Tuesday, December 29, 2009

አብረን የምንጓዘዉ ወዴት ነዉ?

አብረን የምንጓዘዉ ወዴት ነዉ? ጌታቸዉ ረዳ www.ethiopiansemay.blogspot.com

የዘንድሮ ፖለቲካ ከምንም ጊዜ አስገራሚ፣ በእግሩ ሳይሆን በራስ ቅሉ ተዘቅዝቆ የሚራመድ ግርምቢጥ ፖለቲካ ሲሆን፣ ይህንን “ግልቡጥ” ፖለቲካ ይዘዉ የሚጓዙ “ግልብጦች” የያዙት የፖለቲካ ትግል እስካሁን ድረስ ሳትሰሙት አልቀራችሁም፣፣ መድረክ የተባለዉ አስገራሚዉ ስብስብ “የድሮ ገዳዬቻችን” ድረጅቱ ዉስጥ ገብተዉ ተመልሰዉ እንድያፍኑን በግል ጥያቄ አቅርቦላቸዉ እንደተቀላቀሉት በአሜሪካ ድምፅ ራዲዬ ከአዳነች ፍስሃየ ጋር ያካሄዱት ቃለ ምልልስ አረጋግጠዉልናል፣፣ ይህ ግብዣም አንድነት የተባለዉ ግዛቸዉ እየመራዉ ያለዉን ድርጅት በሊቀመንበርንት ስትመራዉ የነበረቺዉ “ብርቱካን መዲቅሳ” እንደሆነች ድሮ ስንከታተለዉ የነበረዉ ጉዳይ ነዉ፤፤ UDJ ወይም “መድረክ እየተራመዱበት ያሉበት የፖለቲካ አደረጃጀት ረጂም እንደማይጓዝ ካሁኑኑ ድሮም ዛሬም እየተገነዘብን ያለነዉ ኢትዬጵያዊያን የሚሰጡን መልስ አስገራሚ እየሆነ የመምጣቱ ጉዳይ ነዉ። “በወያነ መንግሥት ሥር ከፍተኛ ሐላፊነት የነበራቸዉ ባለሥልጣናት የፈለገዉ ወንጀል ቢፈጽሙም ዛሬ ወያኔን ስለተቃወሙ ያለፈዉ አልፏል ወደ ፊት እንጂ ወደ ሗላ አንመለስም” የሚል ነዉ። እነ ስየ አብርሃም ሆኑ እነ ነጋሶ እና ሌሎቹ በድንገትም ሆነ በእግዚአብሐር በሞት ከዚህ ኣለም ሳይለዩ በመጪዉ መንግስታዊ ሥርዓት ለመቀላቀል ከፈለጉም “ማስረጃዎች ሳይጠፉ፣ ሳይቃጠሉ ሳይሰወሩ ፣ሳይረሱ,፣….ያጠፉትን ጥፋት በይፋ ለመጪዉ ትዉልድም ሆነ ለሕሊናቸዉ በፍትህ ረገድ ያገለግል ዘንድ እንደ ገብረመድህን አርአያ እና እንደ እነ አስገደ ገብረስላሴ (ያዉም አስገደ የሚኖረዉ ወያኔዎች በሚኖሩት አገር እና ክፍለሃገር ኢትዬጵያ /ትግራይ) የመሳሰሉት የድሮ የወያኔ ባለስልጣኖች የድርጅቱ እና የግለሰቦች ወንጀል በማሕደር ዘግበዉ ለሕዝቡ በይፋ እንዳጋለጡት ሁሉ አዳዲሶቹ የመድረክ ድረጅት አባላትም በወያነ ትግራይ ሥር ሆነዉ የስተዳድሩ እና ይፈጽሙ እና ያስፈጽሙ የነበሩትን ዉሳኔዎች ይፋ ያድርጉ እና መቀጠል ከቻሉ መቀጠል ይችላሉ እያልን የኛ አቁዋም እየገለጽን ነዉ፣፣ እነ ስየም ሆኑ እነ ገብሩ አስራት የሚሰጡን መልስ “መጀመርያ አገሪቱን እናድን ሁላችንን የሚዳኝ መንግሥት ካቋቋምን በሗላ ያኔ ለፍርድ እንቀርባለን..” ይሉናል፣፣ እነ ገረመድህን አርአያ እነ አስገደ ገብረስላሴ ደፍረዉ ማስታወስ የሚችሉትን ያህል በማስታወሻ ዘግበዉ ይፋ ሲያደርጉ እነ ስየ እና ገብሩ ብዙ ምስጢሮችን የተካፈሉ እና የወሰኑ ሰፊ እዉቀት ያላቸዉ ባለስለጣኖች ግን በደፍኑ “አገር እናድን እና በሗላ እንነጋገርበታለን” በማለት ለምን ፈቃደኝነት ለማሳየት እንደለገሙ ግን በቂ ማብራሪያ አልሰጡበትም። እና እና ብዙ ሰዎች የሚገምቱት ግን ላልገማቸዉ ምክንያት ስለ አገር ማዳን ተቆርቁረዉ ሳይሆን “በወንጀሉ ዉስጥ እጃቸዉን በሰፈዉ ያስገቡ ባለስልጣኖች እንደነበሩ” ስለሚገነዘቡት ነዉ። እነ ስየም ሆኑ እነ ገብሩ አስራት መድረክንም ሆነ ሌላ የሥልጣን መሸጋገርያ ተጠቅመዉ ሥልጣን ዳግም ቢወጡ ራሳቸዉን የሚቀጣ የወንጀለኛ መቅጫ ሕግ ፈርመዉ ያጸድቃሉ? ለሚለዉ ጥያቄ መልሱ ግልጽ ቢሆንም ወደ ጥያቄዉ ከመግባታችን በፊት አለመታደል ሆኖ፤“እነ ግዛቸዉ እና እነ መረራ” ካሁኑ ለጥያቄአችን መልስ ሰጥተዉናል እና ለጥያቄያችን ከነ ገብሩም ሆነ ከእነ ስየ መልስ ለማግኘት አንጓጓም። እኔኑን የገረመኝ ጉዳይ ሰዎቹ የድርጅት ተወካዮች እንጂ በሕግ የተመረጡ ያገሪቱ ባለስልጣናት አይደሉም፤የድረጅት መሪዎች በድርጅት ሃላፊነታቸዉ መንግሥት ከመሆናቸዉ በፊት ሕዝቡን ሳያማክሩ “የሰለባዎች ስሞታ “በማፈን” የድርጅት ሥልጣናቸዉን ተጠቅመዉ “የተጠቂዎች እንባ/አቤቱታ” “አፋኞች” መሆናቸዉ ስንመለከት የሕግ እና የአገር አስተዳደር ችሎታቸዉ አገርንና ፍትሕን በሚመለከት በበቂ ማስተዳደር እንደማይችሉ እንገነዘባለን፣፣ ያም ሆነ ይህ መሪዎቻቸዉም ሆኑ የእነሱ ተከታዬቻቸዉ የደቡብ አፍሪካዉ “ማንዴላን” ለይቅርታቸዉ መከታ በማድረግ የመከራከርያ ሽፋን በስፋት በየጋዜጦች እና በኢንተርኔት ሲያቀርቡልን እያዳመጥን ነዉ፣፣መድረክ እና ተከታዬቻቸዉ የሚያወሩት የደቡብ አፍሪካ “ብሔራዊ እርቅ” እንዴት እንደተከናወነ እና ብዙ የተባለለትን እርቅ እንደተጠበቀዉ ዉጤቱ አመርቂ ነበርን? ለመሆዩ እነ ዲክ ክላርክ እና ቦታ እንዲሁም ሌሎቹ የነጩ መንግሥት ባለሥልጣኖች “ለሰራነዉ ወንጀል እንጠየቃለን” ብለዉ ራሳቸዉ ያጸደቁት ሕገመንግሥት/አዋጅ አለ? ከሌለ እንዴት ሲሆን ነዉ እንደ እነ ስየ አብርሃ እንደ እነ ገብሩ ራሳቸዉ ፈቅደዉ ራሳቸዉን የሚቀጡበት ፍርድ ቤት ይመሰርታሉና መለስን ለማስገድ ዕድል ስጧቸዉ የሚሉን? ወይስ የደቡብ አፈሪካዉ “የእዉነት ኡወጪኝ” ደረግ/ኮሚቴ የተጠቀመበት የእርቅ ሰነድ በአጥቂዎች/ባለስልጣኖች ወይስ በሰለባዎች/ተጠቂዎች ተነሳሺነት ምክንያት የተነደፈ ነበር? ከደቡብ አፍሪካዉ ተሞክሮ ኢትዬጵያዊያን ምን ይማራሉ? ለመሆኑ መድረክም ሆነ ሌላ ድርጅት በእንደዚህ ዓይነት ከባድ ጉዳይ የሰለባዎችን ጥያቄ በመናቅ አዳዲሶቹ የፖለቲካ “ጓዶቻቸዉን” ደግፈዉ “ወንጀላቸዉ እንዲናዘዙ መጠየቅ የለባቸዉም….አታስቸግሯቸዉ” በማለት እንደዚህ ለማት መብት አላቸዉ? ቢኖራቸዉስ ሕዝብ አወያይተዉ በድርጅታቸዉ ያጸደቁት ማኒፌስቶ አለ? ይህንንስ ለመራጮቻቸዉ ይፋ አድርገዋል? ለመሆኑ “ለአንድነት እና ለፍትህ ለዲሞክራሲ” ብሎ ራሱን የሚጠራዉ ድርጅት ከራሱ አባሎች እርቅ ማድረግ ተስኖት ፖሊስ ፍለጋ ሲራወጥ ስለ ከባዱ ፍትህ እና ብሔራዊ ወንጀለኞች ጉዳይ አንስቶ ስለ እርቅ ብስለቱ በአርአያነት ለመታየት አጉል ሲመጻደቅ ችሎታዉ ምን ያህል ነዉ? ይህ እና የመሳሰሉት ለማየት ይረዳን ዘንድ ደቡብ አፍሪካን እንደ ናሙና እያመጡ የሚመጻደቁብንና የሚደነቅሩብንን የዘንድሮ “የፖለቲካ ቀሳዉስቶች” ከደቡብ አፍሪካ “ብሔራዊ እርቅ” ለመማር “አቶ እዉቀቱ ተሻለ” በተባሉ ኢትዬጵያዊ የቀረበዉ “ብሔራዊ እርቅ እንዴት? የደቡብ አፍረካ ተመክሮ ሲመረመር” የሚለዉ ፍካሬ በ1992 (ኢትዬጵያ አቆጣጠር) የዘገበዉ አስተማሪ ጥናት በቅጡ ለመረዳት ይረዳን ዘንድ ባጭሩ ዋና ዋነ ፍሬ ነገሮቹን ያንብቡ። እነሆ፣፣ ብሔራዊ እርቅ እንዴት? የደቡብ አፍሪካ ተመክሮ ሲመረመር (በእዉቀቱ ተሻለ) በኖቨምበር 1995 ዓ.ም በፕረዚዳንት ማንዴላ በተሾሙት በጳጳስ ዲዝሞን ቱቱ ሊቀመንበርነት የሚመራዉ “የእዉነት አዉጪኝ ኮሚቴ” አንዱ ክፍል ያጠናከረዉን በደቡብ አፍሪካ ሰብአዊ መብት ረገጣ በሚመለከት የሥራ ዉጤት ለርዕሰ ብሔሩ ፕረዚዳንት ማንዴላ ሐሙስ ዕለት ኦክቶበር 29 ቀን 1998 ዓ.ም. አቀረበ: የኮሚቴዉ ተግባር በቅድሚያ በተሰጠዉ መመሪያ መሠረት ተደረጉ የሰብአዊ መብት ረገጣዎች እና እርምጃዎች መመርምርና አጠናቅሮ ማቅረብ ሲሆን ቅጣት ከመበየን የፍርድ ቅጣት የመስጠት ሥልጣን አልነበረዉም። ኮሚቴዉ 17 አባላት የነበሩት ሲሆን የመጀመሪያዉን የማዳመጥ ስብሰባ ያደረገዉ በኤፕሪል 15 1996 ዓ.ም. ነበር፤፡ የትምሀርትና የካሣ ጥያቄን የሚመረምር በመመደብ ነበር። የሰብአዊ መብት ረገጣን እሚመለከተዉ ክፍል ሥራዉን በጁላይ 1998 ዓ.ም. ሥራቸዉን ይቀጥላሉ። በአጠቃላይ ከ2100 በላይ ከሚሆኑ ሰዎች ስለነበረዉ ሁኔታ ስለደረሰባቸዉ እንግልት፤ስቃይና ሞት የሚገልጹና የሚያስረዱ መረጃዎችን የሰብአዊ መብት ክፍሉ ሲደርሰዉ 2500 ሰዎች ደግሞ በአካል በመገኘት የምስክርነት ቃላቸዉን ሰጥተዋል። ወደ 3500 ገፆች ያሉት ይህ የምርመራ ዘገባ ነዉ እንግዲህ መጀመርያዉ ለፕረዚዳንት ማንዴላ የተሰጠዉ። ዘገባዉ ታትሞ ለሽያጭ ቀርቦ ሁሉም ዜጋ ሊያነበዉ የሚችል መሆኑ ተገልጿል። ሆኖም የዚህ ዘገባ ይዘቱን የመታተም አለመታተም ጉዳይ በሚመለከት ግን ቀደም ብሎ እስከ መጨረሻዉ ሰዓት ድረስ አከራካሪ ሆኖ ቆይቶ ነበር። ይህም የሆነበት ምክንያት የቀድሞዉ ፕረዚዳንት ፍሬድሪክ ዴ. ክላርክ እሳቸዉን በሚመለከት በዘገባዉ ያተካተተዉ እንዲሰረዝ በማለት ለፍርድ ቤት ባቀረቡት ክስ መሠረት ዉሳኔ ማግኘትና በሌላ በኩል ደግሞ ኤ.ኤን.ሲ ኮሚቴዉን በንዝህላልነት የተደረገ፤ ጠቅላላ ትግላችንን በወንጀለኛነት የሚፈርጅ ነዉና ይሰረዝ በማለት ያቀረበዉ ክስ ዉድቅ መደረጉ ነዉ። በፍርድ ቤት የተደረገዉ ክርክር የሚያሳየዉ ቢኖር በፖለቲካ ታዛቢዎች መሠረት ዕርቅ ማግኘት ወይም ማምጣት በጣም አስቸጋሪ መሆኑን ያሰመሩበት ጉደይ መሆኑን ነዉ። ይህነን አስመልክቶ በአሁኑ ጊዜ ኮሚቴዉንና ሥራዉን በቅርበት የሚከታተሉ ታዛቢዎች አካባቢ እየቀረበ ያለዉ መሠረታዊ ጥያቄ ደቡብ አፍሪካ በዋናነት የተከተለችዉ ጎዳና በነጩና በጥቁሩ ሕዝብ መካከል ብሔራዊ እርቅን ላያመጣ ይችላል ወይ የሚለዉ ነዉ። ለዚህ ጥርጣሬያቸዉም በዋና ምክንያትነት የሚቀርቡት ለምሳሌ የምህረት ይደረግልኝ ጥያቄን ተመርኩዘዉ በተግባር አቤቱታ ካቀረቡት ከ7124 ሰዎች መካከል አብዛኛዉ የነፃነት ታጋይ ድርጅት አባላት እንጂ በዋና ተጠያቂነት ከሚፈረጁት ከፀጥታ ጠባቂዎች ከዘረኛዉ መንግሥት አባል አለመሆናቸዉን ከግምት በማስገባት ሲሆን እንዲሁም እስካሁን ድረስ 171 ከቅጣት ነፃ መደረጋቸዉን በማጤን ነዉ። በሌላ በኩል ደግሞ እስከ 2500 የሚሆኑ ተበዳዬች ካሳ ማግኘት ከሚገባቸዉ ዉስጥ ምንም እንኳ መንግሥት በበኩሉ ወደ ሦስት ሚሊያርድ ሚጠጋ ገንዘብ ለካሳ ክፍያ ቢየቀርብም 800 ያህሉ እስከ ኦክቶበር 98 ድረስ ከ350 እስከ 1050 የአሜሪካን ዶላር በጣም አነስተኛ የሆነ የካሣ ድጎማ ተለግሧል። በምርመራዉ መደረግ በተፋላሚዎቹ ዘንድ ስምምነት ቢኖርም እዉነቱን በአደባባይ ከወጣ በሗላ በተሰጠዉ ግምገማ ላይ ከፍተኛ ልዩነቶች የታዩ መሆናቸዉንም ከግምት በማስገባት ጭምርም ነበር። በሌላ በኩል ደግሞ ኮሚቴዉ የገንዘብ እጥረት አለብኝ በማለት ሲያቀርብ የነበረዉን ስሞታ በአንዳንድ ታዛቢዎች አመለካከት የኮሚቴዉ አባላት የተደረገላቸዉን ቅምጥልና ደሞዝ የሥራ መኪና ወዘተ ጋራ ሲነፃፀር በጣም አሳፋሪ መሆኑን በአጥብቆት ገልፀዋል። በዚህ በ“እዉነት አዉጪኝ”ኮሚቴ ፊት ከ1960-94 ዓ.ም. ስለተደረገዉ የሰብአዊ መብት ረገጣ የበዳይም የተበዳይም ሁለት ዓመት ተኩል ያህል ኮሚቴዉ ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ የሚያቀርቡት ቃል ሲመረመር ነበር። በ3500 ገፆች በተጠናቀረዉ ዘገባ ዉስጥ ደቡብ አፍሪካ በዘረኝነት ላይ የተመሰረተ ጭቆና ስር ወድቃ የነበረበችበትና በሌላ በኩል ደግሞ ለፃነት የሚደረግ ትግል ሂደት ዉስጥ በማለፉ ማንም እጁን በደም ያልነከረ ያለመኖሩን የሚገልፅ የኮሚቴዉ ግምገማ ይገኝበታል። (ይህ የማልስማማበት ሐረግ ነዉ። ምከንያቱም ሁሉም ወንጀለኛ ነበር ማለት ማንም ወንጀል የፈፀመ የለም ማለት ነዉ። ማንም ወንጀል ካልፈጸመ ደግሞ “ጥፋተኛ” የለም። ይህ ደግሞ ወንጀለኛን (ካሊብሪቱን) ላለመለየት የሚደረግ የህግ ሽፋን ወይንም ፡ዳተኛነት ነዉ” ምክንያቱም ሁሉም ሕብረተሰብ “ወንጀል” ሊፈጽም ከቶ አይቻለዉም እና ነዉ። እንዲህ ያለ “ድምደማም” በዘመኑ የኢትዬጵያዊያኖች አመለካከት እየተለመደ የመጣ ኩፉ ማሞኝያ ባሕል እየሆነ መምጣቱ እያታዘብን ነዉ (በተለይም ይህን የሚሉት እነማን መሆናቸዉ የ=መገመት አያዳግትም።-ከጌታቸዉ ረዳ) ። ከተለያየ አቅጣጫ የዘገበዉን ድምዳሜም ሆነ ይዘት በሚመለከት ታዛቢዎች እንደሚተነትኑት ከሆነ ብዙዎች ደስተኞች እንዳልነበሩ ይነገራል። ይህንን በቅድሚያ በማወቅ ይመስላል ጳጳስ ዴዝሞንድ ቱቱም ዘገባዉን በሚሰጡበት ጊዜ ይህንኑ ስሜት የሚያጠናክር ንግግር አድርገዋል። ሆኖም በከፍተኛ ተስፋ ሲጠበቅ የነበረዉ ዕርቅን ያመጣል ተብሎ የተጠበቀዉ ግምት ዘገባዉም ሆነ ኮሚቴዉ ሊያሟላ ባይችልም የተደረገዉን ሰብአዊ መብት ረገጣ በአደባባይ እንዲወጣና ሁሉም ዜጋ እንዲያዉቀዉና እንዲገነዘበዉ ለማድረግ በመቻሉ ከፍተኛ ግምት ሊሰጠዉ እንደሚጋባ ይገልፃል። …………..የሰብአዊ መብት ረገጣ ድርጊት ተሳታፊዎች ነበሩት በሰጡት የምስክርነት ቃል እንደተዘገበዉ እንዴት አድርገዉ ዘረኛነት የሚቃወሙትን ዜጎች ሕይወታቸዉ እንደጠፋ እና ከዛም ግድያዉ ይፋ እዳይወጣና እንዳይታወቅ ሬሳቸዉን ለአዞዎች እንደወረወሩ ወይንም በፈንጂ እንዳቃጠሉ በዝርዝር ተዘግቧል። የሬሳ ክምር በእሳት እያቃጠሉ ቢራ ሁሉ ሲጠጣ እንደነበረም ተገልጿል። ያቶ አብዲ አብዱላሂ ያልታደለዉ ትዉልድ መጽሐፍ በወንዶ ገነት የተፈጸመዉን አሰቃቂ ድርጊት ያስታዉሰናል። በሌላ ደግሞ የሰብአዊ መብት ረገጣን በሚገባ ሊያረጋግጡ የሚችሉ መረጃዎችን ያለፉ መንግሥት ባለሥልጣናት ከ1990 ዓ.ም. በሗላ እንዲጠፉ መደረጋቸዉን ኮሚቴዉ ለመገንዘብ መቻሉን አረጋግጣል። ምንም እንኳ ዘረኝነትን መቃወም ትከክል ቢሆንም የነፃነት ትግል መደረጉ ከጥያቄ የሚገባ ባይሆንም በተቃዋሚነት የነበረዉ ኢኤንሲም አሰቃቂ የሆነ ሰብአዊ መብት ረገጣ ፈጽሟል ተብሎ በሦስት ነጥቦች ላይ ሂስ ቀርቦበታል። የመጀመሪያዉ ለዘረኛዉ መንግሥት ይሰልላሉ ተብለዉ የተጠረጠሩ ተጋዬችን መግደል፡ በደቡብ አፍሪካ ዉስጥ ፈንጂ በመጠቀም በተደረገዉ የትግል ስልት በሰሰላማዊ ሕዝብ ላይ የደረሰዉ ሞትና ሦስተኛዉ የ-ኤኤንሲ የጦር ክፍል በ1990 እስከ 1994 ባለዉ ጊዜ ዉስጥ በደቡብ አፍሪካ የፖለቲካ ተቃዋሚዎችን አድፍጦ ገድሏል የሚሉት ናቸዉ።

እዉነት አዉጪኝ ኮሚቴዉ የተጣለበትን ሃላፊነት ለመወጣት በጣረበት ወቅት ወገናዊ ላለመሆን ከፍተኛ ጥረት አድርጓል ተብሎ የሚነገረዉ ለነፃነት ትግሉ ከፍተኛ አስተዋጽኦ በማድረግ በጀግንነታቸዉ የሚታወቁትንም ጭምር ሳይቀር ታሪካቸዉን በሚገባ መመርመሩ ነዉ ተብሎ ይገመታል። ሆኖም ከላይ እንደተገለጸዉ የሚፈለገዉን ብሔራዊ እርቅ ለማምጣት ሆነ ለማስገኘት አልቻለም የሚል ግምት ክብደቱ የላቀ መሆኑ በአጥብቆት የሚነገር ነዉ።….”

በማለት በሰፋት የተነተኑትን አቶ በእዉቀቱ ተሻለ የአገራችን ሁኔታ በማወዳደር ሁለት ነጥቦችን በጥያቄ መልክ በማቅረብ ጽሁፋቸዉን በሁለት ነጥብ ይደመድማሉ።

(1) አሸናፊ ተሸናፊ የሚለዉን ጠፍቶ በሥልጣን ላይ ያለ መንግሥት በፈቃዱ ከሥልጣኑ እንዲወርድ ምን ሁኔታዎች መሟላት አለባቸዉ?

የመንግሥት ሃላፊዎች የነበሩ ሥልጣናቸዉን ሲለቁ ለሰሩት ጥፋት ጥፋተኝነታቸዉን ካመኑ በሕግ እንዳይጠየቁ ከተቃዋሚ ጋር ስምምነት መደረግ አለበት ወይ? (ደቡብ አፍሪካን ቺሌን ያጤነዋል)።”

እንግዲህ በእንደዚህ ሁኔታ ያለፈቺዉ ደቡብ አፍሪካ ለሁለት ኣመት ያህል የተደረገዉ የበዳይ እና ተበዳይ የወንጀል አቤቱታ እና ቃል ማጣራት ሂደት ሲመረመር ደቡብ አፍሪካ በዋናነት የተከተለችዉ ጎዳና በነጩና በጥቁሩ ሕዝብ መካከል ብሔራዊ እርቅን ላያመጣ ይችላል ወይ የሚለዉ ነዉ። ለዚህ ጥርጣሬያቸዉም በዋና ምክንያትነት የሚቀርቡት ለምሳሌ የምህረት ይደረግልኝ ጥያቄን ተመርኩዘዉ በተግባር አቤቱታ ካቀረቡት ከ7124 ሰዎች መካከል አብዛኛዉ የነፃነት ታጋይ ድርጅት አባላት እንጂ በዋና ተጠያቂነት ከሚፈረጁት ከፀጥታ ጠባቂዎች ከዘረኛዉ መንግሥት አባል አለመሆናቸዉን ከግምት በማስገባት ሲሆን እንዲሁም እስካሁን ድረስ 171 ከቅጣት ነፃ መደረጋቸዉን በማጤን ነዉ። በሌላ በኩል ደግሞ እስከ 2500 የሚሆኑ ተበዳዬች ካሳ ማግኘት ከሚገባቸዉ ዉስጥ ምንም እንኳ መንግሥት በበኩሉ ወደ ሦስት ሚሊያርድ ሚጠጋ ገንዘብ ለካሳ ክፍያ ቢየቀርብም 800 ያህሉ እስከ ኦክቶበር 98 ድረስ ከ350 እስከ 1050 የአሜሪካን ዶላር በጣም አነስተኛ የሆነ የካሣ ድጎማ ተለግሧል። በምርመራዉ መደረግ በተፋላሚዎቹ ዘንድ ስምምነት ቢኖርም እዉነቱን በአደባባይ ከወጣ በሗላ በተሰጠዉ ግምገማ ላይ ከፍተኛ ልዩነቶች የታዩ መሆናቸዉንም ከግምት በማስገባት ጭምርም ነበር። በሌላ በኩል ደግሞ ኮሚቴዉ የገንዘብ እጥረት አለብኝ በማለት ሲያቀርብ የነበረዉን ስሞታ በአንዳንድ ታዛቢዎች አመለካከት የኮሚቴዉ አባልት የተደረገላቸዉን ቅምጥልና ደሞዝ የሥራ መኪና ወዘተ ጋራ ሲነፃፀር በጣም አሳፋሪ መሆኑን በአጥብቆት ገልፀዋል። እሚለዉን ስንመለከት፤ ደቡብ አፍሪካ በእንደዚህ ዓይነት ተወላገደ የፍትህ ሂደት ከተጓዘ እርቅ ፤ ከኢትዬጵያ ሁኔታ ጋር ሲነፃፀር “ብሄራዊ እርቅ እያለ ባዶዉን የሚቦተልከዉ “መድረክ” የተባለዉ “ግርምቢጥ” በመጪዉ መንግሥት እነ ስየ እና እና እነ ገብሩ ( እንዲሁም የወያኔ አንጃዎች እና በገለልተኝነት “በተንኮል” አድፍጠዉ እየተከታተሉ ያሉት ከወታደራዊ ስራቸዉ የተገለለሉት ጄኔራሎች እና የጦር ሰዎቻቸዉ………) ሥልጣኑን ቢቆጣጠሩት “ብሔራዊ እርቅ” እተባለ ያለዉ ጉዳይ ራሳቸዉን የሚከስሱበት እና የሰሩትን ወንጀል የሚናገሩበትን “ህግ እና መድረክ” ይቀርጻሉ ብሎ ሚገምት ካለ ይንገረን። ለመሆኑ በታሪክ ዉስጥ ራሱን ለመቅጣት በራሱ አነሳሺነት ፍርድ ቤት ያቋቋመ ወንጀለኛ መሪ ተሰምቶ ታይቶ ያወቃል? ካለ ጠቁሙን። ይሄንን ካልነገሩን ጠቅጥቀዉ ይዘዉን የሚጓዙት ጉዞ የምንጓዘዉ ወዴት ነዉ? ጌታቸዉ ረዳ www.Ethiopiansemay.blogspot.com