Tuesday, October 1, 2019

በዐፄ ዮሐንስ ዘመን የነበረው የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ (በአቻምየለህ ታምሩ) (Posted on Ethiopian Semay)


በዐፄ ዮሐንስ ዘመን የነበረው የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ
(በአቻምየለህ ታምሩ)  (Posted on Ethiopian Semay)
Emperor Yohannes Flag photographed by Achamyeleh Tamiru from the residence of  Yohannes Palace Mekelle
ከታች የታተመው ሰንደቅ ዓላማ የዐፄ ዮሐንስ ፬ኛ ዘመነ መንግሥት የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ነው። ሰንደቅ ዓላማው መቀሌ በሚገኘው የዐፄ ዮሐንስ ፬ኛ ቤተ መንግሥት ውስጥ አሁንም ይገኛል። ይህን ታሪካዊ የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ በካሜራዬ ያስቀረሁት መቀሌ ዩኒቨርሲቲ በማስተምርበት ወቅት የዐፄ ዮሐንስ ፬ኛን ቤተ መንግሥት በጎበኘሁበት ጊዜ ነበር። 

በሰንደቅ ዓላማው መሀል ላይ ያለው ምልክት የሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ ስዕል ነው። ቅዱስ ጊዮርጊስ በብዙ አገሮች ዘንድ ሁሉ የታወቀ እንደመሆኑ በኢትዮጵያም የታወቀ ስመ ጥር ሰማዕት ነው። ለዚህ እንደ አስረጅ በእንግሊዝን፣ በግሪክ፣ በግብጽ፣ በሶርያና በሌሎች 37 የዓለም አገሮች ውስጥ የሚገኙን የቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያናት ማውሳት እንችላለን። እንግሊዝ ውስጥ ብቻ 37 ከተሞች ውስጥ የቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ይገኛል።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን አማኞች ዘንድም ቅዱስ ጊዮርጊስ የኢትዮጵያ ጠባቂ ሰማዕት ተደርጎ ይወሰዳል። የቅዱስ ጊዮርጊስ ጽላት ወደ ኢትዮጵያ የገባው በ፲፫ኛው ክፍለ ዘመን በዐፄ ዐምደ ጽዮን ዘመነ መንግሥት እንደነበር ከክብረ ነገሥቱ መረዳት ይቻላል። ክብረ ነገሥቱ በኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ገዳም ውስጥ ብዙ ዓመታት የኖሩ አባ ልዑለ ቃል የተባሉ መነኩሴ ከሶርያ «ደብረ ይድራስ» ከሚባለው ገዳም የቅዱስ ጊዮርጊስን ጽላት ከገድሉ ጋር አምጥተው ለዐፄ ዐምደ ጽዮን እንዳስረከቡ፣ ዐፄ ዐምደ ጽዮንንም ቤተ ክርስቲያን አሠራለት እንዳሉና ገድሉን ከዐረብኛ ወደ ግእዝ እንደተረጎሙ ያትታል።

የዘመኑ ታሪክ ነገሥት ዐምደ ጽዮን የጊዮርጊስን ጽላት አስይዘው ከጠላቶቻቸው ጋር በመግጠም አሥር ታላላቅ ዘመቻዎችን በድል አድራጊነት እንደተወጡ፣ ንጉሠ ነገሥቱ «ቅዱስ ጊዮርጊስ አማላጄና ረዳቴ ስለሆነ የኢትዮጵያ ጠላቶች ድል ሊያደርጉኝ አይችሉም» እያሉ በቅዱስ ጊዮርጊስ አማላጅነትና ረዳትነት አብዝተው ያምኑ እንደነበር ያስረዳል።

የዐፄ ዘርዓ ያዕቆብ ጸሐፊ ትእዛዝ እንደነበሩ የሚታመነው መርቆርዮስም «አርዌ በድላይ» የተባለ ጠላት ብዙ ወታደሮች አሰልፎ ዐፄ ዘርዓ ያዕቆብን ሊወጋቸው ሲነሳ ንጉሡ የቅዱስ ጊዮርጊስን ጽላት ይዘው ሠራዊታቸውን አስከትተው በመዝመት የኢትዮጵያን ጠላት ድል መትተው ተመልሰዋል ሲሉ ጽፈዋል።

ባጠቃላይ በኢትዮጵያ ነገሥታት ዜና መዋዕል እንደሚነበበው ነገሥታቱ በሚዘምቱባቸው ታላላቅ ዘመቻዎች ሁሉ የቅዱስ ጊዮርጊስን ጽላት ትተው አይንቀሳቀሱም ነበር ይህንን እውነት ለማረጋገጥ ቢፈለግ በዓድዋ ላይ ከኢጣልያ ጦር ጋር በተደረገው ውጊያ ማለትም በዓድዋ ጦርነት ወቅት ቅዱስ ጊዮርጊስ አደረገው በተባለው ተሳትፎ «ኢትዮጵያን በዓለም ታሪክ በጦር ኃይል ስምንት ጊዜ እጥፍ የሚበልጣትን አገር አሸንፋ ታዋቂ የነፃነት አገር እንድትባል አድርጓታል» በሚል የሚቀርበውን ታሪክ መመልከት ይበቃል። 

የዳግማዊ ዐፄ ምኒልክ ጸሐፌ ትዕዛዝ የሆኑት ጸሐፌ ትዕዛዝ ገብረ ሥላሴ እንደጻፉት ዳግማዊ ዓፄ ምኒልክ ወደ ዓድዋ ሲዘምቱ በአራዳ ገነተ ጽጌ ቤተ ክርስቲያን የሚገኘውን የቅዱስ ጊዮርጊስን ጽላት አስይዘው ነው የዘመቱት። ጦርነቱንም ቅዱስ ጊዮርጊስ የእርዳታ እጁን በመዘረጋቱ ኢትዮጵያ ድል እንዳደረገችና ብዙ የጠላት ሠራዊት እንዳለቀ አትተዋል።

በወቅቱ የነበረ አንድ የኢጣልይ ጋዜጠኛ ወደ አገሩ ባስተላለፈው መልዕክት አንድ በነጭ ፈረስ ላይ የተቀመጠ ጀግና እንደፈጃቸውና ይህ በነጭ ፈረስ ላይ የተቀመጠው ቅዱስ ጊዮርጊስ ከኢትዮጵያ ሠራዊት ጎን ተሠልፎ የኢጣሊያን ሠራዊት አርበደበደው የምንዋጋው ከሰው ጋር ብቻ ሳይሆን ከእግዚአብሔርም ጋር ሰለሆነ በጦርነት ድል ልንመታ ችለናል ሲል ዘግቧል። በዚህም የተነሣ ቅዱስ ጊዮርጊስ ተራዳኢነቱን፣ ፈጥኖ ደራሽነቱን፣ ስለት ሰሚነቱንና አማላጅነቱን የሚያምኑት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ምእመናን የቅዱስ ጊዮርጊስ ጽላት በተተከለበት፣ ቤተ ክርስቲያኑ በተሠራበት፣ በዓሉ በሚከበርበትና ስሙ በሚጠራበት ሥፍራ ሁሉ እየተገኙ በጸሎትና በምስጋና ያስቡታል፤ «ፍጡነ ረድኤት» ይሉታል።

ይህንን ሁሉ ሀታተ መዘርዘሬ በዐፄ ዮሐንስ ዘመነ መንግሥት በነበረው የኢትዮጵያ ሰንደ ዓላማ መሃል ያለውን የቅዱስ ጊዮርጊስ ስዕል ከሃይማኖታዊነቱ ባሻገር ትርጉሙ ጠባቂ ሰማዕት ለኢትዮጵያ መሆኑን አጽዕኖት ለመስጠት ነው። 

የቅዱስ ጊዮርጊስን መስቀል በሰንደቅ ዓላማቸው መካከል ባደረጉት በእንደ እንግሊዝ፣ ዴንማርክ፣ ስዊድን፣ ኖርዌይ፣ ፊንላንድ፣ ወዘተ አገሮች የየአሩን ሰንደቅ አላማ ለማክበርና ከሰንደቁ በፊት ለመውደቅ እንደ ሃይማኖታቸው ስርዓት ቃለ መሀላ በመፈጸም ዜጋ የሚሆኑት የመላው ዓለም የእስልምና እምነት ተከቻዮች የቅዱስ ጊዮርጊስ መስቀል ላለባቸው ሰንደቅ ዓላማዎች ቃለ መሃላ የሚፈጽሙትና ለማሉበት ሰንደቅ በጦር ሜዳ ሕይወታቸውን የሚሰጡት የቅዱስ ጊዮርጊስን መስቀል ትርጉም በሃማኖታዊ ምልክትነቱ ሳይሆን በአገር ጠባቂነቱ ወስደውት ነው። ኢትዮጵያን ክርስቲያኖች ጭምር ነብዩ መሐመድ ስለ ኢትዮጵያ በተናገሩት መልካም ነገር የሚኮሩትና የሚጠቅሱት ሃይማኖታቸው እስላም ስለሆኑ ሳይሆን ነብዩ «ኢትዮጵያ አትንኩ» ያሉት የኢትዮጵያ ጠባቂ የአደራ ቃላቸው አገራዊ ፋይዳው ስላለው ነው። 

ባጭሩ በዐፄ ዮሐንስ ዘመነ መንግሥት የነበረው የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ መሀል ያለው የቅዱስ ጊዮርጊስ ምልክት ትርጉምም ልክ ከተለያየ ዓለም ወደ እንግሊዝ፣ ዴንማርክ፣ ስዊድን፣ ኖርዌይ፣ ፊንላንድ፣ ወዘተ አገሮች የሚሄዱ የእስልምና እምነት ተከታዮች የሚምሉበት ሰንደቅ ዓላማ መሃል እንዳለው መስቀል አይነት አገራዊ ትርጉምና ፋይዳ ነው ያለው።

በሰንደቅ ዓላማው መሀል የቅዱስ ጊዮርጊስ አርማ የሌለበትን የዐፄ ዮሐንስ ዘመነ መንግሥት የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ አጥብቀው ከሚጠሉት ብሔርተኞች መካከል ቀዳሚዎቹ የትግሬ ብሔርተኞች ናቸው። በሌላ አነጋገር በዐፄ ዮሐንስ ሰንደቅ ዓላማ ከሁሉ በላይ የዘመቱት የዐፄ ዮሐንስ ልጆች ነን የሚሉን የትግሬ ብሔርተኞች ናቸው። ዐፄ ዮሐንስ እድል አግኝተው ቀና ቢሉ ከሁሉ በላይ የሚያፍሩት የዐፄ ዮሐንስ ልጆች ነን በሚሉት በትግራይ ብሔርተኞች ይመስለኛል። ዐፄ ዮሐንስ በተደራቢነት የሚናገሩትን ቋንቋዬ ነው ብለው ብሔራዊ ቋንቋ ያደረጉትን አማርኛን «በትግሬ ላይ የተጫነ» ብለው ከሁሉ በላይ የዘመቱት ነውር ጌጡ የሆኑት የትግሬ ብሔርተኞች ናቸው። 

ዐፄ ዮሐንስ ከሰመራ ከተማ በካቲት 11 ቀን 1873 .. ለጀርመኑ ንጉሥ ቀዳማዊ ዊልሄለም በጻፉት ደብዳቤ፤
«[አገሬ] በምስራቅ በደቡብ ወገንም ዲካው[ድንበሩ] ባሕር [ሕንድ ውቅያኖስን ማለታቸው]ነው። በምዕራብ በሰሜን ወገንም ባሕር በሌለበቱ ከኑብያ፥ ከካርቱም፣ ከስናር ከሱዳን በስተቀር ጋላ፣ ሻንቅላ፣ እናርያ፣ አዳል የያዘው አገር ሁሉ የኔ ነው። አሁን እንኳ በቅርብ ከሸዋ በታች ያለው ሐረር የሚባል አገሬ በቱርክ ተይዟል። ይህን ሁሉ መጻፈ ያገሬ ድንበሩ ይታወቅ ብዬ ነው።»

ሲሉ ያሰመሩትን የኢትዮጵያ ድንበር አፍርሰው የዛሬዋን ኢትዮጵያ «ምኒልክ ነጻ የነበሩ የአፍሪካ አገሮችን ወርሮ የፈጠራት የብሔር፣ ብሔረስችቦች እስር ቤት የሆነች ኢምፓዬር ናት» ብለው ከሁሉ በላይ በዐፄ ዮሐንስ አገር ላይ የዘመቱት፣ የዐፄ ዮሐንስን ኢትዮጵያ ያፈረሷትና ያደሟት «የዐፄ ዮሐንስ ልጆች ነን» የሚሉን ጉደኞቹ የትግሬ ብሔርተኞች ናቸው። እነዚህ አሳፋሪዎች «አባታችን ናቸው» የሚሏቸው ዐፄ ዮሐንስ ቀና ቢሉ የትኛውን የአባታቸውን ራዕይ ወረስን ብለው ይነግሯቸው ይሆን? 

ማፈሪያዎቹ የትግሬ ብሔርተኞች በዚህ አላባቁም። አዲስ አበባን እንደ ኦነጋውያን ሁሉ ፊንፊኔ እያሉ በመጥራት ከኦሮሞ ውጭ ያለው የአዲስ አበባ ነዋሪ [ትግሬን ጭምር] እንደ ኦነጋውያን ሁሉ ሰፋሪ እያሉ ሲሳደቡ የሚውሉት ግራኝ አሕመድ ኢትዮጵያን በወረረ ጊዜ የበረራውን የዐፄ ዳዊት ቤተ መንግሥት ላለማስደፈር በአማራው በአዛዥ ደገልሃን የሚመራው የባሌ ጦር በዛሬው አዲስ አበባ ዙሪያ ተጋድሎ ሲያደርግ አብረው ሲፋለሙ የወደቁት የትግሬ መኳንንት ሮቤል ደም የፈሰሰበትን ምድር ነው። 

ታሪኩን ለማታውቁ የትግሬ ገዢ የነበሩትና በዘመነ መሳፍንት ዘመን አንጋሽ የነበሩት ራስ ሚካኤል ስሑል በረራን ከግራኝ አሕመድ ለመከላከል በተደረገው ተጋድሎ የወደቁት የትግሬ እንደርታ ተወላጁ የትግሬ መኳንንት ሮቤል ዘር ናቸው። እፍረተ ቢሶቹ የትግሬ ብሔርተኞች የስሑል ሚካኤል ልጆች ነንም ይላሉ። ይህን የሚሉን እነዚህ አሳፋሪ ፍጡራን ግን የስሑል ሚካኤል እንሽላት[ስምንተኛ ትውልድ] የሆኑት ትግሬ መኳንንት ሮቤል የወደቁበትን የዛሬውን አዲስ አበባ አካባቢ የትግሬ መኳንንት ሮቤል ትውልዶችና አብረዋቸው የወደቁት የአዛዥ ደገልሃን ልጆች ርስት አይደለም ብለው የትግሬ መኳንንት ሮቤልንና የአዛዥ ደገልሃንን ትውልዶች ሰፋሪ እያሉ ከኦነጋውያን ጋር ሲሳደቡ እየዋሉ ነው። እንደሚኮሩባቸው ሁሉ እነ ዐፄ ዮሐንስን «አባቶቻችን ናቸው» እያሉ «አባቶቼ ናቸው» በሚሏቸው ወደምት ሰዎች ታሪክና ስራ ላይ የዘመቱና የእነዚህ ቀደምት ሰዎች አሻራ ያወደሙ እንደ ትግሬ ብሔርተኞች አይነት ፍጡር በታሪክ ውስጥ ስለመኖሩ እጠራጠራለሁ። አቻምየለህ ታምሩ
(Posted on Ethio Semay)