ታምራት ነገራን የዘለፉ You Tube ላይ የተገጠገጡ
ሻዕቢያዊ ቋንቁኛ የሚናገሩ ኢትዮጵያውያን !
ጌታቸው ረዳ (Ethio Semay)
01/06/2020
ከኦሮሞ ነገድ የተወለደው ኢትዮጵያዊው አርበኛችን
የአዲስ ነገር ጋዘጣ ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ታምራት ነገራ ሰሞኑን ኤርትራን አስመልክቶ የሰጠው ‘አንጀት አርስ’ አስተያየት ኤርትራውያኖችን
እሳት ውስጥ እንደተጠበሰ ሥጋ “አንጨርጭሯቸዋል”። ስለሆነም ደስ አሰኝቶኛል። ኤርትራውያኖቹን ብቻ ሳይሆን ከአፍንጫቸው ሥር ተነጥፎ የተንጣለለው
የታሪክ እውነታ ማየት የተሳናቸው የዩቱብ “ካፕግራስ” ልክፍት ስብስቦች ኢትዮጵያውያንም ሳይቀሩ ኤርትራኖችን ወግነው ይህንን የቁርጥ
ቀን ልሳናችን ኤትዮጵያዊው ታምራት ነገራን ባልተገረዘ ምላሳቸው ሲጨሁና ሲዘልፉት ሰምቼ ይህነን ትችት ለመጻፍ አነሳስቶኛል።
አንዳንዶቹ የቁጭቱ ምሬት ግፊት በስነ ኣእምሮ ዳሰሳ ከማየት ይልቅ የቃላት ስንጠቃ ገብተው የተቹት የማውቃቸው የኔ ሰዎችም አሉ። ትችቴ እነሱን አይመለከትም። እኔ የምተቸው
ኢትዮጵያውያን ሆነው የራሳቸውን የታሪክ ሃሁ ያላነበቡ ሕክምና ሊደረግላቸው
የሚገባ በዩ ቱብ Capgras syndrome እና በ FOMO syndrome”
የተለከፉ በሽተኞች በባሕረነጋሽ ፖለቲካዊ ክርክር አንድም ነጥብ መመለስ እንደማይችሉ ከሚዘላብዱት የስድብ ውርጅብኝ አልፈው እርግጠኛ
የታሪክ ዕውቀትና ግንዛቤ የላቸውም።
ታምራት ያደረበት “አገራዊ ቁጭት” የምሬቱ ርቀት ያልገባቸው ‘ሎሌዎች’ ኤርትራኖቹ መመለስ ሲገባቸው “ነርቫችን ተነካ
ብለው” በታምራት ላይ ዘለፋ ማውረዳቸው የበሽታቸው ከባድነት ያየንበት
አጋጣሚ ነው።
አንዳንዶቹ ከጥቂት አመታት በፊት የወያኔ አርማና ልብስ ለብሰው አብረው ሲጨፍሩ የታዘብናቸው ያህል ዛሬ ደግሞ ሻዕቢያን ወክለው በኢትዮጵያዊው ታምራት ነገራ ሰብኣዊ ክብር ላይ አረፋቸው
ሲደፍቁ ማየት “ልክፍቶቹ” የተጓዙበት የሎሌነታቸው ርቀት የሚገርም ነው። ሎሌ ሎሌውን በመተካካት የሚጓዙበት የዕብዶች ዓለም ማየት
የጊዜው እንግዳነት ነጋሪ ነው።
ለነዚህ “ዩ ቱብ ልክፍቶች” የሚስማማ አንድ የትግርኛ ምሳሌ ልስጣችሁና ለኤርትራኖች እና ለወያኔዎች እንዲሁም ለነዚህ
አዳዲስ ሎሌዎች የታረክ ክርክርና ጥያቄ በማንሳት በክፍል ሁለት ስለ ኤርትራ ጉዳይ ነገ ይለጠፋል ጠብቁኝ። እስከዚያው
ድረስ እነዚህን ሎሌዎች የሚስማማ አንድ የትግርኛ ምሳሌ ልጥቀስና
ነገ እንገናኝ። እንዲህ ይላል፡ (አዲኣ ገዲፋስ ሓትናኣ ትናፍቕ) “እናትዋን ትታ አክስትዋን ትናፍቃለች”።
አማራዎችም እንዲህ ይላሉ፤ ግጥሙ እንዲህ ይላል፤-
ከምበሳው መኝታ ጊደር ተኝታበት
እሙም ቢልባት እሙም አለችበት
እንዲህ ካለው ጊዜ እኛም ደረስንበት
አመሰግናለሁ ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ)