Monday, December 16, 2024

እንደ እነ ዶ/ር ዮናስ ብሩ ዶክተር ከመባል ማይምነት ተፈልጎ የማይገኝ ወርቅ ነው። ጌታቸው ረዳ 11/16/24

 

እንደ እነ ዶ/ር ዮናስ ብሩ ዶክተር ከመባል ማይምነት ተፈልጎ የማይገኝ ወርቅ ነው።

ጌታቸው ረዳ

11/16/24

(የኦሮሞ አባገዳ መሪዎችና የከተማው ተጠሪዎች እንዲሁም በኦነግ መሪነትና አቀነባባሪነት ባሌ ውስጥ በሚኖሩ አማራዎች ላይ ጥቅምት 2019 (በፈረንጅ አቆጣጠር) የታወጀው የጀነሳይድ የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ አዋጅ (የገበያ ውስጥ በንባብ የታወጀው አዋጅ) በሚቀጥለው ሰሞን በክፍል 2 አቀርባለሁ። ይጠብቁ) እስከዛው ወደ እዚሁ ክፍል 1 እንግባ።)

ይህ ሰው ዶ/ር ዮናስ ብሩ ይባላል።በየሚዲያው ሲለፈልፍ ታገኙታላችሁ። ኢትዮጵያ ውስጥ የዘር ማጥፋት (ጀነሳይድ) አልተፈጸመም እያለ  የግፉአን ጀሮ የሚያደነቁር ያልተሞረደ ምሁር ነው። ይህ ሰው በዚያ አላቆመም ፤ ሃገራዊው የአምሐርኛ ቋንቋ ተወግዶ በእንግሊዝኛ መተካት አለበት እያለ የሚከራከር ነው።“አምሐርኛ የሚናገር ኦነግ ያልሆነ ግን ከኦነግ የባሰ ኦነግ ነው ቢባል ሲያንሰው ነው”። በሁለመናው ክርክሩ ወያኔም ጣሊያንም ነው ቢባልም ይመጥነዋል። 

በየሚዲያው የሚለፈልፈው ይህ ሰው እራሱን “የጀንሳይድ ተመራማሪ ሊቅ” አድርጎ በማቅረብ “ጀነሳይድ አልተፈጸመም” ከማለቱ አልፎ “አምሐራ” ላይ ምን ፀብ እንዳለው ባለውቅም ቃሉ ከምላሱ አይለይም። አስገራሚነቱ ደግሞ እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ ምሁር እራሱን ከወቀሳውና ከድክመት ነጻ አድርጎ ሌሎቹንና  የአምሐራ ምሁራን ላይ ጣቱን በመቀሰር የማያባራ ጅራፋን ሲያስጮህ ሁሌም የሚሰማ ፈረንጆቹ <<ሂፖክሪት>> የሚሉት <<ናርሲስት>> ነው።

ሰውየው ብዙ ጊዜ የምታዩት ጋዜጠኛ ርዕዮት ዓለሙ እና ተቦርኖ በየነ በሚያዘጋጁት <<ምን ጊዜም ሚዲያ>> ላይ የዘወትር እንግዳ ነው። እዛም ሌላም ቦታ ስለ አምሐራ ምሁራን ሲለፈልፍ፤ ስለ ጀነሳይደም አለመፈጸሙ ሲራቀቅ ታደምጡታላችሁ።ዮናስ ብሩ የጸረ አምሐራው የኦነጉ ጠ/ሚ የአብይ አሕመድ ደጋፊ ሆኖ ከዳኒኤል ክብረት በባሰ ዋና አፈቀላጤ ሆኖ ሲስቸግረን የነበረ ነው። አሁን ስለ አምሐራ ስቃይ ተቆርቋሪ ሆኖ የአምሐራ ምሁራንን አላዳናችሁትም ወዘተ… እያለ ሌት ተቀን ሲጮህ መስማት ትንሽ ይሉኝታ የማይሰማው ሰው ነው። 

ፍሬ ነገሩ ሃቅነት አለው።የአምሐራ ልሂቃን ብቻ ሳይሆኑ የኢትዮጵያ ምሁራን ባጠቃላይ ለሕዝባቸው ስቃይ በእንዝህላልነታቸውና አጥቂውንም በመደገፍ ተጠያቂ ናቸው እያልኩ ስረግማቸው እንደነበር እኔን ለዘመናት የምታውቁኝ ሁሉ ታውቁኛላችሁ። ያንን እዚህ ጊዜ አላባክንም።

ዮናስ ብሩ ግን ልዩ የሚያደርገው “ጀነሳይድ” (የዘር ማጥፋት) ወንጀል ኢትዮጵያ ውስጥ አለመፈጸሙ የሚከራከረውና እንደ ማስረጃ አድርጎ የሚያቀርበው ተጎጂዎቹ በሚያቀርቡት ስሞታና በሚወሰድባቸው የጭፍጨፋው ዘዴና መንገድ ሳይሆን  <<እንደ እነ ፕሮፌሰር መስፍን የመሳሰሉ ቡድኖች እና እንደ ኢንተርናሺናል ኮርት (አይ ሲ ሲ) ፤ ዩ ኤን እና የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን>> የመሳሰሉት ደርጅቶች “ኢትዮጵያ ውስጥ ጀነሳይድ/የዘር ማጥፋት/ አልተፈጸመም ብለዋልና “አልተፈጸመም” ብሎ ይከራከራል።

ዮናስ ብሩ ብቻ ሳይሆን አምሐራ ላይ ጀነሳይድ አልተፈጸመም እንዲሉለት ትሕነጎችም ፤ ብርሃኑ ነጋም፤ ዳንኤል ክብርትም የመሳሰሉ ለተጨማሪ ማስረጃ እንዲሆኑለት ቢጠቅስ ልጠቁመው። እንኳን ዮናስ እንደ ማስረጃ የጠቀሳቸው ተቋማትና ቡድኖች ቀርቶ ትልቁን የተባበሩት መንግሥታት የሰው ልጅ መብት መከታ ተብየው ድርጅት ለምስክርነት ቢያቀርብም፤ የተባበሩት ምናምን የሚባሉት፤ አሜሪካ ምናምን ፤ ጀኔቫ ምናምን ፤አውሮጳ ምናምን የሚባሉት ሁሉ እንኳን የኢትዮጵያ ዕልቂት (እነሱ የሚፈልጉትና የሚያቀጣጥሉት) ቀርቶ ሩዋንዳም ብሩንዲም ግልጽ የዘር ጭፍጨፋ ሲደረግ አንዳልተፈጸመ ዓይናቸውና ጆሮአቸው የዘጉ ናቸው።

“CONCPIRACY  TO MURDER – THE RWANDA GENOCIDE – BY LINDA MELVERN” ሳነብ በብሩንዲም ይሁን ረዋንዳ የዘር ማጥፋቱን ክንዋኔውና ደረጃው ተፈጽሞ እያዩም ዓለም ጆሮውን መክደኑን ሳነብ ልክ ኢትዮጵያ ውስጥ ተመሳሳይነቱ 90 ከመቶ ነው።

ከነገድ መታወቂያ እያዩ መጨፍጨፍ ጀምሮ እስከ ዘርና ሃይማኖትን ለይቶ መጨፍጨፍ እስከ በጭፍጨፋው የመንግሥት ሃላፊዎችና ሥርዓቱ ጭፍጨፋውን መመመራቱን  ተጨፍጫፊዎቹ እንዳያመልጡ መንገድ መዝጋት ፤ ከሚኖሩበት አካባቢ ባስቸኳይ እንዲወጡ ማወጅ፤ በግድያው ላይ ገጀራ፤ ቢላዋ፤ ጠመንጃ መጠቀም ፤ አካለትን መቆራረጥ ፤ ቤቶቻቸውችን በእሳት ማቃጠል፤ የመሳሰሉ የጭፍጨፋ ዘዴዎች ፤ እንዲሁም ጠላት የተባለው መለያ ስም መስጠት፤ ለምሰዳሌ ሁቱዎቹ ቱትሲዎችን INYENZi (ኮክሮች/colonizers/ድምበር ጥሶ የገቡ “ወራሪዎች”) ሲልዋቸው ፤ ኢትዮጵያም አክራሪ አሮሞዎቹና አክራሪ ሶማሊ ነፃ አውጪ ድርጅት እና በሶማሌ የወያኔ መንግሥት ተወካይ “አብዲ ኢሌ” ጨምሮ አምሐራን NEFTEGNA “ነፍጠኛ/Colonizer/ያለ ክልሉና ያለ አገሩ በወረራ የኖረ” ከሚሉት “የመለያ መጠሪያ” ወዘተ…  ስንመለከት በሁለቱም አገሮች የተደረጉ እና እየተፈጸሙ የጭፍጨፋ መንገዶች በሁለ ፣ማቸው አንድ ናቸው።

 በተለይ ድግሞ መጽሐፉ ላይ ስለ BURUNDI እንዲህ ይላል፡

<< In the years between 1959 and 1994 the idea of genocide, although never officially recognized, became part of life. … In a special report produced by the Carnegie Endowment for International Peace, congressional aide was quoted: <<By the end of May, we knew it was genocide from official classified information from the State Department, the reaction from the UN was muted. …. ’Then just like Rwanda, AFTER FEW DAYS IN THE HEADLINES, Burundi sank back into obscurity. The killing continued.>>

ባጭሩ ላለማስረዘም “<ብሩንዲ ውስጥ በግንቦት መጨረሻ፣ ከእስቴት ዲፓርትመንት ይፋዊ ሚስጥራዊ መረጃ ቡሩንዲ ውስጥ በሁቱዎች የተፈጸመው ጭፍጨፋ የዘር ማጥፋት መሆኑን እናውቅ ነበር፣ ይህንን በሚመለከት የተባበሩት መንግስታት ይህንን ቢያውቅም ከመናገር ተቆጠበ። …. ከዚያ ልክ እንደ ሩዋንዳ ከጥቂት ቀናት ከርዕሰ አንቀጾች ጫጫታ በላ ምንም ሳይደረግ ቡሩንዲ ወደ ጨለማዋ ህይወትዋ ተመለሰች። ግድያውም ቀጠለ።’ ይላል።

ስለ ሩዋንዳም ያነበብከት መጽሐፍ እንዲህ ይላል

<<…The fact of genocide was never officially acknowledged, no one was punished. Rwanda slept back into obscurity>> 

<<...የዘር ማጥፋት እውነታ መቼም በይፋ አልተረጋገጠም በዘር ማጥፋት ወንጀል ከተካፈሉት ሁሉ አንድም ሰው አልተቀጣም። በዚህም ሩዋንዳ ድቅድቅ ጨለማ ውስጥ ገባች።>> ይላል።

ኢትዮጵያ ውስጥም በ35 አመት ውስጥ ይህ ሁሉ ደም መፍሰስና ጭፍጨፋ ፤ ጦርነት፤ ዕልቂትና መፈናቀል ፤ የጅምላ ዕስር ሲፈጸም አንድም “በመንግሥት ላይ ያሉ ወይንም የነበሩም ይሁኑ በምንግሥት ሐላፊነት የሌሉና ያልነበሩ የወንጀሎቹ አቀናባሪዎች ፤ፈጻሚዎች እና “ሐላፊዎች” አንድም ሰው አልተቀጣም።እንደውም ታስታውሱ እንደሆን ከሁለት አመት በፊት ወለጋ ውስጥ ለመቁጠር የሚያዳግት አምሐራዎች ሲጨፈጨፉ ፤ የመንግሥት ምክር ቤት ተብሎ በተሰየመው ፓርላማ ተብየው ምክር ቤት ፤ ሰል ተጨፈጨፉት ነብሳት የአምሐራ “ክልል” ተወካይ በክርስትያን ታደለ ፀሎት እንዲደረግ ሲጠይቅ እንደተከለከለ የሚታወስ ነው። ። ይህ የሚያሳየው ጭፍጨፋው መንግሥታዊ እጅ እንዳለበት የሚያሳይ ነጋሪ ምልክት ነው። ኢትዮጵያ ውስጥ ጀነሳይዱ በመንግሥት ዕውቅና የተደረገ ነው።

ሩዋንዳም ከፍተኛ ጭፍጨፋ በቱትሲ ላይ ሲፈጸም እንደምታስታውሱት የተባባሩት መንግሥታት ሰላም አስከባሪ በሩዋንዳ ተጠሪ የነበሩት ካናዳውው ሌ/ጀኔራል ሮሚዮ ዶልየር  ሩዋንዳ ውስጥ ጭፍጨፋ እየተካሄደ ነውና ከቁጥጥር ውጭ ከመሆኑ አስቀድሜ ጭፍጨፋውን ለማስቆም እንዲመቸኝ ተጨማሪ ወታደርና ወታደራዊ ቁሳቁሶች፤ አይሮፕላኖች ወዘተ… ይላክ ብሎ ለተባበሩት መንገሥታት ተደጋጋሚ ተማጽኖ ቢያቀርቡም ፤ ምን ነበር የተሰጣቸው መልስ? መልሱ የሚገርም ነበር። ግድያው በሚያዝያ ወር ከተጀመረ በኋላ ጄኔራል ዳላይር የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ተጨማሪ ድጋፍ እንዲላክልኝ ብለው በድጋሚ ቢማጸኑም፣ በመያስደነግጥ ሁኔታ ጥያቄው ውድቅ ተደረገ። የዘር ማጥፋት በተጀመረ በጥቂት ቀናት ውስጥ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት በሀገሪቱ የሚገኘውን የተባበሩት መንግስታት የሰላም አስከባሪ ሃይል ከ2,500 ወደ 270 ወታደሮች እንዲቀንስ ወሰነ

ይህ ሁሉ እየታወቀ ዶ/ር ዮናስ ብሩ “አይ ሲ ሲ” እንዲህ አለ  ሰብአዊ ኮሚሽን ኢትዮጵያ ውስጥ ጀነሳይ ተፈጸሟል ለማለት ከተሰጠው የዘር ማጥፋት ክራይቴሪያ አያሟላም “እንደውም መሳቂያ  ነው የሆኑት” ወዘተ… " እያለ ሲያሾፍ መደመጡ የሚያሳዝን ነው።  የተጠቀሱ ድርጅቶች መልሳቸው ለአምሐራ ሕዝብ የሚሆነው ልክ ቡሩንዲ እና ሩዋንዳ ለይ እንደተጫወቱት ጨዋታ በአምሐራ ጭፍጨፋም መልሳቸው ተመሳሳይ ነው።

ዮናስ በሚያስቆጣ ንግግሩ <<ሥርዓቶቹ ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ አማራው ሲይሰተማቲክ ታርጌትድ ሆኗል>> ይልና ሆኖም <<ጀነሳይድ አልተፈጸመም>>፡ <<የዘር ማጥፋት መፈጸሙን ማስረጃ ማቅረብ  አይሲሲ ኮርት ላይ ሳይሆን ሸክሙ ተጎዳሁ በሚለው ወገን ነው ሸክሙ።>> ይላል። ለአምሐራው በሩዋንዳ ጭፍጨፋ ወቅት ከተባባሩት መንግሥታት ለጀኔራል ሮሚዮ  ከተሰጠው መልስ ውጭ ኢትዮጵያ ውስጥ ለተጎዳው ወገን የተለየ መልስ አይጠበቅምና ሸክሙ ፍትሕ አሰፍናለሁ በሚሉት ድርጅቶች ላይ እንጂ በተጎጂው አይደለም። በተጎጂ ላይ ሸክሙ ሞልቶ የፈሰሰ ነው።

ዮናስ እንዲህ ይላል፡

<<ዩኤንም ሆኑ ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉት ሰብአዊ መብት ተቋማት ኢትዮጵያ ውስጥ “ጀነሳይድ ተፈጽሟል የምንልበት ኤቪደንስ የለም ነው ያሉት>> ይላል። ሩዋንዳ ውስጥ ጀነሳይድ አልተፈጸመም የሚለው ዩ ኤን እና የስርዓቱ ተቀጣሪ የሆኑት የሃገር ውስጥ ተቋማት ምን ሊሉ ይጠበቃል? ሌላ ቀርቶ “ጣሊያን ኢትዮጵያን ስትወር” የተሰጠው መልስ ዶ/ር ዮናስ ብሩ እንዴት ዘነጋው? ኢትዮጵያ እኮ በክርስትያንነትዋዓድዋ ድል በማግኘትዋየዓባይ ወንዝ አምንጪ ባለቤት በመሆንዋ በበርካታ የጠላት ዓይን ውስጥ የገባች አገር ነች።

እጅግ አንጀት የሚያሳርረው “የናርሲስቱ” ዮናስ ብሩ ንግግር ደግሞ የሚከተለው ነው።

<< ጀነሳይድ ተፈጽሟል እየተባለ የሚነገረው እንደ ፖለቲካ አጀንዳ ለመጠቀም ተብሎ እወንደሆነ ቢገባኝም “ማተር” የሚያደርገው ግን ኢትዮጵያውስጥ ጀኖሳይድ አምሐራውም፤ ኦሮሞውም፤ ትግሬውም፤ ጋምቤላውም፤ ጉራጌውም…. ወዘተ… (ኢትዮጵያ ውስይ) አልተፈጸመም የሚለው ነው።>> ይላል።

 እውነት ጀነሳይድ ተፈጽሟል እየተባለ የሚነገረው እንደ ፖለቲካ አጀንዳ ለመጠቀም ተብሎ ነው? አምሐራ እስላም እና አምሓራ ክርስትያን በመታወቂያችን ተለይተን ከጭፍጨፋው እንዳናመልጥ ተከበን፤ ነብሰ ጡሮች ሆዳቸው እየተቀደደ ህጻኑን እየቆራረጡ እናትየው ከሞተችም አፍዋ ላይ ከትተው፤ የተረፈውም የአምሐራ ሥጋ ይጣፍጣል እያሉ የሰው ሥጋ የበሉ ፤ የሰው ደም የጠጡ፤ የሞተ የወንድ ሬሳ የሚጋሰሱ የሰው አራዊቶች ናቸው የገጠሙን እያሉ ከግድያ ያመለጡ “አብየት የፍትህ ያለህ” ያሉ ተጎጂዎች አውነት ለፖለቲካ አጀንዳ መጠቀሚያ ብለው ነው “ጭፍጨፋ ተፈፀመብን” የሚሉት? 

  ጸሐፊ ተሻለ መንግሥቱ የተባለ ከጥቂት አመታት በፊት የጻፈውን ለዮናስ መልስ ቢሆን ልጥቀስ፡

ነፍጠኛን (አማራን) አጥፍተን በኦሮሙማ የገዳ ሥርዓት የሚመራ ታላቁን አባት ሀገር ኦሮምያን እንገነባለን!” ብሎ በመነሳት በየቦታው የሚገኝን አማራ የሚያርድና የሚያሳርድ አክራሪ ኦሮሞ መኖሩ ለጄኖሳይድ መኖር ዋናው መገለጫ ሊሆን  አይችልም? ከተፈለገም የወደቀውን ፀረ-አማራ የሕወሓት ማኒፌስቶ መጨመርም ይቻላል እኮ ይቻላል፡፡ ይላል ተሻለ መንግሥቱ  (“ኢትዮጵያ ውስጥ ጄኖሳይድ አልተፈጸመም” የሚባለው እውነትነውን? ሲል ጸሐፊ ተሻለ መንግሥቱ ከጥቂት አመታት በፊት የጻፈውን ዮናስ ሊያጣጥለው ይሆን።

ዮናስ በሰው ደም የጎመዘዘ ቀልድ ከመቀለድ ተሎ ቢወጣ አስተዋይነት ነው።እስኪ ዮናስ ብሩም ሆነ አይ ሲ ሲም ይሁን በሰው ደም የሚቀልደው የተባባሩት መንግሥታት ሰብአዊ መብት መከላከል ድርጅት እውነት ጀነሳይድን ለመካለከልና ጥፈተኞችን ለመቅጣት የወጣው ሕግ የሚዳኙ ቢሆኑ ታች ከማቀርበው የሚከተለው የራሳቸው ሕግ ኢትዮጵያ ውስጥ አልተፈጸመም?

የዘር ማጥፋት ኮንቬንሽን፣ ወይንም የዘር ማጥፋት ወንጀል መከላከልና መቅጣት ኮንቬንሽን በመባል የሚታወቀው፣ የዘር ማጥፋት ወንጀልን የሚገልጽ እና ወንጀል የሚፈርጅ ዓለም አቀፍ የህግ ስምምነት ምንድ ነው የሚለው?

“In the present onvention, genocide means any of the following acts committed with intent to destroy, in whole or in part, a national, ethnical, racial or religious group, as such:

በአሁኑ ኮንቬንሽን ውስጥ የዘር ማጥፋት ማለት አንድን ብሔር፣ ብሔረሰብ፣ ዘር ወይም ሃይማኖታዊ ቡድንን በሙሉ ወይም በከፊል ለማጥፋት በማሰብ ከሚከተሉት ድርጊቶች ውስጥ የትኛውም ሊሆን ይችላል፡-

ከታወቁት 8 ቱ የጀነሳይድ ደረጃዎችን መዘርዘር ትቼ እንደገባን ባጭሩ እነዚህን ልግለጽ፦

() የቡድኑ አባላትን መግደል;

 

() በቡድኑ አባላት ላይ ከባድ የአካል ወይም የአእምሮ ጉዳት ማድረስ;

 

() አካላዊ ውድመትን በሙሉ ወይም በከፊል ለማምጣት የተሰላ የቡድን የሕይወት ሁኔታዎችን ሆን ብሎ ማድረስ;

 

() በቡድኑ ውስጥ መውለድን ለመከላከል የታቀዱ እርምጃዎችን መተግበር;

 

() የቡድኑን ልጆች በግዳጅ ወደ ሌላ ቡድን ማዛወር”[12]

 

(a) Killing members of the group;

(b) Causing serious bodily or mental harm to members of the group;

(c) Deliberately inflicting on the group conditions of life calculated to bring about its physical destruction in whole or in part;

(d) Imposing measures intended to prevent births within the group;

(e) Forcibly transferring children of the group to another group”[12].

እነዚህ ሁሉ ዶ/ር ዮናስ ብሩም ሆነ እራሱ አይ ሲ ሲ እና የተባባሩት ምንግሥታት ኢትዮጵያ ውስጥ በጋምቤላ አኝዋኮች ላይ (የኦባም ሜቶ ክላን/ዘሮች) እና አምሐራ (ሶማሊ ኦጋዴን ኦረሚያ በሚባለው አርሲ/ወለጋ….) በጋሞ ማሕበረሰብ ኗሪዎች ቡራዩ/አሸዋ ሜዳ/ ላይ እንዲሁም ትግሬዎችም  ላይ (በተራ ቁጥር A B C E) ልክ ናዚዎች በይሀዶች ላይ እንዳደረጉት <<የጅምላ አፈሳ ኮነስንትረሺን ካምብ አስገብቶ በመላዋ ኢትዮጵያ ያሉ ትግሬዎች  አፍሶ የሕሊና እና አካል ጥቃት ዮናስ ብሩ ሲከላከልlት የነበረው በኦነጉ አብይ አሕመድ ትዕዛዝ በትግሬዎች ላይ (A B C E) አልተፈጸመም?  ሌሎችም እዚህ ያልሄድኩባቸው ወዘተ…ወዘተ… ላይ በተቀመጠው ዝርዝር መስፈርት <<ዘርን ማጥፋት>> ወንጀልና እቅድ አልተፈጸመም? አምሓራው ላይ ግን ሁሉም A B C D E ተፈጽመዋል።

ለምሳሌ በወያኔ ዘመነ ንግሥና ወቅት አምሐራው ላይ ሁሉም አይነት የዘር ማጥፋት ሲፈጸም በተራ ቁጥር “D” አምሐራው ላይ ብቻ ተፈጽሟል። ይህንን በሰፊው ለማንበብ ወዳጄ ዶ/ር አሰፋ ነጋሽ ያቀረበው ዘገባ ያንብቡ፡

 << PERPETRATING GENOCIDE OR PROMOTING FAMILY PLANNING? THE UNETHICAL USE OF BIRTH CONTROL PROGRAM AS INSTRUMENT OF AMARA ETHNOCIDE

Assefa Negash, M.D. Amstelveen, Holland – the 17th of July 2017

የወያኔ የጤና ሚኒሰትርና የወያኔ መንግሥት እውቅና ትዕዛዝ መሰረት ኖርፕላንት የሚባል የእርግዝና መከላከያ ዘዴ 10 አመት ጀምሮ ያሉ ልጃገረዶች አራጌ ማርያም ተብሎ ወደሚጠራው ትምህርት ቤቷ ነጮችና ሀገሬኛዎች አብረው በመምጣት የኖርፕላንት የእርግዝና መከላከያ መጠቀም እንዳለባቸው እንዲወስዱ አንዴት እንደተደረገና አንዳንዶቹም “ቺፕስ” ከቆዳቸው ሥር ተተክሎላቸው ለበሽታና ለስቃይ እንደተዳረጉ የዶ/ር አሰፋም ሆነ የሌሎች ዘገባዎችን መመልከት ትችላላችሁ።

የጀነሳይዱ ተያያዢነቱ የነ << ሄንሪ ክሲንጀር>> እና  የነ <<ቢል ጌት እና መሊንዳ ፋውንደሺን>> የሕዝብ ብዛት  ቅነሳ በኢትዮጵያ ሰነዱ ላይ ትመለከታላችሁ። እንደተባለውም አምሐራው በ2. ሚሊዮን በላይ ሕዝብ ከሕዝብ ቆጣራ አንደቀነሰ ፓርላማ ውስጥ የተነገረው ታስታውሳላችሁ። (d) Imposing measures intended to prevent births within the group; የሚለው አምሐራው ላይ የሕዝብ ብዛት እንዲቀንስ እና ዓይነስውራን እንዲበዙ እንዲሁም የህጻናት ሞት እንዲከሰት ተደርጓል። ስለዚህ ዶ/ር ዮናስ <<ሸክሙ በ ዩ ኤን ወይንም በ አይ ሲ ሲ ሳይሆን ተቀጠቂው የማቅረብ ሃላፊነት አለበት>> እያለ ዮናስ የሚያሾፈው ጎምዛዛ ፌዝ በእውነተኛው ሰነድ ላይ መቀለድ ነው። ይህ ሁሉ ዘገባና ወንጀል <<ጀነሳይድ ተፈጽሟል እየተባለ የሚነገረው እንደ ፖለቲካ አጀንዳ ለመጠቀም ተብሎ ነው >> እያለ መቀለዱ በአምሐራም ሆነ በጋምቤላ (Anuak አኝዋክ) እና በጋሞ ሰዎች ህይወት ላይ መቀለድ ነው።ለዚህ ተጠያቂ የቢል ጌት እና የኦባማ የሱዛን ራይስ ወዳጅ/ተላላኪ/  የዛሬ የዓለም ጤና ጥበቃ ተብየው ዲሬክተር የወያኔው “”ሲ ሲ”” ዶ/ር ቴድሮስ  አደሃኖም ገብረየሱስ  ብዙ ሰዎች በዚህ ወንጀል ተባባሪነት ይከሱታል።

ልክ እንደ ሩዋንዳው ጀነሳይድ ኢትዮጵያ ውስጥ በተደጋጋሚ ለብዙ አመታት በመንግሥት አስተባባሪነት አምሐራው ላይ የተፈጸመውን ጀነሳይ ዮናስ ብሩ ቢገባው ከሚሊዮን ወንጀሎች አንዱን ልጥቀስለት፡(የባለውን አዋጅ በክፍል 1 እንደማቀርብ አትዘንጉት)።

አንድ ስማቸው እንዲገለጽ ያልፈለጉ የጊምቢ ባለስልጣን ለቢቢሲ አማርኛ በሰጡት ቃለ ምልልስ እንደተናገሩት "የጸጥታ ሃይሎች" ሰኔ 11 ቀን 2007 በጊምቢ የተፈፀመውን ጭፍጨፋ አንድ ቀን ቀደም ብሎ ቀበሌውን ለቀው እንዲወጡ መደረጉን ይገልጻሉ። ይህ የሚያሳየው በአማራ ላይ የደረሰውን ጭፍጨፋ የሚያሳይ በመንግሥት ቅንብር የተፈጸመ መንግሥታዊ የዘር ጭፍጨፋ ጀነሳይድ ነው

በአንድ ጉድጓድ ውስጥ 22 ልጆቻቸውን እና የልጅ ልጆቻቸውን ጨምሮ 61 ተጎጂዎችን የቀበሩ አዛውንቱ አቶ መሀመድ ዩሱፍ ለቢቢሲ እንደተናገሩት በምን ሁኔታ ላይ እንዳሉ የጠየቃቸው የመንግስት አካል እንደሌለ ተነግሯል።ጊምቢ ላይ የተፈጸመው ጀነሳይድ ወንጀል በአብይ አህመድ እና በናዚ ኦነግ ጥምረት አንደሆነ ሩዋንዳ ላይ………..ያነበብነው ተመሳሳይነት አለው። ዮናስን በምን ማስረጃ እናስተምረው?

የዘር ፍጂት ኢትዮጵያ ውስጥ ለ35 አመት ያለ ማቆም ተፈጽሟል። በአጭሩ አንድ ነገድ ወይ ጎሣ በሌላው ጎሣ ወይም ነገድ ላይ ጥላቻንና በቀልን አሳድሮ ከምድረ ገጽ ሊያጠፋው ይፈልግና ከማሰብ ጀምሮ በማቀድ፣ ያሰበውን በመሰሎቹ መሃል በመቀስቀስና በማነሳሳት፣ ያነሳሳውን ወገኑን በጠላው ነገድ ላይ እንዲዘምት በማዘጋጀት፣ የዕልቂት ቅድመ ዝግጅቶችን በማከናወን በመጨረሻም ሃሳብና ዕቅዱን ወደተግባር ለውጦ ግዳይ ማስቆጠር ማለት ነው፡፡ ይህ ደግሞ ብዙ መራቀቅንና ፍልስፍናን የሚጠይቅ ጉዳይ አይደለም፡፡ ዶ/ር ዮናስ ብሩ ይህንን ቀላሉ (ኤለመንታሪ ዕውቀት) ለማወቅ ሆን ብሎ ለማወዛገብ ካልሆነ እንዴት ኢትዮጵያ ውስጥ የለም ሊል ይችላል?

የት ሆፒታል እንደሆነ አላውቅም፡ ይላል ጸሐፊ ተሻለ መንግሥቱ ጀነሳይደ ኢትዮጵያ ውስጥ አልተፈጸመም ሲሉ የሰማቸው ለነ ፕሮፌሰር ብርሃኑና ኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ ሲገልጽ ፤ እንዲህ ሲል፦

 <<አንድ ታማሚ በህክምናው ዓለም በሀኪሞች ቋንቋኢክስፓየርያደርግና ወደ ሬሣ ክፍል ይላካል፡፡ በተላከ በማግሥቱ የሬሣ ክፍል ሠራተኛው ያን በድን ከፍኖ ቤተሰብ ወዳመጣው ሣጥን ሊከተው ሲል ሟቹ ድንገት ከሞት ይነቃል፡፡ እንደነቃም በድንጋጤምንድን ነው? ምን እያደረግኸኝ ነው?” በማለት ከፋኙን ይጠይቀዋል፡፡ ከፋኙም ሥራውን ሳያቋርጥሞተህ ነዋ! እየገነዝኩህ እኮ ነውይለዋል፡፡ ከሞት የነቃው ሰውዬምአሃ! አሁንማ ከሞት ተመለስኩ አይደል? ተወኝ እንጂ!” በማለት ይከራከረዋል፡፡ ሬሣ ገናዡምወይ ሞኞ! አሁን አንተ ከዶክተሩ ልትበልጥ ነው? በል ሞተሃል ተብለሃል አርፈህ ተገነዝ? አለው ይባላል፡፡>> ይላል።

እነዚህምሁራንም” (ፕሮፌሰር ብርሃኑና ዳንኤል በቀለ እኔም ልጨምር ዶ/ር ዮናስ ብሩ) ስንትና ስንት አማሮች ወደውና ፈቅደው ባልተፈጠሩበት ማንነታቸው ምክንያት አንገታቸው ተቆራርጦ፣ ጭንቅላታቸው ተፈልጦ፣ ወገባቸው ተጎማምዶ ሰው ለሚባሉ የሰው አውሬዎችና የዱር አውሬዎች ሲሣይ ሆነው መቅረታቸውን፣ እንደየእምነታቸው የጸሎት ፍትሃት በክብር እንኳን እንዳይቀበሩ እንደአልባሌ ቆሻሻ በግሬደር በአንድ ጉድጓድ ውስጥ መቀበራቸውን ልቦናቸው እያወቀ ለተቀማጭ ሰማይ ቅርብ ነውና እነሱና የነሱ የሆነ ስላልሞተ ብቻ ይህን መሳይ ወራዳ መልስ ሲሰጡ ይስተዋላሉ፡፡ የኛ የብዙዎቻችን ችግር የሌሎችን ችግር መረዳት አለመቻላችን ነው፡፡ አማሮች የተገደሉት በአማራነታቸው እንጂ በሰውነታቸው አይደለም፡፡ ይህንን እውነታ መካድ መማር ሳይሆን መደደብ ነው ይላል። ተሻለ መንግሥቱ።

እውነት ነው ፤ መማር እንደዚህ የሚያደነቁር ከሆነ ማይምነት ተፈልጎ የማይገኝ ወርቅ ነው፡፡ በመተከል፣ በወለጋ፣ በበደኖ፣ በአርባ ጉጉ፣ በአሰቦት፣ በአጣዬ፣ በከሚሴ፣ በሸዋ ሮቢት፣ በቤንሻንጉል፣ በባሌ፣ በሐረር፣ … በአማራነታቸው ምክንያት የሞቱ ዜጎች ደምና አፅም በገዳዮች ብቻ ሳይሆን የግድያውን ዓይነት በሚክዱ ሰዎች የእንቅልፍ ሰዓት እየመጣ ዕረፍት ይንሳቸው፡፡ ሁለተኛ ግድያ እኮ ነው!! ይላል ተሻለ።

 እንደ እነ ዶ/ር ዮናስ ብሩ ዶክተር ከመባል እውነትም ማይምነት ተፈልጎ የማይገኝ ወርቅ ነው።

ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay