Wednesday, December 7, 2022

መርዘኛዋ “ርዕዮት ዓለሙ ጎቤቦ” እና የአብይ አሕመድ የርዕዮተዓለም ውትፍ ነቃዩ “ዮናስ ብሩ” ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay) 12/2/22

 መርዘኛዋ “ርዕዮት ዓለሙ ጎቤቦ” እና የአብይ አሕመድ የርዕዮተዓለም ውትፍ ነቃዩ “ዮናስ ብሩ”

ጌታቸው ረዳ

(Ethiopian Semay) 12/2/22

“ርዕዮት ዓለሙ ጎቤቦ” ማን ናት? አገር ውስጥ የእንግሊዝኛ ቋንቋ መምህር ነበረች የሚባልላት በወያኔ ስርዓት ታስራ ከተፈታች በኋላም  ወደ አሜሪካ በመምጣት የብርሃኑ ነጋ የግል ንብረት በነበረው ‘ኢሳት’ በተባለ የሻዕቢያና የኦነግ አለቅላቂ ሚዲያ ውስጥ በተንታኝነት ተመድባ “ለግንቦት 7 ህይወቴ እስከመስጠት ድረስ እታገልለታለሁ” ብላ ቃል በመግባት የጸረ አማራው አንዳርጋቸው ጽጌ እና የብርሃኑ ነጋ ርዕየተ-ዓለም አቀንቃኝ የነበረች ነች።

ከዚያም አብይ አሕመድ የተባለ የጠለፋና የግድያ ሥራ የሚካሄድበት “ኢንሳ” የተባለው የስለላ ድርጅት መስራችና ህቡእ የኦነግ አባል የነበረው የዛሬው የኦሮሙማ መንግሥት መሪ ሆኖ (በነገራችን ላይ ይህች ልጅ በትውልድ ሐረግዋ “የሲዳማ፤የወላይታ፤የጉራጌ ሰው ትሁን ወይንም “ኦሮሞ” አላውቅም የኦሮሙማ ትርጉም “ትግራዋይ” እንደማለት እንጂ ኦሮሙማ የሚባል “አጀንዳ” የለም ብላ አጀንዳው ከመሰረቱትና በዝርዝር ካሰፈሩትና አጀንዳውን ከፈጠሩት ኦሮሞ ነን ከሚሉ “እነ ኢብሳ ጉተማ ፤ እነ ዳውድ ኢብሳ፤ አሰፋ ጃለታ፤ መሓመድ አሕመድ …….ወዘተ” የተሻለ ዕውቀት አለኝ ብላ የምትከራከር ነች ፤) አብይ ወደ ሥልጣን ሲመጣ ግማሹ አብይን ለማገልግል ቆርጦ ሲነሳ ግማሹ ደግሞ አብይን በመቃወም ኢሳት “ፍርስርሱ” ወጥቶ በነበረበት ወቅት ይህች ልጅ ባልዋ ከሚባለው “ተቦርነ በየነ” (ተወልደ በየነ) እና ዛሬ ኢትዮ 360 ተብሎ ድንቅ ስራ እየሰራ ያለው ሚዲያ ጋር ተቀላቅላ ስትሰራ ቆይታ ምክንያቱን ባላወቅነው ምክንያት ተገንጥላ ከፍቅረኛዋ (ባልዋ) ጋር ሆና “ምንጊዜም ሚዲያ” የተባለ  ዩቱብ ሚዲያ መስርታ እየሰራች የምንሰማት ይህች  ልጅ ርዕሱ ከተጠቀሰው የአብይ አሕመድ “ውትፍ ነቃይነት” መቁረጥ አላስችል ብሎት ዛሬም አብይን አደንቃለሁ እያለ ራሱን የሚያደነቁር “ያልተማረ ምሁር” ዶ/ር ዮናስ ብሩ እና ጸባየ ሸጋ የሆነው ባለ ብሩህ ኣእምሮ “ፕሮፌሰር ግርማ ብርሃኑ” ከዚህ በታች ባለው  የቪዲዮ ርዕስ እንዲወያዩ አቅረባቸው ነበር።

በሚያሰዝን መልኩ መርዘኛዋ ርዕዮት የአማራ ጀነሳይድ አልተፈጸመም ብሎ በሚከረካረው እና ስለ አማራ በቆሙት ዜጎችና ምሁራን ላይ እንደፈለገው ሲዘረጥጣቸውና ሲያቦካ በቂ ጊዜ ስትሰጠው፤ (ለዚህም ምክንያት አላት- ዮናስ የዘወትር የሚዲያ ደምበኛዋ ነውና የሚጠበቅ ነው) በአንጻሩ ደግሞ “ፕሮፌሰር ግርማ ብርሃኑ” ስለ አማራ ጀነሳይድ መልስ ለመስጠት በሚሞክርበት ወቅት ጣልቃ እየገባች አንዴ ከርዕሱ ውጭ እንዳንሄድ እየሰገሁ ነኝ ትለዋለች፤ አንዴ ሌላ ቀን እናድርገው እያለች በረጋ ምሁርነት መልስ ለመስጠት ለማስረዳት ሲሞክር የጃርት እሾህ እንደወጋት ደሮ ጣልቃ ገብታ በመርገፍግፍ ሃሳቡን ለመቅጨትና ለማደናቀፍ በሚያስነቃባት መንገድ ጠልቃ እየገባች፤ አንዳንዴም እንዳይነቃባት ጨዋ መስላ የማደናቀፍ ስራ ስትሰራ ትሰሟታላችሁ።

 

ያልተማረው ምሁር ዶ/ር ዮናስ ብሩ (ዶ/ር ቢቸግር) በነገራችን ላይ  “ዶ/ር ቢቸግሮች”  ብየ የምጠራቸው ምን አይነቶቹ ምሁራን እንደሆኑ ካሁን በፊት ገልጫለሁ፡ (ሌላው ዶ/ር ዜሮ-ያልኩት ምሁርም  ትዝ ይላችሁ እንደሆነ “ዶ/ር ዜሮ” ተብሎ እስከዛሬ የሚታወቅበት መጠሪያ ስም የሰጠሁት አሁን በመልካም ትግል ውስጥ ስላለ ስለ ሰውየው ማንነት ዛሬ አልፈዋለሁ) ዛሬ ደግሞ “ዶ/ር ቢቸግር” ለመስከረም አበራ እና ከእስክንድር ነጋ ጀርባ ላይ መውረድ አልቻለም (በዚሁ የቪዲዮ ውይይትም ሁለቱን ሲያኝካቸው ትሰማላችሁ-የእስክንድር ስም እያነሳ ለምን እንደሚባንነው ግን ጥናት ያስፈልገዋል)።

በተለይ ደግሞ በተደጋጋሚ እስክንድር ነጋን የማኘኩን ነገር ለማውራት ይከብዳል፤ እጅግም ያማል። ባልደራስ ከተመሰረተበት ቀን ጀምሮ ጠምዶታል። ዶከተር ቢቸግር (ዶ/ር ዮናስ ብሩ) ፌስ ቡክ “The Peacock is spreading its beautiful wings. Esku is spreading COVID-19” እያለ አብይ አሕመድ በኮቪድ እስክንደርን እንዲከስ ሲወተውተው በሳታየር /በአግድም/ ታነቡታላችሁ። የዶ/ር ዮናስ ብሩ ፌስ ቡክ Koki Abesolome  በሚል የብዕር ስም ታገኙታላቸሁ። ለምሁራን የለኝ እጅግ የወረደ ክብር ለሁሉም ሳይሆን እንደ እነ ዶ/ር ቢቸግሮች ዓይነትን ነው።

በዚህ አጋጣሚ ዮናስን የምወድለት ጠንከር ያለ ትዕግስቱን የሚፈታተን ጽሑፌ በመሰንጀር ስልክለት “በጨዋ ደምብ ሲመልስልኝ አይቸዋለሁ”፤ ለዚህም አመሰግነዋለሁ። ሆኖም ያንን በሌሎቹ ቢያደርገው ይመረጥ ነበር።

ዶ/ር ዮናስ የመውቀው ኢትዮጵያን ሪቪው በሚባልና ሬጅሰተር ሲባል በነበሩት መጽሔቶችና “ኢ. ኢ. ዲ. ኤን” እየተባለ ሲጠራ በነበረው “ዶ/ር ቢቸግሮች” (ምሁራን )የሚነጋገሩበት የሃሳብ ልውውጥ መረብ ላይ ለብዙ አመት ነው። የሆኖ ሆኖ የአብይ አሕመድ የርዕዮተዓለም ውታፍ ነቃዩ “ዮናስ ብሩ” መስከረምና እስከንድርን ደጋግሞ መጥመዱ እንዲሁም አማራ ላይ ጀነሳይድ አልተፈጸመም ብሎ ለዚህ ምሰክርነቱ የሚረዳውን አለም አቀፍ የጀነሳይድ “ክራይቴሪያዎች” ከማንበብ ይልቅ “ሩዋንዳ” ላይ ጀነሳይድ አልተፈጸመም ብለው ሆን ብለው ሕዝብ እስኪያልቅ ያሴሩት ምዕራባዊያን እና የተባበሩት መንግስታትን፤ “ሰብአዊ መብት ድርጅቶች”ን እና የአብይ አሕመድ ተቀጣሪ የሆነው ማፈሪያው የዳኒኤል በቀለን ድርጅት ዋቢ አድርጎ የሚከራከረው “ያልተማረ ምሁር” እና የመርዘኛዋ “ርዕዮት ዓለሙ ጎቤቦ” አድሎአዊ አወያይነት እነሆ!

ጌታቸው ረዳ

(Ethiopian Semay)

ምሁራንና ምሁርነት-ወዲህና ወዲያ Mengizem media Reeyot Alemu With Dr.Yonas Biru and Pro.Girma Birhanu Dec6,22

 

https://youtu.be/WziZLaZrVAw