Friday, September 18, 2020

የዓለም አቀፍ የወንጀል ፍርድቤት ኢትዮጵያ ውስጥ እየተፈጸመ ላለው የዘር እና የሃይማኖት እልቂት የሰጠው አሳዛኝ መልስ ላስነብባችሁ! ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ ድገጽ አዘጋጅ) Friday, Sept 18, 2020

 

የዓለም አቀፍ የወንጀል ፍርድቤት ኢትዮጵያ ውስጥ እየተፈጸመ ላለው የዘር እና የሃይማኖት እልቂት የሰጠው አሳዛኝ መልስ ላስነብባችሁ!

ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ ድገጽ አዘጋጅ) Friday, Sept 18, 2020

 


አርበኛው ወንድሜ “አገሬ አዲስ” የሚመራው ዓለም አቀፍ የኢትዮጵያውያን መድረክ” የተባለው የመብት ተሟጋች ድርጅት አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያንን በማስተባበር ጊዜኣዊ መንግሥትነት ነኝ በማለት ክፍተቱን በመጠቀም በአሳሳች “የሕሊና ጠለፋ ስልት” በመጠቀም የሕዝብን ጩኸት በመንጠቅ ሥልጣን ላይ ተኮፍሶ የሚገኘው የኦነጎቹ የኦሮሙማው ፖለቲካ ዕቅድ ዋና አስፈጻሚ ሆኖ በሕዝባችን ላይ የዘርና የሃይማኖት ጭፍጨፋ እንዲካሄድ ዋና ተዋናይ የሆነው የወያኔ (የኢንሳ የጠለፋ ዋና ሹም) ፤ የሻዕቢያ ሰላይ (ቅጽል ስም “ዓሳ ነባሪ”) እንዲሁም የኦ.ነ.ግ አባል በመሆን የሁለት “ዓለም ሰላይ” የነበረው “የወያኔ/ኢሕኣዴግ’ ኮለኔል የዛሬው ጠ/ሚ “አብይ አሕመድ” እየተመራ ባለው ፋሺስታዊና ሥርዓተ አልባዊ ሥርዓት እውቅና እና አስታጣቂነት ኢትዮጵያ ውስጥ አሁንም እየተካሄደ ያለው የሃይማኖትና የዘር ማጥፋት ወንጀል ለዓለም አቀፍ International Criminal Court (“ICC”) ፍርድቤት ባቀረበው አቤቱታ የተሰጠው አሳዛኝ መልስ እነሆ ጉዳችንን አንብቡ።

 

የፍርድቤቱ መልስ ከማንበባችሁ በፊት “አገሬ አዲስ” የሚመራው “ዓለም አቀፍ የኢትዮጵያውያን መድረክ” ለናንት ለኢትዮጵያዊያን አገር ወዳዶች የተማጸነውን ደብዳቤ ጥቂቱን ፍሬ ነገሮችን ጨምቄ ላስነብባችሁ፡

እንዲህ ይላል፡

 

መስከረም 4 ቀን 2013 ዓም(14-09-2020)

    ባለቤት ያቃለለውን አሞሌ ባለእዳ አይቀበለውም!

  ውድ ኢትዮጵያውያን በዚህ  ጽሁፍ ልናሳውቃችሁ የምንወደው ሁላችንንም በሚመለከት ጉዳይ ላይ የዓለም አቀፍ የወንጀል ፍርድ ቤት ድርጅታችን ላቀረበው አቤቱታ የሰጠውን መልስ ነው።

በተለያዩ ወቅቶች በተከታታይ በተለያዩ ያገራችን ክፍላተ ሃገር  ከተሞች   በተለይም ከሦስት ወራት በፊት  አሸባሪዎችና ነውጠኞች በሰላማዊ ዜጎች ላይ የፈጸሙትን ጭፍጨፋ ወይም እልቂት(ጀኖሳይድ) በተመለከተ ለዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት በአውሮፓውያን አቆጣጠር በጁላይ 15 ቀን 2020 አቤቱታ አቅርበን ነበር።አቤቱታውን ተከትሎ ፍርድ ቤቱ  ከዚህ ጋር አባሪ ያደረግነውን ምላሽ በዛሬው ዕለት ማለትም በአውሮፓውያን አቆጣጠር በሴፕቴምበር 14 ቀን 2020  ሰጥቶናል።

በላከልን ምላሽ እንደተብራራው የዓለም አቀፍ የወንጀል ፍርድ ቤት ለጉዳዩ ትኩረት የሚሰጠውና የሚያዬው በመንግሥታት በተለይም ወንጀሉ የተፈጸመበት አገር መንግሥት ለፍርድ ቤቱ ጥያቄ ሲያቀርብ  እንደሆነ በግልጽ አብራርቷል።አያይዞም ጉዳዩ በሌሎች አስተማማኝ ድርጅቶች በኩልም የተጠናቀረ ማስረጃ ያለው አቤቱታ ቢቀርብ ፍርድ ቤቱ ጉዳዩን ለማዬት እንደሚችልም ጨምሮ ገልጿል።

ውድ ኢትዮጵያውያን፣

 ይህንን ወንጀል አስመልክቶ በስልጣን ላይ ያለው የኢትዮጵያ መንግስት በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ  የወንጀሉ ተባባሪ እንደመሆኑና ያንንም ለመሸፋፈን የሚያደርገውን ማወናበድ  ስንመለከት ለተበደሉት ወገኖቻችን ጥብቅና በመቆም  ወንጀለኞቹ ተገቢውን ቅጣት እንዲያገኙ  በአገር ውስጥም ሆነ፣ለዓለምም ፍርድ ቤት አቤቱታ ያቀርባል  የሚል ግምት ሊኖረን አይችልም።ለይምሰል በአገር ውስጥ የሚካሄደው የፍርድ ሂደትም በሆነ ባልሆነው ምክንያት ሊቋረጥና ወንጀለኞቹ በነጻ የሚለቀቁበት ዕድሉ ከፍተኛ እንደሆነ የእኛም ሆነ የብዙዎች ስጋትና ጥርጣሬ ነው።ይህንን በዓለም ማህበረሰብ የተወገዘ ኢሰብአዊ የሆነ ድርጊት እንዳልተፈጸመ አድርጎ የማዬቱ አዝማሚያ ክህደት ከመሆኑም በላይ ዋጋ ቢስ በማድረጉ ሌሎቹ ትኩረት እንዳይሰጡት አድርጓል።ለዚያም ነው ባለቤት ያቀለለውን አሞሌ ባለዕዳ አይቀበለውም ያልነው።  

ስለሆነም በየአቅጣጫው የሚደረገው  የተበታተነ ጥረት በአንድ ብሔራዊ  የሕግ ባለሙያዎች ስብስብ በኩል ቢቀናጅ ሌሎቹን ሊያሳምንና የዓለም ፍርድ ቤቱን ትኩረት ሊያገኝ ይችላል ብለን እናምናለን።ለዚያም መንደርደሪያ እንዲሆን  ድርጅታችን ለላከው የአቤቱታ ደብዳቤ ያገኘውን ምላሽ ከዚህ ጥሪ ጋር አያይዘን ልከነዋልና ሳይውል ሳያድር አስፈላጊው እርምጃ እንዲወሰድ አጥብቀን እናሳስባለን።በተለይም የኦርቶዶክስ ተዋህዶና የእስልምና እምነት ተከታዮች የጥቃቱ ሰለባ በመሆናቸው ተቋማቱ ከሰብአዊ መብት አስከባሪ ድርጅቶች ጋር  በተቀናጀ መልኩ ለዓለም ፍርድ ቤት አቤቱታቸውን ቢያቀርቡ ተሰሚነት ሊኖራቸው ይችላል ብለን እናስባለን።

ምናልባትም ጉዳዩ የአፍሪካ ህብረትን ስለሚመለከት፣በአንድ አባል አገር ሕዝብ ላይ የተፈጸመና ወደፊትም ወደ ሌሎቹም ያፍሪካ አገሮች ሊዛመት የሚችል  ስጋት በመሆኑ፣ከሩዋንዳ ተመክሮ በመውሰድ  በኢትዮጵያ  መንግሥት በኩል መሰራት የሚገባው የጸረ ጭፍጨፋ( ጀኖሳይድ) አቤቱታ በህብረቱ በኩል ትኩረት እንዲያገኝ የማድረጉ ሥራ ቢሠራ ምናልባት ውጤታማ ሊሆን ይችላል የሚል ግምት አለን።ስለሆነም ጥረቱ ሁለገብ መልክ ቢይዝ እንደሚበጅ አምነን ትኩረት እንዲሰጠው ለማሳሰብ እንወዳለን።

ለፍትህና ለዴሞክራሲ አንድ ላይ እንቁም!

የሕዝባችንን መብትና የአገራችንን ክብር በዓለም አቀፍ መድረኮች እናስጠብቅ!!i

ዓለም አቀፍ የኢትዮጵያውያን መድረክ

International Ethiopian solidarity Forum(IESF)

E mail inter.ethiopiansolidarityforum1@gmail.com

 የፍርድቤቱን መልስ እነሆ ከታች አንብቡ፡

 

Dear Sir, Madam

 

On behalf of the Prosecutor, I thank you for your communication received on 17/07/2020, as well as any subsequent related information.

 

As you may know, the International Criminal Court (“the ICC” or “the Court”) is governed by the Rome Statute, which entrusts the Court with a very specific and carefully defined jurisdiction and mandate. A fundamental feature of the Rome Statute (Articles 12 and 13) is that the Court may only exercise jurisdiction over international crimes if (i) its jurisdiction has been accepted by the State on the territory of which the crime was committed, (ii) its jurisdiction has been accepted by the State of which the person accused is a national, or (iii) the situation is referred to the Prosecutor by the Security Council acting under Chapter VII of the UN Charter.

 

Based on the information currently available, it appears that none of these preconditions are satisfied with respect to the conduct described. Accordingly, as the allegations appear to fall outside the jurisdiction of the Court, the Prosecutor has confirmed that there is not a basis at this time to proceed with further analysis. The information you have submitted will be maintained in our archives, and the decision not to proceed may be reconsidered if new facts or evidence provide a reasonable basis to believe that the allegations fall within the jurisdiction of the Court. The decision may also be reviewed if there is an acceptance of jurisdiction by the relevant States or a referral from the Security Council.

I hope you will appreciate that with the defined jurisdiction of the Court, many serious allegations will be beyond the reach of this institution to address. I note in this regard that the ICC is designed to complement, not replace national jurisdictions. Thus, if you wish to pursue this matter further, you may consider raising it with appropriate national or international authorities.

 

I am grateful for your interest in the ICC. If you would like to learn more about the work of the ICC, I invite you to visit our website at www.icc-cpi.int.

 

Yours sincerely,

 Agere Addis

inter.ethiopiansolidarityforum1@gmail.com

Mark P. Dillon

Head of the Information & Evidence Unit

Office of the Prosecutor

 Post Office Box 19519, 2500 CM The Hague, The Netherlands Boîte postale 19519, 2500 CM La Haye, Pays Bas Telephone / Téléphone: + 31 70 5158515 • Facsimile / Télécopie: + 31 70 5158555 • http://www.icc-cpi.int

ዓለም አቀፍ የኢትዮጵያውያን መድረክ

International Ethiopian solidarity Forum(IESF)

E mail inter.ethiopiansolidarityforum1@gmail.com