Friday, February 13, 2009

የሞራል ጸጋ የተላበሱ እናት ወ/ሮ ማንአህሎሽ ጎላ ጌታቸዉ ረዳ

ምንጭ ከኮሎኔል አስናቀ እንግዳ (ማነዉ በደለኛ? ከሚለዉ መጽሃፋቸዉ) ክብርት ወይዘሮ መንአሀሎሽ ጎላ ፋሽስታዊ አገዛዝ ተቃዉመዉ ልጆቻቸዉን ትተዉ በመዉጣት ታጋይ ሃይሎችን ሲረዱ ቆይተዉ ትግሉ እየረገበ ሲሄድ በሁኔታቸዉ ግፊት ወደ ሱዳን በመሄድ በስደት ላይ የነበረዉን ተቃዋሚ ሃይል ሲረዱ ቆይተዋል። ወደ አሜሪካ ከመጡ ጀምሮ ለአንድነት ለዲሞክራሲ ለፍትህ የሚታገሉትን ተቃዋሚ ሃይሎችን በመደገፍ ላይ ይገኛሉ።
ወ/ሮ ማንአህሎሽ ጎላ የመለስ ዜናዊን ሚስት አዜብ መስፍንን ያሳደጉ ናቸዉ። መለስ ዜናዊም የጋብቻ ትስስርን በመጠቀም ስልክ እየደወለ ለማግባባትና ደጋፊያቸዉ ለማድረግና በእሳቸዉም አማካይነት የወልቃይት ጠገዴን ሕዝብ ለመያዝ ብዙ ሞክሮ ነበር።ባለቤቱ አዜብም ለማግባባት ከፍተኛ ጥረት አድርጋለች።ስምን መልአክ ያወጣዋልና አጅሪት ክብርት ወይዘሮ ማናህሎሽ ለነሱ ከንቱ ጥረት አልተበገሩላቸዉም። እሳቸዉ በሃጢአት የሚገኝ ምቾትና ጥቅም ይበልጥብኛል ብለዉ ያልተታለሉ የከሃዲዎችን የሙታን መንፈስ የተጸየፉ፤የነቁ አገር ወዳድ ለመሆናቸዉ የሞራል ጸጋን የተላበሱ ናቸዉ። ድንቁርና መደብ በሰራበት በወያኔ የአመራር ቡድን በሐረርጌና በአርሲ በድንቁርና ያልተደረገ የግፍ ዓይነት የለም። በበደኖ በገደል የተወረወሩት በገለምሦ በመቻራ እየተቆራረጡ በዘር ማጥፋት ዘመቻ ነዉ። በጎንደር ክፍል ክፍለሃገር በወልቃይትና ጠገዴ ከጎንደር ክፍለ ሃገር ተነጥለን ወደ ትግራይ አስተዳደር አንዛወርም በማለታቸዉና ብዙ አዛዉንት እየተለቀሙ ግህን በሚባለዉ የመሬት ዉስጥ አሰቃቂ እስር ቤት እና በመቀሌ እስር-ቤት እወንዲማቅቅ ተደርጓል ከፋኝን አብልታችሗል አጠጥታችሗል በመባል መሬታቸዉን ተቀምተዋል። የሴቶች ክብረ ንጽህና ተደፍሯል።መቸም ደንቆሮዉ ወያኔ በሚያስተዳድረዉ በወልቃይትና ጠገዴ ሕዝብ ላይ ያልፈጸመዉ ግፍ የለም። በደብረ ታቦር ሕዝብ ላይ ደንቆሮዉ ወያኔ የተደራረበ ግፍ ፈጽሞበታል። ከደርግ ጋር በማበር ወግታችሁኛል በሚል በቂም በቀል የሚገባዉን መብቱን ሁሉ ከልክሎታል። በተለይም የደብረ ታቦርን ከተማ እንዳይለማ አድርጎ ጨርሶ ለማጥፋት እየጣረ ነዉ። አንድን ግለሰብ ጀኔራል ሃይሌን ደግፋችሗል በማለት ምንም የማያዉቁትን አርሶ አደሮች እየሰበሰበ እረሽኗል።ልዩ ልዩ ስቃይም ፈጽሞባቸዋል። ደብረታቦር አዉራጃም ሆነ ከተማዋ መሰረታዊ የልማት አዉታር ሊዘረጋባቸዉ ቀርቶ ያሏትንም አጥታለች። በአዲሰ አባባ ከተማ የተረሸኑት ምሁራን ተማሪዎችና የፋብሪካ ሰራተኞች የወያኔ የድንቁርና ሰላባ የሆኑት እጅግ ብዙ ናቸዉ።ከዚህም ሌላ የኤርትራንም ሆነ የትግራይ የመገንጠል ቅስቀሳና ማኒፌስቶ የተቃወሙ የትግራይ አዛዉንቶች ከያሉበት እየለቀሙ የረሸኗቸዉን ታሪክ ነገ ፈልፍሎ ያወጣዋል። ወያኔ በትግራይ ዉስጥ ታሪክ የሚያዉቁትን አዛዉንቶች ሲያመቸዉ በግልጽ ሳያመቸዉ በስዉር ስለ አጠፋቸዉ በአንድ ወቅት ሽበት ያለዉ ትልቅ ሰዉ በትግራይ አልነበረም። በደቡብ ኢትዮጵያ ያሉትን ብሔረሰቦችን ተቃዋሚየን ትደግፋላችሁ እየተባሉ ያለ ፍርድ ተገድለዉ የመሬት ማዳበሪያ የሆኑ አያሌ ናቸዉ። በሽፍታዉ ወያኔ የጋምቤላ ሕዝብ ነገዶችን ኑየርና አኝዋክን እርስ በርሳቸዉ እያጋጩ የብዙ ሰላማዊ ሰዎች ሕይወት እነዲጠፋ አድርጓል።ወ ያኔ የጥወፋት ሠራዊቱን ወደ ጋምቤላ ልኮ በግፍ በመጨፍጨፍ ሕይወታቸዉን ለማዳን ጋምቤላዎችን በመጨፍጨፍ ሕይወታቸዉን ለማዳን ጋምቤላዎች ወደ ሱዳን ተሰድደዉ በረሃብ እና በበሽታ በመሰቃየት ላይ ናቸዉ። በጠቅላለዉ በኢትዮጵያ ብሔረሰቦችና ነገዶች ላይ የፈጸሙት ልዩ ልዩ ግፍ ተዘርዝሮ የሚያልቅ አይደለም። የአእምሮ ቀዉስ ያለባቸዉ በሽተኞች ብሎ ማለፍ ይሻላል። በኦነግ ምክንያት የተረሸኑትም ቤቱ ይቁጠረዉ። በመለስ ዜናዊና ቡድኑ ጤናቸዉ ተመርምሮ ጤናማ መሆናቸዉ በባለ ሞያ ሓኪሞች (ሳይክያትሪስቶች) ከተረጋገጠ በአገር ክሕደትና ሕዝብን እርስ በርሱ በማጨፋጨፋቸዉና በሌሎች ወንጀሎች ተከሰዉ ሊፈረድባቸዉ ይገባል።//-// ኢትዮጵያ ለዘላም በነጻነቷና በምሉእ ሉአላዊነቷ ለዘላም ትኑር! ሕዝብን እና አገርን የደፈሩ እና የበደሉ ለፍርድ ኢቅረቡ! ጌታቸዉ ረዳ የካቲት 2000 ዓ/ም የትዮጵያ ሰማይ ዌብሎግ አዘጋጅ http://www.ethiopiansemay.blogspot.com/ getachre@aol.com