Monday, August 7, 2017

ኢትዮጵያዊያ ወጣቶች በቅኝ አዙር አገዛዝ በጴንጤና በመጤ እፆች ማንነታቸው ተነጥቀዋል ጌታቸው ረዳ ኢትዮ ሰማይ አዘጋጅ



ከአዘጋጁ ማስታወቂያ-
 በቅረብ ጊዜ አዲስ መጽሐፌን ለማንበብ ተዘጋጁ።

ኢትዮጵያዊያ ወጣቶች በቅኝ አዙር አገዛዝ በጴንጤና በመጤ እፆች ማንነታቸው ተነጥቀዋል

ጌታቸው ረዳ ኢትዮ ሰማይ አዘጋጅ

እንደምን ሰነበታችሁ። ጥንት ያንበረከክናቸው፤ ዛሬ በወያኔ በር ተከፍቶላቸው ቅኝ ገዢዎች የልብ ልብ ተሰምቷቸዋል። ያሰቡት ተሳክቶላቸዋል። የትግሬው በጋሚዶ “ወሮበላ ስርዓት” ጫካ ውስጥ  እያለ “ጸረ ኢምፔሪያሊስ ነኝ እያለ  ኣንዳልተሞላቀቀ ሁሉ፡ ወያኔ ለገንዘብና ለሥልጣን ሲል የኢምፔሪያሊሰት አሽከር ሆኖ የሕዝባችን ማንነትና ክብር እንዳሻቸው እንዲረግጡን ለባዕዳን አሳልፎ ወጣቶቻችንን ሰጥቷቸዋል።



ትናንት ይህ ትችት አጠናቅሬ አንደጨረስኩ፤ ዛሬ የተላለፈው አዲስ ዜና ደግሞ የ8 እና የ 6ዓመት ወንዶች ልጆች በግብረሰዶማዊያን እየተደፈሩ መሆናቸውና ለዚህም ወላጆቻቸው የሕሊና ሕክምና እንዲደረግላቸው ለፋሺስቶቹ አቤት ቢሉም፤ ወያኔዎች ኢትዮጵያን ለማጥፋት ስለመጡ፤ እሮሮአቸውን ለማድመጥ አልፈለገም ሲሉ ወላጆች በአሜሪካ ድምፅ አማርኛ ስርጭት ዘጋቢዎች ቀርበው ለሕዝብ አቤት አሉ። ልቡ ገንዘብረፍያ ላይ ነውና ስለ ህዝባችን ደንታ የለው ወያኔ የቅጥረኛነት ሥራው እየሰራ ነው።

ጉዳችን ብዙ ነው። አንድ ወንጀል በሌላ ወንጀል እያነባበረ በሕዝባችን ላይ ስቃዩ እየጨመረብን ያለው የትግሬው ወያኔ፤ ለወደፊቱ የምትመካባቸው ወጣቶቻችን በሃይማኖት፤በአደንዛዥ እፅ ተበክሎ ማንነቱን እንድያጣ የባሕር ማዶ ፈረንጆች እና የናይጄሪያ የሕሊና ሰላቢዎች መጫወቻ ሆኖ እንዲዋረድ የትግሬዎች መንግሥት ፈቅዷል። ኢትዮጵያ መሬቷም፤ ሕዝቧም፣ሃይማኖትዋም ተደፍሯል። በሌቦች አልጠግብ ባይ ወረበሎች እና የአገር ክብር በማያውቁ ብሔራዊ ስሜት በራቃቸው ለመንጋ ኢምፔሪያሊስቶች ያደሩ ‘ወያኔዎች’ ሕዝባችን እንዴት አየተዋረደ እንዳለ፡ ከዚህ ቀጥሎ ያለው አሳዛኝ ቪዲዮ እንድትመለከቱ እጋብዛለሁ።


 The Blind and the dead : Ethiopian Pentecostal cults ይህንን ሰው ያደርገዋል ብሎ መገመት ያስቸግራል




የሚለውን ቪዲዮ ይኼው ተመልከቱና ፍረዱ። በስደትም በአገርም ተበትኖ የሚገኘው ኢትዮጵያዊ ወጣት አንዴት እያዋረደው አንዳለ ይህ ማስረጃ ስታዩ የወያኔ ልማትና ዕድገት በግልጽ ትረዱታላችሁ።
TTigray-Festival-attendees-dancing-to-Tigrinya-music-at-the-Tigray-Festival-in-Denver-
አሳዛኙ ክስተት፦ የወያኔ ጭፈራ አቅላጮች በአውሮፓ፤ካናዳ፤ አውስትራሊያ፤ዓረብ አገሮች፤ሱዳን እና አሜሪካ ያሉ ትግሬዎች እየተሰባሰቡ የወያኔን ባንዴራ ለብሰው “ወጋሕ ትበል ለይቲ” (እስከንጋቱ አስረሽ ምቺው ጭፈራ”) ሲጨፍሩ ፤ በሌላ ወገን ኢትዮጵያዊያን ወጣቶች በአለቆቻቸው ወያኔዎች ሴራ ለባዕድ ሃይማኖት (ለህሊና ማሰርያ ሴራ) መሬት ላይ እየተረጉ እየተሰቃዩ ስንመለከት፤ ሕዝባችን በባዕዳን አምልኮት ቅኝ ግዛት ቀምበርነት አንዳይላቀቅ የታሰረበትን ካቲና/ሰንሰለት/ እያጠበቁለት መሆናቸው በታሪክ ተጠያቂዎች ያደርጋቸዋል።

ለኢትዮጵያ ወጣቶች አልቀሱ!!!

ጌታቸው ረዳ (አትዮ ሰማይ አዘጋጅ) getachre@aol.com