በ21ኛው ክ ዘመን ትግራይ ሃገር የመሆን ሕጋዊ መብትና ዘለአለማዊ ይያቄ
ማኒፌስቶ 11
ትርጉም
ጌታቸው ረዳ
(ኢትዮ
ሰማይ) Ethio Semay
March 13, 20213/
ክፍል 1
በ21ኛው ከ/ዘመን ትግራይ ሃገር መሆን ሕጋዊ መብትና ዘለአለማዊ የባለቤትነት ይያቄ በሚል ርዕስ ወያኔ ያደራጀው ‘ነፃ ትግራይ’ በሚል ስም የሚጠራው ድርጅት ዛሬ ከወያኔ ጋር ተቀላቅሎ ጫካ ውስጥ የመሸገው ይህ ድርጅት ጦርነቱ ከመጀመሩ በፊት በ2019 ያሰራጨው እኔ ማኒፌስቶ 11 ብየ የሰየምኩት በ2011 ዓ. ም የተሰራጨ ባለ 45 ገጽ ማኒፌስቶ ባለፈው ሳምንት ስለዚህ ማኒፌስቶ አላማና በኤርትራ ያለው አመለካከት ለትግርኛ አንባቢዎቼ የተቸሁበትን ‘ቶጎሩባ. ኦርግ’ በተባለ የኤርትራ ድረገጽና በኔ ፌስቡክም ታትሞ መኖሩ ይታወሳል። ብዙዎቹ ወደ አማርኛ ተርጉምልን ስላሉኝ እነሆ ሁሉም እንኳ ባይሆንም፤ አለፍ ብየ ጠቃሚ ነጥቦችን አቀርባለሁ። ይህ ትርጉም ስለ ኤርትራ ባለው ካለፈው የትግርኛ ጽሑፌ ከለጠፍኩት በጣም የተለየና ስፋት ያለው ስለ ኢትዮጵያ የሚመለከት ስለሆነ በክፍል በክፍል በየሳምንቱ እለጥፈዋለሁ፤ ተከታተሉ።
ይህ “ሕቶ ትግራይ ኣብ
21 ክ/ዘመን መሰል ምውናን ተፈጥሮኣዊት፣ ሕጋዊትን ዘልኣለማዊትን ሃገረ ትግራይ” ገጽ 25) በሚል በትግርኛ የተጻፈወው ማኒፌስቶ
በ5 ምዕራፎች የተከፈለ 46 ገጽ የያዘ ነው።ገጽ 25 ላይ የትግራይ አገር ለመሆን እና ከኢትዮጵያ ለሚሰነዘርባት ጥቃት ለመቀነስ
ኤርትራን በትግራይ ቁጥጥር ስር ማድርግ አስፈላጊነት እንደሚከተለው ያትታል።
ከተጋሩ ኤርትራ ብሔረተኞች
(ትግርኛ ከሚናገሩ ኤርትራኖች ማለቱ ነው) የሚኖረን ዝምድና መሰረት በማድረግ ከሰራንበት በላያችን ላይ ለሚደርሰው አደጋ ይቀንሰዋል።
ኤርትራን አሁን እየገዛት ያለው ህግደፍ (ሻዕቢያ) ላለመሞት እያደረገው ያለው መንፈራገጥ ካመከንነው ከመፍረስ የማይድን ሃይል ነው።
በተቻለን መጠን ከሆነልን (ትግራዋይ ብሄርተኛ ኤርትራዊ) ኤርትራ ውስጥ ያለው የትግርኛ ኤርትራዊ ብሔረተኛው ሃይል ህግደፍን ተክቶ
ሥልጣን እንዲይዝ ለማድረግ አስፈላጊውን ዋጋ እንድንክፍል የሚጠይቀን አጀንዳችን መሆን አለበት።
ይህ አጀንዳ/ዕቅድ/ ከተቃና
ከኤርትራ ትግርኛ ተናጋሪው ስለ መጪው ዕድላችን የጋርዮሽ አገር የምንምሰርትበት አጋጣሚ ይፈጥራል። ይህ ካልተቃና ደግሞ የኤርትራ
ሉአላዊ አገርነትዋን ኣክብረን ከኛ ጋር አብሮ ሊሰራ የሚችል ዳሞክራስያዊ መንግሥት እንዲፈጠር የተቻለን እናደርጋለን። ይላል። (“ሕቶ ትግራይ ኣብ 21 ክ/ዘመን መሰል ምውናን ተፈጥሮኣዊት፣
ሕጋዊትን ዘልኣለማዊትን ሃገረ ትግራይ” ገጽ 25)
http://www.aigaforum.com/.../The-Tigrayan-National...
ይህ ማኒፌስቶ “ኢሳያስ ከተወገደ
በሗላ በወያኔዎች/በትግሬዎች/ የምትገዛ ኤርትራ ለመመስረት ያቀደ ነው። ማኒፌስቶው የሚናገረው ጭብጥ በትግርኛ እንዲህ ይላል፡
“ኢትዮጵያን ኤርትራን ኣፍሪስና
- “ብናትና ረብሓ ቃኒና “ትግራዋይ ብሄርተኛ ኤርትራዊ” ኣብ ኤርትራ ንህግደፍ ተኪኡ ስልጣን ክሕዝ ክንድዝካኣል ዋጋ ክንከፍል
ኢና፡፡” ኢትዮጵያና ኤርትራ አፍርሰን ሻዕቢያን የሚተካ ትግርኛ ተናጋሪ ኤርትራዊ ቡድን ወደ ሥልጣን በማስወጣት አስፈላጊው መስዋዕት
እንከፍላለን” ይላል። ይህ አባባል ቀጥተኛ ትርጉሙ ለ27 አመት በቅኝ ግዛትንትና አፓርታይድነት ሲገዝዋት የነበረቺዋን ኢትዮጵያ
ሲያጥዋት ሌላ ተተኪ የቅኝ ግዛት ሆና የምታገለግላቸው ሌላ ግዛት (ኤርትራ) ማፈላለግ ለህልውናቸው ዋና ዋስ ነው ይላል፡፡
ወያኔዎቹ ኤርትራ ውስጥ ወደ
ሥልጣን እንዲመጣ እናደርጋለን የሚሉት “ትግራዋይ ብሄርተኛ ኤርትራዊ” ማለት ማን ነው?
“ትግራይ ብሄረተኛ” ማለት
ትግርኛ ተናጋሪ በዛሬው አባባላቸው “ማሕበረሰብ ትግርኛ” ማለት ሲሆን የተቀረው “የኩናማ፤ዓፋር፤ሳሆ፤ቢለን፤ትግረ፤ቢንዓሚር
.. “ብሄረ ትግርኛ” ከሚባለው በባህልም በቋንቋም ስለማይገናኙ ትግርኛ
የማይናገሩትን ነገዶች የትግራይ የቅኝ ተገዢዎች ሆነው “ጉዙኣት” አንደ ሁለተኛ ዜጋ “ሰከንድ ሲትዝን” ሆነው እንዲደራጁ ለማድረግ
ማንፌስቶ ትግራይ በግልጽ ያትታል። ይህ የወያኔዎች የቅኝ ግዛት መስፋፋት ክትግርኛ ተናጋሪ ውጭ ፍላጎታቸው በሄዱበት ቦታ ሁሉ ሌላውን
በሁለተኛ ዜጋ የማድረግ ዓላማ ፋሺሰታዊ ባህሪያቸው ማሳያ ነው።
ምዕራፍ 1 አንቀጽ 1፡2 ላይ
እንዲህ ይላል፦
1.2. በ130 ዓመት ውስጥ
ያልተመለሰ የትግሬዎች ጥያቄ ምንድነው?
ዛሬ ኢትዮጵያ ውስጥ እንሰደባለን፤
እንገደላለን፤እንደበደባለን፤ የትግራይ ባለሃብቶች እንዳያድጉ ተደርጓል፤በትግሬዎች ላይ ፖለቲካዊና ቢሮክራሲያዊ ተጽዕኖ እየባሱ እየሄዱ
ነው። የትግሬዎች ሃብት ንብረት እየተዘረፈ ነው፣በወታደራዊና በአካዳሚ ረድፍ የተሰለፉ የትግራይ ተወላጆች ልዩነት እየተደረገባቸው
ነው።”
ከ100 ሽሕ ሂወት በላይ ገብረናል፡ ብዙ ሺህ ቆስለን የጠላታችንን ሥርዓት
አፍርሰን ኢትዮጵያን ነጻነትና መብት አጎናጸፈን። ያ ሁሉ ላብና ደማችንን አፍስሰን ተጠቃሚዎች ሌሎች እንጂ ትግሬዎች ልንሆን አልቻልንም።ነጻነት
አምጥተንለታል ባልንባት አገር በ27 አመታት ውስጥም ምቾት አልሰጠችንም። አሁንም አገሪቷ ከ1983 ዓ.ም በፊት እንደነበረቺው ለኛ
ለትግሬዎች ጸር ሆናለች። በእኛ ለይ የታየው ጥላቻ ከ27 አመት ከነበረው በባሰ ቀጥሏል። በብዙ ሕዝቦች እንድንጠላ ተደርጓል። እዚህ ላይ ሕዝብ ሕዝብን ይጠላል ወይ?
ብላችሁ ለምትጠይቁ ጠያቂዎች መልሱ “አዎ” ሕዝብ አይሳሳትም ፤ ሕዝብ ጥላቻ አያንጸባርቅም የሚባል ‘ጮሌነት’ እዚህ ላይ ቦታ የለውም።
ሕዝብ አንደሚሳሳት፤ሕዝብ ጥላቻ እንደሚያንጸባርቅ ባለፉት አመታት በኛ ላይ የተደረገው ጥላቻ ማየት ችለናል።
ከጥላቻ የጸዱ ጥቂቶች ሊኖሩ
ይችላሉ፤ ሆኖም እነዚህ እኛን ልያድኑን አይችሉም። የሚያድነን እራሳችንን መከላከል ስንችል እና በራሳችን እምነት ሲኖረን ብቻ ነው።
ይላል።
በመቀጠል በትግርኛው።
“እዞም ሎሚ ብግልጺ ኣንጻርና ዶው ዝበለ ሓይሌታት ዝሓለፉ 800 ዓመታት ኣንጻርና
ዝነበሩ ንሓዋሩ ውን ዘይቕየሩ እዮም፡፡ እዞም ጸሊእትና እዚም ንዓና ምጥቃዕን ምጉዳእን ከም ኣተሓሳስባ ጥራሕ ዘይኮነ ከም መንነት
ሃኒጾሞ እዮም”
ትርጉሙም፡
“እነኚህ ዛሬ በግልጽ ጠበኝነታቸውን
በኛ ላይ እያራመዱ ያሉት ለ800 አመት ጠላታችን የነበሩ ለወደፊቱም ሆነው የሚቀጥሉ ጥላቻን እንደ የማንነታቸው መለያ ይዘውት የቀየ
ነው።”
“ባጠቃላይ ለሚያጋጥሙን ችግሮች
ለመፍታት ጥላቻን የማንነታቸው መለያ ያደረገው ጠላታችን ባህሪና አስተሳሰብ እንዲታረም ከመጣር ይልቅ የራሳችን ችግር መፍታት እንጂ
እነሱን በማስታመም ላይ ማትኮር የለብንም። እስካሁን ድረስ እንደ ስልትና ስትራተጂ አድርገን የተከሄደበት የ130 አመት ጉዞ የተሳሳተ
ነበር።
ብሄራዊ ጥያቄአችን ግን ምንድነው?
እኛ ተጋሩ በዛሬዋ አፍራካ
ቀንድ በሚባለው አካባቢ ከሺዎች ዘመናት በፊት የነበርን፤ ያልተቋረጠ ባህል፤ታሪክ ሰልጣኔ ያለን ሕዝብ ነን፡፡ ታሪካችንና ሰልጣኔአችን
ደግሞ ለቋናቋ፣ ባህልና፣ ስርዓተ-ክብርና፣ ስነ-ጥበብ፣ ስነ-ሙዙቃና፣ ሰነ-ጽሑፍ ተደምሮ የማንነታችን መላያዎች ሆነው ቆይተዋል፡፡
እነኚህ ማንነቶች ከሌሎቹ ኢትዮጵያዊያንም ሆነ ከሌሎቹ ሕዝቦችም የተለየ ሕዝብ እንድንሆን አስችሎናል። ይህ ማንነታችን ለማስጠበቅ
ከሺዎቹ የተለያዩ ጠላቶች ጋር ተዋግተን ጠብቀነዋል። ጣለቶቻችን የሚጠሉን ማንነታችን ስለሚጠሉ ወይንም ማንነታችንን ሊነጥቁና የራሳቸው
ለማድረግ ነው። ይህ ሃቅ የሚለወጥ አይደለም።
እውነታው ይህ ከሆነ፤ እኛ
ትግሬዎች ለማንነታችን የምናደርገው ትግል እልባት ለምን አላገኘም? እንዴትና ለምንድነው ታግለን ድል አድርገናል ባለንበት ወቅት
መልሰን ወደ አደጋ ልንወድቅ የቻልነው? አዎ! ዛሬም 100 አመት ያደረግነውን አዝጋሚ ትግል በተለይ በ20ኛው ክ/ዘመን መጨረሻ
ላይ ያደረግነው የ 17 አመት መራራ ትግል አድርገን በድል ስናጠናቅቅ ለምንድነው እንደ ብሄር በማንነታችን ላይ ፍጹም የሆነ አደጋ
ላይ ሊገጥመን የቻለው?
ችግሩ የኛ ጥያቄ ዲሞክራሲ
አይደለም። ዲሞክራሲ የሁሉም ዓለም ሕዝቦች ፍላጎት ነው። ሆኖም ብሄራዊ ጥያቄ ብቸኛ የሆነ የኛ ብቻ የሆነ ጥያቄ ስለሆነ ሌሎች
እንዲወስኑልን ወይንም እንደ ዲሞክራሲ የምንጋራው ፍላጎት ወይንም ጥያቄ አይደለም። በተለይም እኛ ትግሬዎች በዓለም ውስጥ የስልጣኔ
ምንጮችና ስልጡኖች ከሚባሉት ጥቂት ሕዝቦች ውስጥ ኩሩዎች ነን። ስለሆነም ይህ ኩራት በያንዳንዱ የትግራይ ተወላጅ ሕሊና የታተመ
ሰለሆነ ጠላቶች ሊኖሩን የግድ ነው። ይህ ደግሞ ጠላቶቻችን የራሳቸው ማንነት ከኛው ጋር ስለሚጻረር ሊነጥቁን ወይንም ሊያጠፉብት
ሲሞክሩ ቅራኔ መፈጠሩ አይቀሬ ነው። ይቅ ቅራኔ ቀጣይ እንጂ ማቆሚያ የለውም። ስለሆነም ጥያቄችን የማንነት ጥያቄ ነውና የትግራይ
ሕዘብ ጥያቄ የማንነት ጥያቄ ሆኖ ይቀጥላል።
ጠላቶቻችን የሚጠሉን ምክንያት
ታግለን ያመጣንላቸው መብት ከልክለናቸው አንዳይደለ እነሱም ያውቁታል ሰላማዊ ህይወት እንዳመጣንላቸውም ጠፍቶአቸም አይደለም። እነሱ “ልዕልና ተጋሩ” (የትግሬ የበላይነት)’ አንደሚሉትና ለብቻችን ስለተጠቀምንም
አይደለም: ለጥላቻቸው ምክንያት እርግጥ በታታሪነታችን እንደምንበልጣቸው በዲሞክራሲያዊ አሰራርም አንደምንበልጣቸውና የበላይነት እንደሳየናቸው
መሆኑንም ጠፍቶአቸው አይደለም ፤ለጥላቻቸው መነሻ ምክንያት ማንነታችንን ስለሚጠሉት ነው።
የሚፈልጉት አድርጉ የሚሉንን
አድርግን ብንምበረከክላቸውም ፤ ምንምቢሆን የቀረጹት አለን የሚሉት የራሳቸው ማንነት ካላቸው የማንነት ህለውናቸወ በእኛ ላይ የሚያንጸባርቁት
ጥላቻና ቅናት የተመሰረተ ስለሆነ ማንነታቸው ካለ ጥላቻ ሊቀጥል አይችልም። በሺ ዘመናት በጋብቻ ተዋልደን ተዛምደንም ቢሆን “አጥንት”
እየቆጠሩ እኛን መጥላታቸውን አያቆሙም። ሃገራዊ (ኢትዮጵያዊ አገር
ወዳድ) ነኝ ብሎ ከነሱ ጋር የወገነ ትግራዋይም አያምኑትም። የነሱ ስህተት በእሱ ላይ ተጠያቂ በማድረግ ይጭኑበታል። ባጭሩ ማንነታችንን
ጥለን እሺ ብንላቸውም እኛን ከማጥቃት አይመለሱም። ይህንን ላንዴና ለመጨረሻ ዕልባት ለማስገኘት የራሳችንን ብሔራዊ ጥያቄ ባግባቡ
አለመያዛችን ነው።
ከፈረሱ ጋሪው በማስቀደማችን
የምንወስንብትን ዕድልና አጋጣሚውን ከእጃችን በማስወጣት ለሌሎች አሳልፍን ሰጠነው ብቻ ሳይሆን ማንነታችንም ሌሎች እንዲወስኑልን
ዕድል ሰጥተናቸዋል።
ታግለን የራሳችንን ጌቶች እንዳንሆን
ከጠላቶቻችን አልጋ ላይ አብረን አንድንተኛ መርጠናል።በ1983 ዒ/ም ጣላቶቻችንን አሸንፈናል ብለን ያቺ እነሱ ጋር የምንጋራት አገር
ለነሱ እንደሚያመች እንገንባት ብለን ከሚገባን ተልዕኮ እና ጉልበት ጨርሰን እራሳችን ተመልሰው እኛኑን እንዲያሸንፉን ዕድል ሰጠናቸው። ስለ ዲሞክራሲ ዕውቀት የሌላቸው ሗላ ቀር ጠላቶቻችን ባላቸው የሕዝብ ብልጫ
ድምጽ ይጠቀሙ ብለን እነሱን ለማስተማር በተዘረጋው ሜዳ ላይ ተኝተን በእንዝህላልነት ጠብቀናቸው፡ እኛን አዳክመው ወጥመድ ውስጥ
አስገብተው እኛን በዲሞክራሲ አሽንፈው አገሪቷ ከእጃችን ነጠቁን። እና አሁን ብሔራዊ ጥያቄችንን ጥለን ወደ እዛቺኛዋ አገራቸው ከነሱ
ጋር እንቀላቀል ወይስ ከስሕተታችን ታርመን ወደ እማይቀረው የትግራይ አገረ መንግሥት መስረታችን እናፋጥን?
ሓቁ ግን ዛሬም ቁጥሩ የማይናቅ
የትግራይ ምሁራንም ሆኑ ባለሃብቶች እውነታውን ላለመቀበል “ኢትዮጵያ አገራችን ነች፤ ጥያቄ ካለ ኢትዮጵዊነታችንን ይዘን መመለስ
ይቻላል” ማለታቸው አይቀሬ ነው። እነዚህ ቁጥራቸው የማይናቅ ትግሬዎች አሁን ያለቺው ኢትዮጵያ እና እኛ ኢትዮጵያ የምንላትን የተለየች
ሌላዋ በታሪክ የምናውቃት የጥንት የኛ የምንላት ኢትዮጵያ ለየብቻ መሆናቸው የታሪክና የፖለቲካ አረዳዳቸው ፍጹም ግርድፍ የሆነ ነፃ
ያልወጣ አስተሳሰብ ተከታዮች ናቸው።”
I. ስለሆነም ስለ ብሔራዊ ማንነታችን አመለካከት እና ስለ ኢትዮጵያ ማንነት በሁለት የተለያዩ አመለካከቶች ማብራራት የግድ ሆኗል።የኛ የምንላት የትግሬዎች ኢትዮጵያ እኛ ትግሬዎች በቅርጽም በጂኦ ፖለቲካዊ አስተዳደር እንደፈለግናት ስናስተዳድራት የነበረች የኛዋ የጥንትዋ ኢትዮጵያ ህልውናዋ ያበቃው በ 1890 ዓ/ም/ ነው፡፡ አሁን ያለቺዋ ኢትዮጵያ ግን እኛን እና ኤርትራን እሚባሉ አገሮች በ19ኛው ክ/ዘመን መጨረሻ ……………
ክፍል ሁለት
ይቀጥላል……………