Friday, August 8, 2008

The EPLF General Sebhat Efreme & His Interview

የሻዕቢያዉ ጀነራል ስብሓት ኤፍሬም “ከሃይለሥላሴ እና ከደርግ ሠራዊት ሲንጻጸር የወያኔዉ ጦር እጅግ ደካማ ነዉ” አለዉ። ከጌታቸዉ ረዳ ሳንሆዘ- ካሊፎረንያ ሐምሌ 2000 ዓ/ም “ወዲ ኤፍሬም” በመባል የሚታወቀዉ በጀኔራልነት እና በመከላከያ ሚኒስትርነት ማዕረግ የሚጠራዉ የሻዕቢያዉ ባለስልጣን “ታዓጠቕ” (ታጠቅ) ተብሎ በተሰየመዉ አሥመራ ዉስጥ የታተመዉ አዲስ የሻዕቢያ የትግርኛ መጽሄት፤ ሰሞኑን(በፈረንጅ በሐምሌ/ጁላይ ወር 2008 ቁጥር 14) (በኛዉ አቆጣጠር ሐምሌ/2000 )ባወጣዉ ልዩ እትሙ ላይ ለቃለ መጠይቅ ቀርቦ የሰጠዉ 64 ገጽ ሙሉዉን ባላቀርበዉም አለፍ አለፍ ብየ ጠቃሚ ጉዳዮችን ወደ አማርኛ ተርጉሜ ላንባቢያን አቀርባለሁ። << ….የኤርትራ ትልቁ ስጋታችን ነዉ ብልን የምንሰጋዉ ‘ኢትዮጵያ ለወደፊቱ የኢርትራ ትለቁ ሸክም አንዳትሆንብን ነዉ የምንሰጋዉ። ምክንያቱም ኢትዮጵያ በቀጣይ የዉስጥ ሽኩቻና ቀዉስ ከመወጠርዋ በላይ፤ አገሪቷ ድሃ በመሆኗ ያለ የዉጭ ዕርዳታ መኖር ይቸግራታል ፤አትችልም።ተያይዞም ጦርነት እንደ ዓላማ ስለያዙት በድህነትና በረሃብ በቀጣይ ይሰቃያሉ። በረሃብና በድህነት የሚሰቃይ ጎረቤት ደግሞ መጨረሻዉ ሸክሙ ለጎረቤት ነዉ። ይህ ሁኔታ አሁን ባሉበት የዉስጥ የፖለቲካ ፍትግያና ድህነት አንዲሁም መራቡን ከቀጠሉበት፤ ሸክማቸዉ ሊከብደን ነዉ።…….>> በማለት ኤርትራ ዳቦ ቅርጫት የወ ያኔ ኢትዮጵአ ደግሞ ኤርትራ ተመጸዋች እነደምትሆን ስጋቱን የገለጸበት ረዥሙ ቃለ-መጠይቅ አንብቡ አነሆ። ወያኔን እንዴት ትመለከተዋለህ ለሚለዉ ኣጠቃላይ ጥያቄ ስብሓት ኤፍሬም ሲመልስ <<አንደሚታወቀዉ አሁን እያየነዉ ያለዉን አዲሱ የዓለማችን ስርዓት ሲታይ ወያኔ በዚህ መነጽር ዉስጥ እስገብተህ የአሜሪካኖች አገልጋይ መሆኑን ነዉ ምትደመድመዉ ።…….>> ወታደራዊ ሚዛኑ-ወያኔ’ና የደርግ እንዲሁም ከሱ በፊት የነበረዉ ጦር ስታነጻጽራቸዉ ወያኔ በየትኛዉ መመዘኛ ታስቀምጠዋለህ? ለሚለዉ ጥያቄ ሰፋ ያለ መግለጫ ሰጥቶበታል። << የወያነ ጦር ከዚህም ከዛም የተጠረቃቀመ ጦር ከመሆኑ ባሻገር፤ ተዋጊዉና አዋጊዎቹ ካለፉት ማለትም የደርግና ከሱ በፊት የነበሩ የኢትዮጵያ ሰራዊቶች ሲታዩ ወያኔ ደካማ ነዉ።…>> ኢትዮጵያና ኤርትራ ስታወዳድራቸዉ አሁን ሁለቱም አገሮች በምን ላይ ታስቀምጣቸዋለህ ? ለተባለዉም አንዲሁ አስገራሚ በሆነ መልስ መልሶታል። << ኤርትራና ኢትዮጵያ ስታነጻጽራቸዉ፤ - ኤርትራ ከጥዋቱ 5፡00 ሰዓት በንጋት ላይ ስትገኝ፤-ኢትዮጵያ ከምሽቱ 5፡00 ሰዓት ላይ ሆና የጭለማዉ ጉዞ መጛዙን የጀመረችዉ አሁን ነዉ።ንጋት ላይ ለመድረስ ረዥሙ የጨለማዉ ጉዞ መጛዝ ሊኖርባት ነዉ። >> ፈረንጆቹ ከንጋቱ 5 ሰዓት ሲሉ ጠዋት11 ሰዓት ማለት ነዉ። በአንድ ወቅትድሮ ከረን/ናቅፋን ለማስለቀቅ 6 ወር የፈጀ እልክ አስጨራሽ ዉግያዎች ተካሂደዉ አንተ በተካፈልክበት በ3ኛዉ ባታልዮን (607 እና 301- ባታልዮን) ስንመለከት፤ አንዴት አንድ ስፍራ ለማስለቀቅ ያን ያህል ረዥም ዉግያ ለካሄድ ቻለ? << ሁለት ነገር እናያለን። እዛ የነበረዉ የጠላት ጦር በጣም በጣም ሃይለኛ ነበር። እኛ የደረስነዉ ከተዳከመ በጣም ከደከመ በሗላ ነዉ። እዛ የገጠመን የጠላት ጦር ብርቱ ነበር ለማለት ምትደፍርበት ምክንያት ብዙ ነዉ። አንደኛ ለ6 ወር ሙሉ ያለ ምንም ረዳት ተከበህ ሌሊት ሌሊት ጦርነት ገጥመህ ቦታህን ሳትለቅ መጋተሩ በጣም አስገራሚ የሆነ አዋጊና ተዋጊ ጦር መኖሩን ታያለህ።በጣም ካባድ ነዉ።ቀላል አይደለም። የጠላት ጦር ያሳየዉ ቁመናም ይሄንን ነበር። የ607 እና 301 ባታልዮን ሰራዊት በጠላት ላይ ያደረገዉ ከበባ እና ቦታን የማስለቀቅ ዉግያ፤ በጣም ፈታኝ ነበር። ለ6 ወር ያክል ዙርያዉ በከበባ ገብቶ ሲዋጋ እሱን ለመርዳት በሄልኮፕተር የመጡት አየር- ወለዶች በፓራሹት ሲወርዱ ህዋ ላይ እንዳሉ ብዙዎቹ ተጎድተዋል።ሁለታችንም ረዥም ዉግያ አካሂደናል። እዛ የነበረዉ የጠላት ጦር ኮማንዶ፤ ምርጥ ከሚባሉት አንዱ ነበር። እንደነዚያ አይነቶቹ ምርጥ የጠላት ተዋጊዎች ከኛ ባታልዮን ጋር በተለያዩ የዉግያ አዉድማዎች ላይ፤ሁለት ሦስቴ ያክል ገጥሞናል። በተለይም “ሃብረንጋቓ’ የነበሩ የጠላት የክብር ዘበኛ ተዋጊ ሃይሎች አስደናቂ የመዋጋት ብቃት ነበራቸዉ። እንደነዚህ ዓኢነቶቹ ብርቱ የጠላት ሃይል ለማዳከም በተለይም ዙርያዉ ፈንጅ በታጠረ ምሽግ በኛ በኩል መከፈል የነበረበት እዳም ያን ያህል መሆኑ አትዘንጋ። በጣም ፈታኝ ነበር።……… ……..እንደሚታወቀዉ የናቅፋ ተራሮች እርስ በርስ በትይዩ የቆሙ ናቸዉ። ያንን በፈንጅ የታጠረዉ ወረዳ ጥሶ ለመግባት በጣም ክፉ ነዉ። እዛ የነበረዉ ጠላት አዋጊ “ማሞ” ይሉታል፡- “ማሞ” ብርቱ የጦር አዋጊ ነበር። የቦታ አያያዝና የጦሩ አስገራሚ አሰላለፍ ሞያተኛ ነበር።>> <….ለረዥም ጊዜ ተከቦ ተዋግቷል። በሄሊኮፕተር አየር ወለዶች ሊረዱት ሞከሩ፤ግን ለረዥም ጊዜ ተከቦ ስለተዋጋ መጨረሻተዳከመ። እኛም የማጥቃት ስልታችን ከሌሊት ወደ ቀን አዙረን በቀን ይዋጉናል የሚል ጥርጣሬ ስላልነበራቸዉና አድርገነዉም ስላማናዉቅ፤ ጦሩ ጥበቃዉን አላልቶ ፤ተዝናንቶ በነበረበት ሰዓት ገብተን ዉግያ ከፍተን መጨረሻ ሊደመሰስ በቃ…..።>> <<ስለዚህ ወያኔ በዚህ እኩል ልታየዉ አትችልም። መሰተረታዊ ባህሪዉ የአዲስ ዓለም ስርዓት አገልጋይ ነዉና። ወ ያነ ማለት “በግ” ማለት ነዉ። በግ ትንሽ ሳር ከጣልክለት፤ሳሯን ተደፍቶ ሲጎራርድ፤ ከሗላዉ ምን እየተዘረፈ እና እየተደረገ እንዳለም አያዉቅም። ለወያነ ግን ትንሽ-ሲጥሉለት ይጠቅመዋል። ወያነ የሕዝቡን ንብረት ሲነጥቅ፤ እየጣሉለት ያሉት ጌቶቹ ደግሞ አገሪቷን ያራቁታሉ። ለሱ ብሔራዊ ጥቅም/ልማት ..የሚለዉ የዘረፋዉ መንገድ ነዉ። የስነ-አእምሮ ዉግያ እያካሄድኩ ነዉ ሚለዉም ቢሆን የአዲሱ ዓለም ስርዓት አገልጋይነቱ ለመግለጽ ነዉ። አጼ ሃይለስላሴ የመገነኛ ብዙሃን ፤ራዲዮ አላስፈለጋቸዉም ነበር፤ ምክንያቱም ስራዉ የሚከናወነዉ በቤተ-ክህነቱ በኩል ነበርና። አንደዚያ ዓይነት የቅስቃሳ ክንዋኔ ለወያኔ የሚያካሂዱለት ደግሞ አሜሪካኖች ናቸዉ። ምክንያቱም፤የአዲሱ ዓለም ስርዓት የማገልገል ስራ በአንጻሩ ለወያኔ ስለተሰጠዉ። ስራዉ ያን ተልእኮ ማገልገል ነዉ። ይህ አዲስ ስርዓት እየተባለ ያለዉ የዓለም ህዝብ ተቃዉሞታል። ያሜሪካን ሕዝብ ሳይቀር ተቃዉሞታል። ወያኔ ብቻ ነዉ ባገልጋይነት የቆመዉ።የስነ-ኣእምሮ ትግል የማካሄዱ ስራ በደረግ ጊዜም የነበረ ነዉ። ወያኔ አሁን እየደገመዉ ያለዉ ያንኑ ነዉ። “ዉግያ” እያለ የሚጠራዉ ያነን ነዉ። <<…..በወታደራዊ መልኩ ግን የደረግ ሰራዊትና የወያነ ይለያያል። የደረግ ሰራዊት በወታደራዊ ስነምግባረና በሙያዉ የተለየ ነዉ።ሌላ ስራዉን ትተህ፤በጣም እልከኛ ተዋጊ ሰራዊት ነበር። የደረግ የጦር አለቆች በሰራዊቶቻቸዉ አድናቆትንና ተወዳጅነት ያተረፉ ነበሩ።አዋጊዎቹን ስትመለከት፤በጣም ጎበዞች ፤ሃይለኞች ነበሩ።እነ ረጋሳ ጅማ እነ ታሪኩ ላይኔ….ወዘተ.ወዘተ..የሚባሉ አዋጊዎቻቸዉን ስትመለከት ከፍተኛና ልዩ ችሎታ ያላቸዉ አዋጊዎች ነበሩ። በጣም ልዩ ነበሩ። እልከኞች ነበሩ።
የኛ ሰራዊት ከእነደዚያ ዓይነቱ ምርጥ አዋጊና ተዋጊ ጦር መግጠማችን ያኮራናል። የጠላት አዋጊዎችም በኛ ሰራዊት አድናቆትን አትርፎላቸዋል። በእንደዚህ ዓይነት ሃየለኛ ሰራዊት እና አዋጊዎች ባየነበት ዓይናችን የወያኔን ጦር ስንመለከት አንደነዚያ ዓይነት አዋጊዎችና ባለሞያተኞች የሉትም። ለሽታ ፈልገህ አታገኝባቸዉም……….። << ….ወያኔን ከአዲሱ የዓለማችን ስርዓት ጋር አያይዘህ ነዉ ማየት ያለብህ። አዲሱ የ ዓለማችን ስርዓት ዓለምን በ ኢኮኖሚና በዲፕሎማሲ አንቆ ሊይዝህ የሚፈልግ ነዉ።ከዚም ከዚህም እየዘረፈ ወደ ሌላ መጓዝ። ያለንበት ዓለም በዚህ እየተመራ ስላለ በዓለም ዉስጥ ያሉት የብዙሃን የመገናኛ ጋዜጦች ሁሉ ተቆጣጥሮ ሁሉም ጋዜጦች በአንድ ርዕስ አንዲዘጋጁ ያደረግጋል።ከሚተነተነዉ ርዕስም አብሮ ትንሽ ወታደራዊ ነክ ጉራ ይጨመርበታል።
ከሚተነተነዉ የስነ ዓእምሮ ትነተና ዉስጥ የወያኔ ሃይል ትነሽ ነጥብ ነች።የወያኔ ጦርነት የስነ-ዓእምሮ ጦርነት ነዉ። ሌላዉ ነገር ዉስጡ ባዶ ነዉ። ያ የስነ ዓእመሮ ጦርነት ነጥለህ ብትለየዉ የወያኔ አቅም ኢሚንት ነዉ። ምን ዉግያ አለዉ?የለዉም! ወታደራዊ ስልቱ ስፍር ቁጥር የሌለዉ የሰዉ ሃይል ሰብሰቦ መዋጋት ብቻ ነዉ። ትንሽ ቦታ ለማግኘት በብዙ ሺህ የሚቆጠር የሰው ሕይወት ያስፈጃል። ኤርትራ 19,000 ሺህ ሰዉ ሲሰዋባት ዉያኔ 170,000 ሺህ ሰዉ ነዉ ያስፈጀዉ። የከፈለዉ ሕይወት በጣም ብዙ ነዉ። ታሞ በህመም የሞተ ሳይጨምር ማለት ነዉ። የደርግ ሰራዊት እኮ ልክ አንደፊተኛዉ ሰራዊት በስለቱም በጥንካሬዉም እያደገ የመጣ ሰራዊት ነበር። የወያኔ ሰራዊት ጥርቃሞ ነዉ። ከዚህም ከዚያም ለቃቅሞ ያቆመዉ ነዉ።
ከወያኔ በፊት የነበረዉ ጦር በፍጹም ታወዳዳሪ አይገኝላቸዉም። ወያኔ አቅሙን መጥኖ ስለመያዉቅ፡ አቅምም ስለሌለዉ፤ የኢኮኖሚ ረዳት የሌላትን ኤርትራን በኢኮኖኖሚ እናንቃታልን እያለ ነዉ የስነ እምሮ ዉግያዉን እየነዛ ያለዉ።
<<……..የዓእምሮዉ ጦርነቱን አብረዉ የሚያጫፈሩት አንዳንድ ኤርትራዊያን አቅጥረኞቹን ድሮ የተረሱ ፤የበሰበሱ ፤የሞቱ በድን ድርጅቶችን አፈላልጎ እያስባሰባቸዉ ነዉ። አነዘሂም በነገርኩህ በዛዉ በስነ ዓእምሮዊ ዉግያዉ ዉስጥ እንደ ፓኬጅ ጨምራቸዉና ገምግመዉ። ግልጽ ነዉ! ዉግያዉ ከዚያ አያልፍም። ወያኔ ሊያደረጋት የሚችላት አቅሙ ያች ብቻ ነች። በዚህ መለኪያ ስትመዝነዉ የወያኔ አቅም ለመገመት የሚያሳስት ነገር አይደለም።>> የወያኔ ሰራዊት ገፍቶ ወደ ዉስጥ ኤርትራ በመዝለቁ እንደ ዋታደራዊ የበላይነት ተደርጎ ይታያል።የሄንን እንዴት ትመለከተዋለህ? << ወያኔ በወታደራዊ ሃይል የበላይነት ለማግኘት ሦስት ጊዜ=ሞከረ።መጀመሪያ፤ሁለተኛ፤…..ሦስተኛ ጊዜ የባሰ መጣበት። ከዚያ ወዲያ መቀጠል ስላልቻለ አቅም ስላልነበረዉ ወደ አልጀሪስ ለመሄድ ተገደደ። እዛም በሽንፈት ተከናንቦ የውርደት ዉርደቱን አገኘ።በሽንፈት ላይ ሽንፈት ኪሳራ ደረሰበት። ያካሄደዉ ዉግያ የስነ ዓእምሮ ዉግያ ነበር፡ በሺዎቹ የሰዉ ሕይወት ታስፈጅና በምትኩ፤ ትንሽ ቦታ ይዘህ ከየአቅጣጫዉ ጋዜጠኞችን ሰብስበህ “ኑ እዩልኝ፤ዘግቡልኝ” ይላል። የኛ ጦር በ ኤርትራ ምድር በየአቅጣጫዉ በስፋት ስለዘረጋነዉ፤ ወያኔ በሺዎቹ የሰዉ ሃይል ሰባስቦ በአንድ አቅጣጫ መጣ። ያ ዕድል ነበር ለወያነ የሰጠነዉ። እኛ በአቅማችን እንተማመናለን።ይሄ የሚያስጨንቀን አይደለም።የዉግያ ሙያ የሚያዉቅ ያዉቀዋል። ቀስ እያልን እንደምንጠርገዉ ያዉቅ ነበር። ለዚያም ነበር ያቆመዉ። አስኪ እንደዉ በእወነቱ ወያነ ከጸሮና ዉግያ ወዲያ ዉግያ መቀጠልና ማሰብ ነበረበት? ያ የታየዉ የሬሳ ክምር፤የዉትድርና ብቃት ምለክት አይደለም። በዓለም ጋዜጦች የተዘረጋዉ በቲቪ የታየዉ የሬሳ ክምር እኮ ሙሉዉን አልታየም። በዓይን ስታየዉ እኮ የክምሩ ብዛት በእዉነቱ “በፍሊት” መርዝ የተፈጁ ነበር የሚመስሉት። በፍሊት የተገደሉም እንደዚያ ዓይነት የሰዉ ሬሳ “ክምር፤ በክምር ላይ ተደራርቦ” ማየት ያስቸግራል። 170.000 ሰራዊት አስፈጅቶ አንዴት ድል በድል ሆንን ይላል? አቅም ኖሮት ወያኔ ቢችል ኖሮ ነበር 10 ጊዜ ወደ ፍርድ ቤት እየሄደ ዉሸትና መለማመጥ የመረጠዉ? ያ ሊያደርገዉ የሚችለዉ አቅሙ ያኔ አብቅቷል። ጊዜዉ አልቋል። አሁን የቀረዉ ፕሮፖጋንዳ የስነ ዓእምሮ ፤ጉራና መዋሸት ብቻ ነዉ።
ወያነ ደካማ መሆኑን የምታዉቀዉ ባደረጋቸዉ ሥስት ሙከራዎች ላይ ነዉ። የወያኔ የድሮ ተዋጊዎች አብዛኛዎቹ በዉግያዉ ተፈጅተዋል። ትግራይ ዉስጥ የመወያያ ርዕስ ሆኖ የሚነገረዉም ይህነኑ ነዉ። ድል አመጣሁ እያለ ወያነ የሚለፍፈዉ፤-ድሉ ከየት መጣ ቢባል- የስነ ዓእምሮ የፖለቲካ ወግያና የዲፕሎማሲ ዉግያዉ ነዉ። ያነን የስነ እምሮዉ ዉግያዉ ብትለየዉ ወታደራዊ አቅሙ 20% አይበልጥም። …ወያነ ኤርትራን ቢቆጣጠር ነብሰጡሮች ቁጥቋጦ ስር ነበር የሚወለዱት። ተመልከት ለአማራ ህዝብ እያደረጉት ያሉትን ግፍ። መልከመልካም ሚስቶቻቸዉን እየነጠቁ ያማግጧቸዋል። ልጆቻቸዉም አንደዚሁ። ባኦጋዴን፤ በሶማሊ እየፈጸመ ያለዉን ድርጊት በአልጀዚራ በቲቪ ያየነዉ ነው።>> ወያነ የያዛቸዉን ሉአላዊ መሬታችን አልሰጥም ብሏል በዚህ የምትለዉ ነገር ካለ አስተያየትህ? <<ወያነ ከግዛታችን ካስነሳልን በጀ! ለሱም ይበጀዋል። ካላነሳም ማስነሳቱን የሚከብድ አይደለም።የድምበር ክርክር ጉዳይ ያበቃለት የሞተ ጉዳይ ነዉ። ኢትዮጵያን ስንመለከት አርግዛለች።ምን እንደምትወልድ ግን ሕዝቡ እየተጠባበቀ ነዉ። በእወነቱ ኢትዮጵያ ማርገዝ በተገባት ነበር? አያስፈልጋትም።ሕዝቡ ከወያኔ ማነቆ ተገላግሎ ወደ ሌላ ሽግግር እያመራ መሆኑን እያታዘብን ነዉ። ይህ ከድምበር ጋር የተያያዘ ይሁን አይሁን ሌላ ጉዳይ ነዉ። በኛ በኩል ፤የድምበር ጉዳይ አልቆለታል። የተባበሩት መንግሥታት ከዚህ ተባሯል። የቀረ ነገር ካለ፤ “ተመድ” ስሙን አንዴት ያስመልስ/ያ’ሳድስ ነዉ። ስሙን በእንዴት መልክ ማሳመር እንዳለበት የራሱ የግሉ ጉዳይ ነዉ። ለራሱ ችግር ሲል። የ ኤርትራ ጉዳይ አንደሆነ ያለቀለት ነዉ። የኛ የተሰጠዉ መሬት በፈለግንበት ሰዓት መልስን መዉሰዳችን የማይቀር ነዉ። ዓለምም ብትሆን ወዳ ሳትሆን በግዷ የኛዉን ትቀበላለች። ኤርትራንም እኮ ወዶ የሰጠን ሃይል የለም። ተመድ እኮ በ 50 ዎቹ ወደ ኤርትራ መጥቶ ነገር አበላሽቶ ሄደ። ነጻ ስናወጣት ተመልሶ መጣ። አሁንም መሬታችን ካስመለስን በሗላ፤ ያ ሲሆን- ተመልሶ እንደገና ይመጣል። ይሄ እኮ ነዉ ተመድ ማለት። ሌላ ተመድ የለም። የማናዉቀዉ ሌላ ተመድ የለም። ሄልኮፕተራችሁ ከዚህ አስነሱ፤ ልቀቁ ብለን ስናስነሳቸዉ አዉቀዉታል፡ ያኔ ያለቀ መሆኑን ያቃሉ።>> …….ኤርትራ ኢትዮጵያን ለማጥቃት ህጋዊም ሆነ ወታደራዊ መብት አላት።ተመድ ኖረ አልኖረ፤ተመድ ሄደ አልሄደ ጦርነት ሊያስቆም አይችልም።ለዚህ ነዉ ኤርትራ ዉስጥ ሲነጋ በነሱ ምሽት ሆኖ ጨለማዉ ገና መያያዝ የጀመሩት። ገና አልነጋላቸዉም። ኢትዮጵያ ሰላም አንድታገኝ ብልን ድሃ ስለሆነች በዉስጣዊ ዉጥረት ስለተወጠረች ሰላም እንድታገኝ ብለን፤ ለኛም ሸክሙ አንዲቀለን፤ ሸክማቸዉ የኛ እንዳይሆን፤ብለን እጃችን አስገብተናል።ኤርትራ አንደ መዓከላዊ ስበት ሆና መታየትዋ የማይቀር ነዉ። ……እሳቱ እየነደደ ነዉ።እኛ ከእሳቱ አጠገብ ነን፡ ያለነዉ።አሳቱ ነዶ ወደ አመድ ለመለወጥ ሊቀረዉ በቁጥር ስንት ያክል የማገዶ እንጨቶች እንደቀሩ የሚያዉቀዉ ከእሳቱ አጠገብ ላይ ያለዉ ሰዉ ነዉ የሚያዉቀዉ።ከእሳቱ አጠገቡ ላይ ያለነዉ ደግሞ እኛ ነን።……>>
በማለት “ተዓጠቕ”/ታጠቅ ከተባለዉ ወታደራዊ መጽሄት የሰጠዉ ቃለ መጠይቅ አንኳር አንኳር ነጥቦች እነዚህ ነበሩ።.
ኢትዮጵያ ለዘላም ትኑር!!!!-