናችን የሳቸውና የሌሎች ሰዎች ፍየሎችና ከብቶች በጎች ቀላቅለው ሲነዷቸው የነበሩ እነኛ 3 ታጋዮችና 10 የሚሆኑ ጀሌዎች (ሚሊሽያዎች) ጠርተን የሚመለከታቸው ክፍሎች እስክናነጋገር ድረስ እየነዳችሗቸው ያሉትን እንሰሳት በሙሉ ካመጣችሗቸው መልሳችሁ ውሰዷቸው፡ ብለን አዘዝናቸው። ትዛዙን ላለመቀበል ብያጉረመሩሙም ሳይወዱ መለሷቸው። ጉዟችንን ቀጠልን። በለስ ከተባለች ትንሽ ከተማ ደረስን። በዛች ትንሽ ከተማ ውስጥ ከላይ ቆራሮ እና ከታች ቆራሮ የተለቀሙ በሺዎቹ የሚቆጠሩ ዜጎች ህፃናት ሽማግሌዎች ሳይቀሩ ልጆቻችሁ/ቤተሰቦቻችሁ ከተሸሸጉበት ቦታ አምጧቸው ተብለው መጠለያ በሌለው አውላላ ሜዳ ላይ ልክ እንደ አውጫጭ በጥበቃ ተከብበው ታጉረው ታስረው አየን። ራቅ ብለህ በሺ የሚቆጠሩ የታሳሪዎቹ ንብረት የሆኑ ላሞች፤ከብቶች የቤት እንሳሰት ጠባቂ አልባ ሆነው የሌባ ቀለብና እና የጅብ እራት ሆነው ለአደጋ ተጋልጠው ይቀራመቷቸዋል።ያ አልበቃ ብሎ በሌሎች ቦታዎችም በሰለኽለኻ በኩል ስናልፍ የታዘብናቸውም ቢሆን በለስ ውስጥ ካየነው የባሰ በየጠባብ ማጎርያ እስር ቤት ክፍል ውስጥ በብዛት ታጭቀው፤ምግብ ውሃ ተከልክለው፤ንፅህና በጎደላቸው ክፍሎቸ ታጉረው በቅማል በላብ በእድፍ ምክንያት በታይፎይድ (በተላላፊ በሽታ በአር ኤፍ) በወባ በሽታና በተቅማጥ እየተሰቃዩ ጠረኑ ለህዋሳት የሚዘገንን ሽታው የማያስጠጋ ማጎርያ እስር ቤት ታጉረው አየን። ይህን ስመለከት በስልጣኔ እንድፈታቸው ፈልጌ ነበር፡የሰለኽለኻ ሕዝብም እርምጃው በጣም ስለተቃወመው እንዲፈቱ ግፊት ያደርግ ስለነበር ድርጊቱ በውስጤ እጅግ አስቆጣኝ። ይሕ ግፍ የተመከተ ሰብአዊነት የተላበሰ ሰውም ምን እንደሚሰማው የታወቀ ነው። እኔም የተወለድኩባት መንደሬ በመሆኗ ለመንደሩ ተቆርቁሮ ነው ፤አድልዎ በማድረግ ነው የፈታቸው እንዳልባል ”ነብሴ ላዘሬ ብለሽ ታገሺ” ብየ ውስጤ እሳት እየነደደበት ወደ ውቅሮ ማራይ (አክሱም አጠገብ) ተጓዝን። ውቅሮ ማራይም በሺ የሚቆጠሩ እንሰሳት እና ሰዎች የታሰሩ ገጠመኝ። አክሱም ከተማም አንደዚሁ በሺዎቹ የሚቆጠሩ እስረኞች አንዳሉ ተገነዘብኩ። ዓድዋ/ዓዲ አቡን እንደደረስንም ባካባቢውና ከተማው ውስጥ የነበረው የእህል ማከማቻ ጎተራ በሺዎቹ የሚገመቱ እስረኞች ታጉረውበት እንዳሉ ካገኘናቸው ገበሬዎችና ታጋዮች በኩል እንዲህ ያለ አሳዛኝ የእስራት አስገዳጅ ዘመቻ በመላ ትግራይ ውስጥ በሰፊው እየተጧጧፍን እንደሆነ እና በተለይም አልታገልም ወይም ልጄ የት እንደሸሸ/ሸሸች አላውቅም ያለ ሁሉ ንብረቱ እየተቀማ እየተጎተተ ፍዳውን አየ። ኩፍኛ የተጧጧፉባቸው ማጎርያ እስር ቤቶች የተባሉት በዓድዋ፤አክሱምና ሽሬና ተምቤን ውስጥ የከፋ እንደሆነ ነገሩን። ጉዟችን ወደ ሃገርሰላም ነው። ያ ከሽሬ ጀምሮ አክሱም እስከ ዓድዋ ድረስ ያየነውና የሰማነው በሕዝብ ላይ የደረሰው ግፍ ጉዟችን የከፋና በሃሳብ እንድንዋጥ አድርጎት ነበር። ጉዟችን ወደ ሀገረሰላም ከማቅናታችን በፊት የተመለከትነው አሳዛኝ ድርጊት ዓድዋ ውስጥ ለነበሩ ማዕከላዊ ኮሚቴ ባለሥልጣኖች ስለ ሁኔታው አሳሳቢነት መንገር እንዳለብኝ ወሰንኩ። ስለሆነም ሁኔታውን ለመንገር የማአከላዊ ኮሚቴ አባላት ወደ ሆኑት ወደ አረጋሽ አዳነ፤ቢተው በላይ፤ሓሰን ሽፋ፤ አብርሃ ማንጁስ፤ካሕሳይ ቆራይ ወደ ሚተኙበት ቤት አመራን። እነኚህ የደጀን መሪዎች ቤት ዘግተው በኮንትሮባንድ የመጣ መጠጥና ከውጭ አገር የመጣ የቆርቆሮ ቢራ እየተጎነጩ በውጭ አገር ቪዲዮ ካሴቶች እየተዝናኑ ሲመለከቱ ደረስንባቸው። መጀመርያ በሩን ስናንኳኳ እኛ መሆናችንን ካወቁ በሗላ ግቡ፤አረፍ በሉ እንኳን ደህና መጣችሁ ቤት ለእንግዳ ከማለት እና እንደታጋይ ጓዶቻቸው ከማስተናገድ ይልቅ ”ጉዳቸውን” እንዳናይባቸው በማለት በሩን ከፍተው ሐሰን ሽፋና ቢተው በላይ ወደ ደጅ በመውጣት እንደማንም ሰው ከደጅ አነጋግረው ሊመልሱን ዳዳቸው። ዘግናኙ ሁኔታ በዝርዝር ነገርናቸው። በማይገባ ውሳኔ ወላጆቻችን ፤ሕዝባችን በቁር በበሽታ በረሃብ በሙቀት በጠባብ ክፍል ታጉሮ ለተላላፊ በሽታ ለስቃይ ተዳርጎ ንብረቱና ከብቱ በድርጅታችን እየተወረሰ ታስረው ተሰቃይተው እየሞቱ፤ እህሉ ከብት፤በግ ፍየሉ ንብረቱ ሁሉ ወርሳችሁ ለስቃይ ዳርጋችሁት በወረሳችሀት ገንዘብ በመፈንጨት ትጠጣላችሁ ትበላላችሁ። ጭራሽኑ ይህ የተበደለ ሕዝብ ልጅ ከወላጁ ተሰብስቦ አንድ ቀን ይበላችሗል፡ጭራሽኑ ለምናካሂደው ትግል እንቅፋት ነው። እያልን ስንነግራቸው፤ ሓሰን ሽፋ በማሾፍ ገጽታ ተመለከተን፡ ቢተው በላይም ”ተደፈርን” ብሎ ተቆጣ። ቆየት ብላ አረጋሽ አዳነ መጣች። እየነገርናቸው ያለውን ጉዳይ አዳመጠች። ብዙ ከተጨቃጨቅን በሗላ ወደ ነበሩበት ክፍላቸው ተመልሰው በመግባት ስብሰባ ካደረጉ በሗላ ”ሁሉም ይፈቱ ነገር ግን 150 ብር እየተቀጡ ይውጡ” የሚል ውሳኔ አሳለፉ። አሁንም ጭቅጭቅ ገባን። ገንዘብ እየከፈሉ ይፈቱ አሉ እንጂ መቸ መፈታት እንዳለባቸው ላቀረብነው ጥያቄ አልመለሱትም። መጨረሻ አክርረን ስናጠብቅባቸው እስረኛ በሙሉ ከዛሬ ጀምሮ እንዲፈታ፤ የታመሙትንም ሕክምና እንዲያገኙ ሓኪሞች እንዲሰማሩ እናደርጋለን አሉ። እኛም ከምድብ ቦታችን ተነስተን ለአስቸኳይ ስብሰባ ለመሄድ አስበነው የነበረውን ጉዞ ሠርዘን ወደ ሗላ በመመለስ ያስተላለፋችሁትን ማዘዣ መልዕክት ይዘን እንድንመለስ የመፍቻ ወረቀት ትእዛዝ ስጡን አልናቸው። እነሱም በስምምነታችን መሠረት ወረቀት ሰጥተውን የወደፊት ጉዟችን ሰርዘን ወደ ሗላ በመመለስ በሌሊት ገስግሰን ወደ አክሱም፤ሰለኽለኻ፤ሽሬ አድያቦ ወረዳዎች ውስጥ ላሉ እስር ቤቶች እንዲዳረሱ አደረግን። እኛ ባሰማነው ተቃዉሞ በመላይቱ ትግራይ ውስጥ ታጉሮ በግፍ ታስሮ ሲሰቃይ የነበረ በሺዎች የሚገመት እስረኛ እንዲፈቱ ተደረገ። የተወረሰው ንብረትም ሆነ ላም ከብት ፍየል በግ እንዲመለስለት ትዕዛዝ ይተላለፍ እንጂ ብዙ እንሰሳ እና ንብረት የክፍሊ ሕዝቢ (በየገጠሩና በየከተማው የተመደቡ የሕዝብ ድርጅት ጉዳይ ሓላፊዎች) ሓላፊዎችና የወያኔ ሚሊሺያዎች ምግብ ሆነው የተቀሩትም ያለ እንክብካቤ በዘራፊና በአራዊት እየተበሉ የትም ቀርተዋል። እኛም ውሳኔውን እንዲፈፀም ካደረግን በሗላ ወደ መድረሺያችን ወደ ሃገረሰላም (ተምቤን) ጉዟችን በቀን ቀጠልን። ሃገረሰላምም በሰላም ገብተን ጉዳየችንን እንደፈፀምን ወደ ምድብ ቦታችን ከመመለሳችን በፊት ወዲያውኑ አከታትለን በሕዝብ ላይ እየደረሰ ያለው ግፍ ለተወልደ ወልደማርያም፤ለመለስ ዜናዊ፤ለዓባይ ፀሃየ፤ለስየ አብርሃ እና ለስብሐት ነጋ ነገርናቸው። በጣም አሳዛኝና አሳሳቢ ሁኔታ እንደሆነም በሰፊው አስረዳናቸው። እነሱም ወደ የሕዝብ ጉዳይ ክፍል ሓላፊዎችና የትግራይ ደጀን ሓላፊዎች በመጻፍ የታሰረው ሕዝብ እንዲፈታ ተጨማሪ ትእዛዝ በጽሑፍ ጽፈው ሰጡን። ቀደም ብየ እንደገለጽኩት ሰዎቹ በኛ አቤቱታ በማዘዣ እንዲፈቱ ይደረግ እንጂ የቤት ንብረታቸው ላምና ፈየል ደሮ እና በግ ተወርሰው አብዛኛው የትም ባክኖ ቀረቷል። ይህ በ1983 ዓ.ም ከሽሬ እስከ ዓድዋ ድረስ ባጋጣሚ ስጓዝ ድንገት ያየሁት በሕዝብ ላይ የደረሰ ግፍ እንጂ በሌሎች ወረዳ ጣቢያዎች ከተሞች ገጠሮች በሰው ልጆች ሲፈፀም የነበረ ኢሰብአዊ ግፍ ቢገለጥ ተጽፎም አያልቅ፤ ብዙ መጻሕፍቶችም በወጡት ነበር።በዚህ መጽሐፍ ላይ በጨረፍታ እንደማስረጃ የጠቀስኩት ባይኔ ያጋጠመኝ በሕብ በጅምላ በድርጅታችን የተፈጸመ ግፍ ለታሪክ ፃሐፍት መነሻ እንደሚሆናቸው በማሰብ ነው።” (አስገደ ገብረስላሴ -ጋህዲ ቁ 3 የትግርኛው ቅፅ 289-293) አንግዲህ ከላይ እንዳነበብነው የወያኔ ትግራይ የገበና ማሕደር መሠረት ድርጅቱ እጅግ የከፋ አረመኔ ቡድን ሲመራው በትግራይ ኗሪ ላይ ያደረሰው አሰቃቂ ግፍ ነበር። ስትራቴጂካዊ መጥቃዕቲ (ወሳኝ/ዘላቂ የማጥቃት ዘመቻ) በሚል የጦርነት ትልም ሲያቅዱ የጠበቁትን የሰው ሃይል ጌቶቻቸው ሻዕቢያን ለማዳን ወደ ኤርትራ በመላክ ብዙ ሺሕ የትግራይ ታጋይ በማለቁ ምክንያት ስለተማናመኑ፤ በግድም በውድም 80,000 አዲስ ወጣት ታጋይ ያስፈልገናል ስላሉ ለወታደራዊ ስልጣና በማንቁርቱ እየታነቀ ወደ ማሰልጠኛ ጣቢያ ሲወረወር፤ የሸሸውም የቤተሰቡን ንብረትና የቤት እንሰሳ እየተወረሰ እየታጎረ በተላላፊ በሽታ በተቅማጥ በወባ በቅማል በመሳሰሉት ለስቃይ ተዳርጎ በኮንሰንትሬሽን ካምፕ/በማጎርያ እስርቤቶችና አውላላ ሜዳ ላይ ተከብቦ የደረሰበት ግፍ ፤-አሳሪዎቹና አድራጊ ፈጣሪ የወያኔ ማአከላዊ ኮሚቴዎቹ ግን ቢራና ዊስኪ እየጎነጩ፤በውጭ አገር ፊልሞች እየተዝናኑ ዓለማቸው ሲቀጩ እንደነበር ከውስጥ አዋቂ በይፋ ሲገለጥ የሚሰማችሁ ስሜት ለናንተው ለሰው ልጆች መብት የቆማችሁ ዜጎች ሁሉ ለሕሊና ፍርድ ልተውና ልሰናበታችሁ። እውን እንዲህ ያለ ግፍ እየፈፀሙ የነበሩት እነ አረጋሽ እነ ገብሩ እነ ስየ ምነዋ አንዲት ቀን ተሳስተውም ቢሆን በሕዝብ ላይ ሲፈጽሙት የነበረውን አንዲት ገጽ እንኳ ቢናዘዙ ምን አለበት? እነኚህ ደሞተራዎች ናቸው የአዲሲቱ የኢትዮጵያ ነፃ አውጪዎች እያሉ አቃጣሪ ሚዲያዎችና ጋዜጠኞች ስደልሉን የከረሙት። አንቺ መሬት ስንቱን ጉደኛ ጫንቃሽ ላይ ተሸክሽ ትዞርያለሽ! አምላኬ ሆይ ይቅር በላቸው! ጌታቸው ረዳ። መጽሐፌን ለማንበብ ዕድል ያላገኛችሁ $25.00 ብቻ በመላክ (ለአሜሪካ አገር ብቻ) በስልክ ቁጥር 408 561 4536 ወይንም P.O.Box 2219 San Jose, CA 95109 በመላክ ልታገኙ ትችላላችሁ። መልካም 2003 አዲስ ዓመት!