ይድረስ ለጎጠኛው መምህር (አማርኛ) እና ሓይካማ (ትግርኛ) መጽሐፌን ለመግዛት ዕድሉን ያላገኛሁ ካላችሁ በሚከተለው አድራሻ ደውላችሁ ማግኘት ትችላላችሁ Telephone (408) 561 4836 (Getachew Reda P.O.Box 2219 San Jose, CA 95109) getachre@aol.com http://www.ethiopiansemay.blogspot.com/ የምፅዋ፤የአልጌና እና የዓይደር አጥንቶች እሾህ ሆኖው ይውጉዋችሁ! ጌታቸው ረዳ http://www.ethiopiansemay.blogspot.com/ “ኢካድ ፎረም.ካም” እና “ኢትዮሚድያ.ካም” እና በመሰል ድረገፆች ሰሞኑን ተጠናክሮ እየወጣ ያለው የፖለቲካ ሰበካ (ፕሮፓጋንዳ)አስገራሚ ነው። “ግንቦት7”የተባለው ጎጠኞች የሚመሩት ድርጅት ኤርትራ ድረስ ሄዶ የሻዕቢያ እርዳታ በመጠየቅ ኢትዮጵያን ከመለስ ዜናዊ አስተዳደር ነፃ እናወጣለን ብሎ መሄዱን የሚነግሩን ፅሁፎች መለጠፍ ጀምረዋል።በዚህ ላይ ሁለት ጽሁፎች ቀርበዋል። አንዱ ጥቁር ጫካ የተባሉ ጸሓፊ የአርበኞች ግምባር ደጋፊ ሲሆኑ ሌላው ጸሓፊ ደግሞ የግንቦት7 ደጋፊ የሆነው “የኢትዮጵያን ሕዝብ በመጨፍጨፍ፤በማባረር አሁንም ብዙ ምርኮኛ በባርነት በሳህል ተራራዎችና በተቀሩት ምድረበዳዎች በልማት ሥራ ከደቡብ አፍሪካ ሮቢን ሁድ እስር ቤት ባልተናነሰ በሰንሰለት ታስረው ጉድጓድ ውስጥ ታፍነው ለሸቅል ብቻ ሊወጡ የሚፈቀድላቸው ዛሬም እንዳሉ ከኤርትራኖቹ ራሳቸው የተዘገበ ጉዳይ ሆኖ እያለ፡ “ጭራቆቹ”የሻዕቢያ ባለሥልጣኖች “ለኢትዮጵያ ሕዝብ በጎ አመለካከት አላቸው” እያለ መወትወት ያልሰለቸው ያለ ማባራት ሁሌም “ጸረ ትግራይ ሕዝብ” ቅስቀሳ የሚካኼድበት “ካረንት አፌርስ” የተባለው “ፓልቶክ” እና “ኢካድ ፎረም” የተባለው ድረገጽ ባለቤት ነኝ የሚለን የግንቦት7አፍላ/ወጣት “ተክሌ”የተጻፉ ጽሁፎች በሚመከት በዚህ ዓምድ አንመለከታቸዋለን። እንኚህ ሁለት ጽሁፎች ስለ ግንቦት7አማራጭ የለሽነት የሚሰብኩን ቢሆኑም በፋሽስቱ “በኤርትራ ህዝባዊ ሓርነት ኤርትራ”ግምባር/ወታደራዊ የሽምቅ መንግሥት ያላቸው አመለካከት ግን ተቃራኒዎች ናቸው። “አርበኞች ግምባር፤ግንቦት7፤የሻዕቢያ ሰላዩ ተስፋዬ ገብረአብ ከፍል 4”በጥቁር ጫካ የቀረበው የግንቦት7 አመራር (አንዳርጋቸው ጽጌ)እና የኢሳያስ አፈወርቂ መንግሥት ግንኙነትና ለዓመታት አስመራ ከተማ የመሸገው “አርበኞች ግምባር” ተብሎ የሚጠራ ድርጅት የሚተነትነው ጽሑፍ በመረጃ የተደገፈ ጠቃሚ ዘገባ ቢሆንም ግንቦት7ን በጎንደር፤በወሎ እና በጎጃም ሕዝብ የሚደገፍ ድርጅት መሆኑና እነኚህ ሦስት (የሸዋ አማራ ሕዝብን አልጨመረም) የአማራ ሕዘብ አካባቢ ተብለው የሚታወቁት ክፍለሃገሮች “ግንቦት7ን” /መንፈስ/ ብለው እንደሚጠሩትና ነፃ የሚያወጣቸው ድርጅትም “ግንቦት7 መሆኑን” በጉጉት እየተጠባበቁት እንዳለ ጎንደር ድረስ አንድ ቤተሰብ ጋር ደውለው መረጃውን እንዳገኙትና እሳቸውም ቢሆኑ የአርበኞች ግምባር አባል ሆነው “ግንቦት7”እንደሚደግፉ ሳይሸሽጉ ገልጸውልናል። ጉድ ነው!!! የሻዕቢያ እና የተጠቀሱት ድርጅቶች ግንኙነት ባጭሩ በመረጃ አስደግፈው ያቀረቡት ትንተና ተቀባይነት ያለው ቢሆንም አሳማኝ ዘገባቸው በሚከተለው ሁኔታ ጭቃ እንዲቀባ አድርገውታል።ስለ አርበኞች ግምባር ልባቸው ሲደማ ለግንቦት7ም እንዲህ ሲሉ ግሩም ሲገቡልን የነበረውን ዘገባቸው በዘገባው መደምደምያ ላይ ድነገት በጭቃ ቀቡት ያልኩትን ልጥቀስ እነሆ። “ጽሁፌን ወደ ማጠቃለሉ ስገባ ባሁኑ ሰአት በውጭ አገርም በውስ አገርም ሁሉም ሕዝብ ያለ ግንቦት7 ሌላ ወሬ መስማት አይፈልግም። ትልቅ ተቀባይነት አግኝታችሗል። ሕዝቡ እምነቱ በናንተ ነው። ስለዚህ መታገል ያለባችሁ የሕዝቡን ጠላት ነው። ከዚህ ከሚደግፋችሁ ሕዝብ ውስጥ ደግሞ አማራው አንዱ ነው። ባሁኑ ሰአት በጎንደርም በጎጃምም በወሎም ያለ ሕዝብ ትኩረቱና ፍላጎቱ ከናንተው ጋር ነው። ቤተሰቦቼን እንኳን አደረሳችሁ ለማለት ጎንደር ስደውል ዘመቼ ገና የናፍቆት ሰላምታዬን ሳልጨርስ “ስለ ግንት7ላወራቸው ፈለጉ”(ቅንፍ የኔ)፡ይህ ማለት ታለቋ መሪያችን ብርቱካን ቅንጅት መንፈስ ነው እንዳለችው አሁንም ግንቦት7 “መንፈስ ነው፤ በሁሉም ቤት ገብቷል” (ቅንፍ የኔ) አማራውን ለማስጨፍጨፍ ባደባባይ ያወጀውን ሳታስጠጉ “አማራው ምን ይሰማዋል? ምን ይለናል? ብላችሁ አስቡ” (ቅንፍ የኔ)” ጸሐፊው ግንቦት7 ዋርካ ፤ጥላ ነው… በማለት ፕሮፓጋንዳቸውን ያደመቁበት ጽሑፍ ነው። ስለ እኚህ ፀሐፊ ስለ አስመራው ዘገባቸው አክብሮት ቢኖረኝም ከላይ እንደገለጽኩት የግንቦት7 ቅስቀሳቸው በውሸት መዳከራቸው ከምራቸው ተነሳስተው በሃገራዊ ቁጭት የዘገቡትን ዘገባቸው ታጠቦ ጭቃ አደረጉት። በጽሑፋቸው ላይ ብዙ የተሳሳቱ ትንተናዎችን ዘግበወዋል። ከላይ የጠቀስኩትን ስለ ግንቦት7 አባባላቸው የምመለስበት ስሆን፡ ለምሳሌ ለምሳሌ በሻዕቢያ አቀነባባሪነት ባኦነግ መሪነትና ተሳታፊነት የተካሄደው ዘግናኙ የወለጋው ዕልቂት ኦነግ ሳይሆን ሻዕቢያ ነው በማለት ድርቅ ሲሉ፤ ለዚህም “ኮሎኔል ጎሹ ወልዴን”ጠይቁ በማለት በማስረጃነት ይጠቅሳሉ (ኮሎኔል ዶ/ር ጎሹ ወልዴ ጥሩ ኢትዮጵያዊ የኦሮሞ ተወላጅ፤ጠንካራ አገር ወዳድ መሆናቸውን ባውቅም-ዋሺንግተን በአሜሪካን ኮንግረስ ቀርበው ከነ ፕሮሰር መስፍን ጋር በመሆን በወንበዴዎቹ በወያኔ እና በሻዕቢያ ተወካዮች ላይ (በሻዕቢያው በርሐ እና በወያኔው አሰፋ አብርሃ) የሴናተሮችን አፍ በተፈጥሮ የተሰጡት አፍዝዝ አደንዝዝ አስደናቂና አኩሪ የንግግር ችሎታቸው መቸም የማልረሳው እና የሚያኮሩኝ ዜጋ ቢሆኑም) ኮለኔሉ ስለ ወለጋ እልቂት እና ስለ ሻዕቢያ ምን እንደሚያውቁ ባላውቅም እኔ ያለኝን መረጃ እና ሻዕቢያ በወቅቱ በራዲዮኑ ያስተላለፈው የትግርኛ ዜና እና ኦነግ በጋራ የተሳተፉበት ግዳጅ መሆኑን መረጃው በእጄ እንደነበር አስታውሳለሁ (በ ኢ-ኢ ዲ ኤን የውይይት መድረክም ቅጂው ለጥፌው እንደነበር አስታውሳለሁ)።(በዚህም ተጨማሪ ይህን አስመልክቶ የታሪክ ምሁሩ ዶ/ር አለሜ እሸቴ የዘገቡትን ጉግል ፈልጎ ማንበብ ጠቃሚነት አለው።) ሌላ በተጨማሪ 2008 (በሻዕቢያ ዘመን አቆጣጠር) የሻዕቢያው ጀነራል ኤፍሬም (ወዲ ስብሓት) ያደረገው ቃለ መጠይቅ (“ተዓጠቕ” በሚለው የትግርኛ መጽሔታቸው)ላይ ታጋይ መኮንን የተባለው የግዳጁ የኮማንዶ መሪ ከኦነግ ጋር መበሆን ያደረገው የወቅቱ ጥቃት እነሱ ዓወት/ግዳይ (ድል/ግዳጅ)ይሉታል እኛ “ዕልቂት/ጭፍጨፋ”እንለዋለን፦ የሚጠቅሱ መረጃዎች እንዳሉ የታወቀ ነው። የህ የጠቀስኩት ምክንያት ኢትዮጵያዊ አይደለሁም የሚለው የሰለቸኝን ጭራቁን ኦነግ ለመተቸት ሳይሆን ጸሐፊው ሻዕቢያ እንጂ ኦነግ የለበትም በማለት ሲያስተምሩን ውሸት ከሆነ ደግሞ በግልፅ ወጥታችሁ ሞግቱኝ ስላሉት ሁኔታ በጨረፍታ ለመግለጽ ነው። አሁን በዚህ ብዙ አልገፋበትም። አሁን ከላይ የገለጽኩት ጥቅስ (ስለ ግንቦት7) ያሉትን ልመለስና ወደ ሁለተኛው ጸሓፊ እገባለሁ። ጥቁር ጫካ ስለ ግንቦት7ፍቅራቸውና ሦስቱ የአማራው አካባቢ ክፍለሃገሮች መረን የለቀቀ ፍቅር እንዳለው እንደሚከተለው ገልጸውታል። “ከዚህ ከሚደግፋችሁ ሕዝብ ውስጥ ደግሞ አማራው አንዱ ነው። ባሁኑ ሰአት በጎንደርም በጎጃምም በወሎም ያለ ሕዝብ ትኩረቱና ፍላጎቱ ከናንተው ጋር ነው። ቤተሰቦቼን እንኳን አደረሳችሁ ለማለት ጎንደር ስደውል ዘመቼ ገና የናፍቆት ሰላምታዬን ሳልጨርስ “ስለ ግንት7 ላወራቸው ፈለጉ” (ቅንፍ የኔ)፡ይህ ማለት ታለቋ መሪያችን ብርቱካን ቅንጅት መንፈስ ነው እንዳለችው አሁንም ግንቦት7 “መንፈስ ነው፤ በሁሉም ቤት ገብቷል” (ቅንፍ የኔ) አማራውን ለማስጨፍጨፍ ባደባባይ ያወጀውን ተስፋዬን ሳታስጠጉ “አማራው ምን ይሰማዋል?ምን ይለናል?ብላችሁ አስቡ” (ቅንፍ የኔ)” ወንድሜ አቶ ጥቁር ጫካን ልጠይቅ፦ በጨረፍታም “በኢመይል ደብዳቤ”እንደላኩለዎት አሁንም በድጋሚ በይፋ እዚህ ልጠይቀዎት። የጠቀሱት ሦስቱ የአማራ ክፍለሃገር አካባቢዎች ፍቅሩ፤ፍላጎቱና ትኩረቱ ከግንቦት7 “መንፈስ ነው” ጋር ነው ሲሉን በወያኔ መሳፍንቶች ዓይን ውስጥ የገባው የሸዋው አማራ ለግንቦት7 ያለው ፍላጎት ፍቅርና ትኩረት ምን እንደ በላው አልነገሩንም። የሸዋ አማራ ብቻውን ተነጥሎ የነ ብርሃኑ የነ አንዳርጋቸው የነተመስገን ማዴቦ “መንፈስ”ለምን እንዳልማረከው የጎንደር ቤተሰብዎ በዚህ ያለዎት ነገር ቢኖር አንድ ቢሉን?ለመሆኑ ቤተሰቦችዎ እንኳን አደረሳችሁ ለማለት ላዲሱ ዓመት ሲደውሉ “ገና የናፍቆት ሰላምታዬን ሳልጨርስ “ስለ ግንት7 ላወራቸው ፈለጉ” ሲሉን እውን ከእርስዎ ይልቅ ለግንቦት7 ናፍቆት አይሎባቸው ነው የርስዎን ናፍቆት ሳያስጨርሱ ስለ ግንቦት7 ፍቅርና ነፍቆት ትኩረታቸው ሊስበው የቻለው?በጣም አስገራሚ የናፍቆት ሰላምታ ነበር የተለዋወጡት። አገር ጥሎ፤ባሕር ተሻግሮ በናፍቆት የሚቃጠለው ቤተሰብዎን ለማነጋገር ሲደውሉ የፖለቲካ ድርጅት ቅድሚያ ሰጥቶ የርስዎን የናፍወቆት ሰላምታ አቋርጦ ለድረጅት ፍቅርና ናፍቆት ቅድሚያ የሚሰጥ የሰላምታ ልውውጥ (ያውም ኑሮአቸውና ልጆቻቸው በምቾት ውጭ አገር እያስተማሩ የሚገኙ የግንቦት7 መሪዎችና ድርጅታቸው! ላም አለኝ በሰማይ ወተትዋንም አላይ!) ስሰማ የመጀመርያ ጀሮየ ነው። በጣም አስገራሚ መንፈስ~! እውነትም መንፈስ! ለመሆኑ አማራው ብቻ ለግንቦት7 ፍቅሩ የለገሰው በምን የትግል ማሕደሩ ይሆን? ለመሆኑ የርስዎ መረጃ ከአንድ የስልክ ጥሪ እና ከአንድ ቤተሰብ ጋር ያደረጉት ውይይት መላውን (ሦስቱን) አብዛኛው አማርኛ ተናጋሪ አካባቢዎች ያሉበትን ክፍለሃገሮች እንደ የሕዝብ ጥናት (ሪሰርች) አድርገው ለኛ ሲያቀርቡ ተቀባይነቱ ምን ያህል ተአማኒነት እንደሚሆን መዝነው ነበር? ለግንቦት7መልክትዎን ሲያስተላልፉም አስገራሚው ምክርዎ እንዲህ ይላል፡ “አሁንም ግንቦት7 “መንፈስ ነው፤ በሁሉም ቤት ገብቷል” (ቅንፍ የኔ) አማራውን ለማስጨፍጨፍ ባደባባይ ያወጀውን ተስፋዬን ሳታስጠጉ “አማራው ምን ይሰማዋል? ምን ይለናል? ብላችሁ አስቡ” (ቅንፍ የኔ)” ብለዋል። ወንድሜ አቶ ጥቁር ጫካ፡ ምክርዎ እንከን የለውም። ተስፋዬ ገብረአብ የተባለው የሻዐቢያ እና የኦነግ ነገረፈጅ መሆኑ እውን ነው። እሱን እያቀበጡት ያሉት በትልቁ “ግንቦት7የተባለው መሪ ብርሃኑ ነጋ እና ተከታዮቹ፤ እነ ክንፉ አሰፋ (ኢትዮ -ፎረም.ኦርግ)ኢካድ ፎረም.ካም (ተክሌ)፤ካረንት አፈይርስ ፓልቶክ (የሻዕቢያ፤የኦነግ እና በስሜት የሚከንፉ ፀረ ትግራይ ሕዝብ የሆኑ ግራ የተጋቡ አንዳንድ ውዥምብራም ኢትዮጵያዊያን/ኢትዮጵያዉያት የመለስ ዜናዊ ተቃወሚዎች ነን የሚሉ ስብስቦች እና የግንቦት7 ደጋፊዎች በሙሉ) እንዲሁም ኢሳት የተባለ አዲሱ የቴሌቪዥን ጣቢያ (ከሻዕቢያ ደጋፊዎች ጋር የሻዕቢያ ባንዴራና እና የኢትዮጵያ ሰንደቃላማ አብረው በማውለብለብ ለሻዕቢያ ድጋፍ ባደባባይ ሰልፍ የወጡ እነ ንአምን ዘለቀ የሚመሩት የቴሌቪዢን ጣቢያ/መደብር…)እና የሻዕቢያው ወኪል ኤልያስ ክፍሌ እና አገር ውስጥ የሚታተም “አውራምባ ታይመስ”ተብሎ የሚታወቀው ሌላኛው ውዥምብራም ጋዜጣ)ተስፋዮ ገብረአብ የተባለው የወያኔ፤የኦነግና የመሳሰሉ ያን የሻዕብያ ውሻ እያቀለጳጰሱብን ያሉት እነኚህ ናቸው። ሌላ ቀርቶ የስዬ አብርሃን እናት “አንቺ”እያለ በመዘርጠጥ ሲጽፍ ሆን ብሎ እንደጻፈው ዋለጌነቱ ቢረዳውም ትላልቁን፤ አረጋዊውን፤ ቄሱን፤ባሕታዊውን፤እናቶችን፤ያገር መሪዎችን፤ነገሥታትን ባንቱታ ሳይሆን በአንቺና በአንተታ ባንድ ጆሮዋቸው የማንጠልጠሉን የባንዳዎቹ የሻዕቢያ ባሕል መላበሱን በፖለቲካ ውስጥ የሌሉበትን የስዬ አብርሃ ወላጅ እናት (ያውም በዕድሜ በጣም አረጋዊ የሆኑትን እናት) አንቺ እያለ ሲዘልፍ ሻዕቢያነቱ ያስታውቅበታል። ያላነበባችሁ እንዳትኖሩ ለሬከርዱ እነሆ እንዲህ ነበር ያለው፡ (“ፍርድ ቤት ስቀርብ እናቴ በትምኒት ተደግፋ መጥታ ነበር…”(ስዬ አብርሃ ነው እንዲህ እያለ ያለው በአዲሱ መጽሃፉ ውስጥ)በዚህ አያበቃም (ተስፋዬ ገብረአብ ነው በዙሁ አላበቃም እያለ ያለው)። ከመታሰሩ በፊት እናቱን ከወንድሙ ከምህረተአብ ቤት (ምህረተአብ የታሰረ ቀን) አጊኝቷት እንደነበርና ሶፋ ላይ ቁጭ ብላ እንደነበር ጭምር ይነግረናል።”) ስለዛ የሻዕቢያ ሰላይ አዛውንትን የመዝለፍ ዋልጌነቱን እዚህ ልተውና አቶ ጥቁር ጫካ “አማራውን ለማስጨፍጨፍ ባደባባይ ያወጀውን ተስፋዬን ሳታስጠጉ “አማራው ምን ይሰማዋል? ምን ይለናል? ብላችሁ አስቡ” (ቅንፍ የኔ)” ስለሚሉት ትንሽ ልበል። አማራውን ለማስጨፍጨፍ ባደባባይ ያወጀው ሰላዩ ተስፋዬ ገብራብ ብቻ አይደለም። እርስዎ “መንፈስ” የሚሉትን ግንቦት7 የሚመራው የእስላሞች ኮፍያት/ኮፊያ አጥልቆ አሥመራ ኮምቢሽታቶ ላይ የሚሞላቀቀው አንዳርጋቸው ጽጌም በአማራው ሕብረተሰብ ላይ የዕልቂት ጥሪ አውጆ ለትውልድ የሚተላለፍ መጽሐፍ ከትቦ አስተላልፏል። በተለይም ደግሞ “ብሔሬ/አገሬ/ፋዘር ላንድ/ማዘር ላንድ- በትግርኛው “ዓዲ አቦ” ኢትዮጵያ ነው” ያለውን ሁሉ በጠላትነት እንዲታይ የሕሊና ከበባ እንዲደረግበት ከሻዕቢያዎቹ/ከጀብሃዎቹ…ከእነ ተስፋዬ ገብረ አብ ፤ከእነ መለስ ዜናዊ፤በረከት ስማኦን፤አርከበ ዑቁባይ፤ቴድሮስ ሐጎስ፤ስዩም መስፍን፤ስብሓት ነጋ…እና ከመሰል የወያኔ ቡችላዎች ጋር ሆኖ ከባድ ቅስቀሳ አድርጓል። አንዳርጋቸው “ኦሮሞ ነኝ” ብሎ በመጽሐፉ ይፋ ቢያደርግም አሁንም እርስዎ እንደሚነግሩን “አንዳርጋቸው ተስፋዬ ገብረአብ የሻዕቢያ ሰላይ/መረጃ መሆኑን ያውቃል ነገር ግን እርስዎ እንዳሉት አስመራ ውስጥ ኢትዮጵያዊያኖቹን እየራቀ የእስላም ቆብ አጥልቆ ከቀንደኛው የኢትዮጵያ ጠላት ጋር አሥመራ ውስጥ ከተስፋዬ ገብረአብ ቤት ውስጥ ዕቃውን ጠቅልሎ ገባ። ብለውናል። አስገራሚ ታሪክ ነው የነገሩን። ሁለቱም አንድ ናቸው።አንዳርጋቸው ከተስፋዬ ገብረአብ ምን ይለየዋል? ፍቅራቸው የጸና ነው። አሁንም ከጠላታችን ጋር ነው እየተሻሸ ያለው። ብርሃኑም አንዳረጋቸውም ለሰላዩ ያላቸው አክብሮትና ፍቅር በጣም የናረ ነው። ያ ፀረ አማራ የሚቀሰቅስ መጽሐፍ ጻፈ፤ ያም እንደዚሁ ጸረ አማራ የሚያነሳሳ መጽሐፍ ከተበ! ከሁለት መልከ ጥፉ ዝንጀሮ ማን ይመርጧል? ግንቦት7ን የሚያደንቁ እንደርስዎ ያሉ የግንቦት 7አድናቂ የአርበኞች ግምባር አባሎች ከዚህ ጸረ ኢትዮጵያና ጸረ አማራ ግለሰብ ጋር በእፍ-እፍ ፍቅር የተለከፉት አንዳርጋቸውና ብርሃኑ ስለሚመሩት ድርጅት ማድነቅ/መደገፍ የአማራው ሕዝብ ምን ይለናል ማለት የነበረበት ይልቁንስ እንደርስዎ አይነት ሰው ነበር። ያውም እርስዎ በጽሑፍዎ እንደነገሩን ከሆነ የተስፋየ ገብረአብ አዲሱ መጽሐፍ (እስካሁን አላነበብኩትም)አማራው ከአደሬውና ከትግሬው ቂም እንዳለውና እንዲጨፋጨፍ ፕሮፓጋንዳ እንደጻፈ” ያ የጥላቻ መጽሐፍም ግንቦት7 አሳትሞ ለገበያ እንዳዳረሰው ገልጸውታል። ታዲያ ግንቦት7 በአማራው ሕዝብ የሚደገፍ እና የአማራው ሕዝብ ትኩረት እንደሳበ የሚነግሩን አማራው የሚጨፈጨፍበት ሰበካ የሚቀሰቅስ መጽሐፍ ከተሸጠ እና ለገበያ ይፋ ከሆነ ቆይቷል፡ ታዲያ የሸዋው አማራ ሕብረተሰብ ክፍል የተስፋዬ ገብረአብ ተንኮልና የግንቦት7መሪዎች (ያውም አንዳርጋቸውና ብርሃኑ መጽሐፉን በአራሚነት እንደተሳተፉበትም ይነገራል) በማከፋፈሉ/በሕትመቱ/በማስታወቅያው የተሳተፉበትን “የጥላቻ መጽሐፍ” አንብቦት ሆኖ ይሆን ትኩረቱን ሳይስበው ቀርቶ፡ የጎጃም የጎንደር እና የወሎ አማራ ሕዝብ መጽሐፉ አልደረሰውም ሆኖ ይሆን ወይስ ስለ’ዛው “የጥላቻ መጽሐፍ” የሚነግረው አጥቶ? እንደው “ማን ይሙት!” ለመሆኑ አንዳርጋቸው ጽጌ ማን እንደነበር የዚህ ክፍል ሕዝብ አያውቀውም ማለት ነው? እስኪ መልሱን ከእርስዎ ልስማ? ወደ ሌላኛው ግንቦት7 አዳማቂ፤ደጋፊ እና ሰባኪው ወጣት ተክሌ ጽሑፍ እናምራ። “አሁንም፤ ኤርትራ መዳኚያችንም መጥፊያችንም ትመስላለች-..ክፍል አንድ ኤርትራ፣ አርበኞች ግንባር፣ ግንቦት ሰባት” በሚል ርዕስ የቀረበው የተክሌ ጽሁፍ “ግንቦት ሰባት በግሌ ባደባባይ ከኤርትራ መንግስት ጋር መነጋገርና መስራት ካልጀመረ፡ሌሎች የስራ መንገዶች ሁሉ ተዘግተዋልና ትግላችን እዚያው ባለበት መርገጥ ነው ባይ ነኝ።”የኢትዮጵያን ህዝብ ነጻ ማውጣት በሚደረግ ትግል ውስጥ ግንቦት ሰባትም ይሁኑ ሌሎች ሀይሎች ከኤርትራ ጋር በኢትዮጵያ ስምም ቢዋዋሉ፡ የኢትዮጵያን ጥቅም አሳልፈው እስካልሰጡ ድረስ ምንም ጥፋትም ክፋትም የለውም። ባህሩንም የባህሩንም በር አሳሌፎ የሰጠ መንግስት አዱስ አበባ ቁጭ ብሎ የለ፡ ያውም እኛ በኢትዮጵያ ዘሊቂ ጥቅም ላይ ከሌሎች ሀይላት ጋር አንዋዋልም፡ ሌላ ሽሽት ነው።መንገዳችን ኤርትራ ብቻ ነች። እነሆ ምክንያቶቼ።” ሲል ምክንያቶቹን ይዘረዝራል። ወይ ጉድ! ሻዕቢያ ድረስ ሄደን ፤ እግር ስመን ተዋጊ ሃይል እንዲያሰለጥንልን በቁሳቁስና በሞራል እገዛ ቢያደርግልን ኢትዮጵያን ከወያኔ ጦር ነፃ ማውጣት ይቻላል ነው የሚሉት እኒህ ወገኖች። ልጁ የሚለን የኢትዮጵያ ጥቅም አሳልፈው እስካልሰጡ ድረስ ምንም ጥፋትም ክፋትም የለውም ነው። እያለን ያለው። ልጁ የጣሳቸው ሕጎች አሉ። እጠቅሰዋለሁ። አንደኛ ሻዕቢያ የኛ ጠላት ነው። የኤርትራኖችም ጠላት ነው። ቡድኑ ፋሺስት ነው። መሪውዬውም ሕግ ቢኖር ኖሮ በተለያዩ ወቅቶች በዓለም አቀፍ ሕግጋት የሚያስጠይቀው ወንጀል የፈጽመ የጦር ወንጀለኛ ነው። ከሃይለስላሴ፤ከደርግ እስከ ወያኔ ድረስ ያሉት ወቅቶች የፈጸማቸው ወንጀሎችን ይጠቅሰዋል። በሗላ እምለስበታለሁ። “ለመታገል ኤርትራ የሚሄድ ሁሉ የሸቀጥ ነጋዴዎች ሳይሆኑ እራሱ ሸቀጥ ነው አለኝ።”ሲሉ ጥቁር ጫካ የተባሉት ጸሐፊ አስመራ ውስጥ ከሚገኝ አንድ የአርበኞች ግምባር አባል በሚገባ አብራርተውታል። “ኤርትራ ውስጥ በራስህ፤በወገንህ ዓላማ/አጀንዳ መታገል አይቻልም።በግድ በሻዕቢያ ጥቅም እየተደለልክ፤በሻዕቢያ ዓላማና ስልት ነው መታገል ያለብህ። እሱ በፈቀደው! ይኼን የማይቀበል ወደ መጣበት እምቢ ብሎ መመለስ ነው። አቅም የለውማ!!!! ባዶ እጅ ተይዞ ሸዕቢያን በምኑ ነው ወደ ጠረጴዛ አስጠግቶ እኩያ አድርጎ መደራደር የሚቻለው!?እምቢ አልስማማም ያለ ቀኝ ሗላ ዙሮ ወደ ለንደን ይሄዳል፤ የሚቀበል ደግሞ በሆዱ እየተገዛ ናቅፋና ዶላር እየፈሰሰለት ያገለግላል። ስለዚህ ሸቀጥ ሆነ ማለት ነው። ይኸ ደግሞ ጥቁር ጫካ ቁልጭ ባለ ሁኔታ አብራርተውልናል። ይኼን በሚመለከት ለመረዳት ሲል ኤርትራ ውስጥ ያለ ወዳጃቸው እቅጩን ነግሯቸው እንደነበር አቶ ጥቁር ጫካ ከላይ በጠቀስኩት ክፍል አራት ዘገባቸው ላይ ዘግበውታል፡ ያን ማንበብ ነው። ስለዚህ ወጣት ተክሌ የሚያምታተው “የሻዕቢያ መኳንንት/ባለስልጣኖች ለኢትዮጵያ በጎ የሚመኙ ናቸው” ግንቦት7 በሕዝብ ስም ከሻዕቢያ ሹማምነት ጋር የኢትዮጵያን ጥቅም አሳልፈው እስካለሰጡ ድረስ ቢዋዋሉ ምንም ክፋት የለውም” ይለናል። የፖለቲካ ጌኞነት ካልሆነ በቀር ግንቦት7ም ይሁን ሌሎቹ ወደ ፋሸስቶቹ መንደር ሲገሰግሱ ከሻዕቢያ ጋር ሲደራደሩ “እራሳቸው የሚሸጡ ሸቀጦች”ናቸውና የሚደራደሩበት ካርታ/ቺፕ/ጠጠር፤መደራደርያ የላቸውም።የባሕር ወደብ መጠየቅ አይችሉም፤ በስታሊናዊ/ሞኦይስት/ማርክሲሰት/ኮሚኒስት/ፋሺስታዊ የብሔር አደረጃጀት ስልት ካልተደራጁ ዕጣቸው ተመልሰው ወደ መጡበት አገር ባዶ እጅ መጓዝ ነው። ከሻዕቢያ ልሳን የማይጠፋ “ዓጋሜዎች ጠግበዋል1”ሲሉ ዝም ብሎ ማዳመጥ ነው። አማራ/ነፍጠኛ/አድጊ ቦታውን አስይዘነዋል!ሲሉም ዝም ብሎ ማድመጥ ነው። ይኼንና እነኚህን የመሳሰሉ ሞሶሊናዊ ትምክህቶች አርፈው ማድመጥ ካልቻሉ፤ ዕጣቸው ባዶ እግር ወደ እንግሊዝ፤ዴንማርክ፤ አሜሪካ… መመለስ ነው። ኢትዮጵያዊን ነን የሚሉ ሻዕቢያን በጦርነት ከሚዋጉ የቀይ ባሕር ዓፋሮች (ዓሰብና ምፅዋ ተወላጆች)ኢትዮጵያዊያ አፋሮች እና ሌሎቹ ጋር ግንኙነት ማድረግ አይችሉም። እነኚህ ሁሉ የሻዕቢያ መደራደርያዎች ናቸውና ‘የማይነኩ-ለድርድር የማይቀርቡ ሕጎች ናቸው። ታዲያ አስመራ ድረስ እየሮጡ ዕርዳን ብለው ፋሺስቶቹን የሚማጠኑ ኢትዮጵያዊያን የፖለቲካ ድርጅቶች የሚደራደሩባቸው ምን የመደራደርያ መቁጠርያዎች ይዘው ነው አንድ ሁለት ብለው ሻዕቢያን ሊደራደሩ የሚችሉት። ምንም! እራሳቸው ሸቀጦች ናቸውና የመደራደር መብት የላቸውም! ሻዕቢያን የሚጠይቁት “ጠመንጃ፤ማሰልጠኛ ቦታ፤ስንቅ፤ትጥቅ፤ መጠለያ፤ አሰልጣኝ፤መሸጋገርያ ዲፕሎማቲክ ፓስፖርት ቪዛ….” ሲሉት ፡ ሻዕቢያ ደግሞ ይህንነ ለማግኘት “በብሔር ተደራጁ፤የባሕር ወደብ መብት አትጠይቁ፤መንግሥትነት ስትረከቡም ለወደፊቱ እንዳትጠይቁ በፌርማችሁ አረጋግጡ ቢላቸውስ? (ተክሌ የሚለውን “ሕዝብ ባይፈቅድም ድርጅቶች የመደራደር መብት አላቸው” የሚለውን ማለት ነው ድረድር ማለት?) ተክሌ ያልገባው (ወይንም ገብቶት ነገር ግን ሆን ብሎ የጀሌ ሰበካ/ፕሮፓጋንዳ እያዳመቀም ሊሆን ይችልል) ነገር “ዘላቂ የኢትዮጵያ ጥቅም እስካልተደራደሩ ድረስ ማንም ድርጅት/ግንቦት7… በሕዝብ ስም መደራደር መፈራረም ይችልል” ሲል ተክሌ ነገሩ እጅግ አልገባውም። “ተመጽዋች ተደራዳሪ ስላልሆነ አቅም ስለሌለው ደካማ ወገን የሚደራደረው በዘላቂ ያገሪቱ ምስጢሮችና ሉዓላዊነት ነው! (ይኼ ደግሞ ባለፈው ታሪካችን ታይቷል) ወያኔ ለሱዳን አስቀድሞ እንደሸጠን አይነት!። ወጣት ተክሌ ያልገባው ነገር እያልኩት ያለሁት ጉዳይ “ከሻዕቢያ ጋር ድርድር ሲደረግ “ሻዕቢያ እንደማንም አገር/ጎረቤት/ሕብረተሰብ/መንግሥት ሰላማዊ የኢትዮጵያ አጋር/ወዳጅ/መልካም በጎ እይታ ያለው ሳይሆን “ጠላት ነው”! ጠላት ሆኖ ከሚታይና በግብርም የታየና በመታየት ላይ ያለ ጠላት የሚመደራደርህ ዘለቄታ ባለው በብሔራዊ ጥቅምህ እና ደካመ ጎንህ ነው! ሻዕቢያ የኢትዮጵያን ብሔራዊ ዘለቄታ ጥቅም መቆጣጠር ቅድሚያ አጀንዳው እና የሕይወቱ ዋስትናው ነው! ያ ካልሆነ ኤርትራ የምትባል አገር በሻዕቢያ ቁጥጥር ስር መኖር አትችልም! ስለዚህ ነው ሻዕቢያ ማንንም ከኢትዮጵያ የሚመጣ ቡድን የኢትዮጵያን ዘላቂ ዕድገትና ጠቀሜታ ላስጠብቅ የሚል ቡድን ድጋፍ የማይሰጠው! ዘላቂ ሀገራዊ ጥቅም ማስጠበቅ የሚባለው አጀንዳ ራሱ ቃላቱ “ከኤርትራ ጋር ጦርነት የሚቀሰቅስ ነው!” ስለሆነወም ሻቢያ በራሱ ላይ ለመዝመት የሚመጣ (ዘለቄታው የሚጻረር ቡድንን) ለመርዳት የማይፈልገው! ተቃዋሚዎቹም ቢሆን እንዳልኩት የሕዝብ መብት ለመደራደር መብቱስ ይቅርና “የሚደራደሩበት አቅምም የላቸውም”! ስለዚህ ተክሌ ራሱን ማታለል ካልሆነ ግንቦት7 አንድ አንዳርጋቸውና 15 ሰዎች በስድስት አመት ውስጥ ተሰነይ ውስጥ/ሳዋ ውስጥ (? በጥቁር ጫካ ዘገባ መሰረት) ጦር እያሰለጠነ ማለት (ራሱን ባልዘረጋበት ሁኔታ ሆኖ) የሕዝቡን ዘለቄታ ለመደራደር ይችላል ማለት ሓማ ቱማ “ቃለ አጋኖ” የሚለው ወይንም ጉረኛ ፖለቲካ ከማስተጋባት ሌላ የሚፈይደው የለም! በማለት የምከራከረው ለዚህ ነው። ወገኖቼ ሆይ! ባለፈው ታሪካችን ስናስታውስ ከሻዕቢያ ጋር ተዳብለው የሰለጠኑ እና የተጎዳኙ ወይንም ዛሬ እንደ እነ ተክሌ እና ንአምን ዘለቀ እንደ እነ ክንፉ አሰፋ እና የግንቦት7 መሪዎች እና ምሁራን ወዘተ ወዘተ… ስለ ሻዕቢያና ወያኔ መሪዎች ሰብአዊነት፤በጎነት፤ነፃ አውጪነት፤አሳቢነት ሲሰብኩና የዋሁን ሕብረተሰብ ሲያደናግሩ ኖሮው መጨረሻ ላይ ተው ልክ አይደለም ሲባሉ አንሰማም ብለው፤ ሁለቱ ወረበሎች አስመራና አዲስ አባባ ሲቆጣጠሩ “”ዋሽንግተን ኮነግረስ ውስጥ አሰፋ አብራሃ የተባለው የወያኔ አፈቀላጤ/ቱልቱላ (ከ እንግሊዝ አገር/ለንደን) “ኢምፔርያል ኢትዮጵያ” “ኮሎኒያሊስት ኢትዮጵያ’ ሲል ፕሮፌሰር በርሐ ወልደገርግስ የተባለው ሌላኛው የሻዕቢያ ጡሩምባ ነፊም ኤርትራኖች ከኢትዮጵያ ነፃ መውጣታቸው ጥቁር አሜሪካኖች ከባርነት ቀንብር ነፃ በመውጣት “ፍሪ አትላስ”እንዳሉት ሁሉ፤ የእስራል አይሁዶችም ከናዚዎቹ ቀንበር ነፃ እንደወጡት ሁሉ ኤርትራኖችም ከኢትዮጵያ ቅኝ ግዛት ኮሎኒያሊስቶች ከባርነት ቀንበር ሰንሰለቱን በጥሰው ነፃ በመውጣታቸው ከበሮ እየደለቁ ደስታቸውን በመላው ዓለም በመግለጽ ላይ ይገኛሉ። ዓለም የዓይን ምሰስክር ነው! ብሎ ነበር። እንኚህን ሓሰተኞች፤ከዳተኞችና ጭራቆ ድርጅቶች እየካቡ ታዝበን ስንገጥማቸው “ተውዋቸው”“አትውቀሱዋቸው” ሰንደቃላመይቷን ቢያበሻቅጡም ታሪክ ቢዘልፉም ’አትቃወሙዋቸው፡ ደርግን የጣሉልን አዳኞቻችን ናቸው፤የብሐረሰብ መብት ተማጓቾች ናቸው…..ሲሊን የነበሩ ሁሉ አንድ ሳምንት ሳይቆዩ “በተናገሩት ምላስ አፍረው የገዛ ምላሳቸው ቀረጠሙት” አንዳንዶቹ ዛሬ ከኛ በባሰ ሲጮኹ ይታያሉ (አንዳንዶቹ’ማ የፏስሰቶቹ ቀንደኛ የናዚ “ጉበል” ሆነው መጽሐፍ ሲጽፉ የነበሩ ናቸው)። ዛሬም ያ ታሪክ በተጠቀሱት ቡድኖች ካለፈው ትምህርት ሳይቀስሙ እንደ አህያ ያ ስንፍና ዛሬም እየደገሙ “ኤርትራ ገዳያችን/አዳኛችን” ነች ወደ ሻዕቢያ እንንበርከክ ሲሉ ወደ ፋሽስቶቹ እንሸብረክ እያሉ አሳፋሪ ሰበካ በመስበክ ሰሞኑን የውርደት ሰበካ በማጧጧፍ ላይ ይገኛሉ። ይህ የተቀነባበረ ጸረ ኢትዮጵያ ዘመቻ መልከ ብዙ ቢሆንም በተጠቀሱት ሚዲያዎችና የሚዲያ በለቤቶች የሚዘረጉት የኤሊቲሲዝም ክበብ/ቡድን ሰበካዎች ለመቋቋም ዛሬም በድጋሚ እንዳለፉት ሁሉ ትግሉ መጦፍ አለበት እላለሁ። ትግላችን በጸረ ኢትዮጵያ ቡድኖች፤ጠባብ ትምክህተኞች፤ኤሊቲሲዝም’የሊሂቅ/የፈርሳም ክለብ ፖለቲካ አራማጆች የሚነዙት ሰበካ ላይ ማነጣጠር ወቅታዊ ነው። በደርግ ወቅት ደርግ ወቅት ወያኔ፤ሻዕቢያ ኦነግና ወያኔዎች እንደነበሩ ሁሉ ዛሬም ጠላት የሚባሉት ወያኔዎች ብቻ ሳይሆኑ ከሻዕቢያ ከጭራቆቹ ከነ ኦነግ ጋር እንጠጋ “ሻዕቢያ አዳኛችን ወይንም ገዳያችን” ነው፤ ከሱ ጋር ካልተደራደርን፤ካልተጠጋን የኢትዮጵያ ሕልውና ለዘላለሙ ያከትማል። ፈጣሪያችን ሻዕቢያ ነው፤ ሊገድለንም ሊያድነንም የሚችለው እሱ አንድ ሻዕቢያ/ኤርትራ ነው!! እንጠፋለን! ብሎናል ተክሌ የተባለው የግንቦት7 ሰባኪ ወጣት። እኛ በጭካኔ ያደጉ የሻዕቢያ ወጣቶችና መሪዎቻቸው አብረን ስላደግን እናውቃቸዋለን፡ ተክሌ ባህሪያቸው አያውቃቸውም። በዕድሜም የበሰለ አልመሰለኝም።ያደገው ቦረና ይመስለኛል። ስለዚህ የተስፋዬ ገብረአብ ሰበካ እንደ ጋቢ ሲከናነበው ሙቀት እንደሚጥማት እንቁራሪቷ ለጊዜውም ተመችቶት “ገዳያችንና አደኛቺን ሻዕቢያ/ኤርትራ ነው/ነች” እያለን ያለው የኢካድ ፎረም ባለቤት ወጣቱ ተክሌ ኤርትራ በማን እጅ እንዳለች መንገሩ አስፈላጊ ሆኖ አግኝቼዋለሁ። ኤርትራ የትግራይን ወጣት፤እናቶች፤አባቶች፤መምህራን እና ህጻናት ዓይደር ላይ በክላስተር ቦምብ በአይሮፕላን የፈጀ በፋሽስቶች በወረበላ (ራግ ስቴት) እጅ በሻዕቢያዊያኖች እጅ ነች። ተክሌ እና ግንቦት7 መሪዎች ስለ ትግራይ ህፃናትና ስለ ኢትዮጵያ ሰላማዊና ወታደራዊ ነብሳት መጨፍጨፍ በሕሊናቸው ማሕደር ውስጥ አልተዘገበም። ቢኖርም ጉዳይ አላሉትም። እኛ ግን አልረሳነውም፡ በወቅቱ አነጋገር “ኤርትራ ማለት ሻዕቢያ መሆኑን ተረዱልን”። በደመኛ ጠላታችን የተያዘቺው ኤርትራ (ሻዕቢያ)ገዳይ እንጂ አዳኛችን ልትሆን ከቶ አይቻላትም። ስትገድለን መሸብረክን ዳግም የሚሰብኩ ተሸብረኩ የሚሉን ሃፈረት ትርጉም የማያውቁ ነብሳት ማወቅ ያለባቸው በኛ እና በኤርትራ ሻዕቢያ መካከል ያለው ነባራዊ ሁኔታ “የጥይት ዝናም እንደ ማባራት ቢልም በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል የቆየው ጦርነት አበቃ ምዕራፉም ተዘጋ ለማለት አያስደፍርም። “የተኩሱ ድምፅ እየሞተ መሄድ ወይም የጥይት ማጓራት ማቆም፤በተጨማሪ፣ የተሟሟቀ ውጊያ ወሬ ጊዚያዊ ዝምታ የሰላም መገኘት ምልክት አይደለም”(አምባገነኖችን እንዴት እንቀላቀላቸው?) ጦቢያ ቁጥር 12 ቅፅ 7 ቁጥር 12 1992 ዓ.ም.) የምንለው አሁንም ግንቦት ሰባትና ሌሎቹ ወደ አስመራ በመገስገስ የሻዕቢያን መሪ በርና የሻዕቢያ “ባይቶ” በማንኳኳት የሚማጸኑትንም ሆነ “ሻዕቢያ አዳኛችንም ገዳያችንም ነው” በማለት የአዳኝና የገዳይነት መለኮታዊ ኦምኒፖተንስነት የሚሰብኩን የሻዕቢያ ቱልቱላ ኢትዮጵያዊያኖች (ስዬ አብርሃ በምርጫው የክርክር መድረክ ወቅት የሻዕቢያን ቱልቱላ አርከበ ዑቁባይን “የሻዕቢያን ሚሊዮን ሕዝብ (ሕጻንት…አረጋዊያን..ነብሰ ጡሮችን…) ነብሰገዳይነት እያነሳችሁ ባታስፈራሩን ይሻላል!!” እንዳለው እውነታ ሁሉ) ከገዳዮቻችን ጋር ጦርነቱ ስላባራ ሞተናል እና እንንበርከክ የሚሉ “የመንፈስ ሙታኖች” “የሻዕቢያ ጌታነት አሰልጣኝነትና ገዳይነትና አዳኝነት እየነገሩን”አንድንባንን የሚማጸኑን የዘመናችን ሰባኪዎች ሊያውቁት የሚገባ መልዕክት የጦርነቱ ምዕራፉ እንዳልተዘጋ ያውቁልን ዘንድ በዚህ አጋጣሚ መልክቱ ይድረሳችሁ። የኛ የውሻ ልጅ (አወር ሳን ኦፍ ኤ ቢች) ገዳያችን እንጂ አዳኛችን ሊሆን የማይችልበት ምክንያት ዘርዝሩ በክፍል ሁለት ይቀጥላል………….. ሻዕቢያ ስለ ኢትዮጵያ በጎ አሳቢነትና አዳኝነት አትስበኩን! ክፍል 2 ይቀጥላል…. ጌታቸው ረዳ “ኢትዮጵያን ሰማይ” ብሎግ አዘጋጅ። www.ethiopiansemay.blogspot.com getachre@aol.com
Tuesday, September 21, 2010
Subscribe to:
Posts (Atom)