Wednesday, January 2, 2013

ማሳሰቢያ


ማሳሰቢያ

 
ማሳሰቢያየ ከመጀመርየ በፊት አክብሮታችሁን ለመግለጽ በደብዳቤዎቻችሁ ውስጥ ጊዜአችሁን እና ገንዘባችሁን በማውጣት ካርድ ገዝታችሁ ለላካችሁልኝ በርካታ ክቡራን ኢትዮጵያዊያን ወንድሞች እና እህቶቼ ሁሉ ልባዊ ምስጋናየን አቀርባለሁ። እግዚአብሔር ያክብርልኝ፤ብድራችሁ መላሽ ያድርገኝ እንዲሁም ይህ መጽሐፍ ለማስተዋወቅ ለተባበራችሁኝ የድረ ገጽ ባለቤቶች ሁሉ ከልብ አመሰግናለሁ።
(408) 561 4836
ደቂቀ ተወልደመድኅን

ወያኔዎች የደበቁት የፕሮተስታንት

ታሪክ በትግራይ

ስለ ሚለው አዲሱ መጽሐፌ አስቀድሜ መጀመሪያ ላይ በማስታወቂያ ላይ እንደገለጽኩት እንደሚታወቀው አዲሱ ትውልድም ሆነ በጠቅላላ የኢትዮጵያዊያን የማንበብ ልምድ አነስተኛ እና ዳተኛ መሆኑን በማገናዘብ መጽሓፉ ሲታተም በቁጥር እጅግ አነስተኛ የሆነ ብዛት ነበር ያሳተምኩት። ዕድሜ “ለጥቂቶች” ግን የተግባር ሰዎች በሆኑት አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን ትብብር፤ መጽሐፉ ተሽጦ አልቋል። እንደገለጽኩት ይህ ታሪካዊ መጽሐፍ በኢትዮጵያዊ ደራሲ ሲታታም የመጀመሪያ ነው። መጽሐፉ በእጃችሁ ያላስገባችሁና ለመጪው ትውልድ ለማስተላለፍ ዕድሉን ያላገኛችሁ ዜጐች በጣም እያዘንኩ፤ እንደ ጠያቂው ብዛት ገምግሜ ለሁለተኛ ጊዜ የሚታተም መሆኑን አለመሆኑን ለወደፊቱ አሳውቃለሁ። ላሁኑ ግን አልቋል። ሁለት መጽሐፍቶች አልቀዋል (የወያኔ ገበና ማህደር እና ደቂቀ ተወልደመደህን አልቀዋል።) አሁን የቀረው ይድረስ ለጎጠኛው መምህር” ጥቂት ቅጆዎች አሉኝ።
 
ሁለት ነገር ልበል (1)
ብዙዎቻችሁ (ትግሬዎችም ሆናችሁ ሌሎች ) እነኚህ ሁለት ሰዎች በትግራይ ታሪክ በትግርኛ መጽሐፍ መጻፍ ጀመሩ ከተባሉት ሦስት የትግራይ ተወላጆች ሁለቱ እነኚህ ህ ናቸው (ላሁኑ ጐልተው የሚታወቁት ሦስቱ ደብተራ ፍስሃ፤አለቃ ተወልደመፍህን እና ጐበዜ ጐሹ ናቸው)።
በአፅንኦት ልታተኩሩበት የሚገባ አንድ አስገራሚ የወያኔዎች ክስ እና ወያኔዎች እነኚህን ሰዎች  ለፖለቲካቸው መጠቀሚያ ንዴት እንደተጠቀሙባቸው (በተለይ ሁለቱ) ልብ እንድትሉት ላብራራ።
የትግርኛ ቋንቋን መጻፍ ጀምረን የነበርነውን መብታችን “አማራዎች” ትግርኛ አንዳያድግ በመጨቆን “ትግራይ” ውስጥ ትግርኛ አንዳይጻፍ አግደው “አማርኛ” አንዲስፋፋ አድርገዋል በማለት አማራውን ሲወነጅሉ፤ አንነዚህን ሰዎች በመጥቀስ ነው፤ እንደማስረጃ ሁሌም የሚከራከሩት ። በየራዲዮናቸውና በትግርኛው ቮ. ኦ. ኤ ሳይቀር የእነዚህ ሁለት ሰዎች ስም ሁሌም እያነሱ አማራውን ሲወነጅሉ የሚደመጡት። እዚህ ላይ ልብ ማለት ያለብን እነዚህ ሰዎች ጀመሩት የተባለው “ትግርኛን” የመጻፍ ልምድ ለወያኔዎች መጠቀሚያ እና አማራውን መወንጀያ በማድረግ ስማቸውን ሲየነሱ፤ እነዚህ ሁለት ሰዎች በትግራይ ማሕበረሰብና እና አስተዳዳሪዎች የደረሰባቸው ሃይማኖታዊ  የመብት ረገጣ ፤ሰቆቃና ስደት “ሳያወሱ” የሸዋ / የአማራ ንጉሥ ብለው ወደ እሚጠሩት ወደ 14ኛው ክ/ዘመን ንጕው የነበረው ወደ ንጉሥ ዘርአ ያዕቆብ በማትኰር ትግሬዎች በሃይማኖታቸው አምነት ተነሳ በአማራ አስተዳዳሪዎች እና ነገሥታቶች ደረሰባቸው ብለው ወደ እሚከስሱት ጭቆና ላይ ማትኰራቸው ወያኔዎች ምንኛ መሰሪዎች እና ጐሰኞች መሆናቸወን ይህ ተጨባጭ መረጃ ነው።
ባንዳዎቹ የነዚህ ሰዎች የትግርኛ ጽሑፍ ጅማሮ ለአማራው መክሰሻ ሲጠቀሙበት እነዚህ የአክሱምና የዓድዋ ተወላጆች የሆኑት ሁለቱ ሊቃውንት የደረሳበቸው መንግሥታዊና ማሕበረሰባዊ ጭቆና በትግራይ ሰዎች ግን መደበቃቸው እጅግ አሳዛኝ ወንጀል መሆኑን ልብ አንድትሉት ነው። በጻፍኩት መጽሐፍ እነኚህ ሰዎች ምንኛ ለመብታቸው ሲከራረከሩ በጥልቀት ትመለከታላችሁ። ያ ሁሉ ወያኔዎች ደብቀውታል። ምክንያቱም አማራዎች ፍትሕ አጉዳዮች፤ ትግሬዎች ግን ሁሉም ነገር የተሟላላቸው ልዩ ፍጥረት የሆኑ “የፍትሕ ሰዎች” ነን እያሉ አጉል ስለሚመጻደቁ ያነን ሆን ብለው በመዝለል የነዚህ ሰዎች ሥራ ብቻ መዝዘው ለፖለቲካ መጠቀሚያ ማድረጋቸው ምንኛ መሰሪዎች እና ለውሸት የቆሙ መሆናቸው ነው።

 
አስገራሚ የሚያደርገው ሌላው አሳዛኙ ገጽታው ደግሞ፤ እነኚህ ሁለት ሰዎች በተለይ አንደኛው በወያኔ ውስጥ ከፍተኛ ደረጃ የሚገኙ የልጅ ልጆች አሏቸው። ሌላኛው ደግሞ የወያኔ አጫፋሪዎች ሆነው የጐሳ ፖለቲካ አፋፋሚዎች ሆነው ለወያኔ የሚያንጨበጭቡ የልጅ ልጆች አሏቸው። ይገርማል!

ሌላው (2ኛው) ነጥብ           

መምጣቴ ላልቀረ አንድ ነገር ብየ መልካም ልደት አንዲሆንላችሁ አምኛለሁ።መልካም መልካሙን ለኢትዮጵያ ወዳጆች እየተመኘሁ፤ ሞትና ሐፍረቱን ለወያኔዎች እመኛለሁ። በሰው ልጆች ደም ታጥበው የማይባንኑ “ጥቋቁር ጣሊያኖች” ብለን የምንጠራቸው የናዚና የፋሺስቶች ግልገል የሆኑት “የወያኔ ትግራይ” መሪዎች “በታሪክ ክርክር” አሸንፈናቸዋል! በግል አነሳሽነት የጻፍኳቸው መጽሐፍቶቼ በታሪክ መድረክ አሸናፊነታቸው አረጋግጠዋል። አንዳቸውም መረጃዎቼን ማፍረስና መቃወም አይቻላቸውም፤ አልቻሉምም።

በጐሳና በቋንቋ ዜጐችን ለያይቶ በማስተዳዳር በዓለም ታሪክ የተተፋው  አሳፋሪው የጣሊያኖችና የደቡብ አፍሪካው “አፓርታይድ” ስርዓት ተግባራዊ ያደረገው የወያኔ ቡድን ዜጐች ጠመንጃቸውን አስፈትቶ አንይወጉት ባዶ እጃቸወን አስቀርቶ፤ ለጊዜው ሥልጣኑን በጠመንጃ አፈሙዝ ቢቆጣጠረውም፤ጠመንጃ የማያምበረክካቸው “ታሪክ” የተባሉት ጦረኛ ብዕሮቻችን ወያኔን ለዘላለም አንደማያንሰራራ አድርገው አንገቱን አስደፍተውታል።
 
ከወደቁ በሗላ መፈራገጥ ለመላላጥ፤የሚለው ብሂል ወያኔን በእርግጥ የሚገልጸው ብሂል ነውና ፤ወያኔ በስልጣን ላይ መሆኑን ባሸናፊነት የወጣ መስሎት ከሆነ ገበናውን ዞር ብሎ መመለክቱ ይበልጥ ይረዳዋል። ፋሽስቶቹ የወያኔ ትግራይ ግልገሎች በታሪክ የቆሸሸሸ ገበና ይዘው ከባዶ ኪስ ተንስተው ያገሪቱን ንብረት እየዘረፉ ያለ ምንም ሐፍረት “የቢራ ፋብሪካ፤ የቆዳ ፋብሪካ፤ የድንጋይ ፋብሪካ የገረድና አሽከር፤የባርያ ሻጭ ድርጅት ባለቤቶች ….ወዘተ ቢሆኑም ታሪክ ግምባራቸው ላይ የጻፈባቸው “ቆሻሻ” ገበና መፋቅ አይቻላቸውም።
ሊገላገሉ የሚችሉበት መንገድ ቢኖር፤ ውርደታቸውን በቁም ከማየታቸው በፊት እንደ የፋሺስቶቹ ቅጥረኛ “ሟቹ” መሪያቸው ‘መለስ ዜናዊ’ ባጭሩ ከዚህ ዓለም ሲገላገሉ ብቻ ነው።ያንን ዕድል እንዲያገኙ የሞት ጥሪያቸውን የሚያቀላጥፈው ወረቀት ተሎ እንዲልክላቸው ፋሽሲቱ መሪያቸውን መማጠንና መከተል አለባቸው።
አለቃቸው መለስ ዜናዊ “ኢትዮጵያን” ወደብ አልባ አድርጐ ባዶ ቤት  እንዳስቀራት ሁሉ እሱም  ‘ጣብብ ሳጥን’ ውስጥ ታሽጐ የዘላለም እስር ቤት ገብቶ “ባዶ ቤቱን”
እያጣጣመው ነውና “የቁም ውረደት” ከማየት እነሱም የመሪያቸው ኰቴ እየተከተሉ “የሳጥን ቤት” ኑሮአቸውን እንዲያቀላጥፉ ፈቃደኝነታቸውን እንዲያሳዩን አንማጸናቸዋለን።
በእነሱ እጅ የስንቱን ቤት ጨልሟል፡ቤተሰቡን የተወለደበት የትውልድ ስፍራው፤ አገሩ አንዳያይ ተከልክሎ በናፍቆት ተቃጥሏል። የወያኔ ፋሺስት ግልገሎችም የመሪያቸው ኑሮ አንዲያጣጥሙ ለኢትዮጵያ አምላክ ፋይሉን አንደገና በተቀሩት አንዲያቀላጥፍ ልመናችንን እናቀርባለን።እኛ ብንሞትም የመሪያቸው መሞት አስቀድመን በማያታችን ቅሬታ አይሰማንም። ምኞታችንም አውራው እንዲቀነጥሰው ነበርና “ቀነጠሰው”! አዛኞችም፤አልቃሾችም በዚህ አጋጣሚ ‘ገና ታዝናላችሁ”፤“ታለቅሳላችሁ”። በአምላክ ጥበብ ገብታችሁ መፈትፈትን አቁሙ!
ትግላችን ረዢም ቢሆንም መጨረሻ ላይ የኛ ታሪክ በአሸናፊነት መውጣቱ አይቀሬ ነው።

የወጋ ቢረሳ የተወጋ አይረሳም ነውና በቤተ አምላክና በአማራ ሕዝብና ክብር/ዲግኒቲ/ ላይ የዘመተው ‘ወያኔ’ ቢረሳውም  ቤተክርስትያኒቱ አልረሳችውምና “ዋና ዋና  አለቆችን” ሳጥን ውስጥ አሳፍሮ ለፍርድ ጥርቷቸዋል። በተቀሩት ላይም አጭር ማዘዣ እየተዘጋጀላቸው ነውና እስከዚያው ድረስ አምላክን አመስግኑ!  ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር! getachre@aol.com
(408) 561 4836