Thursday, March 14, 2019

ተቃወሚው ስለ ዲሞክራሲ ሲቃዥ ከርሞ አሁን ዘግይቶ አገር አድን መዝሙር መዘምር ጀምሯል (ቱ ሌት) ኢትዮ ሰማይ!


ከትናንትዋ ትችት ተቆርጣ የቀረቺው ትችት እነሆ፡
አብይ ቢወርድ አገር ወደ ማድ ትቀየራለች ለሚሉ የዲያስፖራ “ኢትዮጵያዊ አክቲቪስቶች” እና “የተገንጣይ ፋሺስት አክቲቪሽቶች” መፈክር አንድ እየሆነ መጥቷል። እሱም “አብይ” ከሠልጣን እወርዳለሁ ቢል ማን የተካልናል? የሚል”የይቆይልን” የማስፈራሪያ ታክቲክ እያስተጋቡ ነው።

 ፋሺዝም እና አፓርታይድ ቢሰፈርስ “አገር ትፈርሳለች” የሚሉ ናቸው እና “አፓርታይዱ የወያኔ እና የኦሮሞዎቹ አፓርታይድ በዘርና በቋንቋ የሚያስተዳድር ስርዓት ስለሆነ “እሱን ማፍረስ የደፈረሰው እንዲጠራ ዋነኛው የግባችን ትኩረት ስለሆነ’ “ፋሺዝም እና አፓርታይድ አይነቀል የሚሉ አክቲቪስቶች ከትግሬ ፋሲስት ቡድን በጥምረት እየሰራ ያለው የአብይ አፓርታይድ መንግሥት ምንነቱ አላወቁትም ወይንም “አብይ ቢወርድ” አገር ይተላለቃል የሚለው ምክንያታቸው “ፋሺስቶቹ አብይ አሕመድን እና ለማ መገርሳ” እያወረዱት ያለው የሕዝብ ጭፍጫፋና ውርደት “ዝምታን መረጣችሁ” ተብለው ለተጠየቁት የመልስ ሽፋን እንዲሆናቸው “ሓፈርታቸው ለመሸፈን” የሚጠቀሙበት “አፓርታይድ መሪዎች” ቢወርዱ አገር አመድ ትሆናለች የሚለው “የዲፈንሲቭ- ስኬር ታክቲክ” መጠቀምን መርጠዋል።

 “ከወያኔ ይልቅ……ቲም ለማ እንመርጣለን” የሚለው ምርጫቸው ያስቃል፡ ወያኔ አብይ ጋር ነው፤ደብረጽዮን ጌአቸው፤አርከበ፤ ሰዓረ፤ፈትለወርቅ፤አበይ ነብሶ … ወደ መቀሌ አልሸሹም አብረው አብይ ጋር ናቸው (ያውም የአብይ አማካሪዎች ናቸው- ዓይነ ስውሩን የአብይ አማካሪ ሆኖ የተሾመው የሕግ አማካሪው “እርኩሱ” አባይ ነብሶን ተመልከቱልኝ)። ስለዚህ አሁንም ወያኔ ኦሮሞዎች ጋር ሆኖ በጥምረት እየገዛችሁ ነው!


አፓርታይድ መግዛቱን ከቀጠለ የባሰውን እልቂት እንጂ እየተሻለው የሚሄድ ስላልሆነ፤ “የደፈረሰው አፓርታይድ” ከነ ኮተቱ እንዲወገድ ደምጻችን ከፍ ማድረግ መቀጠል አለብን። “እልፍ አስከልካዮች “የማስፈራሪያ ታክቲካችሁን አቁሙ!”። ይቀጥል? እስከ መቸ? የሚለውስ ብንጠይቃቸው የጊዜ ገደብ ሊሰጡን ይችላሉ?? ሰሞኑን በዚህ ጉዳይ ሰፋ ያለ ትችት ስለሚቀርቡ ተከታተሉን። 
ተቃወሚው ስለ ዲሞክራሲ ሲቃዥ ከርሞ አሁን ዘግይቶ አገር አድን መዝሙር መዘምር ጀምሯል (ቱ ሌት) ኢትዮ ሰማይ!
ተቃዋሚውም፤ምሁሩም ሚዲያ ተቺዎችም ለ27 አመት ያተኮሩበት  የሕሊና አደንዛዥ ዕጽ “ዲሞክራሲ” የሚባል ነበር። እኔ ለ27 አመት “አገር አድን ነው ማተኮር ያለባችሁ ስላቸው ከላይ የጠቀስኩዋቸው ክፍሎች “ቅዠታቸው” ዲሞክራሲ ብቻ ነበር። እነ ብርሃኑ ነጋ እነ አንዳርጋቸው እነ ..እነ .እነ… መሰረተ ድንጋያችን “ዲሞክራሲ” ነው እያሉ ኦነግን ሰብስበው በየአዳራሹ ሲቃዡ፤ ኦነጎች እና ወያኔዎች ‘በገሃድ አገር ሲሸረሽሩ ነበር። ሌላ ቀርቶ እነ ሲሳይ አገና አስከ ሁለት በፊት “ኦነጎችን እና የመሳሰሉ “ቬተራን” ነፃ አውጪ ግምባሮች ተገቢውን ጡሮታ እና ክብር ከመንግስት ድጎማ ይደረግላቸው እያሉ ስለ እነ ሌንጮ፤ስለ እነ ዳውድ ኢብሳ ደህንነት እና ክብር በኢሳት ሲደሰኩሩ ነበር! በኦነግ ፖለቲካ የተቃኙ ባለስልጣኖች ግን አዲስ አበባ ቁጭ ብለው ባንክ ሲያዘርፉ ፤ ዜጎች በቢላዋ በቆጨራ አንገት ሲቆርጡ፤አምጫቶች ከመኖያ ቤቶቻቸው በቡልዶዞር ሲያስፈርሱ ነበር (አስከ ትናነት ሰምንት)። 
  
ዛሬም በፋሺዝም ስርዓት ውስጥ ሆነው ጋዜጠኞችም ምሁራኖችም ያ የደነዘዙበት ስለ “ዲሞክራሲ” ቅዠታቸው አልለቀቃቸውም። አሁን  አንዳርጋቸው ጽጌ በቅርቡ ከቅዠቱ ወጥቶ ‘ዲሞክረሲ’ ሳይሆን አገር ችግር ላይ ነው ማላቱ የሚደገፍ ቢሆንም፤ ለበርካታ አመታት አገር አድን ሳይሆን  “ኦነግ/ሌንጮ/ ኢትዮጵያን በዲሞክራሲ ለማዳን ተነስቷል” እያሉ ስለ የማይጨበጠው ‘በቀላሉ የሚነጠቅና የሚሄድ “አመጸኛ እና ጽንኛ ጎሰኞች” ጭምር ለማስነገስ የሚፈቅድ ‘ዲሞክራሲ’ የተባለ ከረሜላ ለመቆርጠም ‘ሲቃዡ’ ሕዝቡን ሲያጃጅሉ ከነበሩት አንዱ ቅዠታሙ የኢሳቶቹ የግንቦት 7 ካድሬ ጋዜጠኞች “ጀግኖች” አንዳርጋቸው ጽጌ እና ብርሃኑ ነጋ ነበሩ። እስከ ትናንት ድረስ ቅዠታቸው “ዲሞክራሲ’ ነበር።

የሲ ኣይ ኤው “ደላላ” አብይ አሕመድ የተባለ የኦነግና የህወሓት ፖለቲካ አቀንቃኝ  ታይቶ ተሰምቶ የማይታወቅ ዲሞክራሲን በወርቅ ሐረግ በተሰራ “መሶብ” ይዞልን መጥቷልና አብረን እንብላ ብለው ጫማው ስር ሲደፉ ማየት የካፋ አስገራሚ ክስተት አልነበረም። ድጋፋችሁ ጥሩ ነው ግን እባካችሁ ረጋ በሉ፤ ድጋፋችሁ በመጠን አድርጉት ስንል፤ “ለደንቆሮ” አዝማሪ ግጥም እየሰጡ “አብይ” “አብይ”፤ “ለማ፤ለማ”  እያሉ ፋሺስቶችን በማቆለጳጰስ አገር አሁን ወዳለችበት አሰቃቂ ሁኔታ አደረስዋት።

“በሚዲያ ኤቲክስ ተብው” ስም ከፋሺስት ሙሶሎኒ ጋር የሚመሳሰሉ ፋሺስቶችን “ክቡር ጠ/ሚኒሰቲር እገሌ’ ክቡር….እገሌ እያሉ እያቆለጳጰሱ ክብርናን እና ልዕልናን እያስለበሱ ወጣቶች ፋሺስቶችን በክቡርነት እንዲጠርዋቸው እያደረጉ የሕሊና አጠባ አስተዋጽኦ በማድረግ የሚታወቁ ኢሳቶችም ዛሬ ኢሳት ቴ/ቪዥን ጋዜጠኞች የፖለቲካ መሪዎቻቸው እነ ብርሃኑ ነጋ እና አንዳርጋቸው ጽጌ ከተሸሸጉበት ምህዋር አውጥተው አንዳርጋቸው ጽጌ ‘አገር ችግር ላይ መሆንዋን ተናገረ’ ማለት ጀምረዋል።

ጉዳት ከመድረሱ በፊት እነ ተቃዋሚ ተብየው እነ እንዳርጋቸው እነ ሞላጫ ፖለቲከኛው እነ ብርሃኑ ነጋን ስለ ዲሞክራሲ ጋጋታህ ጊዜው አሁን አይደለም ‘ተው’ ብለን ስናስጠነቅቅ፤ ጀሮ ዳባ ብለው፤ አሁን እነ አንዳርጋቸው ጽጌ “የአገር አድን” መዝሙር መዘመራቸው የሚደገፍ ቢሆንም፤ “ቱ-ሌት” (ጉዳቱ ደርሷል)።

እስክንድር ነጋም ይኼ አገር ሳይድን ስለ ዲሞክራሲ ማውራትህ ተው ብየ ከመታሰሩ በፊትም ሆነ ከተፈታም በላ በራሴ ብሎግ በትችት አስጠንቅቄው ነበር። እርሱም አልሰማም። ይባስ ብሎ “ኦነግን ያልጨመረ ፖለቲካ ኢትዮጵያ አትድንም እያለ ኦነግን ፖለቲከኛ አድርጎ ድንጋይ ሲያቀብል ነበር። አሁን ኦነግ ተደምሯል። ውጤቱ ግን “ዘረፋ፤ግድያ፤ሁከት፤ልቅሶ ሞት፤ ስርዓተ አልባ እንደሆነ ከዚህ ወዲያ ምስክርነት ላመጣላችሁ አልችልም”። ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ አሁን እየሰራ ያለው እና እየሄደበት ያለው መንገድ ግን ወድጄዋለሁ፡ በዛው ይቀጥል። 

ሁላችሁም ፖለቲከኞች እና ምሁራን ማስተዋል ያለባችሁ፤ -“ህጻናት እና እርጉዞች አረጋውያን እና መነኮሳት..” ቤቶቻቸው በላያቸው ላይ በቡልደዘር ሲፈርስባቸው እናንተ ‘ስለ ዲሞክራሲ” ቅዠታችሁ አቁሙ እና አገር ማዳን ኢትዮጵያን የማዳን ክተት አዋጅ ፤ ቅስቀሳ ስበኩ!! የተፈናቀሉ ዜጎቻችን ወደ መኖርያቸው የሚመለሱበት ሕግ ይመስረት፤ ምግብ ይቅረብ፤መጠለያ ይቅረብ፤ ወንጀለኞች በዓለም አቀፍ ፍ/ቤቶች ይከሰሱ!!! ስለ ዲሞክራሲ ቅዠታችሁ አቁሙ!! ለጥቋቁር ጣሊያኖችን ስለ ዲሞክራሲ ውትወታ ጉዳያቸው አይደለም። ጆሮ ኣይሰጡትም እና ቅዠታችሁን አቁሙ! ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ የጀመረው የአዲስ አበባ ወጣቶች አንቅስቃሴ እንዳይቀዘቅዝ ግድግዳ ሆናችሁ ያንን እንቅስቃሴ ለአዲስ የለውጥ መዘውር እንዲሆን አንዲጠናከር፤ አዲስ አበባ እና መላው አገሪቱ ወንጀለኞች ለፍርድ ይቅረቡ፤ የሚሉ “የተቃውሞ ሱናሚ” “ሰልፎች መናወጥ” አለበት። ፖለቲከኞች በየ አዳራሹ ከነጃዋር መሞዳሞዳችሁን አቁሙ! መሳቃያ ትሁኑ!  

ደጋግሜ፤ደጋግሜ ‘አብይ እና ለማ መገርሳ’ ፋሺሰቶች ናቸው ብየ፤ የጥገና እንጂ ስር ነቀል ለውጥ አያመጡም ብየ በቃለ መጠይቄ ደጋግሜ ስናገር፤ የኛ ዲሞክራቶች ጫማ መሳለም፤ ደንቆሮ አዝማሪም “አብይ፤ለማ” እያለ በመወጥወጥ (ማዜም) ደምጻችን ሳይሰማ ቀርቶ ይኼው አሁን ያልነውን ሁሉ ሆኗል።እነ አብይ እነ ለማም ሆኑ የወያኔዎቹ አሳፋሪ ገረድ የነበረቺው “ሙፈርያት ካሚል” የመሳሰሉት ሁሉ “በፋሺሰት ርዕዮት” ኮንታሚኔትድ (የተበከሉ) ስለሆኑ ሊድኑ አይችሉም ብለናል። አሁን ዜማችሁ ቀይሩ። የኦሮሞ ሦስተኛ ዙር ፋሺዝም እንደሚመጣ ለበርካታ ወቅት ጽፌአለሁ። ታስታውሳላችሁ ብየም አምናለሁ። አሁን ሦስተኛው ዙር የኦሮሞ ወረራ ፋሺዝም ገሀድ ሆኖ ፊታችሁ ላይ ተገትሮ ቆሞ እያያችሁ ነው። አሁን ፋሺሰቶችን እንደካባችሁሗቸው፤ ፏሲቶችን አውርዱዋቸው እና ሕዝባችን ከዚህ ፋሺስት መንጋ አድኑት
ኢትዮ ሰማይ!