Sunday, March 30, 2008

The Heroes We BetrayedThe Heroes We Betrayed

የከዳናቸዉ ጀግኖች!

(በጌታቸዉ ረዳ)


ብ/ጄኔራል ዉበቱ ጸጋዬ በአፍአቤት ግንባር የናደዉ ዕዝ ዋና አዛዥ። ዛሬ በሕይወት ከሚገኙ ጥቂት ጀግኖች።

“እኛ ሌላ ዓለም አናዉቅም። ኢትዮጵያ ብቻ ነዉ የምናዉቀዉ”። በሚለዉ በአንድ በልመና የሚኖር የጀግና ወታደር እሮሮ ኢትዮጵያዊ ሰላመታየ ይድረሳችሁ። የዛሬዉ ቆይታችን <ወያነ ትግራይ> ብቻ ሳይሆን “እኛም ጭምር” ከከዳናቸዉ <ጀግኖቻችን> ጋር ይሆናል።

ይህ ዓመድ አንብበዉ ሲጨርሱ አብሮ የቀረበ ወደቀኝዎ በኩል በኦዲዮ ቪድዮ ከፍል ጋር አብሮ የቀረበዉን የአረብና የምዕራብ ቄሳሮች ቅጥረኛ የሆነው “ሻዕቢያ ” የቀረጸዉ የምጽዋዉ <አዉደዮ-ቪድዮ> ጦርነት ይመለከቱ።

የሻለቃ ዳዊት ወልደጊዮርጊስ <ክህደት በደም መሬት> መጽሐፍ ያነበበ ልቦና ያለዉ ሰዉ፤ የከዳናቸዉ ጀግኖቻችንን ምንኛ እነደረሳናቸዉ ከማስታወስ አልፎ፤ የከዳተኝነታችን እርቃን መጠኑ ለህሊና ይቆጠቁጣል። ያላንዳች ሰቀቀን ተዝናንተን እየተጓዝንባቸው ያሉት ሁሉ “የክሀደት” ስም በተሰጣቸዉ የጎዳና አደባበዮች ላይ በመሆኑ ኢትዮጵያዊነታችን ጥለናል።በተዘዋዋሪም በቀጥታም በማወቅም ባለማወቅ ስብስቦቻችን ሁሉ ለካሃዲዎችና ለቅጠረኞች አመቺ በመሆናችን የታሪክ ዝሙት እየፈጸምን ነው።

ወግ ሆኖብን ትልልቁን ዘርጥጦ መዝለፍ፤ በየጦር ሜዳዉ ስለኛ ያለፉትን አፈር ሰናለበሳቸዉ ተሎ እየረሳን፤ ጀግኖቻችንን ለበሉና ኣዳዲስ የክህደት ጎዳናዎች ለሚቀይሱሉንን የታሪክ ትሎች ጉንጉን አበባዎችን እየስታቀፍን ሰንደቅአላማዎቻቸዉን እያዉለበለብን ፤የክደት ወረርሽኙ ይሄዉ በቁመና ሲቀጥፈን ይታያል ።

ኢትዮጵያን ለማስከበር በመተማ፤ በዶጋሊ፤ በሳሓጢ፤ በጉንደት በዓድዋና በተቀሩት ጦር ሜዳዎች
በመሰለፍ በግንባር ጦር አዝማችነት የተሰለፉትን ነገስታቶችና ራሶች በክብር ስናስታዉስ ፤ በቅረብ በትዉልዳችን ዘመን ያነን ኮቴ እና አርማ ተከትለዉ
በኤረትራና በትግራይ በረሃዎች ከታሪክ ድንኮች ጋር የወደብ ባሕሮቻችንን ላለማስነጠቅ በየሸንተረሩ ለወደቁት ወታደራዊ ጀግኖቻችን ግን ለአክብሮታቸዉና ገድሎቻቸዉን በሚመለከት የሚዘግብ ሲመፖዝየም ማዘጋጀት ይቅርና የት እንደደረሰና ምንስ እየሆኑ እንዳለ ባለማሰባችን ተከድቷል!

ይህ ዝገጅት ለማቅረብ የገፋፋኝ ሁኔታ ልግለጽ። ብረቅየዉ የኢትዮጵያ ልጅ የምድር ጦር ድመጻዊዉ ታምራት ሞላ በጸና መታመሙንና ፤ለሱም እርዳታ ለማሰባሰብ በጎ አሳቢ ኢትዮጵያዉያን መረባረባችዉን ስሰማ አደነቁሁዋቸዉ።ታድያ በማሰተባበሩ ግዳጅ የተሰማሩ በጎ አድራጊ ኢትዮጵያዊያኖቹ ለህዘቡ ስያስተዋዉቁ የተጠቀሙበት ቃል <ለናት አገሩ ሲል በየጦር ሜዳዉ ተሰልፎ ግዳጁን በሙያዉ የተወጣ…….> የሚል ሀረግ ያሰምሩበታል። ነገሩ ሀቅ ቢሆንም፤ ታመራት ሞላ ሁላችን የምናከበረዉ ዉድ ኢትዮጵያዊ ነዉና መርዳት ግዴታችን ነዉ። ሆኖም ብዙ፤ በበዙ ሺሕ ሚለዮን የጦር ሜዳ ጀግና ከነቤተሰቡ በረነዳ ላይ ወድቆ ደረቱ ላይ ያሸበረቀዉ መዳልያ ከደረቱ ወርዶ ወለል አፈሩ ላይ ተነጥፎ መለመኛ ሲአደርገዉ ያየን ስንቶቻችን ደረስንለት? ስንቱስ በየባዕድ አገር የራቢጣ ትምከህተኛ መጫወቻ ሆኖ “የወገን ያለህ ድረስ” ሲለን “ስንቶቻችን” በግነን በቁጭት በርብርቦሽ ደረስንለት? (በዚህ አጋጣሚ የላቀ አከብሮትና ምሰጋና እንግሊዝ አገር ለሚኖሩ ለኮማነደር አሰፋ ሰይፉና ዋሺንግተን አሜሪካ ለሚኖር የኢትዮጵያ ራዲዮ አዘጋጅ አቶ ምርጫዉ ስንሻዉ ይድረሳቸዉ) ፤ ስንቱ የጦር ጄኔራል፤ ስንቱ የጦር ሜዳ ወታደር ታምሞ ተሰቃይቶ ለህዝብ ድረሱልኝ ሲሰማ ተረባረብንለት? <መታወቅ> (እዉቅ፤ዝነኛ..) ማለት ምን ማለት ነዉ? ለአገር ደህንነት ሲል የሞተዉ እግሩ ሽባ ሆኖ በረንዳ ላይ ተጋድሞ ለማኝ የሆነዉን ጀግና ዝነኛነቱ ምን ያህል ለህዝቡ ደጋግመን አስተዋዉቀናል? መሁሩ ምን እየሰራለት ነዉ? ከኢትዮጰያ ገዳይ፤ከወደብ ዘጊዉ ከወያኔ ጋር “ኩት ኩት” እያሉ የአስገነጣይና የዘረኝነት መጻህፍት ሲያሳትሙ ሲፈጽሙና ሲአስፈጽሙ የነበሩት ዛሬ በተቃዋሚ ስም ጀግኖች እየተባሉ በዉጭ በያአዉሮፕላን ማረፍያ አደባባይ “እልልታ፤ ወሮ ወሸባየ” እየተዘፈንላቸዉ ስንመለከት፤ የሕሊና ቀጫጫነታችን ማስረጃ አይመስላችሁም ? ።

የጀግንነት ሙያ የተወጡ ጀገኖች መድረኩን ለነሱ ልልቀቅና ምንኛ እንደካድናቸዉ ካንደበታቸዉ እነሆ። ፍርዱ ለህሊናችሁ ልተዉ።

ክህደት በደም መሬት ከሚለዉ መጸሃፍ ከሻለቃ ዳዊት ወልደጊዮርጊስ የተገኘ የወታደሮች እሮሮና ቅሬታ።በሚከነክን፤ አንጀት በሚበላ ንግግር በአንድ ጀግና ኤርትራዊ የኢትዮጵያ ወታደር ልጀምር።

ሻለቃ ዳዊት እንዲህ ይላሉ “ናይሮቢ ያገኘሁት የሐምሳ አለቃ አሰጋኸኝ ምህረተአብ በግንባር ላይ በነበረበት ጊዜ ስለተከፈለዉ መስዋዕትነት እነዲህ በማለት ሁኔታዉን ይገልጠዋል።

< እኔና ብዙ ጓደኞቼ የተመለመልነዉ ከኤርትራ ነዉ። 11 ዓመት በሠራዊቱ ዉሰጥ ከተራ ወታደርነት ጀምሮ አገልግአለሁ። ወደ ወንበዴዎች ለመቀላቀል ብዙ ግፊት ቢኖርብኝም እሱን ሁሉ ተቋቁሜ ነዉ እስከመጨረሻዉ የተዋጋሁት። ለሀገር ፍቅር ስንል ነዉ። እስከመጨረሻዉ ለመዋጋት ፈልገን መሪዎቹ ሸሽተዉ ወደ ዓረብ አገር ሄዱ። እኛም ተበተንን። ሻዕቢያም ገባ። እጃችንን ለሻዕቢያ ከመስጠት ብለን በዙዎቻችን ብዙ ወራት በረሃ ተንከራተን እዚሁ ኬንያ ገብተን ስደተኝነት ጠየቅን። ከኔ ጋር የተመለመልን 28 ነብርን፡ ዛሬ ሁሉም በዉጊያ ሞተዋል። እኔ ከወታደርነት እስከ አመሳ አለቅነት፤ ከጓድ አዛዥነት እስከ ሻምበል አዛዥነት ደርሼም ነበርኩ። ሻምበሉን ስረከበዉ 123 ወታደሮች ነበሩ። 80 በመቶ አለቁ። ተተኪ ከሌሎች ቢመጡልኝም በዚያዉ መጠን አለቁ። ዉጊያዉን ስናካሂድ ሰ6 ዓመት ቤተሰቦቼን አላየሁም። ከተማም ገብቼ አላዉቅም። አሰብ የሞቱት ጓደኞቼ ይታወሱኛል። አዲስ አበባም ሄጄ እንደሌሎች ወታደሮች ለማኝ ሆኘ መዋረድ አልፈልግም። እዚሁ ሰዉ በማያዉቀኝ ሀገር ሆኜ በትዝታና በቁጭት ጊዜየን እገፋለሁ።>>

እዛዉ ያገኘሁት የአስር አለቃ አስማማዉ በላይነህ ደግሞ፤

<<እኔ ለአጭር ጊዜ ነዉ ሠራዊቱ ዉሰጥ ያገለገልኩት። በዚያ አጭር ጊዜ ብዙ ችግር አይቻለሁ።ኤላበርዕድ ላይ በተደረገዉ ለሰሦስት ቀን ዉጊያ ብቻ ከዉጊያዉ በሗላ 11 ሺ የወገን ወታደር ማለቁን ገምተናል። በሻዕቢያ በኩል ከዚህ የበለጠ ነበር የሞተዉና የቆሰለዉ። እንዴት አድርጌ ከዚያ መዓት ተርፌ እዚህ እነደደረስሁ አላዉቅም። ዘመዶቼ ጎጃም ናቸዉ። አንድ ቀን ለመመለስ አስባለሁ፤ ቁጣዉ ሲበርድልኝ>> ብሎኛል።

ኡጋንዳ ያገኘሁት የሐምሳ አለቃ አለምነህ የሚባል ወታደር በተለያዩ የሰሜን ዉጊያዎች ላይ ተሳትፏል። ሁኔታዉ እንዲህ ይገልጠዋል።

<< የወገን ሬሳ ለማንሳት ፈጽሞ አይቻልም። ጊዜም የለም። አቅምም የለም። ለመቅበር እነኴን ጊዜ የለም። የቆሰሉትን ጥለን ነዉ ብዙ ጊዜ የሄድነዉ። ከበላይ የሚመጣዉ ትእዛዝ “ጊዜ አታጥፉ፤ ቁስለኛ አታንሱ” ስለሆነ፤ በሕይወት ሲኖሩ የሚችሉ ስንት ወዳጆቼ ሜዳ ላይ እየተሰቃዩ ሞተወል። አንዳንድ ጊዜ ጨርሰኝ ሲል ጨክነን ያደረግንበት ጊዜ አለ። ብዙ ጊዜ ወይ እራሳቸዉን ይጨርሳሉ ወይንም እዚያዉ የሻዕቢያ መሳቂያ ሆነዉ ይሞታሉ። አሥመራ ዙርያ፤ ከረን አካባቢ ባሬንቱና ተሰነይ አካባቢ በተሳተፍንባቸዉ ዉጊያዎች ረግጬ ያለፍኩት የወንድሞቼ ሬሳ ቁጥር ስፍር የለዉም። አሁን ሳስታዉሰዉ እንቅልፍ ይነሳኛል። ጀግኖች ነበሩ። ለሀገራቸዉ ተወጉ። ተሰዉ። የተረፉት በየበረሃዉ ሲነከራተቱ፤ ሲቆስሉ፤ ሲራቡ ኖረዉ ዛሬ ሲለምኑ ማየትም፤ ስማቸዉን ማንሳትም አልፈልግም። በጣም እጅግ ያሳዝናል። እናት ኢትዮጵያ መቼ ነዉ ዉለታቸዉን የምትከፍላቸዉ?>>

አንድ በአዲስ አበባ የሚኖር ወዳጄ አንድ የቀድሞ ወታደር አገናኘኝ። “የሐምሳ አለቃ በላይ አንጋጋዉ ነኝ” አለ። እዉነተኛ ስሙ እንዲታወቅ አልፈለገም። እነደነገረኝ አዲስ አበባ በየሆቴሎቹ በራፍ ላይ ቡትቶዉን ለብሶ እየተዘዋወረ ይለምናል። ቤት የለዉም። እንዲህ ሲል አጫወተኝ።

<< በዘጠኝ ዓመት በኤርትራ በተለያዩ ቦታዎች አገልግያለሁ። ከአዲስ አበባ ነበር የተመለመልኩት። አባትና እናት የለኝም። ጥቂት ዘመዶች ነበሩኝ። ሊያዩኝም አልፈልግም። እነሱነም ችግር ላይ ናቸዉ። ሁለት ጊዜ ቆስያለሁ።ከረንና ባሬንቱ አካባቢ ቁጥር ስፍር የሌላዉ ዉጊያ ተሳትፌያለሁ። ስንት ጓደኞቼ ሲሞቱ፤ አካላቸዉ ሲቆረጥ <ኢትዮጵያ ወይንም ሞት!> እያሉ እየፎከሩ በጥይት ዝናም ሲረግፉ አይቻለሁ። እኛ ዓለምን አናዉቅም። ኢትዮጵያ ብቻ ነበር የምናዉቀዉ። ከተመለመልኩበት ጊዜ ጀምሮ ዘጠኝ ዓመት ሙሉ ቤተሰቦቼን አላየሁም፡ ጡረታም የለኝም አሥመራ ስትያዝ ብዙ ተንገላታን። እንደዉሻ ተባረን እዚሁ ዘረገፉን። ለሀገሬ መስሎኝ ነበር የተዋጋሁት። ሀገሬም ከዳቺኝ። መንግስትም አዋረደን። የዚያን ጊዜ አንደ ጓደኞቼ ብሞት ኖሮ እላለሁኝ። የሞት ሞት ነዉ አሁን የምኖረዉ።>

መደምደምያ
የኢትዮጵያ ምሁራን በቁም የሞሞታቸዉን ዓይነተኛዉ ማስረጃዉ ይሄ ነዉ። በሕየወት እያለ የነቀዘ ሙሁር ምልክቱ፤ ጀግኖቻችን ለለማኝነት ሲዳረጉ ለነጻ አዉጪነት ተዋጊ እነኳን አለተጠቀሙባቸዉም። ከዚህ ወዲያ ኢትዮጵያ ከባንዳዎች ነጻ አወጥተዉ እኛም ወደ አገራችን ይመልሱናል ብለን በምሁራን ተስፋ የጣልን ሁሉ እርማችን እናዉጣ። የምናየዉ የፖለቲካ ሥራ ልግጫ (ጨዋታ) ነዉ። ዝና ፍለጋ ነዉ።ጀግኖቻችንን አስረሱን፤ እኛኑም እዚሁ በባዕድ አገር አስረጁን ! አምላክ ብቻ ቀረን እሱ በጥበቡ ነጻ ያዉጣን!

እናንት የተከዳችሁ ለእናት አገራቸዉ ብላችሁ በየዱሩ ያራዊቶች መጫወቻ ሆናችሁ ለቀራችሁ፤አስታዋሽ ላጣችሁ፤ በየበረንዳዉና በስደት የምትንከራተቱት ሃዉልት ቀርቶ አገር ላጣችሁት ለተከዳችሁ ጀግኖች የኢትዮጵያ ወታደሮች ያኢትዮጵያ አምላክ ከናንተዉ ጋር ዪሁን!
ጌታቸዉ ረዳ
ሳን ሆዘ ካሊፎርኒያ
(መጋቢት 2000 ዓም)
(March 30, 2008)

The Heroes We Betrayed

The Heroes we Betrayed የከዳናቸዉ ጀግኖች! (በጌታቸዉ ረዳ)
Photo ብ/ጄኔራል ዉበቱ ጸጋዬ በአፍአቤት ግንባር የናደዉ ዕዝ ዋና አዛዥ። ዛሬ በሕይወት ከሚገኙ ጥቂት ጀግኖች። “እኛ ሌላ ዓለም አናዉቅም። ኢትዮጵያ ብቻ ነዉ የምናዉቀዉ”። በሚለዉ በአንድ በልመና የሚኖር የጀግና ወታደር እሮሮ ኢትዮጵያዊ ሰላመታየ ይድረሳችሁ። የዛሬዉ ቆይታችን <ወያነ ትግራይ> ብቻ ሳይሆን “እኛም ጭምር” ከከዳናቸዉ <ጀግኖቻችን> ጋር ይሆናል። ይህ ዓመድ አንብበዉ ሲጨርሱ አብሮ የቀረበ ወደቀኝዎ በኩል በኦዲዮ ቪድዮ ከፍል ጋር አብሮ የቀረበዉን የአረብና የምዕራብ ቄሳሮች ቅጥረኛ የሆነው “ሻዕቢያ ” የቀረጸዉ የምጽዋዉ <አዉደዮ-ቪድዮ> ጦርነት ይመለከቱ። የሻለቃ ዳዊት ወልደጊዮርጊስ <ክህደት በደም መሬት> መጽሐፍ ያነበበ ልቦና ያለዉ ሰዉ፤ የከዳናቸዉ ጀግኖቻችንን ምንኛ እነደረሳናቸዉ ከማስታወስ አልፎ፤ የከዳተኝነታችን እርቃን መጠኑ ለህሊና ይቆጠቁጣል። ያላንዳች ሰቀቀን ተዝናንተን እየተጓዝንባቸው ያሉት ሁሉ “የክሀደት” ስም በተሰጣቸዉ የጎዳና አደባበዮች ላይ በመሆኑ ኢትዮጵያዊነታችን ጥለናል።በተዘዋዋሪም በቀጥታም በማወቅም ባለማወቅ ስብስቦቻችን ሁሉ ለካሃዲዎችና ለቅጠረኞች አመቺ በመሆናችን የታሪክ ዝሙት እየፈጸምን ነው። ወግ ሆኖብን ትልልቁን ዘርጥጦ መዝለፍ፤ በየጦር ሜዳዉ ስለኛ ያለፉትን አፈር ሰናለበሳቸዉ ተሎ እየረሳን፤ ጀግኖቻችንን ለበሉና ኣዳዲስ የክህደት ጎዳናዎች ለሚቀይሱሉንን የታሪክ ትሎች ጉንጉን አበባዎችን እየስታቀፍን ሰንደቅአላማዎቻቸዉን እያዉለበለብን ፤የክደት ወረርሽኙ ይሄዉ በቁመና ሲቀጥፈን ይታያል ። ኢትዮጵያን ለማስከበር በመተማ፤ በዶጋሊ፤ በሳሓጢ፤ በጉንደት በዓድዋና በተቀሩት ጦር ሜዳዎች በመሰለፍ በግንባር ጦር አዝማችነት የተሰለፉትን ነገስታቶችና ራሶች በክብር ስናስታዉስ ፤ በቅረብ በትዉልዳችን ዘመን ያነን ኮቴ እና አርማ ተከትለዉ በኤረትራና በትግራይ በረሃዎች ከታሪክ ድንኮች ጋር የወደብ ባሕሮቻችንን ላለማስነጠቅ በየሸንተረሩ ለወደቁት ወታደራዊ ጀግኖቻችን ግን ለአክብሮታቸዉና ገድሎቻቸዉን በሚመለከት የሚዘግብ ሲመፖዝየም ማዘጋጀት ይቅርና የት እንደደረሰና ምንስ እየሆኑ እንዳለ ባለማሰባችን ተከድቷል! ይህ ዝገጅት ለማቅረብ የገፋፋኝ ሁኔታ ልግለጽ። ብረቅየዉ የኢትዮጵያ ልጅ የምድር ጦር ድመጻዊዉ ታምራት ሞላ በጸና መታመሙንና ፤ለሱም እርዳታ ለማሰባሰብ በጎ አሳቢ ኢትዮጵያዉያን መረባረባችዉን ስሰማ አደነቁሁዋቸዉ።ታድያ በማሰተባበሩ ግዳጅ የተሰማሩ በጎ አድራጊ ኢትዮጵያዊያኖቹ ለህዘቡ ስያስተዋዉቁ የተጠቀሙበት ቃል <ለናት አገሩ ሲል በየጦር ሜዳዉ ተሰልፎ ግዳጁን በሙያዉ የተወጣ…….> የሚል ሀረግ ያሰምሩበታል። ነገሩ ሀቅ ቢሆንም፤ ታመራት ሞላ ሁላችን የምናከበረዉ ዉድ ኢትዮጵያዊ ነዉና መርዳት ግዴታችን ነዉ። ሆኖም ብዙ፤ በበዙ ሺሕ ሚለዮን የጦር ሜዳ ጀግና ከነቤተሰቡ በረነዳ ላይ ወድቆ ደረቱ ላይ ያሸበረቀዉ መዳልያ ከደረቱ ወርዶ ወለል አፈሩ ላይ ተነጥፎ መለመኛ ሲአደርገዉ ያየን ስንቶቻችን ደረስንለት? ስንቱስ በየባዕድ አገር የራቢጣ ትምከህተኛ መጫወቻ ሆኖ “የወገን ያለህ ድረስ” ሲለን “ስንቶቻችን” በግነን በቁጭት በርብርቦሽ ደረስንለት? (በዚህ አጋጣሚ የላቀ አከብሮትና ምሰጋና እንግሊዝ አገር ለሚኖሩ ለኮማነደር አሰፋ ሰይፉና ዋሺንግተን አሜሪካ ለሚኖር የኢትዮጵያ ራዲዮ አዘጋጅ አቶ ምርጫዉ ስንሻዉ ይድረሳቸዉ) ፤ ስንቱ የጦር ጄኔራል፤ ስንቱ የጦር ሜዳ ወታደር ታምሞ ተሰቃይቶ ለህዝብ ድረሱልኝ ሲሰማ ተረባረብንለት? <መታወቅ> (እዉቅ፤ዝነኛ..) ማለት ምን ማለት ነዉ? ለአገር ደህንነት ሲል የሞተዉ እግሩ ሽባ ሆኖ በረንዳ ላይ ተጋድሞ ለማኝ የሆነዉን ጀግና ዝነኛነቱ ምን ያህል ለህዝቡ ደጋግመን አስተዋዉቀናል? መሁሩ ምን እየሰራለት ነዉ? ከኢትዮጰያ ገዳይ፤ከወደብ ዘጊዉ ከወያኔ ጋር “ኩት ኩት” እያሉ የአስገነጣይና የዘረኝነት መጻህፍት ሲያሳትሙ ሲፈጽሙና ሲአስፈጽሙ የነበሩት ዛሬ በተቃዋሚ ስም ጀግኖች እየተባሉ በዉጭ በያአዉሮፕላን ማረፍያ አደባባይ “እልልታ፤ ወሮ ወሸባየ” እየተዘፈንላቸዉ ስንመለከት፤ የሕሊና ቀጫጫነታችን ማስረጃ አይመስላችሁም ? ። የጀግንነት ሙያ የተወጡ ጀገኖች መድረኩን ለነሱ ልልቀቅና ምንኛ እንደካድናቸዉ ካንደበታቸዉ እነሆ። ፍርዱ ለህሊናችሁ ልተዉ። ክህደት በደም መሬት ከሚለዉ መጸሃፍ ከሻለቃ ዳዊት ወልደጊዮርጊስ የተገኘ የወታደሮች እሮሮና ቅሬታ።በሚከነክን፤ አንጀት በሚበላ ንግግር በአንድ ጀግና ኤርትራዊ የኢትዮጵያ ወታደር ልጀምር። ሻለቃ ዳዊት እንዲህ ይላሉ “ናይሮቢ ያገኘሁት የሐምሳ አለቃ አሰጋኸኝ ምህረተአብ በግንባር ላይ በነበረበት ጊዜ ስለተከፈለዉ መስዋዕትነት እነዲህ በማለት ሁኔታዉን ይገልጠዋል። < እኔና ብዙ ጓደኞቼ የተመለመልነዉ ከኤርትራ ነዉ። 11 ዓመት በሠራዊቱ ዉሰጥ ከተራ ወታደርነት ጀምሮ አገልግአለሁ። ወደ ወንበዴዎች ለመቀላቀል ብዙ ግፊት ቢኖርብኝም እሱን ሁሉ ተቋቁሜ ነዉ እስከመጨረሻዉ የተዋጋሁት። ለሀገር ፍቅር ስንል ነዉ። እስከመጨረሻዉ ለመዋጋት ፈልገን መሪዎቹ ሸሽተዉ ወደ ዓረብ አገር ሄዱ። እኛም ተበተንን። ሻዕቢያም ገባ። እጃችንን ለሻዕቢያ ከመስጠት ብለን በዙዎቻችን ብዙ ወራት በረሃ ተንከራተን እዚሁ ኬንያ ገብተን ስደተኝነት ጠየቅን። ከኔ ጋር የተመለመልን 28 ነብርን፡ ዛሬ ሁሉም በዉጊያ ሞተዋል። እኔ ከወታደርነት እስከ አመሳ አለቅነት፤ ከጓድ አዛዥነት እስከ ሻምበል አዛዥነት ደርሼም ነበርኩ። ሻምበሉን ስረከበዉ 123 ወታደሮች ነበሩ። 80 በመቶ አለቁ። ተተኪ ከሌሎች ቢመጡልኝም በዚያዉ መጠን አለቁ። ዉጊያዉን ስናካሂድ ሰ6 ዓመት ቤተሰቦቼን አላየሁም። ከተማም ገብቼ አላዉቅም። አሰብ የሞቱት ጓደኞቼ ይታወሱኛል። አዲስ አበባም ሄጄ እንደሌሎች ወታደሮች ለማኝ ሆኘ መዋረድ አልፈልግም። እዚሁ ሰዉ በማያዉቀኝ ሀገር ሆኜ በትዝታና በቁጭት ጊዜየን እገፋለሁ።>> እዛዉ ያገኘሁት የአስር አለቃ አስማማዉ በላይነህ ደግሞ፤ <<እኔ ለአጭር ጊዜ ነዉ ሠራዊቱ ዉሰጥ ያገለገልኩት። በዚያ አጭር ጊዜ ብዙ ችግር አይቻለሁ።ኤላበርዕድ ላይ በተደረገዉ ለሰሦስት ቀን ዉጊያ ብቻ ከዉጊያዉ በሗላ 11 ሺ የወገን ወታደር ማለቁን ገምተናል። በሻዕቢያ በኩል ከዚህ የበለጠ ነበር የሞተዉና የቆሰለዉ። እንዴት አድርጌ ከዚያ መዓት ተርፌ እዚህ እነደደረስሁ አላዉቅም። ዘመዶቼ ጎጃም ናቸዉ። አንድ ቀን ለመመለስ አስባለሁ፤ ቁጣዉ ሲበርድልኝ>> ብሎኛል። ኡጋንዳ ያገኘሁት የሐምሳ አለቃ አለምነህ የሚባል ወታደር በተለያዩ የሰሜን ዉጊያዎች ላይ ተሳትፏል። ሁኔታዉ እንዲህ ይገልጠዋል። << የወገን ሬሳ ለማንሳት ፈጽሞ አይቻልም። ጊዜም የለም። አቅምም የለም። ለመቅበር እነኴን ጊዜ የለም። የቆሰሉትን ጥለን ነዉ ብዙ ጊዜ የሄድነዉ። ከበላይ የሚመጣዉ ትእዛዝ “ጊዜ አታጥፉ፤ ቁስለኛ አታንሱ” ስለሆነ፤ በሕይወት ሲኖሩ የሚችሉ ስንት ወዳጆቼ ሜዳ ላይ እየተሰቃዩ ሞተወል። አንዳንድ ጊዜ ጨርሰኝ ሲል ጨክነን ያደረግንበት ጊዜ አለ። ብዙ ጊዜ ወይ እራሳቸዉን ይጨርሳሉ ወይንም እዚያዉ የሻዕቢያ መሳቂያ ሆነዉ ይሞታሉ። አሥመራ ዙርያ፤ ከረን አካባቢ ባሬንቱና ተሰነይ አካባቢ በተሳተፍንባቸዉ ዉጊያዎች ረግጬ ያለፍኩት የወንድሞቼ ሬሳ ቁጥር ስፍር የለዉም። አሁን ሳስታዉሰዉ እንቅልፍ ይነሳኛል። ጀግኖች ነበሩ። ለሀገራቸዉ ተወጉ። ተሰዉ። የተረፉት በየበረሃዉ ሲነከራተቱ፤ ሲቆስሉ፤ ሲራቡ ኖረዉ ዛሬ ሲለምኑ ማየትም፤ ስማቸዉን ማንሳትም አልፈልግም። በጣም እጅግ ያሳዝናል። እናት ኢትዮጵያ መቼ ነዉ ዉለታቸዉን የምትከፍላቸዉ?>> አንድ በአዲስ አበባ የሚኖር ወዳጄ አንድ የቀድሞ ወታደር አገናኘኝ። “የሐምሳ አለቃ በላይ አንጋጋዉ ነኝ” አለ። እዉነተኛ ስሙ እንዲታወቅ አልፈለገም። እነደነገረኝ አዲስ አበባ በየሆቴሎቹ በራፍ ላይ ቡትቶዉን ለብሶ እየተዘዋወረ ይለምናል። ቤት የለዉም። እንዲህ ሲል አጫወተኝ። << በዘጠኝ ዓመት በኤርትራ በተለያዩ ቦታዎች አገልግያለሁ። ከአዲስ አበባ ነበር የተመለመልኩት። አባትና እናት የለኝም። ጥቂት ዘመዶች ነበሩኝ። ሊያዩኝም አልፈልግም። እነሱነም ችግር ላይ ናቸዉ። ሁለት ጊዜ ቆስያለሁ።ከረንና ባሬንቱ አካባቢ ቁጥር ስፍር የሌላዉ ዉጊያ ተሳትፌያለሁ። ስንት ጓደኞቼ ሲሞቱ፤ አካላቸዉ ሲቆረጥ <ኢትዮጵያ ወይንም ሞት!> እያሉ እየፎከሩ በጥይት ዝናም ሲረግፉ አይቻለሁ። እኛ ዓለምን አናዉቅም። ኢትዮጵያ ብቻ ነበር የምናዉቀዉ። ከተመለመልኩበት ጊዜ ጀምሮ ዘጠኝ ዓመት ሙሉ ቤተሰቦቼን አላየሁም፡ ጡረታም የለኝም አሥመራ ስትያዝ ብዙ ተንገላታን። እንደዉሻ ተባረን እዚሁ ዘረገፉን። ለሀገሬ መስሎኝ ነበር የተዋጋሁት። ሀገሬም ከዳቺኝ። መንግስትም አዋረደን። የዚያን ጊዜ አንደ ጓደኞቼ ብሞት ኖሮ እላለሁኝ። የሞት ሞት ነዉ አሁን የምኖረዉ መደምደምያ የኢትዮጵያ ምሁራን በቁም የሞሞታቸዉን ዓይነተኛዉ ማስረጃዉ ይሄ ነዉ። በሕየወት እያለ የነቀዘ ሙሁር ምልክቱ፤ ጀግኖቻችን ለለማኝነት ሲዳረጉ ለነጻ አዉጪነት ተዋጊ እነኳን አለተጠቀሙባቸዉም። ከዚህ ወዲያ ኢትዮጵያ ከባንዳዎች ነጻ አወጥተዉ እኛም ወደ አገራችን ይመልሱናል ብለን በምሁራን ተስፋ የጣልን ሁሉ እርማችን እናዉጣ። የምናየዉ የፖለቲካ ሥራ ልግጫ (ጨዋታ) ነዉ። ዝና ፍለጋ ነዉ።ጀግኖቻችንን አስረሱን፤ እኛኑም እዚሁ በባዕድ አገር አስረጁን ! አምላክ ብቻ ቀረን እሱ በጥበቡ ነጻ ያዉጣን! እናንት የተከዳችሁ ለእናት አገራቸዉ ብላችሁ በየዱሩ ያራዊቶች መጫወቻ ሆናችሁ ለቀራችሁ፤አስታዋሽ ላጣችሁ፤ በየበረንዳዉና በስደት የምትንከራተቱት ሃዉልት ቀርቶ አገር ላጣችሁት ለተከዳችሁ ጀግኖች የኢትዮጵያ ወታደሮች ያኢትዮጵያ አምላክ ከናንተዉ ጋር ዪሁን! ጌታቸዉ ረዳ ሳን ሆዘ ካሊፎርኒያ (መጋቢት 2000 ዓም) (March 30, 2008)

The heroes We Betrayed

The Heroes we Betrayed የከዳናቸዉ ጀግኖች! (በጌታቸዉ ረዳ) ብ/ጄኔራል ዉበቱ ጸጋዬ በአፍአቤት ግንባር የናደዉ ዕዝ ዋና አዛዥ። ዛሬ በሕይወት ከሚገኙ ጥቂት ጀግኖች። “እኛ ሌላ ዓለም አናዉቅም። ኢትዮጵያ ብቻ ነዉ የምናዉቀዉ”። በሚለዉ በአንድ በልመና የሚኖር የጀግና ወታደር እሮሮ ኢትዮጵያዊ ሰላመታየ ይድረሳችሁ። የዛሬዉ ቆይታችን <ወያነ ትግራይ> ብቻ ሳይሆን “እኛም ጭምር” ከከዳናቸዉ <ጀግኖቻችን> ጋር ይሆናል። ይህ ዓመድ አንብበዉ ሲጨርሱ አብሮ የቀረበ ወደቀኝዎ በኩል በኦዲዮ ቪድዮ ከፍል ጋር አብሮ የቀረበዉን የአረብና የምዕራብ ቄሳሮች ቅጥረኛ የሆነው “ሻዕቢያ ” የቀረጸዉ የምጽዋዉ <አዉደዮ-ቪድዮ> ጦርነት ይመለከቱ። የሻለቃ ዳዊት ወልደጊዮርጊስ <ክህደት በደም መሬት> መጽሐፍ ያነበበ ልቦና ያለዉ ሰዉ፤ የከዳናቸዉ ጀግኖቻችንን ምንኛ እነደረሳናቸዉ ከማስታወስ አልፎ፤ የከዳተኝነታችን እርቃን መጠኑ ለህሊና ይቆጠቁጣል። ያላንዳች ሰቀቀን ተዝናንተን እየተጓዝንባቸው ያሉት ሁሉ “የክሀደት” ስም በተሰጣቸዉ የጎዳና አደባበዮች ላይ በመሆኑ ኢትዮጵያዊነታችን ጥለናል።በተዘዋዋሪም በቀጥታም በማወቅም ባለማወቅ ስብስቦቻችን ሁሉ ለካሃዲዎችና ለቅጠረኞች አመቺ በመሆናችን የታሪክ ዝሙት እየፈጸምን ነው። ወግ ሆኖብን ትልልቁን ዘርጥጦ መዝለፍ፤ በየጦር ሜዳዉ ስለኛ ያለፉትን አፈር ሰናለበሳቸዉ ተሎ እየረሳን፤ ጀግኖቻችንን ለበሉና ኣዳዲስ የክህደት ጎዳናዎች ለሚቀይሱሉንን የታሪክ ትሎች ጉንጉን አበባዎችን እየስታቀፍን ሰንደቅአላማዎቻቸዉን እያዉለበለብን ፤የክደት ወረርሽኙ ይሄዉ በቁመና ሲቀጥፈን ይታያል ። ኢትዮጵያን ለማስከበር በመተማ፤ በዶጋሊ፤ በሳሓጢ፤ በጉንደት በዓድዋና በተቀሩት ጦር ሜዳዎች በመሰለፍ በግንባር ጦር አዝማችነት የተሰለፉትን ነገስታቶችና ራሶች በክብር ስናስታዉስ ፤ በቅረብ በትዉልዳችን ዘመን ያነን ኮቴ እና አርማ ተከትለዉ በኤረትራና በትግራይ በረሃዎች ከታሪክ ድንኮች ጋር የወደብ ባሕሮቻችንን ላለማስነጠቅ በየሸንተረሩ ለወደቁት ወታደራዊ ጀግኖቻችን ግን ለአክብሮታቸዉና ገድሎቻቸዉን በሚመለከት የሚዘግብ ሲመፖዝየም ማዘጋጀት ይቅርና የት እንደደረሰና ምንስ እየሆኑ እንዳለ ባለማሰባችን ተከድቷል! ይህ ዝገጅት ለማቅረብ የገፋፋኝ ሁኔታ ልግለጽ። ብረቅየዉ የኢትዮጵያ ልጅ የምድር ጦር ድመጻዊዉ ታምራት ሞላ በጸና መታመሙንና ፤ለሱም እርዳታ ለማሰባሰብ በጎ አሳቢ ኢትዮጵያዉያን መረባረባችዉን ስሰማ አደነቁሁዋቸዉ።ታድያ በማሰተባበሩ ግዳጅ የተሰማሩ በጎ አድራጊ ኢትዮጵያዊያኖቹ ለህዘቡ ስያስተዋዉቁ የተጠቀሙበት ቃል <ለናት አገሩ ሲል በየጦር ሜዳዉ ተሰልፎ ግዳጁን በሙያዉ የተወጣ…….> የሚል ሀረግ ያሰምሩበታል። ነገሩ ሀቅ ቢሆንም፤ ታመራት ሞላ ሁላችን የምናከበረዉ ዉድ ኢትዮጵያዊ ነዉና መርዳት ግዴታችን ነዉ። ሆኖም ብዙ፤ በበዙ ሺሕ ሚለዮን የጦር ሜዳ ጀግና ከነቤተሰቡ በረነዳ ላይ ወድቆ ደረቱ ላይ ያሸበረቀዉ መዳልያ ከደረቱ ወርዶ ወለል አፈሩ ላይ ተነጥፎ መለመኛ ሲአደርገዉ ያየን ስንቶቻችን ደረስንለት? ስንቱስ በየባዕድ አገር የራቢጣ ትምከህተኛ መጫወቻ ሆኖ “የወገን ያለህ ድረስ” ሲለን “ስንቶቻችን” በግነን በቁጭት በርብርቦሽ ደረስንለት? (በዚህ አጋጣሚ የላቀ አከብሮትና ምሰጋና እንግሊዝ አገር ለሚኖሩ ለኮማነደር አሰፋ ሰይፉና ዋሺንግተን አሜሪካ ለሚኖር የኢትዮጵያ ራዲዮ አዘጋጅ አቶ ምርጫዉ ስንሻዉ ይድረሳቸዉ) ፤ ስንቱ የጦር ጄኔራል፤ ስንቱ የጦር ሜዳ ወታደር ታምሞ ተሰቃይቶ ለህዝብ ድረሱልኝ ሲሰማ ተረባረብንለት? <መታወቅ> (እዉቅ፤ዝነኛ..) ማለት ምን ማለት ነዉ? ለአገር ደህንነት ሲል የሞተዉ እግሩ ሽባ ሆኖ በረንዳ ላይ ተጋድሞ ለማኝ የሆነዉን ጀግና ዝነኛነቱ ምን ያህል ለህዝቡ ደጋግመን አስተዋዉቀናል? መሁሩ ምን እየሰራለት ነዉ? ከኢትዮጰያ ገዳይ፤ከወደብ ዘጊዉ ከወያኔ ጋር “ኩት ኩት” እያሉ የአስገነጣይና የዘረኝነት መጻህፍት ሲያሳትሙ ሲፈጽሙና ሲአስፈጽሙ የነበሩት ዛሬ በተቃዋሚ ስም ጀግኖች እየተባሉ በዉጭ በያአዉሮፕላን ማረፍያ አደባባይ “እልልታ፤ ወሮ ወሸባየ” እየተዘፈንላቸዉ ስንመለከት፤ የሕሊና ቀጫጫነታችን ማስረጃ አይመስላችሁም ? ። የጀግንነት ሙያ የተወጡ ጀገኖች መድረኩን ለነሱ ልልቀቅና ምንኛ እንደካድናቸዉ ካንደበታቸዉ እነሆ። ፍርዱ ለህሊናችሁ ልተዉ። ክህደት በደም መሬት ከሚለዉ መጸሃፍ ከሻለቃ ዳዊት ወልደጊዮርጊስ የተገኘ የወታደሮች እሮሮና ቅሬታ።በሚከነክን፤ አንጀት በሚበላ ንግግር በአንድ ጀግና ኤርትራዊ የኢትዮጵያ ወታደር ልጀምር። ሻለቃ ዳዊት እንዲህ ይላሉ “ናይሮቢ ያገኘሁት የሐምሳ አለቃ አሰጋኸኝ ምህረተአብ በግንባር ላይ በነበረበት ጊዜ ስለተከፈለዉ መስዋዕትነት እነዲህ በማለት ሁኔታዉን ይገልጠዋል። < እኔና ብዙ ጓደኞቼ የተመለመልነዉ ከኤርትራ ነዉ። 11 ዓመት በሠራዊቱ ዉሰጥ ከተራ ወታደርነት ጀምሮ አገልግአለሁ። ወደ ወንበዴዎች ለመቀላቀል ብዙ ግፊት ቢኖርብኝም እሱን ሁሉ ተቋቁሜ ነዉ እስከመጨረሻዉ የተዋጋሁት። ለሀገር ፍቅር ስንል ነዉ። እስከመጨረሻዉ ለመዋጋት ፈልገን መሪዎቹ ሸሽተዉ ወደ ዓረብ አገር ሄዱ። እኛም ተበተንን። ሻዕቢያም ገባ። እጃችንን ለሻዕቢያ ከመስጠት ብለን በዙዎቻችን ብዙ ወራት በረሃ ተንከራተን እዚሁ ኬንያ ገብተን ስደተኝነት ጠየቅን። ከኔ ጋር የተመለመልን 28 ነብርን፡ ዛሬ ሁሉም በዉጊያ ሞተዋል። እኔ ከወታደርነት እስከ አመሳ አለቅነት፤ ከጓድ አዛዥነት እስከ ሻምበል አዛዥነት ደርሼም ነበርኩ። ሻምበሉን ስረከበዉ 123 ወታደሮች ነበሩ። 80 በመቶ አለቁ። ተተኪ ከሌሎች ቢመጡልኝም በዚያዉ መጠን አለቁ። ዉጊያዉን ስናካሂድ ሰ6 ዓመት ቤተሰቦቼን አላየሁም። ከተማም ገብቼ አላዉቅም። አሰብ የሞቱት ጓደኞቼ ይታወሱኛል። አዲስ አበባም ሄጄ እንደሌሎች ወታደሮች ለማኝ ሆኘ መዋረድ አልፈልግም። እዚሁ ሰዉ በማያዉቀኝ ሀገር ሆኜ በትዝታና በቁጭት ጊዜየን እገፋለሁ።>> እዛዉ ያገኘሁት የአስር አለቃ አስማማዉ በላይነህ ደግሞ፤ <<እኔ ለአጭር ጊዜ ነዉ ሠራዊቱ ዉሰጥ ያገለገልኩት። በዚያ አጭር ጊዜ ብዙ ችግር አይቻለሁ።ኤላበርዕድ ላይ በተደረገዉ ለሰሦስት ቀን ዉጊያ ብቻ ከዉጊያዉ በሗላ 11 ሺ የወገን ወታደር ማለቁን ገምተናል። በሻዕቢያ በኩል ከዚህ የበለጠ ነበር የሞተዉና የቆሰለዉ። እንዴት አድርጌ ከዚያ መዓት ተርፌ እዚህ እነደደረስሁ አላዉቅም። ዘመዶቼ ጎጃም ናቸዉ። አንድ ቀን ለመመለስ አስባለሁ፤ ቁጣዉ ሲበርድልኝ>> ብሎኛል። ኡጋንዳ ያገኘሁት የሐምሳ አለቃ አለምነህ የሚባል ወታደር በተለያዩ የሰሜን ዉጊያዎች ላይ ተሳትፏል። ሁኔታዉ እንዲህ ይገልጠዋል። << የወገን ሬሳ ለማንሳት ፈጽሞ አይቻልም። ጊዜም የለም። አቅምም የለም። ለመቅበር እነኴን ጊዜ የለም። የቆሰሉትን ጥለን ነዉ ብዙ ጊዜ የሄድነዉ። ከበላይ የሚመጣዉ ትእዛዝ “ጊዜ አታጥፉ፤ ቁስለኛ አታንሱ” ስለሆነ፤ በሕይወት ሲኖሩ የሚችሉ ስንት ወዳጆቼ ሜዳ ላይ እየተሰቃዩ ሞተወል። አንዳንድ ጊዜ ጨርሰኝ ሲል ጨክነን ያደረግንበት ጊዜ አለ። ብዙ ጊዜ ወይ እራሳቸዉን ይጨርሳሉ ወይንም እዚያዉ የሻዕቢያ መሳቂያ ሆነዉ ይሞታሉ። አሥመራ ዙርያ፤ ከረን አካባቢ ባሬንቱና ተሰነይ አካባቢ በተሳተፍንባቸዉ ዉጊያዎች ረግጬ ያለፍኩት የወንድሞቼ ሬሳ ቁጥር ስፍር የለዉም። አሁን ሳስታዉሰዉ እንቅልፍ ይነሳኛል። ጀግኖች ነበሩ። ለሀገራቸዉ ተወጉ። ተሰዉ። የተረፉት በየበረሃዉ ሲነከራተቱ፤ ሲቆስሉ፤ ሲራቡ ኖረዉ ዛሬ ሲለምኑ ማየትም፤ ስማቸዉን ማንሳትም አልፈልግም። በጣም እጅግ ያሳዝናል። እናት ኢትዮጵያ መቼ ነዉ ዉለታቸዉን የምትከፍላቸዉ?>> አንድ በአዲስ አበባ የሚኖር ወዳጄ አንድ የቀድሞ ወታደር አገናኘኝ። “የሐምሳ አለቃ በላይ አንጋጋዉ ነኝ” አለ። እዉነተኛ ስሙ እንዲታወቅ አልፈለገም። እነደነገረኝ አዲስ አበባ በየሆቴሎቹ በራፍ ላይ ቡትቶዉን ለብሶ እየተዘዋወረ ይለምናል። ቤት የለዉም። እንዲህ ሲል አጫወተኝ። << በዘጠኝ ዓመት በኤርትራ በተለያዩ ቦታዎች አገልግያለሁ። ከአዲስ አበባ ነበር የተመለመልኩት። አባትና እናት የለኝም። ጥቂት ዘመዶች ነበሩኝ። ሊያዩኝም አልፈልግም። እነሱነም ችግር ላይ ናቸዉ። ሁለት ጊዜ ቆስያለሁ።ከረንና ባሬንቱ አካባቢ ቁጥር ስፍር የሌላዉ ዉጊያ ተሳትፌያለሁ። ስንት ጓደኞቼ ሲሞቱ፤ አካላቸዉ ሲቆረጥ <ኢትዮጵያ ወይንም ሞት!> እያሉ እየፎከሩ በጥይት ዝናም ሲረግፉ አይቻለሁ። እኛ ዓለምን አናዉቅም። ኢትዮጵያ ብቻ ነበር የምናዉቀዉ። ከተመለመልኩበት ጊዜ ጀምሮ ዘጠኝ ዓመት ሙሉ ቤተሰቦቼን አላየሁም፡ ጡረታም የለኝም አሥመራ ስትያዝ ብዙ ተንገላታን። እንደዉሻ ተባረን እዚሁ ዘረገፉን። ለሀገሬ መስሎኝ ነበር የተዋጋሁት። ሀገሬም ከዳቺኝ። መንግስትም አዋረደን። የዚያን ጊዜ አንደ ጓደኞቼ ብሞት ኖሮ እላለሁኝ። የሞት ሞት ነዉ አሁን የምኖረዉ።> መደምደምያ የኢትዮጵያ ምሁራን በቁም የሞሞታቸዉን ዓይነተኛዉ ማስረጃዉ ይሄ ነዉ። በሕየወት እያለ የነቀዘ ሙሁር ምልክቱ፤ ጀግኖቻችን ለለማኝነት ሲዳረጉ ለነጻ አዉጪነት ተዋጊ እነኳን አለተጠቀሙባቸዉም። ከዚህ ወዲያ ኢትዮጵያ ከባንዳዎች ነጻ አወጥተዉ እኛም ወደ አገራችን ይመልሱናል ብለን በምሁራን ተስፋ የጣልን ሁሉ እርማችን እናዉጣ። የምናየዉ የፖለቲካ ሥራ ልግጫ (ጨዋታ) ነዉ። ዝና ፍለጋ ነዉ።ጀግኖቻችንን አስረሱን፤ እኛኑም እዚሁ በባዕድ አገር አስረጁን ! አምላክ ብቻ ቀረን እሱ በጥበቡ ነጻ ያዉጣን! እናንት የተከዳችሁ ለእናት አገራቸዉ ብላችሁ በየዱሩ ያራዊቶች መጫወቻ ሆናችሁ ለቀራችሁ፤አስታዋሽ ላጣችሁ፤ በየበረንዳዉና በስደት የምትንከራተቱት ሃዉልት ቀርቶ አገር ላጣችሁት ለተከዳችሁ ጀግኖች የኢትዮጵያ ወታደሮች ያኢትዮጵያ አምላክ ከናንተዉ ጋር ዪሁን! ጌታቸዉ ረዳ ሳን ሆዘ ካሊፎርኒያ (መጋቢት 2000 ዓም) (March 30, 2008)

The heeroes We Betrayed