Sunday, January 13, 2013

የ“እኛ” ቲቲሆያ (ከወሰን ሰገድ ገ/ኪዳን)


እኛቲቲሆያ
ከወሰን ሰገድ /ኪዳን
አሀዱ

ይህንን ፅሁፍ ለመፃፍ ሳውጠነጥን (150 ዓመት በፊት) የአፄ ቴዎድሮስ ዘመነ መንግስት ዜና መዋዕል ዘጋቢ እንደነበሩ የሚነገርላቸው አለቃ ዘነብመፅሐፈ ሥጋዊ መንፈሳዊበተሰኘው ድርሰታቸው የከተቡት የሚከተሉት አባባል ታወሰኝ፡፡

“…አስተካክሎ ከማይናገር መልዕክተኛ የማለዳ ወፍ ትሻላለች፤ ምነው ቢሉ መንጋቱን በትክክል ትናገራለች፡፡

ይህ የአለቃ ዘነብ አባባል ሁለት ነገሮችን አጉልቶ የሚያሳይ ይመስለኛል፡፡ መልዕክት ወይም መልዕክተኛውን እና ወፏን፡፡ አንደምታም ያለው ይመስለኛል፡፡ ወፍ ስል፣ ሌላ ወፍ ታወሰኝ፡፡

ክልዔቱ

ቲቱሆያበመባል ትታወቃለች፡፡ በደቡብ ምስራቅ አፍሪካ የምትገኝ ወፍ ናት፡- ቲቲሆያ፡፡ በአፍሪካ የነፃነት ትግል ውስጥ ታላቅ ሚና የተጫወቱት እንደነ አለን ፖተን፣ አሌክስ ጉማን እና ፒተርስ አብርሀምንወዘተ የመሳሰሉ ደራሲያን በሥነፅሁፍ ሥራዎቻቸው በነፃነት ተምሳሌተነት የሳሏት ወፍ ናት፡፡ በዝማሬዋ የነፃነትን መምጣት የምታበስር ነቢይ ድምፅ ሆና ከተሳለችባቸው የሥነ ፅሁፍ ሥራዎች አንዱ አንጋፋው ደራሲና ጋዜጠኛ (ነፍስ ይማር) “እሪ በይ ሀገሬበሚል ርዕስ ወደ አማርኛ የተረጎሙት የአለን ፖተን መፅሐፍ ነው፡፡

በአጭሩ ቲቲሆያ የነፃነት ብስራት ድምፅ የምታሰማ ናት፡፡ ለፅሁፌ አግባብነትነፃ ድምፅ ናትብላት ይሻላል፡፡ በዚሁ ወደሌላ ትውስታ ላምራ

ሠለስቱ

በምኖርበት ሰፈር አካባቢ የብዙ ልጆች የሆኑ አንድ እናት አሉ፡፡ ልጆቻቸው በሙሉ ሥራ ስለሚውሉ ብቻቸውን ነው የሚውሉት፡- በሳሎናቸው ጥጋት ከተሰየመ ቴሌቪዥን ውጪ ቀኑን ሙሉ አናጋሪም አነጋጋሪም የላቸውም፡፡ ባለ ዲሽ ነው ቴሌቪዠናቸው፡፡ አጠቃቀሙን ግን አያውቁበትም፡፡ አንድ ቀን ጠሩኝና ሌላ ጣቢያ እንድቀይርላቸው አዘዙኝ፡- ኢሳትን፡፡ በሁለት ሳምንት ውስጥ 4 ቀን ያህል ጣቢያውን ቀየርኩላቸው፡፡

በሌላ ቀን በበራፋቸው አለፍ ስል ኢቲቪ ላይ አፍጥጠው አሠኋቸውናእማማ ልቀይርልዎት እንዴ?” ስል ጠየቅኳቸው፡፡ እጃቸውን ወደከፈቱት ቴሌቪዥን እያወናጨፉ እና እየጠቆሙኝኧረ ተውኝ! ይኸው የለመድኩት (ኢቲቪን ማለታቸው ነው) ምን አለኝ?” አሉኝ፡፡ አባባላቸው ብዙም አልገረመኝም፤አሳሰበኝ እንጂ፡፡ እናም በውስጤወይ ምርጫ ማጣትአልኩኝ፡- ለራሴ፡፡

አርባዕቱ

በሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጪ ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያውያን የተሻለ ህይወት ለማምጣት በማሰብ እንደየመሻታቸው (እንደየምርጫቸው) በመትጋት ላይ የሚገኙ በርካታ ወገኖች አሉ፡፡ በግልና በጋራ፣ በማህበርና በፖለቲካ ድርጅት ወዘተ የተደራጁ፡፡ ገሚሶቹ ሰላማዊ የፖለቲካ ትግልን ስልት፣ ጥቂቶች በኃይልም ጭምር ታግለው የተሻለ የሚሉትን ለውጥ ለማምጣት እየጣሩ መሆናቸው የአደባባይ ምስጢር ነው፡፡ ይሁን እንጂ ሁሉም ወገኖች የተሻለ የሚሉትን ዓላማቸውን ለማሳካት በዋነኛነት የሚገለገለገሉበት መሳሪያ አንድ እና አንድ ነው፡- መገናኛ ብዙሃን፡፡ ማን? ምን? እንዴት? መቼ? ለምን? የሚሉትን ጥያቄዎች ለመመልስ መልዕክትን በሚገባ አስተላፎ ዓላማን ለማሳካት መገናኛ ብዙሃናት(ሬዲዮ፣ ቴሌቪዥን፣ ጋዜጣ፣ መፅሔት፣ ድረ-ገፅ ወዘተ) ታላቅ ሚና ያላቸው መሆኑ የሚያጠያይቅ አይደለምና፡፡

እኛም ሰዎች ተፈጥሮአዊ የሆነ የማወቅ አለንና እየሆነ ያለውን፣ የሆነውን እና ይሆን ዘንድ የሚፈለገውን ሁሉ እናነፈንፋለን፡፡ በተለየም የሀገር ጉዳይ ሲሆን የማወቅ ጉጉታችን ይንራል፡፡ ምንም እንኳአማራጭ የመረጃ ምንጭየሚባሉትና ከባህር ማዶ የሚተላለፉ ኤሌክትሮኒክስ ሚዲያዎችና ድረ-ገፆች ወዘተ በመንግስት እየታፈኑ የማወቅ ጥማታችንን ማርካት ባይችሉም፣ በተቻለን መጠን (በአቋራጭም ሆነ በቀጥታ)መረጃ ለማግኘት እንጥራለን፡፡

በቅርቡ የኢትዮጵያ መንግስት በአሸባሪነት የፈረጀውየግንቦት 7 ኃይልወደ ትጥቅ ትግል መግባቱን የሰማነው በዚህ መልኩ ነው፡፡ 4ዓመት በፊት ሁለቱንም የትግል ስልት (ሠላማዊ እና የትጥቅ) እንደሚከተል በይፋ አሳውቆ የነበረውና በእነ / ብርሃኑ ነጋ የሚመራው ግንቦት ሰባት፣ አንደኛውን በትጥቅ ትግል ቆርጦ ጫካ መግባቱን ወሬ፣ ከመሪዎቹ አንደበት ዝርዝር ማብራሪያ የጠራ መረጃ ለማግኘትም ቋምጠን ነበር፡፡

ከጥቂት ሳምንታት በኋላ መንግስት አሸባሪው የግንቦት 7 ልሣን ነውብሎ የፈረጀውና ደግሞ ደጋግሞ ከማንም ከምንም ያልወገነ ነፃ የሕዝብ ልሣን መሆኑን የሚያሳውቀው ኢሳት (ESAT) የተነገረውን የጦርነት እወጃ በተመለከተ / ብርሃኑ ነጋን ወደ ስቱዲዮ ጋብዞ አነጋገረ፡፡ እኔ እንደሚመስለኝ ወይም እንደገባኝ የኢሳት (ESAT) ሥርጭት የሚዘጋጀው ከሁለት ቦታ ነው፡፡ አምስተርዳምና ሆላንድ፡፡ / ብርሃኑ ስለተባለው የጦርነት እወጃ ቃለምልልስ የተደረገላቸው ጊዜ ነው፡፡ በዋሽንግተን ዲሲ ከኢሳት (ESAT) ቴሌቪዠን ቃለ ምልልስግንቦት 7 የእኛ ኃይል አይደለም፤ ዓላማቸውን ግን እንደግፋለንአሉ፡፡ ይህን ይበሉ እንጂ ስለተባለው ወይም ዓላማውን እንደሚደግፉ ስለገለፁት ኃይል በተብራራ መልኩ ምላሽ ለመስጠት አልደፈሩም፡፡ ለምን? እዚህ ላይ ነው የማወቅና የማሳወቅ መብት የሚከተለው፡፡ ከዚህ በኋላ በርካታ ኢትዮጵያውያን በየድረ- ገፁ ጥያቄዎችም አስተያዮትችም ሰጥተዋል፡፡ የመረረ ተቃውሞዎችና የድጋፍ ድምፆችም ተሰምተዋል፡፡ ተፅፈዋል፡፡ ተነበዋል፡፡ ሌሎች የተዳፈኑ የሚመስሉ ጥያቄዎችንና ትችቶችን ያስደተናገደ አጋጣሚ ነበር ብል አልተሳሳትኩም፡፡

/ ብርሃኑ በአምስተርዳም ከጋዜጠኛ ፋሲል የኔዓለም ጋር ያደረጉትና 1 ሰዓት 20 ደቂቃ በዩቲዩብ የተለቀቀው ሁለተኛው ቃለምልልስ ነው የእኔን ትኩረት የሳበው፡፡ ይህንን ቃለ ምልልስ ተከትሎ በየድረገፁ የወጡ የተሰነዘሩ አስተያየቶች፣ ትችቶችና ለከት ያጡ ስድብ አዘል የአንባቢ ምልልሶች (መፈራረጆች) ናቸው ሀሳቤን እንድሰነዝር ግድ ያሉኝ፡፡ ቲቲሆያ በመሆንና አለመሆን አጣብቂኝ ውስጥ መውደቅ፣ ነፃ ድምፅ (ልሳን) በመሆንና ባለመሆን መሃል መንፈራገጥ ለማንም ለምንም አንዳችም ጥቅም እንደሌለው በአፅንኦት ለመግለፅ ነው ብዕሬን ያነሳሁት፡፡ ለዚህም በአስረጅነት የማጣቅሰው እዛው ባህር ማዶ ድረ-ገፅ ላይ የተነሱ ጉዳዮችን ነው፡፡

አምስቱ

-ሐበሻ የተባለ ድረ ገፅ ላይ ሮቤል ሄኖክ የተባሉ ፀሐፊ የኢሳት ጋዜጠኛ ፋሲል የኔዓለም በቃለምልልሱ ወቅት / ብርሃኑን ሊጠይቃቸው የሚገባ ነገር ግን ያልጠየቃቸው 10 ያህል ጥያቄዎች አንስቶ ለምን ሲል የሰነዘራቸው ጉዳዮችን ነው በአስረጅነት የምጠቅሰው፡፡ ስለ7D ለምን አልጠየቃቸውም? ወይስ ጠይቋቸው የሰጡትን ምላሽ ለዜና ፍጆታ አስቀምጦት ይሆን? ወይስ / ሰለ7D መናገር ዕውቅና እንደመስጠት ይቆጠራል በሚል እምነት ምላሽ ሳይሰጡት አልፈውት ይሆን? ወይስ ይህንን ብቻ ጠይቀኝ ብለው ጥያቄ አውጥተው ሰጥተውት ይሆን? ሲል ይጠይቃል፡፡ ሌላም ጥያቄ ያቀርባል፡፡ ቃለምልልሱ የፈጠረበትን ስሜት ሲገልፅፋሲል የራሱን ቲቪ ፕሮግራም የጀመረ ነው የመሰለኝሲል ይገልፀዋል፡፡ ይህ የሥሜት አገላለፁ ከዋነኛ ጉዳዮች ሁሉ ዋንኛው ጉዳይ ተደርጎ መወሰድና መታየት ያለበት ነው ብዬ አምናለሁ፡፡ አንደምታው ሚዲያ የግለሰብ ተቋም አይደለም፡፡ የህዝብ ነው፤ ህዝብ የማወቅ መብት አለው፤ ህዝብ ማወቅ የሚገባውን ነገር ማስተላለፍ አለበት የሚል የጋዜጠኝነትና የሚዲያ መርህ ይከበር የሚል ነው፡፡

የዘ-ሐበሻው ፀሐፊ ሮቤል ሄኖክ ያልተረዳው ፋሲል የኔዓለምና ጋዜጠኝነት የማይተዋወቁ ወይም ሊተዋወቁ የማይችሉ መሆኑን ነው፡፡ ጋዜጠኝነትና የሚዲያ ተቋማት ለፖለቲካ መሪዎች ልሣንነት ብቻ የቆሙ አይደሉም፣ ሙያውም ሁነ ተቋማቱ ለሥልጣንና ለባለስልጣናት አጎብዳጅ አይደሉም፡፡ ሊሆኑም አይገባም፡፡ እኔ እስከማውቀው ድረስ ፋሲል የኔዓለም ይህ የነፃ ልሳንነት ልምድ የለውም፡፡ አዲስ ዜናጋዜጣ ባለቤት እናጋዜጠኛበነበረበት ወቅት አብረን በሰራንባቸው ጥቂት ወራቶች ውስጥ የታዘብኩት፣ የተረዳሁትና ያስተዋልኩት የፋሲል የኔዓለም አዳር ቀረሽ ውሎ ከዶ/ ብርሃኑ ጋር መሆኑን መሆኑን ነው፡፡ አልጋ የለውም እንጂ የቅንጅት ቢሮ ማደሪያው ሊሆን ምንም አይቀረውም፡፡ ካለ / ብርሃኑ ነጋ ፖለቲከኛ እንደሌለ የሚያምን፣ የዶ/ ብርሃኑ አምልኮ የተጠናወተው ነው፡፡ እንዲህ ዓይነት ሰው ደግሞ የነፃ ልሳን ነፃ ጋዜጠኛ አይሆንም፡፡ ሊሆንም አይችልም፡፡ ከጋዜጠኝነት ሥነ ምግባር ውስጥ አንዱማንኛውንም ሰው ጥብቅ ጓደኛህ አታድርግየሚል ነው፡፡ (ጓደኛ አታድርግ አላልኩም) ጥብቅ ጓደኛ ካደረግከው ከቀረቤታህ የተነሳ ይሉኝታ ማውጣጣት ያለብህን እውነት እንዳታወጣ ያደርግሃል፤ ከጥብቅ ቀረቤታህ የተነሳ እሱን በማመን የተሳሳተ መረጃ ሰለባ ልትሆን ትችላለህ ቀረቤታህ ገደብ ይኑረው የሚለው የጋዜጠኝነት ሥነ-ምግባር፡፡

ጋዜጠኛ የፈለገውን ያህል ዕውቀት ቢኖረው፣ እንደማንኛውም ሰው አላዋቂ መሆን እንዳለበት ነው የሚታወነው፡፡ ተራ-ተርታው ሰው ማወቅ የሚፈልገውንተራጠይቅ ነው የሚለው፡፡ ፋሲል ግን ራሱን የበቃ የነቃ ዐዋቂ አድርጎ ስለሚያምን ለዚህ የሙያ መርህ ቦታ እንደማይሰጥ ነው የማውቀው፡፡ እሱ ከገባው ወይም የገባው ከመሰለው ለሌላው ሰው መረዳት ግድ የለውም፡፡ በዚህ ላይ ፋሲል ሌላ ሰው እንዲሞግተው አይፈልግም፤ የተደፈረ ነው የሚመስለው፡፡ እሱ ካለው በቀር ሌላው ሰው የሚለውን መስማት አይፈልግም፡፡ ከእሱ እምነት ውጪ እምነት የለም፡፡ ብላ ብላ ብላ፡፡ በዚህ እና በዚህ ምክንያት ነው ስለ 7D ሆነ ስለሌሎች ጉዳዮች ያላነሳው የሚል እምነት ነው ያለኝ፡፡ በመግቢያዬ ላይ የጠቀስኩትአስተካክሎ ከማይናገር መልዕክተኛ የማለዳ ወፍ ትሻላለች፤ ምነው ቢሉ መንጋቱን በትክክል ትናገራለችየሚለው የአለቃ ዘነብ አባባል ፍቺው ይኸው ይመስለኛል፡፡ እንደወፏ ያለ ጋዜጠኛና እንደ ወፏ ያለ የሕዝብ ተቋም ያስፈልጋል፡፡ ቲቲሆያ!!

ቲቲሆያን መሆን ያልቻለ ጋዜጠኛ፣ ቲቲሆያን መሆን ያልቻለ ተቋም ሕዝባዊነቱ ያከትማል፡፡ እንደጎረቤቴ እናትትሻልን ቀርቶ ትብስንያስመርጣል፡፡ የሕዝብን ልሳንነት የዘነጋና የሚዘነጋ ይሆናል፡፡

በመጨረሻ

በመጨረሻ ስለ 7D ጥቂት ልበል፡፡ 7D የሚባለው አካል ከዚህ ቀደም ያወጣውን መግለጨ የማየት እድል አግኝቻለሁ፡፡ ስለ 7D የአንባቢያንን አስተያየት እንዲሁ፡፡የወያኔ ተላላኪ ነውከሚለው አንስቶ፣ መሰረታዊ የሃሳብ ልዩነት በባንሳቱ ተገንጥሎ የወጣ ቡድን ነው እስከሚል አስተያየት ድረስ ታዝቤአለሁ፡፡

ግንቦት ስለ ዲሞክራቲክ ኃይል ህዳር 5 ቀን 2005 . ባወጣው ባለ 3ገፅ መግለጫ የተመድ የሰብዓዊ መብት ድንጋጌ አንቀፅ 19 ጠቅሶ ኢሳት (ESAT) በዚህ መሰረታዊ ሕግ ላይ እንደተመሰረተ ያስታውሳል፡፡ በመግለጫው ማጠቃለያምንም እንኳ መስከረም 21 ቀን2005 ዓም የላክንላችሁን መግለጫ ባታወጡትም በሕዝብ ተረድቶ ለሕዝብ አገልግሎት እሰጣለሁ፣ ለየትኛውም ወገን አልወግንም ብሎ ቃል የገባው ኢሳት አሁንም የሚለውን ሆኖ ይገኛል ብለን አናምንም፡፡….ራሳችንን ለኢትዮጵያ ሕዝብ ለማስተዋወቅ እንድንችል በቃለምልልስ ይሁን በሌላ ጣቢያው ይመቸኛል ብሎ በሚያስበው… ” አስተናግዱን ይላል፡፡

ይኼ አባባል ድምፃችን ይሰማ ማለት መሰለኝ፡፡ ድምፅ ሁኑን ማለት መሰለኝ፡፡ እዛው ባሕር ማዶ ጣቢያውድምፅ ትሆናላችሁ ብለን አናምንምከተባለ፣ እንዴትና በምን መልኩ ቲቲሆያን ሊሆን ይችላል የሚል ጥያቄ ያስነሳል፡፡ ይኼ ቀላል ጥያቄ ሊመስል ይችላል፡፡ ማነው የኛ ቲቲሆያ!?