Friday, July 1, 2022

የትግራይ ፋሽስት ፖለቲካ በትግራይ ወጣቶች ህይወት ላይ ያስከተለው መዘዝ በታጋዮች አንደበት ሲነገር! ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay) 7/1/22

 

የትግራይ ፋሽስት ፖለቲካ በትግራይ  ወጣቶች ህይወት ላይ ያስከተለው መዘዝ በታጋዮች አንደበት ሲነገር!

ጌታቸው ረዳ

 (Ethiopian Semay)

7/1/22

ቪደዮውን ለማየት ከመጨረሻ ጽሑፉ ጋር ተያይዟል

ለአስራሰባት ዓመታት በርካታው የኢትዮጵያ ህዝብ ከኢትዮጵያ ምሁራን እስከ ተራው ሰው፤ ከኢትዮጵያ ፓለቲካ መሪዎችና የጦር ጄኔራሎች ጀምሮ በየፈፋውና በየሜዳው ወያኔን ሲፋለም እስከነበረው ተራ ወታደር ድረስ በዚህ በትግራይ ማህበረሰብ ማህጸን ውስጥ ስለተፈጠረው የፋሽስት ጽንስ፤ የአማራን ህዝብና በዚህ ህዝብ የተመሰለችውን ኢትዮጵያን የጥላቻው ዋነኛ ዒላማ ስላደረገው የትግራይ የፋሽስት እንቅስቃሴ ምንነት ሳያውቅ፤ ሳይረዳ ቀረ። ደርግን የተቀላቀሉት ምሁራንም ሆነ የኢሰፓ ካድሬዎች  መሪያቸውን ጓድ መንግስቱ ኃይለማርያምን ተከትለው “አብዮታዊት እናት ሀገር ወይም ሞት፤ሁሉም ነገር ወደ ጦር ግንባር፤ወደፊት በሉለት ይለይለት” እያሉ መፈክር ከማሰማትና የኢትዮጵያን ወጣት ለጦርነት እሳት ከመማገድ፤በውስኪ ከመራጨትና ጮማ ከመቁረጥ በስተቀር በትግራይ ምድር ውስጥ እንደ እሳት ይንቀለቀል የነበረውንና በትግራይ ህዝብ የጎሳ ማንነት ላይ ተመስርቶ ስር እየሰደደ የመጣውን አዲሱን የፋሽስት የፓለቲካ እንቅስቃሴ ተፈጥሮና ባህርይ ሊረዱ አልቻሉም። በሀገሪቱ ሆነ በውጭ ሀገራት ተሰደን ያለነውና ቀለም ቆጠርን ብለን የምንል ኢትዮጵያውያን ምሁራን ነን ባዮች ይህንን በትግራይ ውስጥ እያበበና ስር እየሰደደ የመጣውን የፋሽዝም ችግኝ ተፈጥሮና ባህርይ አልተረዳንም ነበር። (ምንጭ “ተቃዋሚዎች የወያኔን ፋሽስታዊ ተፈጥሮውን ሳናውቀው አርባ ሁለት ዓመታት ቆጠርን!!!!!! አሰፋ ነጋሽ (ዶ/ር)

በዚህ ዓይነት ለአስራ ሰባት ዓመታት በደርግ ወታደራዊ አምባገነን ስርዓት ምክንያት ክፉኛ የተቀጠቀጠውና ቀለም የቆጠሩ ልጆቹትን በቀይ ሽብር የተነጠቀው የመሃል ሀገሩ ሕዝብ (በተለይ ትግርኛ ተናጋሪ ያልሆነው አብዛኛው የኢትዮጵያ ሕዝብ) ራሱንም ሆነ ሀገሩን ከዚህ አስከፊ በትግራይ ሕዝብ ማንነት ላይ ተመስርቶ የቆመ የፋሽስት ድርጅት ጥቃት ለመከላከል ሳይችል ቀርቶ በደርግ መውደቅ ማግስት የትግራይ ፋሽስቶችና የኤረትራ ግብረአበሮቻቸው መዳፍ ስር ወደቀ።

የኢትዮጵያ ህዝብ ይህንን በትግራይ ማህበረሰብ ውስጥ በአክራሪ የትግራይ ብሄረተኛነት አዋላጅነት የተጸነሰ የፋሽስት እንቅስቃሴ ተፈጥሮና መዳረሻ ባለማወቁ ባለፉት ሃያ ሰባት አመታት አሁን ደግሞ ‘አራት አመት’ በኦሮሞፋሺሰቶች ለተጫነበት ታይቶና ተሰምቶ ለማይታወቅ እጅግ ጸረ-ኢትዮጵያ የሆነ ፋሽስታዊ (የአፓርታይድ) አገዛዝ ተጋላጭ ሊሆን ችሏል።

ብሎ ብሎ በመጨረሻ ከ27 አመት የትግሬዎች ኮሎያል አስተዳዳር በሗላ ትግሬዎች ሥልጣን ተነጥቀው ወደ ትግራይ ተመልሰው ምሽግ በመስራት ሕዝቡን የጥይት ማብረጃቸው በማድረግ በለጠፍኩት “የስዕለ ድምጽ” ማስረጃ አሳዛኝ የትግራይ ወጣቶች ህይወት ምንኛ እያላገጡበት እንደሆነ እንመልከት።

ዘጋቢ ፊልም - ድብቁ ሴራ Etv | Ethiopia | News

https://youtu.be/qWFjFf54dN4

 

ይህንን ብትቀባበሉት ይመከራል!

አመሰግናለሁ

ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay)