Thursday, March 4, 2021

ሕዳር 22 ለ23 አጥቢያ አክሱም ውስጥ የሆነው እውነተኛ ዘገባ እነሆ! ትርጉም ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay) 3/3/2021

 

ሕዳር 22 ለ23 አጥቢያ አክሱም ውስጥ የሆነው እውነተኛ ዘገባ እነሆ!

ትርጉም

ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay)

3/3/2021

የዘገባው ባለቤት ከላይ ያለው በፎቶው የሚታየው አክሱማዊ ወጣት ነው። ተርጓሚውም (እኔም/አክሱማዊ) እንዲሁ! ዘገባው ከትግርኛ ወደ አማርኛ የተተረጎመ እውነተኛ ሰነድ። አውነተኛ ያልኩበት ምክንያትም በራሴ መንገድም የተቻለኝን ያህል ማጣራት ሳደርግ ተመሳሳይነት ስላገኘሁበት ነው።

ባለፉት ሳምነታት አክሱም ውስጥ የዘር ጭፍጨፋ ተካሂዶ ወደ 700 የሚያክል አክሱማዊ ኗሪ እንደተጨፈጨፉ የሃሰት ዜና ሲሰራጭ መሰንበቱ ይታወቃል። ታዲያ ይህንን ወሸት በመቃወም እይ/ከሥር በፎቶግራፉ ላይ የምታዩት አክሱማዊ የሆነ የወያኔ ተከታይ ወጣት እውነቱን በራሱ “የማጣራት ሂደት” (ኢንቬሰቲጌሽን) ያደረገውን በዩቱብ ያስተላለፈው የድምጽ እና የምስል (አውድዮ-ቪዲዮ) የትግርኛ ዘገባው ወደ አማርኛ ተርጉሜ አቀርብላችሗለሁ።

ይህ ወጣት ያጣራው ምንጮቹ በቅርብ የሚያውቃቸውታማኞች ያላቸውን እና እንዲሁም ሁኔታው ተከሰተ በታበለው ሰሞን ወደ ሱዳን ተሰድደው እራሱ አነጋግሮ ያገኘውን ዘገባ እንዲህ ሲል ይጀምራል።

“እንደሚታወቀው በተለያዩ የውስጥና የውጭ አገር ዜና ማዕከሎች በተለይም ደግሞ “ለሕዝባችን መከታ እንሁን” የሚለው ቡድን እና የዜና ማሰራጫ ማዕከል ሲሰራጭ የነበረው ከእውነት የራቀ አሳሳች ዜና ሲያሰራጭ እንደነበር ይታወሳል። ይህ ውሸት እጅግ ተጋንኖ በመቅረቡ ለማመን ስለከበደኝ አውነት መሆኑን አለመሆኑን ለማጣራት የበኩሌን ምርመራ ለማድረግ ወስኜ ያገኘሁት የማጣራት ማስረጃ ከነዘህ የሃሰት አሰራጪዎች እጅግ የራቀ ሆኖ ስገኘሁት እነሆ ዛሬ እውነቱን ማቅረብ አለብኝ ብየ ነሆ እውነቱን እንድታውቁት ይሁን….”

 እላቶቻችን በሕዝባችን ላይ እያደረጉት ያለውን ግፍ እቃወማለሁ። ሆኖም እኛ ሁላችንም ስንቃወም ውሸቱን ሳይሆን እውነቱን ብቻ በመናገር ብቻ ነው የላትን ግፍ ማጋለጥ የምንችለው። ይህ የውሸት ዘገባ ሕዝብቻን የሕሊና ሽብርና ፍርሃት እንዲያድረበት ማድረግ ነው። ስለሆነም ላቶች ከሚያደርሱብን ግፍ በላይ “ውሸትን በማሰራጭት በባችን ላይ ወንጀል መፈጸም አድረጌ እቆጥረዋለሁ። ስለዚህ ውሸትን ከማሰራጨት እንቆጠብ”

ሲል ምክሩን ከለገሰ በሗላ ሕዳር ወር 2013 ውስጥ አክሱም ውስጥ ምን ሆነ? የሚለውን ዘገባው እንዲህ ያቀርበዋል።

“የ ‘ፒ ፒ’ ወታደሮች ሽሬን አልፈው ወደ አክሱም ከተማ የገቡበት “ኮንክሪት” (ተጨባጭ) ቀን ባጣራሁት መረጃ መሰረት ቀንዋ ሕዳር 9 ነው። ከሕዳር 9 እስከ ሕዳር 21 ማለትም እስከ ሕዳር ጽዮን እስክያልፍ ድረስ በነዚህ 10 ወይንም 11 ቀናት ውስጥ ሰላም ሆኖ ምንም የተፈጸመ ነገር አልነበረም። ወታደሮቹ አክሱም ብዙም ሳይቆዩ አንድ ሁለት ሦስት የሚሆኑ ሁኔታውን የሚታዘቡ ወታደራዊ ፓትሮሎች ከተማዋ ውስ ትተው ሕዝቡን ባንኮቻችሁ ክፈቱ ንግዳችሁም ከፍታችሁ በሰላም ነግዱ ብለዋቸው ወታደሮቹ ወድያውኑ ወደ ዓድዋ ነው ያቀኑት። ሕዳር 22 ወደ ሕዳር 23 አጥቢያ ሌሊት ከተማዋ ውስጥ የነበሩ ጥቂት የወያኔ ታጣቂ ምሊሺያዎችና ከከተማዋ አፋፍ ውጭ አድፍጠው የነበሩ በወያኔ ሲሰለጥኑ የነበሩ የአክሱም ወጣቶች በመቀናጀት በከተማዋ የነበሩ እነያ ከተማዋን ለመቆጣጠር ከጫፍ ወደ ጫፍ እዚህም እዚያም እያሉ በፓትሮል ሲዘዋወሩ በነበሩት ወታደሮች ላይ በሚያመቻቸው ቦታ እየጠበቁ ደፈጣ ቆይተው በድንገት ሳይታሰብ ጥቃት ፈሙባቸው። 30 የሚሆኑ ወታደሮች ተገደሉ።

ክስተቱ እንደተፈጸመ ዕርዳታ ተጠይቆ ከዓድዋ ወደ 7 ወታደራዊ ኡራል መኪኖች ተጭነው ወታደሮች ወደ አክሱም ገስግሰው ገቡ (አንባቢዎች ከአክሱም ወደ ዓድዋ ርቀቱን ለማታወቁት 25 ኪ.ሜ ርቀት ነው) ።

ነዚህን ለማደን (ሃንት) ለማድረግ በተደረገው የቶክስ ልውውጥ 8 ወጣቶች እና ወደ 8 የሚሆኑ ሚሊሺያ ተዋጊዎች ተገድለዋል። በጠቅላላ የሞቱት 16 ናቸው። የሆነው ይህ ነው። ጭፍጨፋ ምናምን የሚባለው ከዕውነታው አይሄድም።” ካለ በሗላ አንድ የሚገርም ክስተት አብሮ የተነገረው እንዲህ ይላል።

“አብሮም አንድ ክስተት ተከሰተ። አክሱም ከተማ የነበሩ የሕግ ታሳሪዎች ተፈትተው ከተማዋ ውስጥ ተለቅቀው ስለነበሩ፤ ሁኔታውን በማየት የባንክ ዘረፋ አከናዉ። ዘረፋ የተፈጸመባቸው ባንኮች መስተዋቶች እና መዝጊያ በሮቻቸውን በመሰባበር ዘረፋ ፈጸሙ። ዘረፋ ከተፈጸመባቸው ባንኮች ውስጥ ኮመርሻል ባንክ (ቅድስት ማርያም ሆስፒታል አጠገብ ያለው ባንክ) ሁለተኛው አፍሪካ ሆቴል አጠገብ የሚገኘው ባንክ ሦስተኛው “ፀሓይ በርቂ” የተባለው ላይ በነዚህ ቅርንጫፎች ዘረፋ ሲፈጸምባቸው በሌሎች ባንኮች ዘረፋ አልተፈፀጸመም። በዝርፊያው ውስጥ ሕዝቡ እራሱ ዘራፊዎቹን ታግሎ ከሸሸጉበት እየተጠቆሙ ወደ 280,000 (ሁለት መቶ ሰማንያ ሺሕ) ብር የሚሆን ብር በማስያዝ ባንኮቹ እስኪረጋጉ ድረስ ለአክሱም ጽዮን ቀሳውስት ማሕበር በአደራ እንዲቀመጥ አድርገዋል።”  በማለት ሲያጠቃልል፡ እንዲህ ያጠቃልላል፡

“የሆነው ይህ ነው። “ታቦት ለመቀማት 700 ቀሳውስትና ሕዝብ ተጨፈጨፈ የሚባለው ውሸት ሁለተኛ መደገም የለበትም። እንዲያውም አክሱም ቤተክርስትያን አካባቢም ሆነ ከቤተክርስትያኑ ራቅ ያሉ አካባቢዎች ምንም የተፈጸም ግድያ የለም። ቶክሱ የተለዋወጡብት ቦታ ከቤተክርስትያኑ በጣም አጅግ ሩቅ ነው።…” ሲል ያጣራውን እውነታ አጋርቶናል። እኔም ተርጉሜ አቅርቤላች ለሁ። ይህ ጠቃሚ ሰነድ ሼር የመድረጉ የናንተ ድርሻ ነው።

አመሰግናለሁ።

ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay)