Sunday, January 7, 2018

የአክብሮት ምስጋናየ ለኢትዮጵያውያን ማኅበር ጥናትን ምርምር ዘርፍ ጌታቸው ረዳ (የኢትዮጵያን ሰማይ ድረገጽ አዘጋጅ)



የአክብሮት ምስጋናየ ለኢትዮጵያውያን ማኅበር ጥናትን ምርምር ዘርፍ
ጌታቸው ረዳ (የኢትዮጵያን ሰማይ ድረገጽ አዘጋጅ)
የተከበራችሁ ውድ ሊቀ ሊቃውንቶች ወገኖቼ የኢትዮጵያውያን ማኅበር ጥናትና ምርምር ዘርፍ አባሎች ውድ ገብሬ ጉልቱ ውድ ክብርት እህቴ ወ/ሮ የውብዳር ዘለቀ፤ ውድ ወገኔ ገሞራው ማን ያዘዋል፤ውድ ወገኔ ገለበው ሰንጎጎ ውድ ወገኔ ተከስተ ሐጎስ ውድ ወገኔ አውዴ በዳዳ፤ውድ ወገኔ አዩ ይስማን፤ውድ ወገኔ ኃይለ ልዑል ይርጋ፡ ባላችሁበት ምድር የሰላምና የፍስሃ ልደት እንዲሆንላችሁ እየተመኘሁ፤ ከወዲሁ የቀረን አንድ ቀን ስለሆነ ከነ መላው ቤተሰቦቻችሁ እንኳን ለጌታችን መድሃኒታችን ብርሃነ ልደቱ በዓል አደራሳችሁ እላለሁ። ስለ አደረጋችሁልኝ ድጋፍና ማበረታቻ እጅግ፤በጣም እጅግ ከልቤ አመሰግናለሁ እያልኩ ይህችን ማስታወሻ ለሕዝብ ልኬአለሁ ።( visit Welkait.com)

ውድ ሊቀሊቃውንቶች ወገኖቼ ሆይ። ‘ለዑንቁ ደ/ር ጌታቸው ረዳ ዘብሔረ አክሱም’ በሚል የድጋፍና ማበረታቻ ሕዝብ እንዲያውቀው በማድረገችሁ እውነተኛ አገራውያን ዜጎች ከጎኔ መሰለፋቸውን ሳይ ትግሌን ይበልጥ እንድቀጥል አድርጎኛል።

በእያሱ አለማዮህ (ሃማ ቱማ) የሚመሩ ጥቂት የኢሕአፓ አባሎችና ከትግሉ ወጥተናል የሚሉ “የኢሕአፓ-ነበር አባሎች” ድርጅቱን ወይንም መሪዎቻቸውን ስለተቸሁ የሚይዙት የሚጨብጡት በማጣት በኔ ላይም ሆነ በበርካታ ተቺዎች ላይ የስም ማጥፋት እና ዘለፋ በማድረግ ሲረባረቡብኝ አይታችሁ በዜጋዊ እና በፍትሓዊ ሚዛን ተነሳስታችሁ በኔ ጎን ቆማችሁ የስም ማጥፋት ዘለፋቸውን በመመከት በቆምኩበት የዘወትር ኢትዮጵያዊነት መመሪያየ እንድቆም ላበረታታችሁኝ ወገኖቼ እጅግ አመሰግናለሁ።ስለ ኢሕአፓዎች ጉዳይ ትንሽ ልበል፦

ኢሕአፓዎችን አላውቃቸውም። እነሱን ጠልቄ ከማወቄ በፊት በበጎ ዓይን ነበር ሳያቸው የነበረው። ይህ ድረጅት በትግራይ ውስጥ የሚታወቅ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ወይንም “ፓንፍሌት” ቀስቃሽ ወረቀት በትግራይ ከተሞች ውስጥ ለሕዝብ አሰራጭቶ አያውቅም። ትግራይ ውስጥ  አጋሜ አውራጃ ውስጥ “የማሰልጠኛ ካምፕ” እንደነበረው እንሰማለን እንጂ ቅስቀሳቸውንም ሆነ ታጋዮቻቸው አንብቤአቸውም፤ አይቼአቸውም አላውቅም፤ ታጋዮቻቸውንም ዓይቻቸው አላውቅም፡

 (ያየሁዋቸው ጊዜ ስርዓቱን ዘልፈሃል ተብየ በደርግ ካድሬዎች ተይዤ ወደ ሕዝብ ድርጅት ሲወስዱኝ በላንድሮቨር ውስጥ የነበሩ ሁለት ኢሕአፓ ወዶ ገቦች “አንደኛው ተሎ ተናገር! ብሎ ከካድሬዎቹ በላይ ካድሬ ሆኖ እኔን በጥፊ ሊመታኝ ሲል የሕዝብ ድርጅቱ መኪና ሲነዳ የነበረው ግማሽ ካድሬ ግማሽ መኪና ነጂ የነበረው፤ ሰው ሁሉ እሱን ሲያይ ሲሸሸግ የነበረ ካሕሱ/ጨንጨሪኖ/ የተባለው “ካድሬ” ከመሆኑ በፊት ጫመየን የሚጠርግ ደምበኛየ የነበረ ያከብረኝና እጅግ ይወደኝ ስለነበር “እረፉ እንዳትነኩት!” ብሎ እንዳስጣለኝ ትዝ ይለኛል። እኔ እና ወዳጄ “ኪሮስ አለማዮሕ” (ወያኔ በመርዝ ገድሎታል የሚባለው የታወቀው የትግርኛ ዘፋኙ) እስር ቤት ሆነን ኪሮስን “ክፉኛ ደብድበውት ስለነበረ”፤ ካሕሱ ወዳለንበት ክፍል “መጥቶ ደህና ናችሁ?” ሲለን ፤ እኔም “ካሕሱ እስኪ ልጠይቅህ፤ እነዚህ አንተው ጋር የነበሩት ሰዎች ምንድናቸው ልብሳቸው የከተማ አይመስለም እኔን ለማስፈራራትም ቃጣቸው፤ ምንድናቸው?” ብየ ስጠይቀው “አዲስ አቃጣሪዎች ሆነው ለመታየት የቀረቡ የኛን ቦታ ሊወስዱ የሚጥሩ የኢሕአፓ ወዶ ገብ ወንበዴዎች ናቸው።ከገቡ ሳምንት አልሞላቸውም” ሲለኝ ፤ በመገረም “ክው” ነበር ያልኩት። ኢሕአፓ የሚባሉ ታጋዮች ዓይናቸውን ያየሁት ያኔ ነው፤ (ከነመጫሚያቸው፤ዕድፋቸው ባላገር መስለው ማለት ነው።) በቃ። ከዚያ ወዲያ ትግራይ ውስጥ የሚታወቁት ህወሓት ብቻ ነበር።

ያም ሆኖ፤ ደርግ ለስሙ ነበር እንጂ ‘የሕዝብ ድርጀት” ይቆጣጠረው ነበር ሲባል የነበረው የላ ሰነዱ የሚያመለክተው ከ8 አውራጃዎች ውስጥ አመራሮቹ አክሱም ብቻ የካድሬዎቹ ሃላፊ (አፈወርቅ አለመሰገድ- ኬኒያ ድረስ ሄደው የገደሉት የሙሉጌታ አለምሰገድ ታናሽ ወንድም (የመለስ ዜናዊ ልዩ አማካሪ የነበረ ዛሬ ጣሊያን አገር አምባሳደር) ካልሆነ ሌሎቹ አውራጃዎች አመራሮቹ እና ብዙዎቹ ካድሬዎች የህወሓት የውስጥ ወኪሎች እንደነበሩ በህወሓት ሰነዶች ስማቸው ሁሉ ተመዝግበዋል።ሰነዳቸው ስመለከት እኔ እራሴ በጣም ነበር የገረመኝ። በግርፍያው የተሳተፉ አመራሮችና ገራፊዎች በሙሉ ትግሬዎች ነበሩ። በላ ስመለከት “ወያኔዎች” እንደነበሩ ሲነግሩን “በደርግ ስም ስንት ጉድ ተሰራ ነበር ያልኩኝ”። ብዙውን የትግራይ ሰው ኢሕአፓን አያውቅም (ነበሩበት በተባለ ገጠር ምናልባት (?)፤ ከተማ ውስጥ ግን አልበሩም፤ አይታወቁም። ቢኖሩ 3 ወይንም አራት አባሎች ሊሆኑ ይችሉ እንደሆነ እንጂ እነሱ እንደሚያጋንኑት “ትግራይ” ውስጥ ነበርን እንደሚሉት ከተማ ውስጥ አልነበሩም። መኢሶን የሚባለው እማ ጭራሽኑ አናውቀውም። ኢሕአፓ እና መኢሶን አዲስ አበባ፤ ጎንደር፤ወሎ ሐረር….እየተገዳደሉ ነው የሚል በራዲዮ እንሰማ እንደሆነ እንጂ ሁለቱም “ምን ይነት አራዊቶች” እንደነበሩ የትግራይ ሰዎች ትግራይ ውስጥ የነበርነው ስለ እነሱ ምንነት አናውቅም። እስከዚህ ድረስ ነው።

ኢሕአፓን ያወቅኩዋቸው እዚህ ከተማ ውስጥ ነው። ሱዳን ውስጥ በተባበሩት መንግሥታት በስክሪነር (አጣሪ) ሆኜ ተቀጥሬ ስሰራ ብዙ ኢሕአፓዎች ታሪካቸውን እና ወደ ውጭ የመሄድ ዕድላቸው ለምን እንደተከለከሉ ሲነግሩኝ “ሳይመን” ከተባለ ዋናው የስደተኞች ወኪል እና አጣሪ ኦፊሰር እያናገርኩ ወደ ውጭ የመሄድ ዕደላቸውን አቃንቼላቸው እንደነበር ትዝ ይለኛል። እስካሁን ድረስ የ500 ሰዎች ከነቤተሰቦቻቸው ስም እና አድራሻ አቴንስ ውስጥ የተሰጠኝ የስደተኞች ስም ዝርዝር በእጄ አለ ። ብዙዎቹ በኔ ጥረት ነበር የተረዱት።

እዚህ ስመጣም በምኖርበት ከተማ በጣም የሚያከብረኝ የማከብረው የኢሕአፓ አባል የነበረ አንድ እጅግ ቀና የሆነ ወዳጄ በኩል ነበር ኢሕአፓን እና ወረቀቶቻቸውን ለመመለክት የበቃሁት። ጽሑፎቻቸውንም የድሮ ሳይሆኑ እዚህ ከተሰደዱ በላ የተጻፉ ስለሆኑ፤ የሚናገሩት ስለ ኢትዮጵያ አንድነት እና አርበኛነት ወዘተ… ስለነበር ‘እኔም ይህንን ጽሑፋቸውን በመመልከት” አገራዊያን ናቸው አገራቸውን ይወዳሉ በሚል ሰዎች ሲዘልፏቸው “ጹሑፎቻቸውን እያየሁ” ስከላከልላቸው ነበር። የላ ግን የዋለለኝን ጉዳይ ተነስቶ ወድ ወዳጄ እና አስተማርየ ጣሊያን አገር የነበሩት ሟቹ (እግዚአብሔር ነብሳቸውን በገነት ያኑርልን) ፕሮፌሰር ዶክተር አለሜ እሸቴ ስለ ዋለልኝ እና ማርታ ከተገንጣዮቹ ጋር የነበራት ግንኙነት አንስተው የማውቀው ነገር ካለ የመሳሰሉት አንስተው ሲጠይቁኝ፤አስመራ ውስጥ በኤርትራዉያኖች የተጻፈ ሁለት በትግረኛ የታተሙ በጣም በርካታ ፎቶግራፎች እና በርካታ ገጽ የያዙ የትግላቸው ታሪክ የሚገልጽ ሰነድ ሰው አውሶኝ አንብቤው እኔ የማውቀውን ስነግራቸው፤ ሰፊ ውይይት ካወጋን በላ፤ “On the question of Ethiopian nationalities Walelegn as Roamn Prochazka”  Monday, June 2008 አካባቢ ጽፈው አሰራጨው ብለውኝ አሰራጨሁት።

ኢሕአፓ የተባለው ቡድን ዋለልኝ መኮንን ጸረ አማራ እና ጸረ ኢትዮጵያ ነበር ብለህ ተችተሃል በሚል ከኔ ጋር ፍጥጫ ጀመሩና ዘለፋ አወረዱብኝ። ከዚያም በአማራ ማሕበረሰብ በገበሬው፤በሠራተኛው፤ በተማሪዎች ፤በህጻናት፤ በእናቶች፤ በአዛውንቶች እና በእርጉዝ እና በእመጫት አማራ ወገኖቼ ላይ በኦሮሞው እስላመዊ እና በኦሮሞው ፖለቲካዊው ኦነግ፤በትግሬው ህወሓት፤ በኦጋዴን አክራሪ ሶማሊ ቡድኖች እና በመሳሰሉት ነብሰገዳይ ቡድኖችና በርካታ ጽንፈኞች በዚያ ማሕበረሰብ ላይ ባደረሱት በርካታ የዘር ማጥፋትና ዘለፋ ተመልክቼ፤ እንደ ዜጋነቴ እና ወገኖቼ እንደመሆናቸው መጠን ስለ አማራው ብሶት ደጋግሜ ስጮህ እና ወንጀለኞቹ ለፍርድ መቅረብ እንዳለባቸው ስከራከር፤ በኢያሱ አለማዮህ (ሃማ ቱማ) የሚመራ የኢሕአፓ ክንፍ ተከታዮች፤ “ከአማራ በላይ አማራ ለመሆን የሚከጅለው ጌታቸው ረዳ” በማለት ሲኮንኑኝ በጣም ነበር የገረመኝ። ብዙዎቹ ደግሞ አማራዎች እንደሆኑ ሰዎች ሲነግሩኝ መልሶ አግራሞቴን አባባሰው።

ዐማራው ለ26 አመታት በተለያዩ ጸረ አማራ ድርጅቶች ዘመቻ እንደተደረገበት ታሪክ መዝግቦታል። ታሪክ እንዲመዘግበው ካደረጉት አንዱ የኔ መጻህፍቶች ምስክሮች ናቸው። ኢሕአፓዎች ስለ አማራ የቆመውን ሁሉ በጣባብ ጎሰኛነት ኰንነውታል። በርካታ ወዳጆቼ ደውለው ሲነግሩኝ በፕሮፌረስ አስራት ላይ ሲደርስ የነበረው ዘለፋና የስም ማጥፋት ዘመቻ ከወያኔ ቀጥሎ ኢሕአፓዎች እንደነበሩ ነገረውኛል። ለዚህም በወቅቱ ሃዋርያ በተባለ ጋዜጣ እና በመሳሰሉ አገር ውስጥ በሚታተሙ መጽሄቶችና ጋዜጦች ላይ ኢሕአፓዎች ከወያኔ ጋር እኩል ሲረባረቡባቸው እንደነበረ ሰነዶች ይናገራሉ። እያሱ አለማዮህ “ፕሮፌሰር አስራትን” ሌት ተቀን በብዕሩ ሲያኝካቸው ነበር ብለውኛል። እኔም ይህንኑ ባንዳንድ ሰነዶች ተመልክቻለሁ። ስለ ዐማራ ብሶት የሚብከነከን ሰው ሲያይዩ ከወያኔ ቀጥሎ የሚያማቸው ኢሕአፓዎች መሆናቸውን አሁን በግልጽ እየተገለጸልኝ መጥተቶ ይኼው ስለ አማራ እሮሮ በማስተጋባቴ በኔ ላይም ዘመቻቸውን-ከፈቱ።

ይህ ድርጅት ድረጅቶችን በማፍረስ “ሰርጎ እየገባ ማኮላሽት” እና “ስም በማጥፋት” የተካነበት እንደሆነ ብዙ ዜጎች ያማርሩ እንደነበር ብመለከትም፤ ዋለልኝ ለምን ተቸህ እስካሉኝ ጊዜ ድረስ ብዙም አላወቅኳቸውም ነበር። በኔ ላይ ሲዘምቱ ግን- እያደረ ሲነጋ የጫረብኝ ጥያቄ የሚከተለው ነበር፦ “በወቅቱ አዲስ አበባ ወይንም መኢሶን እና ኢሕአፓ ሲጋደደሉበት በነበሩት ከተሞች ብኖር ኖሮ እና በዛው ወቅት ዋለልኝን ብተች ኖሮ ‘ኢሕአፓዎች’ በጥይት እንደሚገድሉኝ እርግጠኛ ሆኜ መገመት እችላለሁ” ነበር ያልኩት። እዚህ ሆነው የእያሱ አለማዮህ ኢሕአፓ ካልቶች/ጀሌዎች/ በኢመይል እና በድረገጾች ሲንጫጩብኝ እዛው የሰው ልጅ ሲገድሉበት በነበረው መሬት ላይ ቢሆኑ ምን ያደርጉኝ ነበር አልኩኝ?

ልክ እናንተ ክቡራን ሊቃውንት በትክክል እንደገለጻችሁት “ኢሕአፓ” ተሓህት የያዘው ሥልጣን ቢይዝ ኖሮ እውነት በዋለልኝ ምክንያት እና ስለ አማራ ለምን ጮህክ “ከአማራ በላይ አማራ ነህ” ብለው ይረሽኑኝ ነበር ማለት ነው። “ወደ ፖልፖትነት ይለወጡ እንደነበር” ያላችሁት ልክ ናችሁ። ይህ ሃቅ ነው። ይህ ድርጅት በጣም አደገኛ ስለነበር አወዳደቁ ልክ በዛው ልክ ባፈጢሙ ወድቆ “መጨረሻው ውሎውን ያደረገው እዚህ ከተራው ስደተኛ” ጋር በድረገጽ ውስጥ ገብቶ ‘በካልት’ ባሕሪ እየታጀበ የአማራን እሮሮ የሚያስተጋቡትን ሰም በማጥፋት ዘመቻ ላይ ገብቶ ራሱን በቀን ሕልም አስገብቶ “ወያኔን የሚጥለው ኢሕአፓ ብቻ ነው” እያለ ስያስቀን ይውላል። በእነ ዋለልኝና በኤርትራኖች በነሳልሕ ሳቤ እርዳታና ፖለቲካዊ ነዳጅ እየተነዳ የኢሕአፓ ትግል ከአነሳሱ ጀምሮ በጠላትነት የፈረጃትን ኢምፔሪያሊስቱ ምኒሊክ የገነባት የ60 አመት ዕድሜ ያላት ኢትዮጵያ የሚላትን እንድትገነጣጠል “እስከ መገንጠል” (እስከ መፍረስ ድረስ) የሰበካትን አገር ፈርሳ ማየት ብቻ ሳይሆን  የአማራውን እሮሮውን ለዓለም ታስተጋባላችሁ ብሎ ሲዘልፈን አድምጠናል።

 የዚህ ድርጀት መሪ ጸረ ዐማራነቱን እና “በገጠሪቲ ኢትዮጵያ የሰው ስጋ መብላት የተለመደ ነው”፤ የኢትዮጵያ ልዕለቶች የሰው ልብ መብላት እና በሰው ደም ገላቸውን ይታጠቡ ነበር”፡ እያለ የታወቁ ክርስትያናዉያን ልዕልቶቻችንና ንጉሣችንን ስማቸውን በማጥፋት ማንነቱን በግልጽ አስቀምጦ መጽሐፍ የጻፈ የኢሕአፓ መሪው እያሱ አለማየሁ እየመራቸው እያወቁም ቢሆን በኛ ላይ ሲመጻደቁ ማየት አውንት ይገርማል! በዚህ መልክ ኢሕአፓ ጠመንጃ ቢኖሮው ልክ እናንተ ወገኖቼ እንዳላችሁት አማራውንም እኔንም ማስቀመጫ ያሳጣን ነበር ። መሪዎቻቸው ጥፋት አደረጉ አላደረጉ፤ ኢትዮጵያን ዘለፉ አልዘለፉ ጉዳያቸው አልነበረም።

ኢሕአፓ የሚባለው ድርጅት ሲያድር እያስገረመኝ መጥቷል። አማራዎች ጉሙዝ ውስጥ በሰው አራዊቶች ተገድለው ስጋቸው ተበልቷል፤ የሚል ዜና እና ከአደጋው አምልጠው በየዱሩ የተሸሸጉ አማራዎች ስልክ ደውለው ድረሱልን ሲሉ የስዊድን ኢትዮጵያ አንድነት ራዲዮ ቃለመጠይቅ አድርጎላቸው ‘አማራዎች ውጡ ተብለው፤አንዳንዶችም ተገድለው ስጋቸው እንደተበላ” በአስደነጋጭ ንግግር ሲናገሩ ሰምቼ ያንን “ለሕዝብ በማድረስ” ይህ ሕዝብ ከድተነዋል! የተከዳ ሕዝብ ነው! እንዲህ እስኪሆን ድረስ ምሁራን ምን እያደረጋችሁ ነው? አማራዎች የሆናችሁ (ሌሎችስ ደህና ይርሱት) የሕግ ጠበቆች ምን እያደረጋችሁ ነው? ተቃዋሚዎችስ ምን እየሰራችሁ ነው?...... ብየ በብስጭት ስለተቸሁኝ እና ሞረሽም «በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል፣መተከል ዞን በሚኖሩ ዐማሮች ላይ የተፈፀመ የዘር ማጥፋት ወንጀል» በሚል ርዕስ ማክሰኞ ነሐሴ ፲፪ ቀን ፪ሺህ፯ .. የሰጠውን በሃቅና በተጨባጭ መረጃ የተደገፈውን ዘገባኢሕአፓ ደጋፊዎችና ነባር ታጋዮች የሆኑ የአሲምባ ድረገጽ አዘጋጆች «በአማራ ሕዝብ ስም ሌሎችን መዝለፍ የሚወገዝ ነው» በሚል ርዕስ ዘጋጀውን መግለጫ ነሐሴ ፳፪ ቀን ፪ሺህ፯ .. በሬዲዮ ስያስተላልፍ፡ በጽሑፍ ደግሞ «አሲምባ» እና «ደብተራው» በተባሉ ድረገጾች በማሰራጨት እንዲህ ሲሉ ዘለፉን፡

እጠቅሳለሁ፤

«በጉምዝ ሕዝብ ላይ የተከፈተው ጸያፍ ዘመቻ የአማራን ሕዝብ ተገን አድርጎ በመሆኑ ሊወገዝ የሚገባው ነው።» በማለት የተሰጠው መረጃው የቱን ያህል አስተማማኝ ነው? ሌላስ ሁለተኛ እና ሦሥተኛ አካል መረጃውን እንዴት ማግኘት ይችላልብሎ ሣይጠይቅ ነው በጉምዝ ሕዝብ ላይ ጸያፍ ዘመቻ አድርገዋል ሲሉ ሞረሽንም እኔንም ከአደጋው ሸሽተው ያመለጡትንም አማራዎች ጭምር የኰነኑን።

ኢሕአፓዎች በዚህ ሳያበቁ እንደገና በሚከተለው አስገራሚ ዘለፋ ዘለፉን።
እጠቅሳለሁ፤-

<<የጉምዝ ሕዝብ/ ቤንሻጉሎች አማራውን ገድለው ጉበቱን፣ ኩላሊቱን፣ የታፋ ሥጋውን በሉ ብሎ ዓይንን በጨው አጥቦ ሕዝብን መዝለፍ አፍሪካን ከሚጠሉ ነጮች የሚጠበቅ እንጂ፣ ለዐማራ ተቆርቋሪ ነን ባዮች ሊሰጥ የሚገባው አደለም ።>> ሲል ተመጻደቁብን።

እኔም መልሴን በሚከተወል ርዕስ <<ንግሥት ዘውዲቱ፤ ልዕልት እቴጌ መነን  እና / /ሥላሴ የሰው ጉበት ይበሉ ነበር? ክፍል -2- መልስ ለኢሕአፓ>> በሚል ከላይ የተመጻደቁብንን <<የጉምዝ ሕዝብ/ ቤንሻጉሎች አማራውን ገድለው ጉበቱን፣ ኩላሊቱን፣ የታፋ ሥጋውን በሉ ብሎ ዓይንን በጨው አጥቦ ሕዝብን መዝለፍ አፍሪካን ከሚጠሉ ነጮች የሚጠበቅ እንጂ ለዐማራ ተቆርቋሪ ነን ባዮች ሊሰጥ የሚገባው ላለው እና እንደገና <<«ሕዝባችን ሰው አይበላም፤ ይህን ውሸት ማሰራጨት ኢትዮጵያ ላይ መዝመት ነው።» በማለት እኛን ውሸታሞች እና በአገራችን ላይ እንደዘመትን አድርገው ከአደጋው ያመለጡትንም እኛንም ስለ ኮነኑን መሪያቸው ኢያሱ አለማዮህ (ሃማ ቱማ) በነገሥታቶችና በልዕልቶቻችን ክብር የሚያጎድፍ የጻፈውን የዘለፋ መጽሐፉን አስደግፌ በማስረጃ መልስ ሰጠሁ።

 ለተመጻደቀብን ብዕራቸው መልስ የሰጠሁት ፤ መሪያቸው እያሱ አለማዮህ (ሃማ ቱማ) ነገሥታቶቻችንን ልዕልቶቻችንን ስም በማጥፋት ዛር የተባለ ውቃቢ ሲነሳባቸው “ጥቁር ጥቁሩን ሰው /ባርያ የሚባለውን? በራሱ አገላለጽ/ እየተመረጠ እየተገደለ ልባቸውን ጠብሰው ይበሉት ነበር ሲል በሚያስደነግጥ ስም አጥፊ ዘመቻ በማድረግ መጽሐፍ ጽፎ ዓለም አንብቦታል። ይህ ሰውን ገድሎ ስጋውን መብላት በገጠሪቷ ኢትዮጵያ የተለመደ ነው ሲል አገራችንን ዘልፏል፤ስማችን አጉድፎታል። እሱ እንዲያ ሰጽፍ ኢትዮጵያ ላይ መዝመት ነው” “……እንዲያ ብሎ የሚጽፉ አፍሪካን ከሚጠሉ ነጮች እንጂ ኢትዮጵያ ነኝ ከሚል አይጠበቅም…” ሲሉ እኛን ሲኮንኑ መሪያቸው እያሱ አለማዮህ (ሃማ ቱማ) <<የኢትጵያ ነገሥታቶችና ልዑልቶች ብቻ ሳይሆኑ በገጠሪቱ ኢትዮጵያም ሰው ሰውን መብላት የተለመደ ነው>> ብሎ መጽሀፍ ሲጽፍ በእኔ እና በሞረሽ ላይ የዘመቱ ኢሕአፓዎች አለቃቸውን <<ኢትዮጵያ ላይ መዝመት ነው>> ብለው እኛኑ ላይ እንደተመጻደቁብን እና እንደ ኮነኑን ዘመቻ አላካሄዱበትም። ለምን? ብየ ስጠይቃቸው እንኳን ሊመልሱ አንዳንዶቹ ጭራሽኑ ኢመይል ስድባቸውን በማዥጎድጎድ ለምን አለቃችንን እኛንም አጋለጥከን ብለው “አበዱ”። ይህንን ትችት ማመዛዘን የተሳነው ፍጡር የሕሊና ቀውስ “የካልት በሽታ” ካልተጠናወተው በስተቀር በሚዛናዊ ጥያቄ ላቀረብኩት ጥያቄ “ጤነኛ ሰው”  ሊያሳብደው አይችልም።

እያሱ አለማዮህ ተንደላቅቆ ተምሮ ያደገባት ኢትዮጵያ የተከበሩ ነገሥታቶቻችን  እና የተከበሩ ወይዛዝርት እና ልዕልቶቻችን በጦር ሜዳ ከወራሪዎች ጦርነትና በዲፕሎማሲ፤ ሕዝብን እያስተባበሩ ከውስጥም ባህል እና ሃይማኖታችንን አዳብረው ያስረከቡት የነዚህ ክቡራን መሪዎች ስሪት እና ውጤት (መሬት) መሆኑን ዘንግቶ ያስረከቡትን አገር ለማፍረስ ብዙ ጥሮ እምቢ ሲለው (ግማሹ ተሳክቶለታል) በመጽሐፍ መልክ ክቡር ስማቸውን አቆሸሻቸው። የአገራችን ገጠሬ ኗሪም የሰው ስጋ መብላት ብርቅ አይደለም፤ ልምዳቸው ነው ብሎ አገራችንን አዋርዷል።

የራሳቸው መሪ ሃማ ቱማ (እያሱ አለማየሁ) ግን አጋረዊ ክብርን የሚነካ ስም በማጥፋት በመጽሐፍ መልክ ጽፎ፤ ያውም ምርጥ ‘የአፍሪካ መጻሕፍቶች’ መካከል ተመርጦ “ቢቢሲ/BBC” ተብሎ በሚታወቀው አለም አቀፍ ራዲዮ/ቲቪ/ ጣቢያ ላይ በየቀኑ ከተነበቡት እና ከተሸለሙት (ኢትዮጵያ ውስጥም በአማርኛ ተተርጓምል ይባላል ?) ታዋቂ አለም አቀፍ መጽሀፍ ሆኖ ተምርጧል። ፈረንጆች የኢትዮጵያን ነገሥታት እና አገራችንን ክብር የሚያዋርድ መጽሐፍ በኢትዮጵያዊ ዜጋ ሲቀርብላቸው “መጽሐፉን ለምን ተመረጠ” ብለን ጥያቄ የምናቀርብ አይመስለኝም። በጣም ግልጽ ነው። ተስፋዬ ገብረአብ የተባለው ሻዕቢያ ምናልባትም ከዚህ ሰውየ ጽሑፍ የቀዳው ይመስለኛል ፤ስለ ቆሪጥ የቀባጠረው፤ ስለ ኦሮሞ አማራ የቀባጠረው መጽሐፍ ከነ ዋለልኝ፤ ከነ ኢሕአፓ መሪዎች ጽሑፎች ይመስለኛል። ተስፋዬ ገብረአብም ‘የቢሸፍቱ ቆሪጦች” እያሉ የኢትዮጵያ ጠላቶች የፈጠሩት የልጆች መሳቂያ የሆነ የጨቅላ የፈጠራ ወሬ እያቆነጃጀ በሻዕቢያነቱ መጽሐፍ ጽፏል። ኢያሱም ከዚያ በባሰ መልከኩ በሚከተለው መጽሐፉ አገራችን እና መሪዎቻችን በሃሰት ስማቸው አጥፍቶአቸዋል። የኢያሱ ዓለማዮህ (ሃማ ቱማ) መጽሐፍ እንዲህ ይላል።

የሚባለው መጽሐፍ ነው።
 
<<“When the wife of the late emperor, Menene herself, was sick, her favorite spirit had called for human hearts in order to get her well and the king, whom leaders of westeren countries eulogized as enlightened, did not hesitate to order his special servants to bring the hearts. Scores of copes were discovered on the streets of Harar, all of them with hearts ripped out.”>>

<<” Empress Zewditu, whom the late emperor overthrew and some say poisoned, used to wash in the blood of black people since her Zar ordered her to, as to prolong her life.”>>

<< “I am sure that even you must have heard that the late emperor himself had a spirit called “Korit” in the Bishoftu Lakes to wich he gave young virgin boys as sacrifice. ..”>> (page 180 -Hama Tuma - The case of the Socialist witchdoctor and other stories (Hama Tuma 1993- second edition 2010 by EWFA- WWW.SBPBOOKS.COM)

<< “The son of Ras Mesfin,, a landlord who had died during the revolution used slaves for target practice…..”>> The Church, wich teaches that all men are created equal, never excommunicated anyone for owning slaves or killing them.”>>

<< “…..once resolved to kill, the ordinary Ethiopians is a deadly creature. Cunning and merciless. The man tracked the slave, lured him into thebushes on a pretext, stabbed him to death, cut his stomach open and pulled out the liver. Wrapping the liver in a piece of cloth, he washed his hands in the stream and brought back the liver to his mother-inlaw, who ululated in a low voice, praised his devotion and courage and took the liver into the hut where his wife was lying.

He never asked what happened to the liver. Did she eat it or tie it to his body? He never wanted to know. His wife got well and subsequently she gave birth to a girl much to his disappointment. The man changed after that; he became withdrawn, avoid sleeping with his wife, never kissed or touched his daughter and increased his intake of arak…………

…to kill a slave (for such purpose) is not such a big deal in a rural Ethiopia.” (Page 181-182) Hama Tuma (The case of the Socialist witchdoctor and other stories (Hama Tuma 1993- second edition 2010 by EWFA- WWW.SBPBOOKS.COM)

ክቡራን ሊቀሊቃውንቶች ወንድሞቼ እና እህቴ ይህንን ክርክሬን መዝናችሁ የድጋፍ እና የማበረታቻ ደብዳቤ ጽፋችሁ ሕዝብ እንዲያውቀው ስላደረጋችሁ፤ በኢትዮጵያዊ ደምብ ወደ ልዕልቲቱ እናት ኢትዮጵያ መሬት  ዝቅ  ብየ ክቡር ጫማችሁን እሳለማለሁ። አመሰግናለሁ። እንዳከበራችሁኝ- እግዚአብሔር ያክብርልኝ። 

እናታችን ኢትዮጵያ እግሯ ላይ ወድቀው የሚሳለምዋትና የሚያከብሯትም ሆነ የሚያዋርድዋት ልጆች ወልዳለች። የናት ሆድ ዥንጉርጉር!

ጌታቸው ረዳ ኢትዮጵያን ሰማይ ድረገጽ አዘጋጅ) getachre@aol.com