Tuesday, April 21, 2015

ኳስ ጨዋታና ፖለቲካ -ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ 
Professor Getachew Haile
ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ
ከድረገጹ አዘጋጅ ማስታወሻ፦

ከዚህ በታች የታተመው ጽሑፍ፤ በአለም አቀፍ የታወቁት የኢትዮጵያ ብርቅዬ ዑንቅ ኢትዮጵያዊው ምሁር የፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ ሃተታ ነው። ጽሑፉ ከዚህ በደራሲው እንደተገለጸው በጽሑፋቸው ያነሱት አብይ የመከራከሪያ ሃተታ፤ ሁሉም ኢትዮጵያዊ የሚከራከርበት ቁም ነገር ነው። ሃተታው “ትግሬዎች በዘመነ ወያኔ ተጠቅመዋል” ባይ ናቸው። እኔም የሳቸውን ሃሳብ የምደግፈው ክርክር ነው።

ጽሑፋቸው ወደ “ኢትዮ-ሚዲያ” ድረገጽ ተልኮ፤ በአዘጋጁ በትግሬ ብሔረተኛው “በአብርሃ በላይ” እምቢተኝነት በሕዝብ እንዳይነበብ የታገደ ጽሑፍ ነው። አብርሃ በላይ የጸረ-ኢትዮጵያ ተገንጣይ ቡድኖች የነ ኦነጎች እና የቅርብ ወዳጁ የነብርሃኑ ነጋ ደጋፊ ቡድኖች፤ እንዲሁም የጥቂት ስብስብ ሊሂቃን ቡደኖች ጽሑፍ በማሸብረቅ ሲያትምላቸው፤ የበርካታ ምሁራን እና አገር ወዳዶች የክርክሮች ጽሑፍ ባለማተም የታወቀ “ጠባብ ብሔረተኛ” መሆኑን በብዙ ሰዎች የተተቸ ነው።  ስለዚህም አልገረመንም! አዘጋጁ አላትምም ብሎ በማፈኑ ከወየነ ሚዲያ አፈና የባሰ አሳፋሪ ጠባብ ብሔረተኛነቱን የሚያጋልጥ ባሕሪው ከመሆን አልፎ እሱም ሆነ፤ “ትግሬ በዘመነ ወያነ ተጠቃሚ አይደለም” የሚሉ ተከራካሪዎች በደፈና ከመካድ በቀር “አንዳችም የመከራከሪያ ነጥብ” እስካሁን ላቀረብናቸው እልፍ ሰነዶች እየተቹ በመረጃዎቻችንን ሊያፈርሱት አልቻሉም። የትግሬ ብሔረተኛነቱን ለማንጸባረቅ፤ “ትግሬ አልተጠቀመም” የሚሉትን “የትግሬ ለማኝ አዲስ አበባ አይቻለሁ” ከሚሏት አንዲት ደካማ የመከራከሪያ “ነጠላ ሐረግ” በቀር ያቀረብናቸውን  ሰነዶች መመከት ያልቻሉትን የፕሪፌሰር መስፍን ወልደማርያምን ጽሑፍ ሲያትም “ተጠቅሟል” የሚል መከራከሪያ የያዙት የፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ ጽሑፍ ግን አፍኖ ህዘብ አንዳይከራከርበት አድር ል። “ትግሬዎች ተጠቅመዋል” ብልን ያልን ተከራካሪዎች በእኔ እና በአቶ ተክሌ የሻው የቀረበ ሰነድ ለማንበብ በዚህ ይመልከቱ (ጽሑፉ በዚህ Ethiopian Semay ብሎግ ላይ ከዚህ በፊት ትምህርት፤ጤና፤ፋብሪካ፤የመሬት መስፋፋት….በትግራይ ከሌሎቹ ንጽጽር የሚተነትን ታትሟል ። እሱን ያንብቡ። በዕውነት  ፕሮፌሰር መሥፍን እንደሚሉት ፣የትግራይ ሕዝብ  በወያኔ አገዛዝ ተጠቃሚ አይደለም? http://ethiopiansemay.blogspot.com/2014/06/blog-post_9.html) ስለዚህም አብርሃ በላይ ይህንን የመጻፍ ነፃነት ሲያፍን አስቀድሞ ሲያገለግለው ከነበረው ከወያኔው ስርዓት የተማረው “የፕሬስ አፈና” ባሕሪ፤ ውጭ አገር መጥቶ አንደገና ያንን አፋና በተቃዋሚዎች ላይ መድገሙ፤ በቅርብ ለተከታተልነው ሰዎች አልገረመንም። የፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ ጽሑፍ ለማንበብ ከዚህ በታች ያለውን ያንብቡ። መልካም ንባብ።

 1
ኳስ ጨዋታና ፖለቲካ

ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ
Professor Getachew at Haile Selassie University graduation day interpreting the King's speech to Dutch language for Dutch guests
ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ
ማስታወሻ፤
ፕሮፈሰር መስፍን ወልደማርያም የትግራይ ሕዝብ በወያኔ አገዛዝ አለመጠቀሙን ለማሳየት ኢትዮሜዲያ ላይ አንድ ጽሑፍ አውጥቶ ነበር። ይህ የኔ ድርሰት የዚያ ተቃራኒው አስተያየት ስለሆነ መውጣት የሚገባው፥ እዚያው ኢትዮሜዲያ ላይ ነበር። ግን የኢትዮሜዲያ ባለቤትበዚህ ድርሰትህ የትግራይን ሕዝብና ሕወሐት/ኢሕአዴግን አንድ አድርገሃቸዋል (“. . . TPLF a synonym with the Tigrai people.”) ብሎ ሊያወጣው አልፈቀደም። በእኔ አስተሳሰብ ይኸ ድርሰት ወያኔንና የትግራይን ሕዝብ አንድ አያደርግም።

ወደ ተነሣሁበት ልመለስና፥ እግር ኳስ ጨዋታ አጥብቄ እወዳለሁ። እንግሊዞች ፉትቦል፥ አሜሪካኖች ሶከር የሚሉትን ጨዋታ ማለቴ ነው። አሜሪካኖች ለምን ሶከር እንደሚሉት ምክንያቱን ለማወቅ አልሞከርኩም፥ አላሰብኩበትምም። በዚህ ጨዋታ ፍቅር የተነደፍኩት፥ በልኩ እንዳደርገውም ብዙ የተቀጣሁበት፥ ገና ፊደል ስቆጥር ነው። ለብዙ ነገሮች ያለኝ ፍቅር እየቀዘቀዘ፥ እየጠፋም ሲሄድ ለኳስ ጨዋታ ያለኝ ፍቅር ግን አሁንም ትኩስ ነው። ዛሬ መጫወት ባልችልም፥ ዋናዋናዎቹን የእንግሊዝና የእስፓንያ የጨዋታ ኅብረቶች (English Premier League and Liga BBVA) ጨዋታቸውን በቴሌቪዠን እከታተላለሁ። እንግሊዞች በጦርነት ጊዜ ለኳስ ጨዋታ ያህል ጦርነት ያቆሙ ነበር የሚሉት ተረት እውነትነት ቢኖረው አይገርመኝም። የወያኔ ባለጸጎችም የእንግሊዝ አገር የእሑድ ቅዳሜን ኳስ ጨዋታ ለማየት እንግሊዝ አገር ድረስ በረር ብለው የሚመጡትም የፍቅር ጉዳይ ሆኖባቸው ነው--እኛ በልጅነታችን አዲስ አበባ ካምፖሎጆ (“ካታንጋየሚባል ስም ከወጣለት ቦታ) ሄደን ተጋፍተን እንደምናየው ማለት ነው። የመግቢያ ዋጋ መክፈል ከቻልኩ ጀምሮከካታንጋጋር ተለያይተናል።

 አሁን ከፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም፥ አንዳንዴም ከአቶ አርአያ አሰፋ ጋር፥ የሳምንቱ የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ስቱዲዩም አዘውታሪ ሆኜ ነበር። እንዲያውም ለዚህ ጽሑፍ መንሥኤ የሆነኝ ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያምየወያኔ ጥላቻ ፍሬበሚል ርእስ በቅርብ ጊዜ በኢትዮሜዲያ ያቀረበው አስተያየት ነው። መስፍን ጽሑፉን፥ወያኔ ለትግራይ ሕዝብ ሀብትንና ብልጽግናን አመጣ ብለው የሚያምኑ ሰዎች ብዙ ናቸው፤ ወያኔ የሥልጣን ወንበሩ ላይ በመውጣቱ ትግሬዎች ሁሉ አልፎላቸዋል ተብሎ ይታመናል፤ በተለይ በአውሮፓና በአሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በዚህ ላይ የጠነከረ እምነት አላቸው፤ . . . የትግራይ ሕዝብ መደህየቱ አልበቃ ብሎት ሲለምንም እየተሳቀቀ ነውበማለት ይጀምራል። ጥቂት እልፍ ብሎ፥ትግሬነታቸው ብቻ እንዲህ የደላቸው በጣም፣ በጣም ጥቂቶች ናቸው፤ ስለዚህ በወያኔ አገዛዝ ትግሬ ሁሉ ተጠቅሞአል ማለት ከጉልህ እውነት ጋር የሚጋጭ ስሕተት ነውይላል።

 እንደ መስፍንንትርክባልለውም እርግጥ በጉዳዩ ብዙ ቁም ነገር የሞላበት፥ ማስረጃ የቀረበበት ውይይት አንብቤያለሁ። ከሳሾቹ ብዙ ማስረጃ ስለሚደረድሩ፥በወያኔ አገዛዝ የትግራይ ሕዝብ አልተጠቀመምየሚሉ የወያኔ ደጋፊዎች ብቻ መስለውኝ አላመንኳቸውም ነበር። የመስፍንን አቋም ስለማውቅ፥ ጽሑፉን 2 ሳነበው ማሰብናተሳስቼ ይሆን እንዴ?” ማለት ጀመርኩ። የትግራይ ሕዝብ ሳይጠቀም ተጠቅሟል፥ እየተጠቀመ ሳለ አልተጠቀመም ማለት ከሁለቱ አንዱ ይቅርታ የሚያስጠይቅ ትልቅ ወንጀል ነው። በእኔ በኩል፥ ወያኔዎች ብዙ ሰው ደሙን አፍሶ የታገለለትን ዲሞክራሲን በማፈን የኢትዮጵያን ሕዝብ ስላሳቀቁት፥ በፍጹም ጥላቻ እጠላቸዋለሁ። ሆኖም የመስፍንን ድርሰት ሳነብ፥ ጥላቻዬ እውነቱን እንዳላይ ዓይኔን ጋርዶት ይሆን ብዬ፥ ቆም ብዬ መረጃዎቼንና አቋሜን መመርመር ጀመርኩ።

የወያኔ ተቃዋሚዎች ያቀረቧቸው መረጃዎች ያሳደሩብኝን እምነት በጀመርኩት የኳስ ጨዋታ ምሳሌነት ልግለጽ። ከፕሮፌሰር መስፍን ጋር ብዙ ጊዜ በሀገር ጉዳይ እንከራከር ነበር። እንደማስታውሰው፥ የተለያየ አስተያየት ይዘን ተነሥተን ውይይታችንን በተመሳሳይ አስተያየት ላይ እንጨርስ ነበር። አሁንም እንደግመው ይሆናል።

የክበብ ቡድኖች ኳስ ጨዋታ የወያኔን ፖለቲካ ለመረዳት አስተዋፅኦ አለው። የአንድ ቡድን አባላት፥ ሁሉም ከቡድኑ አባቶች ጀምሮ፥ በከፍተኛ ደረጃ ይግባባሉ። አይጥ (ጎል) የሚያገባው አንድ ተጫዋች ቢሆንም፥ ውጤቱ የሁሉም ጥረትና ተራድኦ አለበት። ጥቅሙም የሞላ ቡድኑ ስለሆነ፥ ደስታውም፣ ጭፈራውም፥ ሽለላውም አብሮ ነው። የቡድን አባቶችን የሚመርጡት አባላቱ ናቸው--በዘመድ ሳይሆን በችሎታው። ማንም ተጫዋች የራሱን ቡድን የሚጎዳ ጨዋታ አይጫወትም፤ ጥቅም ያስቀራል፥ መልቲነት ያለበት ተጫዋች ቢኖርባቸው ሥራው በግላጭ በአደባባይ ስለሚታይበት ወዲያው ይባረራል።
በግላጭ የሚያዩ የቡድኖች ደጋፊዎች ሁሉ ናቸው። እነሱም ጥቅመኞች ናቸው። በቡድኑ ጨዋታ የሚደሰቱት ወይም የሚያዝኑትና የሚቆጡት ስለዚህ ነው። መቸም ጥቅም በወርቅ ብቻ አይገመትም። እንዲያውም እኮ ወርቅ ለጥቅም መግዢያ እንጂ ራሱ ብቻውን ከጌጥነት ያለፈ፥ ብዙ ጥቅም የለውም።

የአንድ የኳስ ቡድን ጥቅመኞች ምን ያህል ብዙ እንደሆኑ እናስብ። ለምሳሌ፥ የእንግሊዝ ፕሬሚየር ሊግ አባል ቡድኖች ደጋፊዎቻቸው፥ እንደ ወያኔ መኳንንት ኢንግላንግ ድረስ እየበረሩ ለማጨብጨብ የሚያስችል የተዘረፈ ወርቅ ባይኖራቸውም፥ ብዛታቸው እስከ ዓለም ዳርቻ ይደርሳል። እንግሊዝ አገር ለተደረገ ጨዋታ ዓለም ዳርቻ ያሉ ደጋፊዎችና ተቃዋሚዎች እስከመፈናከት የሚደርሱበት አለ። ቡድኑ ደጋፊዎቹን እንዳያስቀይም ብዙ ይጠነቀቃል። ካስቀየመ፥ ደጋፊ ያጣል፤ ይወድቃልም።

ጥቅመኞቹ የጥቅም ደረጃቸው የተለያየ ነው። ለምሳሌ፥ ቡድኑ የክበብ ቡድን ከሆነ፥ የቡድኑ ባለቤት ገፈፉን ያነሣል። ተጫዋቾቹ ጥቅማቸውን የሚረከቡት የተገዙ ዕለት ነው።የጨዋታ ቡድን ባለቤት አለውማለት፥ ባለቤቱ ከፈለገ፥ ምንጊዜም ይሸጠዋል፥ ይለውጠዋል ማለት ነው። ተጫዋቾቹም ከየቦታው ተገዝተው የተጠራቀሙ የመርሰነሪ (Mercenary)ብጤዎች ናቸው። ጀሌው ሕዝብ ግን አንድ ቡድን የሚደግፈው ቡድኑ ብሔራዊ ወይም የሱ ስለሆነ ሳይሆን፥ የሱ መሆኑን በጭፍን አምኖ ነው--በእምነት ብቻ። አለዚያማ፥ አዲስ አበባ ላይ ሆኖ ለሊቨርፑል ማጨብጨብ ትርጉም አይኖረውም።

እስቲ በዚህ አንጻር ወያኔዎችንና ደጋፊዎቻቸውን እንያቸው፤ ወያኔ እንደ አንድ የኳስ ቡድን ነው። እያንዳንዱ አባል የገንዘብ ጥቅመኛ ነው፤ ማስረጃዎቹ እንደሚያመለክቱት፥ ሁሉም አይበለጽጉ መበልጸግ በልጽገዋል። ራሱ ቡድኑም ቢሆን ለገንዘብ የተገዛ ነው ይባላል። በየደረጃው የሚጠቀሙ ጥቅመኛ ደጋፊዎች አሉት።ገዢዎቹ የወንዛችን ሰዎች ናቸውማለቱ ብቻ የሚያረካቸው ሞኞችና አደገኛ ጥቅመኞች ጥቂት አይደሉም፤ ይኸም ጥቅም ነው ማለት ነው። ዋናው ጥቅም ግን የተመሠረተው በኢኮኖሚው ላይ ነው። የውስጥና የውጪ ዐዋቂዎች እንደሚነግሩን፥ የሀገሪቱ ኢኮኖሚ በወያኔ ደጋፊዎች እጅ ተይዟል። የመንግሥት ቁልፍ ሥራ የሚሰጠው ለትግራይ ተወላጆች ነው። አንድ ሰው ሥራ ሲጠይቅ የሥራ ማመልከቻ ይሰጠዋል። በማመልከቻው ላይ ችሎታውንና ዘር ማንዘሩን እንዲመዘግብ ይገደዳል፤ ማንነቱን ይናዘዛል። በዚህ ዘዴ ለአድልዎ ይጋለጣል።

መለስ ዜናዊ፥አይሁድ የአሜሪካን ኢኮኖሚ እንደያዙት የትግራይ ልጆችንም የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ አሲዛቸዋለሁብሎ የፎከረው በፉከራ አልቀረም። ኢኮኖሚውን በጠቅላላ የሚያንቀሳቅሱ የትግራይ ወጣቶች በጥድፊያ እየተዘጋጁ ነው። በመንግሥት ሀብት ወደ አሜሪካና ወደ አውሮፓ ስመ-ጥር ዩኒቨርሲቲዎች የሚላኩ ተማሪዎች የትግራይ ተወላጆች ናቸው። እነሱ እስኪደርሱ፥ አንዳንዱን ሥራ ሌሎች ይዘውት ብናይ ሌሎችም ተጠቅመዋል አንበል። ቦታ ጠባቂዎች ናቸው። የትግራይ መሬት ጠፍ ስለሆነ፥ በሰቲት ሁመራ፥ ወልቃይት ጸገዴ ትግራይ ሆነዋል። ከዚያ የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች ያልሆኑ ገበሬዎች ተባርረው የርሻ መሬታቸውን የትግራይ ተወላጆች ወርሰውታል። የአዲስ አበባ ነዋሪዎች በመብራት እጥረት ምክንያት በጨለማ በዳበሳ ሲያመሹ፥ ትግራይ ውስጥ እንዲህ ያለ ችግር ከተወገደ፥ ዓመታት አልፈዋል። ይህ ሁሉ ሐሰት ከሆነ፥ አቋሜን እለውጣለሁ።

እውነት ከሆነ፥ ታዲያ እንዴት ነው፥ በወያኔ አገዛዝ የትግራይ ሕዝብ አልተጠቀመም ለማለት የሚቻለው? ምናልባት የዚህ ሀገራዊ ወንጀል ዜናው ኢትዮጵያ ውስጥ ለሚኖሩት ታፍኖ፥ በውጪ አገር ለምንኖረው ብቻ ተከሥቶ ይሆን? ሁኔታው የጠበንጃ ጠባይ ተገላቢጦሽ ሆነብኝ። ጠበንጃ ድምፁን ማሰማት የሚጀምረው ተኳሹ ከቆመበት ቦታ ሆኖ፥ የሚመታው ርቆ ሄዶ ነው። የወያኔ አድላዊነት አዲስ ነገር አይደለም። ኢትዮጵያ ውስጥ አልታፈነም። የወያኔ ጥረት፥ትግራይ እስክትለማ ኢትዮጵያ ትድማመሆኑ ውጪ ሀገር ለምንኖረው የደረሰን ኢትዮጵያ ውስጥ በሰፊው ተነግሮ ነው።

መቸም አንድን ሕዝብ በአንድ ትውልድ ከዳር እስከዳር ማበልጸግ አይቻልም። መስፍንትግሬዎች ሁሉእያለሁሉ የሚደጋግማት ስለዚህ ከሆነ፥ እንስማማለን። እንዲያውም፥ሁሉከቁም ነገር አይቈጠርም፤ ለመወያያ ርእስነት ብቃት የለውም። ሁሉም ቀርቶ፥ ዘጠና በመቶው የትግራይ ሕዝብ እስኪያልፍለት ድረስ እንኳን ገና ብዙ ጊዜ ይፈጃል። ጅማሮው ግን ተጀምሮ እየገሠገሠ ነው። ፍሬ ማፍራትም ጅምሯል። እስከዚያ ብዙ ትግሬዎች እንደብዙ ሌሎች ኢትዮጵያውያን ድኾች ሲለምኑ መታየታቸው አይቀርም። እትግራይ ውስጥ ቀርቶ፥ በብልጽግና በዓለም አንደኛውን ደረጃ በያዘችው አሜሪካን አገር እንኳን ለማኞች ሞልተዋል። ተአምራዊ የኢኮኖሚ ሥርዓት ካልመጣ በያዝነው ሥርዓት፥ እስከተጓዝን ድረስ፥ ክርስቶስ፥ድኾች ሁል ጊዜም ከማህላችሁ ይኖራሉያለው፥ የማይሻር ቃል ሆኖ ይኖራል።

በወያኔ አገዛዝ የትግራይ ሕዝብ አልተጠቀመምየሚል እምነት ያለው ሰው ማስረጃው የትግራይ ለማኞች በመንገድ ላይ ማየት ከሆነ፥ አንድ የትግሬ ለማኝ ከብዙ ኢትዮጵያውያን ለማኞች ማህል እስከተገኘ ድረስ፥ በእምነቱ ሊጸናበት ይችላል። ዋናው ቁም ነገር ግን እንዲህ ነው፤ የወያኔ አገዛዝ ለትግራይ ሕዝብ ያደላል ወይስ አያደላም። አያደላም ለማለት የዓይን ምስክሮችን መካድ፥ መለስ ዜናዊንም ውሸታም ማድረግ ይሆናል።ለትግራይ ማዳላትስ አዳልተዋል፤ ግን ሕዝቡ አልተጠቀመምማለትም ይቻል ይሆናል። ግን እንዲህ ያለውን ተቃራኒ አስተሳሰብ ማስታረቅ ቀላል አይሆንም። እያዳሉለት ባይጠቀም፥ ወያኔዎችን ከማዳላት ወንጀል ነፃ አያወጣቸውም። ማዳላት አንዱን ጠቅሞ ሌላውን ጥቅም መንሳት ነው።

ማዳላት አደገኛ በሽታ ነው። ፍሬው ጥላቻ ነው። የተዳላበት ወገን ዳኛውንም የተዳላለትን ወገንንም አብሮ መጥላት፥ ከዚያም አልፎ ማቄምና ክፉ ነገር ማሰብን ያስከትላል። የትግራይ ሕዝብ አልተጠቀመም ማለት የትግራይን ሕዝብ አስጠልተውታል ማለት ከሆነ፥ እኔም እስማማለሁ። ጥያቄው ይኸ ከሆነ፥ በእንደዚህ ያለ ጊዜ፥ይህ ሁኔታ እኮ የወንድማማቾችን መተላለቅ ያስከትላልብሎ መሥጋትና በፍጥነት መፍትሔ መፈለግ የማንም ኢትዮጵያዊ ግዴታ መሆን አለበት። ለጥፋቱ ተጠያቂው የትግራይ ሕዝብ አይደለም። የትግራይ ሕዝብ፥እኛ የምንፈልገው ዕድላችን እንደጥንቱ ከሌላው ሕዝብ ጋር እኩል እንዲሆን ነውቢል የመሪዎቹን አርጩሜ አይችለውም።

እስታሊን የሶቪየት ዩኒዮንን በቴክኖሎጂ ለማራመድ ያደረገውን እናውቃለን። ራሳቸው ትግሬዎቹም ወደመጀመሪያው ላይ ቀምሰውታል። (“ፋሺዝም በትግራይየሚለውን የጋዜጠኛ ሪፖርት እናስተውሳለን።) ስለዚህ ትኵረቱ መሆን ያለበት በደላቸውን እንዲያቆሙ ምክር በሚገባቸው በወያኔዎቹ ላይ ነው። ወያኔዎችና ደጋፊዎቻቸው የኢትዮጵያ ሕዝብ በሰላም እንዲኖር ከፈለጉ (ለመፈለጋቸው ምንም ምልክት አያሳዩንም) ዕርቅ ለማምጣት ዕድሉ ገና አላመለጠም። ብቻ የሚያሳዝነው፥ ኋላ ቀር ፖሊቲከኞች የሚነቁት ዕድሉ ካመለጠ በኋላ ነው። ቅዱስ ዳዊት፥ስሕተትን (በጊዜው) ማን ልብ ይላታልሲል ደምድሞታል።

ወደኳስ ጨዋታው ልመለስና፥ የወያኔ ቡድን አንዳንድ ጊዜ በራሱ ጎል ላይ አይጥ ያስቆጥራል። ባለቤቱን (ኢትዮጵያን) ስለከዳ፥ የባለቤቱን ጥቅም ያላንዳች ይሉኝታ ያዝረከርካል። አገሪቱን ወደብ-አልባ ማድረግ፥ መርከቦቿን መሸጨ፥ ጎሳዎችን ማጋጨት፥ አገር መከፋፈል፥ በኢትዮጵያ ሀብት የሌላ ሀገር ባንክ ማበልጸግ፥ ዓባይን ለመገደብ ካይሮ ድረስ ሄዶ ማመልከቻ ማቅረብ ሁሉ በራስ ጎል ላይ ኳስ ማስገባት (አይጥ-በላ መሆን) ነው። Posted at Ethiopian Semay - you can send your comments getachre@aol.com