Sunday, August 4, 2024

የትግራይ ምሁራን በትግራይ ሕዝብ ጭንቅላት ላይ የተንጠለጠሉ የ Damocles ሰይፎች ናቸው ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay 8/5/24

 

የትግራይ ምሁራን በትግራይ ሕዝብ ጭንቅላት ላይ የተንጠለጠሉ የ Damocles ሰይፎች ናቸው

ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay

8/5/24

አንድ ሰው የዳሞክልስ ሰይፍ በራሱ ላይ ተንጠልጥሏል ሲል ሰውየው አደጋ ላይ እንዳለ በማንኛውም ጊዜ በጣም መጥፎ ነገር ሊደርስበት በሚችልበት ሁኔታ ውስጥ ነው ማለት ነው።

የዳሞክልስ ሰይፍ ከክርስቶስ ልደት በፊት የነበረ የጥንታዊ የግሪክ አፈታሪክ (ልብ ወለድ/apocryphal) ትረካ ነው፡፡ በግሪክ አፈ ታሪክ ውስጥ ዳሞክልስ (ያንድ አካባቢ አገረ ገዥ የነበረ የሲራኩስ ንጉሥ  የዲዮኒሰስ ጓደኛ የነበረ ነው፡፡

ታሪኩ እንደሚለው፣ ዳሞክልስ ንጉሥ ዲዮናስዮስን እያሞካሸ፣ ሥልጣንና ምቾት ያለ ጠላትና ተወዳዳሪ፣ በታላቅ ግርማ የተከበብክ በእውነት የታደልክ ነህ፡ እያለ ብዙ ጊዜ ሲያሞካሸው ሰማውና በምላሹ ዲዮናስዩስ ዳሞክልስን ሕዝብ በተሰበሰበበት ትልቅ ድግስ ጋብዞ ዝናውና ምቾቱ እንዲቀምስ ለአንድ ቀን ከዳሞክልስ ጋር ቦታውን ለመቀያየር ሐሳብ አቀረበለት። ዳሞክልስም የንጉሱን ሃሳብ በጉጉት ተቀበለው።

ዳሞክልስ በንጉሱ ዙፋን ላይ ባማማሩ ባለ ጥልፍ ምንጣፎች፣ ጥሩ መዓዛ ያላቸው ሽቶዎች በተነሰነሱበት አዳራሽ እና በሚያማምሩ አገልጋዮች ተከብቦ ዙፋኑ ላይ እንዲቀመጥ አደረገው።

ነገር ግን በንግሥና ጊዜ ብዙ ጠላቶችን ያፈራ ዲዮናስዮስ ከዙፋኑ በላይ ሰይፍ እንዲሰቀል አዘጋጀ፡፡ በአንዲት  በተመዘዘች ቀጪን ፀጉር የፈረስ ጭራ የተንጠለጠለቺው ይህች ሰይፍ ከዙፋኑ መንበር አናት ላይ “በአየር ላይ ተንጠልጥላ” እንደ የሰዓት ደወል ዥዋዌ እየሰራች ትታያለች፡፡ ይህ ድርጊት ያደረገውም ሆን ብሎ ንጉሥ መሆን ምን እንደሚመስል ፤ ላንድ ቀን ብቻ ሥልጣን አምሮት ለነበረው ወዳጁ ለማሳየት ነበር፡፡

ዳሞክልስም ዙፋኑ ላይ ቁጭ እንዳለ ወደ ላይ ሲመለከት “ሰይፉ” በላዩ ላይ ተንጠልጥሎ አናቱ ላይ “ወደቅኩ፤ ወደቅኩ” ይላል፡፡ዳሞክልስም በመጨረሻ ባንዲት ቀጪን የፈርሰ ጭራ በላዩ ላይ የተነጠለጠለቺው ሰይፍ ሲያይ ንጉሥ መሆን በብዙ ጠላቶች የተከበበ መሆን እንደሆነና አንድ ቀን በሥልጣን ስስት የሞት እጣ እንደሚገጥመው እየነገረው መሆኑ ሲያውቅ ዳሞክልስም  በፍርሃት ከዚያች ደቂቃ በኋላ ንጉሥ መሆን ስለማይፈልግ ዙፋኑን ለመልቀቅ ፍቃድ እንዲሰጠው ለመነው... (እያለ ረዢሙን አፈታሪክ ሥልጣን ላይ ሰለ ወጡ ሰዎች የሥልጣን ጥማቸው ላለመልቀቅ በላያቸው ላይ የተንጠለጠለ ሰይፍ ንጉሡም ሃገሪቱም ይዝዋቸው ወደ ውድመት እንደሚዳርጋቸው የግሪኮች አፈ ታሪክ ይነግረናል፡፡

ባጭሩ አንድ ተንታኝ በአንተ ላይ የተንጠለጠለ 'የዳሞክልስ ሰይፍ' አለ ብሎ ካለህ፣ ህይወትህን በምታውቀው የማያቋርጥ ስጋት ውስጥ ትኖራለህ ማለት ነው፡፡ አንድ ማሕበረሰብም የችግሩ  ምክንያት አውቆ በተሎ ካልነቀሰው ችግሩን ማስቀረት አይቻልም። የሚሆነው ከእሱ ጋር ብቻ መኖር እና አደጋው ፈጽሞ እንደማይከሰት ተስፋ ማድረግ ብቻ ነው፡ያለው አማራጭ፡፡

ሰሞኑን መቀሌ ውስጥ ወያኔዎችና ምሁራን ያደረጉት ትግራይ የገባችበት አጣብቂኝ  መነሻው (እነሱ መሆናቸውን በመደበቅ) ከየት ነው ብለው ለመመርመርና አሁን ከተቸነከረቺበት ማጥ ውስጥ እንዴት ትላቀቅ በሚል የተለመደ ራስን ከሥልጣን ላለመልቀቅና ሐላፊነት ላለመውሰድ ትግራይ ውስጥ ያለው የችግሩ ምንጭ በጥናት አጥኚው ቡድን የቀረበ ጥናት አድምጣችሁ ይሆናል፡፡

ጥናቱ የተነበበው ድሮ በ27 አመት (17 አመት ጫካ ላይም) ኢትዮጵያውያንን ሲያሰቃይ የነበረው የደህንነት ምክትል ሐላፊ የነበረው ዋና አስገራፊና ገራፊ በነበረው አሁን ትግራይ ውስጥ የጊዜያዊ አሰተዳደር የጌታቸው ረዳ አማካሪ የሆነው “ወልደስላሰ ወ/ሚካይል” ለተሰብሳቢ ያነበበው እንዲህ የላል፡

 <የችግሩ መሰረታዊ ምንጭ ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን አክብሮ የሚሰራ አስተዳደር ባለመኖር ነው>  ይላል፡፡ እሱ ብቻ ሳይሆን ዶ/ር ምዑዝ የተባለ "አላማጣዊ ወያነ" አጥኚ ከተባሉት አንዱ ሲሆን ይህንኑ በአጽንኦት ተናግሮታል፡፡ ይገርማል!

አገር ለማፍረስ ታቅዶ የተደነገገ አፓርታይዳዊውን “ሕገመንግሥቱን አክብሮ የሚሰራ ባለመኖሩ እንጂ የትግራይ ሕዝብ አሁን በገባበት ጨለማ ውስጥ ባልገባ” የሚለው የአጭበርባሪዎች ጥናት እንደ ወልደስላሰ ወ/ሚካይል የመሰሉ የሰው ልጅ በድብደባ ሲያኮላሹ የነበሩ ፤ እነ ጌታቸው ረዳ የመሳሰሉ ፥በትግሬ የፋሺዝም አብዮት ፍቅር የወደቁ ፥ እንደ ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል በሰሜን እዝ ጦር ላይ የዘር ፍጅት ፈርመው ያጸደቁ ፤ “ጦርነት መስራት እንችላለን የሚለው “በትግራይዋይነትክሰፕሺናሊዝም’’  እብሪት ተወጥረው ለጦርነቱ ቆስቋሽ መነሻ የሆኑትን እንደ እነ ፤ እንደ እነ ፥ ወዘተ ፥ ወዘተ... የመሳሰሉ ወንጀለኞች አሁንም ሥልጣን ይዘው የሕዝቡን ሕይወት እየተጫወቱበት እንዳሉ ወደ ራሳቸው የሚመለከት ከውጭና ካገር ውስጥ ገለልተኛ አጥኚና “የሕግ ቀጪ” ቡድን እንዲመሰረትና እንዲጠና  አይፈልጉም ፥(አዲስ አበባ አራት ኪሎ ያለው በየጎዳናው እየዞረ ንጉሥ ለመሆን የሚዳዳው ማስቲካ ሲያድል የሚውለው ህጻኑንም ጭምር)፡፡

ስለዚህ ጥናት ብለው ያቀረቡት “ሲምፕተሙን” (የሕመሙ ምልክት/ውጤት) እንጂ የትግራይ ሕዝብ የገባበትና እያሰቃየው ያለው ዋና ምንጭ የሆነው “ተወሳክ” ሊናገሩና ሊዳስሱት አይፈልጉም፡፡ ሰለዚህም ተጋሩ አሁን የገጠማቸው ሕይወት አስቸጋሪ ቢሆንም ከዚህ የባሰ ሊያመጣላቸው የሚችል ሊያስወግዱዋቸው ያልፈለጉ የሚከተሉዋቸው ክንዋኔዎች አሉ ፡፡

እሱም ረቂቅ ትንተና ሳያሰፈለግ በግልጽ አማርኛ እንዲህ ነው፡-

ከሚከተሉት በዙ ታዳጊ የትግራይ  ወጣቶችን ያሰከረ ትግራዋይ ፈተኽ ዘይብል ነጋሳይ አንጋሳይ” (ፍንክች የማይል ነጋሽና አንጋሽ) ዕብሪትነትና እና ልዩ ፍጡርነት (Tigrayan Exceptionalizm) እና የሙጥኝ ብለው ይዘውት ካሉት የሚከተሉት “ሙሶሎኖያዊ” የዘር /ብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች የሚሉት አፓርታይዳዊ  ፤ ብጥብጥ አንሺና አገር አፍራሽ ሕገመንግሥት አሁንም ለማስቀጠል ያላቸው ጽናት፤ የሙጥኝ ማለታቸው፤

እንዲሁም “ሃገረ ትግራይ”

የሚባል አገር የመመሥረት ሩጫና ፍላጎት፤

የአክሱም ሥልጣኔ ብቸኛ ተዋናይ ፤ መሪና ባለት ፡ ታሪክ ሰሪ ትግሬ ብቻ  ነው ከሚለው ፡ የዓድዋ ድል የትግ ብቻ  ነው ፡ የሚለው በማስረጃ መደገፍ የማይቻል ጉራና ፋሺስታዊ ዕብሪት የተጠናወተው ባሕሪ ካላቆሙ፤

በኩሬዋ ትግራይ ከመዋኘት ልምድ ወጥተው በውቅያኖስዋ ኢትዮጵያ መዋኘት ካልለመዱ፤ 

ትግራይ ውስጥ ያሉ የካቶሊክኦረቶዶክስ ፤ ፐሮተስታንትና እስልምና ሃይማኖት መሪዎች በየአዳራሹ የሚናገሩት የፈጣሪና መንፈሳዊ ምክር ይልቅ ፖለቲካዊ ብሔረተኛ ቃላቶችን እንግሊዝኛም ትግርኛም እየደበላለቁ ከሃይማኖት ሰባኪ ይልቅ ወደ ካድነት የሚያሳዩት ነውር ማረም ካልቻሉ...

በትግዎች ፈቃጅና ከልካይነት የሚታደል የኦርቶዶክስ ሃይማኖት የመፍጠር “ኡሉሚናታዊ ዕብሪት”

አሁንም ያልበረደላቸው አማራና ኢትዮጵያን በጠላት ፈርጀው ብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማንም ትግራይ ውስጥ እንዳይታይ ማሰወገድ፤

 እንዲሁም ተኝተው ነቅተው በጥላቻ ተወጥረው በትምሕርት ቤት ፤ አደባባይ፤ ህጻናት ፊት ፤ በየስብሰባው፤ በሃይማኖት በዓላት ትግሬዎችና ጣሊያኖች በክፉ ቃላት ሚያምነዥኩዋቸው በአጼ ምንሊክ ያላቸው ጎጂ የፖለቲካ ትረካ

እንዲሁም በወልቃይትና በወሎ ውስጥ እያደረጉት ያሉት “የግዛት ማስመለስ/ ትግሬዎች (“ግዝአታዊ ሓድነት”)  የሚሉት በናዚዎች Manifest Destiny መርሃግብር (Lebensraum) የሚሉት ተስፋፊ “ለም ቦታና ሰፈራ ፍለጋ” መርሃግብር የሙጥኝ ማለታቸውን ካላቆሙ ወደ ባሰ ጦርነት የሚያስገባ ስለሆነ ሕዝቡ ማየት የተሳነው በቀጭን ክር በላያቸው ላይ ተነጠልጥላ ለመበጠስ የተቃረበቺው የDamocles ሰይፍ አሁን ካዩት ችግር በላይ የባሰ እንደ “ደራሽ ውሃ” ፤ ልክ እንደ ኤርትራኖቹ “ለተጨማሪ ስደት ፤ እልቂት ፤ ሞት ፤ ድህነትና የመበታተን እጣ ይደርሳቸዋል (if not already)፡፡

ሰሞኑን የተካሄደው የመቀሌ ስብሰባና ውሳኔ ከጠቀስኩዋቸው የችግራቸው ምንጮች አንዳቸውም ሊያዩዋቸው አልፈለጉም፡፡ ለዚህ ነው የትግራይ ሊሂቃን በትግራይ ሕዝብ ጭንቅላት የDamocles ሰይፍ ሆነውበት የመጪው አደጋ አዋላጆች ናቸው የምለው፡፡ ባጨሩ የትግራይ ምሁራን መቸውም ቢሆን ከስሕተት የማይማሩ በትግራይ ሕዝብ ሕይወት ላይ የሚያንዣብቡ የDamocles ሰይፎች ናቸው፡፡ 

በችግር ፈጣሪዎችና አባሎቹ ችግር ለመፈታት የሚደረግ ጥናት ቅዥትና ውሃ ቅዳ ውሃ መልስ ከመሆን አልፎ አንድ የስብሰባው ተካፋይ የሆነ ከመድረክ የማይጠፋ የትግራይ ብሔረተኛ ምሁር እንዳለው "በየአመቱ ጨለማን ማስታቀፍ" ነው፡፡

ጌታቸው ረዳ