Tuesday, October 3, 2023

የአባ ሰላማ ቄሮዎች እና የአምሓራ መነኮሳት በአክሱም ጌታቸው ረዳ የ Ethiopian Semay ድረገጽ አዘጋጅ 10/3/23


የአባ ሰላማ ቄሮዎች እና የአምሓራ መነኮሳት በአክሱም

ጌታቸው ረዳ

የ Ethiopian Semay  ድረገጽ አዘጋጅ

10/3/23

በዚህ ስዕለ ድምጽ (አውድዮ ቪድዮ) ተለጥፎ የምታደምጡትና የምትመለከቱት ንፁሀን የአማራ አረጋዊያን መነኮሳት << ወይንም ተጠልፈው ወይንም እንደ ጥንቱ ደግ ዘመን መስሎአቸው በቅንነት አክሱም ጽዮንን ለመሳለም ወደ አክሱም የሄዱ “ፖለቲካው ውስጥ የሌሉበትና ፖለቲካው የማያውቁበት እነዚሕ የእግዚአብሔር አገልጋዮች>>  የወያኔን “ጸረ አምሐራ ትምሕርት” እየተማሩ ባደጉ <<ጽንፍ በረገጡ የሃይማኖትና የነገድ አክራሪ” (ረሊጅየስ ፋናቲክ) ወጣቶች የደረሰባቸው ክብረ ነክ የሆነ አዋካቢ የፍጥጫ ጥያቄ በዚህ ቪዲዮ ትመለከታላችሁ።

በስዕለ ድምፁ ላይ ተቀርጾ የምታዩት እራሱን “ማሕበረሰላማ” ብሎ የሚጠራ <<የወያኔ አክራሪ ኦርቶዶክሳዊ ክንፍ>> የላከው “የአባሰላማ ቄሮ ነው”። በዚህ አሳዛኝ ትዕይንት መነኮሳቱ የደረሰባቸው ውስጣዊ ድንጋጤና መገረም “ልብ የሚሰብር፤ስሜት የሚፈታተን አሳዛኝ “ክብረ ነክ” ትዕይንት እንደተነኩ ከገጽታቸው እና ከጸጥታቸው መገመት ታያላችሁ።

 መነኮሳቱ ሳያስቡት የደረሰባቸው <<ዱብ ዕዳ>> ዋልጌው የወያኔው ቄሮ እንዲህ ሲል በደምፍላት እያንጓጠጠ ይጠይቃቸዋል፡-

<< የትግራይ ወጣት ሲረግፍ፤ ደም በደም ሲሆን የት ነበራችሁ?! ሊቃነ ጳጳሳት ሆነው ትግራዋይ ከሚገዛን ሰይጣን ይግዛን ሲሉ የት ነበራችሁ?! አቡነ ማትያስ እቤት ውስጥ ተዘግተው እንደነበር አታውቁም?! ትግራዋይ በመሆናቸው ብቻ ምግብ ተከልክለው ስንት መከራ ሲያሳልፉ አታውቁም?! ሊቃነ ጳጳሳት ሆነው <<መትረየስ ሲተኩሱስ የት ነበራችሁ?! ተደብቃችሁ ነበራችሁ? የት ነበራችሁ?!>>

በማለት ይህ ሁሉ ፋሺሰታዊ ፍጥጫና ማንጓጠጥ የሞላበት ያልታረመ “ትፋቱ” ወደ ሕሊናቸው ከተፋባቸው በኋላ፤ በሚገርም ሁኔታ <<ወያኔ የሚመራው የወያኔ የተዋህዶ እምነት ክንፍ የሆነው “አባ ሰላማ” የተባለ ሴት አስረጋዥና መነኮሳት ሴቶችን የሚደፍሩ “ዱርየ ጳጳሶች” የሚመሩት ኦርቶዶክስ መሳይ <<ሃይማኖታዊ የፖለቲካ ድርጅት መሪዎች>> ስዕል ያለበት የለበሰው ከናቴራ በኩራትና በትዕቢት እየተወጠረ ሲያሳያቸው ትንሽ ስቅጥጥ አላለውም። “ልጅ ለናትዋ ምጥ አስተማረች” የተባለው ምሳሌ ይሄው ጊዜው ይህ ጊዜ ነው

“አክሱም” በአንደኛ ደረጃ ምናልባትም ቀጥሎ “መቀሌ” ዛሬ ከማንኛቸውም የትግሬ ከተሞች በባሰ መልኩ ‘አክራሪ ኦርቶዶክሳዊ ፖለቲካ” (ፋናቲክ ኦርቶዶክስ squadrist  ወጣቶች) ተጠናክሮ በብዛት ሚታይባቸው ከተሞች ናቸው። አክራሪ ብሔረተኛነት አክራሪ ሃይማኖተኛነትን ይወልዳል (ወይንም በየተራ ይለዋወጣሉ)፡ ትግራይ ውስጥ እየታየ ያለው ይህ ነው።

ይህ ትናንት የተወለደ “ቂጡን ያልጠረገ” ግልገል “ፋሺሰት ወጣት” አንገቱ ላይ ለይስሙላ ያሰረው የውሸት ማተቡን እያሳየ  *ታቦተ ጽዮን ለማሳለም የመጡ ምንም የማያውቁ መነኮሳትን* (ምናልባትም ወያኔ እንደለመደበት ለፍጆታ ሲል እንግዶች አድርጎ ያሳይ እንጂ ከየገዳማቱ ተጠልፈው ሊሆኑም ይችላሉ) <<እኛ ግፍ ሲፈጸምብን የት ነበራችህ? ተደብቃችሁ ነበር?>> እያለ ሲጠይቃቸው፡

እኔ ደግሞ ለዚህ “ግልገል የወያነ ጊሰታፖ” በትውስታ ወደ ኋላ የምጠይቀው ጥያቄ <<27 አመት ሙሉ እነዚህ መነኮሳት እና የመሳሰሉ የዋልድና ሴት መነኮሳት በትግሬ ወያኔ ካድሬዎች  ሲደበደቡና ሲደፈሩ የት ነበር? እርሱን የወለደው ወላጅስ በወቅቱ የት ነበሩ? እናንተየ! እነዚህ ናላቸው የሳቱ ናቸው ተብሎ ሲነገር  እውነት ያልመሰለው ብዙ ሰው ነበር።

በ27 አመት “የትግሬ ሄጂመኒ/ስልቀጣ) ኢትዮጵያ ለነሱ ብቻ የተሰጠች ግዑዝ ዕቃ ነበረች። ሊቆርሷት፣ ወደብ አልባ ሊያደርጓት፣ ሊሸጧት፤ ሊለውጧት፤ ብጥስጥስዋን ሊያወጧት፤ በስጦታ ሊያበረክቷት ባለ ሙሉ ሥልጣን ነበሩ። ቻይናዎች ሰው ሲገድሉ ለዲፕሎማሲ ግንኙነት ሲሉ ገዳዩን በሕግ ላለመጠየቅ በነፃ ይለቋቸው ነበር። ዜጋ ለነሱ የሸቀጣቸው መገበያያ ነበር። የቻይና “ኢንቨስተሮች’ ‘የራሳቸው እስር ቤት’ መሥርተው ዜጎችን መደብደብና ማሰር፣ ደሞዝ ያለመክፈል መብት ነበራቸው “ያውም በኢትዮጵያ ምድር!!”

የምድሪቱ ሉዓላዊ የጠረፍና የምድር አካላትዋ በውጭ ኃይላት በ“ድሮን” (በሰው አልባ አውሮፕላን) ተደፍራ እንድትሰለል ፈቃድ የመስጠት መብታቸው ጥያቄ ውስጥ አይገባም ነበር። በውስጧ የሚንቀሳቀሱ ፍጡራን ሉዓላዊ ክብራቸው በባዕድ ይረገጥ አይረገጥ ለነሱ የተፈጠሩ ንብረቶች ናቸውና ዜጎች ምንም ዓይነት መብት የላቸውም ነበር። አምሐራ ዕስረኛ ላይ ‘ሽንት በላዩ ላይ እየሸኑ’ ፤ ይቀጠቀጡት ይገረፉትና በታሰሩ ዜጎች ላይ ግብረሰዶም ይፈጸምበት ነበር። ኢትዮጵያ 27 አመት ሙሉ የትግሬዎች “ቅኝ ግዛት” ነበረች

አገሪቱ በትግሬዎች ብቻ እንደተገነባች አድራጊ ፈጣሪ አድርገው እራሳቸው ራሳቸውን ሰማይ በመስቀል ስለሚክቡ ኢትዮጵያውያን ዜጎች በነሱ ፈቃድ ብቻ ይንቀሳቀሳሉ፤ ሲፈልጉ ያድኗቸዋል፤ ሲፈልጉ ይገድሏቸዋል፤ ሲፈልጉ ያሰድዷቸዋል፤ ያባርሯቸዋል፤ ይዘርፏቸዋል፤ይደበድቧቸዋል። ይህ የቅርብ ትዝታችን ነው።

ይህ ጮርቃ ይህ ግፍ ይወቅ አይወቅ ባላውቅም በሺዎች ሕይወት መስዋዕት የተገኘ የጦር ሜዳ ድል እና ድምበር መልሰው ለታሪካዊ ጠላት የማስረከብ መብታቸው የተጠበቀ ነበር፡፡ ያን ሲያደርጉ አይከሰሱም፤ ማን ያበደ አለ የሚጠይቃቸው?ተጠያቂዎችም ከሳሾችም፤ ፈራጆችም እነሱ ነበሩና የማይጠየቅ የማይገሰስ መብት ነበራቸው።

ይህ ሁሉ ግፍ ሲፈጸም ይህ <<ወጣት  የት ነበርክ ?!>> የማለት መብታችን የተጠበቀ ነው።  እርሱ ካልኖረ እርሱን የወለዱ ወላጆች የት ነበሩ? ይገርፉ፤ ታጋይ ሆነው አማራን ይገድሉ ወይስ ይመዘብሩ ወይስ ደግሞ ሰውን ሲያዋክቡ ውይስ ተመልካቾች ብቻ ነበሩ? ለመሊው ጥያቄአችን መልስ ለመስማት እንጓጓለን።  

ወያኔዎችና የወለድዋቸው ትውልዶች <<ክፉ ዕብዶችና ክፉ ዋሾች>>  ናቸው። ይህ ወጣት እነዚህን ምስኪን መነኮሳት አባ ሰላማ የተባለ አገርገንጣይ የፋሺሰቶች ኦርቶዶክስ መሳይ ሃይማኖት “ትደግፋላችሀ ወያስ አትደግፉም?” እያለ ከማስጨነቅ አልፎ፤ ስለ አባ ማስያስና ስለ መትረየስ ተኳሾች ጳጳሳት የሚነገርን ነገር አለው።

እንዲህ ይላል፡

<< አባ ማስያስ ትግራዋይ ስለሆኑ ምግብ ተከልክለው ለርሃብ እንደተጋለጡ ይነግረናል?! ሊቃነ ጳጳሳት ሆነው <<መትረየስ ሲተኩሱስ የት ነበራችሁ?! ተደብቃችሁ ነበራችሁ? የት ነበራችሁ? ብሎ መትረየስ ተኳሾች ጳጳሳት እንደነበሩ በዓይኑ እንዳየና እነሱ የት ተደብቀው እንደነበሩ እነዚህን በቁጥጠሩ ባለች ከተማ የተጠለሉ ምስኪን የአምሓራ መነኮሳቶችን ያስጨንቃቸዋል።

ይህ ዕብደት ተራ ዕብደት ብቻ ሳይሆን <<ክፉ ዕብደት>> ነው።

ስለ ‘ክፉ ዕብደት’ አንድ በየ በዚህ ልሰናበታችሁ፡

ነፃነት የሚባል ወዳጄ አለ፡ ወያኔዎችን ሲገልጻቸው “ክፉ ዕብዶች” ናቸው ይላቸዋል። 4 የታወቁ የዕብደት ዓይነቶች አሉ ይላል። Badmad, Mad-mad, Sad-mad, and Glad-mad. የሚባሉ።እነዚህ ሁሉ የዕብደት ዓይነቶች ወያኔ የተያዘበትን የአእምሮ ደዌ ለማወቅ ሞክሬ በመጠኑ የተጠጋጋልኝ የመጀመሪያው የዕብደት ዓይነት ነው – “ክፉ ዕብድ” ወይም “መጥፎ ዕብድ” የሚባለው ነው ይላል። ለምን ቢሉ << መጥፎ ዕብድ እየሣቀ መጥቶ በደቦል ድንጋይ ደረትህን ወይም ማጅራትህን መትቶ ሲጥ ያደርግህና በሞትህ “እየሳቀና እየተዝናና” በመጣበት መንገድ ሊመለስ ይችላል>> ይላል።

 እውነት ነው ወያኔዎችና ወያኔዎች ያስተማርዋቸው ትውልዶች እንደ ወያኔዎቹ ክፉ ዕብዶች ብቻ ሳይሆኑ ሁሉንም የዕብደት ዓይነቶች ያጠቃለሉ ክፉ ዋሾችም ናቸው። Please watch the Video posted below. 

ጌታቸው ረዳ