አፋቸው እንደ ባሕር ኦይሰተር የሚከፍቱ የአብይ አሕመድ አዘጥዛጭ ጋዜጠኛ ሁላ
መለዮ ለባሹን ለማስረሸን ያልፈነቀለው ድንጋይ የለም
ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay)
በጥቂት ወራት ውስጥ ለጠንቋይ በሚያስችግር እንቆቅልሽ በዓረቦች
እና በውጭ ሃይላት ተደግፎ “ሽልማት በሽልማት” የተጥለቀለቀው ፥ ሥልጣን ላይ ተኮፍሶ የሕዝብ አንገት በገጀራ እየተቀላ ሕዝብ እየተፈናቀለ ‘በቃላት ከመፈላሰፍ
እና ከጥገና ውጭ’ መሰረታዊ ለውጥ መምጣትን የሚቃወም ፥ ከፋሺስት ሥርዓት ፍቅር መላቀቅ ያቃተው አብይ አሕመድ የተባለ የወያኔ/ኢሕዴግ ኮለኔል፤ በሚቦተልከው ‘አፍዝ ወ አደንዝዝ’ ሥርዓተ አልባዊ
“የመደመር ፖለቲካ” በመደንዘዝ የነፈዘ ጋዜጠኛ ተብዬ ሁላ ሰሞኑን ወታደሮች አብይ ወደ አለበት ቤተመንግሥት
ብረት ታጥቀው ጥያቄአቸውን ለምን አቀረቡ ብለው በምስኪን ወታደሮቹ ህይወት ላይ የወታደራዊ ፍርድ ቤት ቀርበው ሞት እንዲፈረድባቸው
እስከመድረስ የቃጣቸው አቃጣሪ ጋዜጠኞች እንደ አሸን ፈክተው 24 ሰዓት ሙሉ በወታደሩ ሲረባረቡ ማድመጥ በጣም የሚገርም ነው።
አብይ እራሱ ማን ነው? በሕዝብ ድምጽ የመጣ አይደለም! አይደለም
እንዴ? ንገሩን እንጂ? ኣእላፍ ነብሳት እያጠፉ ፥ በእሳት እና በጋለ ብረት ሰውን እየጠበሱ፥ በወታደራዊ ግልበጣ የመጣ ወታደራዊ መንግሥት በብረት ሃይል ገልብጠው የበረሃ ወረበላ
የፋሺስቶች የመሠረቱት ሥርዓተ መንግሥት ላይ የተቀመጠ መሪ ነው! አይደለም እንዴ? ጋዜጠኛ ተብየ ይህንን እያወቁ
እንደ “የባሕር ኦይሰተሮች” አፋቸውን ከሚገባ በለይ የሚከፍቱ በወታደሩ ላይ ሲመጻደቁ ማድመጥ የሚገርም ብቻ ሳይሆን ከመገረም በላይ
የሆነ እኛ ትግሬዎች “መርመም” የምንለው ዓይነት መገረም
ፈጥሮብኛል።
ይህ ወታደር የተንገላታ ነው። ደሞዝ አነሰኘ ብቻ ሳይሆን ዘብ
ላይ ቆሞ በረሃብ አለንጋ እየተገረፈ “ዘብ እንዲቆም የተደረገ ክፉ ስራ የተፈጸመበት ወታደር ነው”። ለአንድ ወር የማይሞላ
ከከተማ ወደ አንድ ከተማ ያውም የአገር መሪዎች ባለቡት ከተማ፤ ለሥራ ጉዳይ ጊዜአዊ ምደባ ተመድቦ በረሃብ እንዲሰቃይ ያደረጉት
እሩቅ “ጦር ሜዳ በረሃ ውስጥ” ቢልኩት ኖሮ ምን ያህል የርሃብ ስቃይ ይደርስበት እንደነበር መገመት ያቃታቸው ነፈዝ ጋዜጠኞች በወታደሩ
ላይ እንዲህ ሲተቹበት የሚገርም ብቻ ሳይሆን “መርመም” ነው”።
እንዴት ተብሎ ነው? ለምንስ ይጠቅማል ብሎ ነው? በነዚህ ወታደሮች
ላይ ጋዜጠኛ ተብየ የወያኔ ሕገ መንግሥት/ወንጀለኛ መቅጫ ወዘተ…እያጣቀሰ ላሃጩን በማዝረክርክ በወታደሩ ላይ የሕግ አንቀጽ እያጣቀሰ
እስከ ሞት ድረስ እና እስከ ሥራ ማባረር እንደሚያደረስ ለግፈኛ እና ለወያኔ ፋሺስታዊ ወታደራዊ ዳኞችችን ለኮርት ማርሻል
ብትር እያቀበለ ያለው? በእነዚህ ወጣት ወታደሮች እና አዛዦቻቸው ቤተሰብ ላይ የሥራ እና የሕይወት ፈተና እንዲወድቁ አፍ እስኪቀደድ
ድረስ “የብዕር ባሩድ” እያዘነበ ለመከራ ሊዳርጋቸው የፈለገው ጋዜጠኛ ተብየ ምን እሚሉት ግበረገብ ነው እንዲህ የተረባረበበት?
እነዚህ ጋዜጠኞች ተብየዎቹ ምንስ እሚሉት አንጀት ሲኖራቸው ነው ቤተሰቦቻቸው ለስቃይ እንዲዳረጉ ለቅጣት እየገፈፉዋቸው ያሉት? ወታደራዊ
ሕግ ማለት “ፋሺሰት ማለት ነው” ይቅርታ የለውም። የአርማጌዶን፡የገሃነብ ሕግ እና ባሮች የሚቀጡበት ሕግ አልባ እና ጨካኝ ድርጅት
ነው!! ወታደር መሆን አያስመኝም።፡ታዲያ ጋዜጠኞች ተረብየዎች ሕግ ጠቃሾች ሆነው ሲመጻደቁባቸው ማየት የሚገርም! የሚገርም! ነው።
አብይ እራሱ የተቀመጠበት ቤተመንግሥት የትኛው እና ምን የሚመስል
ሕገ መንግሥት ተደፍሮ ነው ሕግ ተደፈረ/ወታደራዊ እዝ ሰንስለት ተደፈረ… የምትሉት? የማን የሕግ እና ወታደራዊ እዝ ሰንሰለት ነው
የምታወሩት? የ ሳዓረ መኮንን? የወያኔ? የኮሎኔለ አብይ አሕመድ እዝ ሰንሰለት? ሕግ ቢኖር ሁለት መንግሥት አለ ሲባል ጀሮ ዳባ ያለው መሪ ነው “ቤተመንግሥት/ሕግ/ተደፈረ”
የምትሉት? ትጥቅ አንፈታም ያለው አሸባሪው እና ጸረ ኢትዮጵያ ጸረ አማራው ኦነግ ‘በግልጽ” ትጥቄን አልፈታም ሲል “የአፍ ወለምታ ነው” ብሎ ሽፋን ለሚሰጥ መሪያችሁ ነው
የመሪያችን ቤተመንግሥት ተደፈረ ብላችሁ ያዙኝ ልቀቁኝ ብላችሁ በወታደሩ ላይ የተረባረባችሁባቸው?
እናንተ ብረት ብትይዙ ኖሮ እንኳን ቤተመንግሥት ገብቶ ምግብ
እና ደሞዝ ጥያቄ ማቅረብ “ወያኔን/መለስ ዜናዊን/ደሳለኝ ሃይለማርያምን’ በጉሮሮው አንቃችሁ ታስወጡዋቸው አልነበረም? ወታደሮቹ
ጠመንጃ ስለያዙ ብርቅ ሆኖባችሁ “ቤተመንግሥት ድረስ ሄደው በሚገርም ብልሃት እና ቁርጠኛነት” ጥያቄአቸውን ለሥርዓተ አልበኛው ጠቅላይ
ሚኒሰትራችሁ ጥያቄአቸውን ስላቀረቡ “ሰማይ ምድር ተገለባበጣችሁ” እይደል?። የትኛው ስሞታ ሰሚ ክፍል ኖሮት ነው ‘ወያኔ’ በእዝ
ሰንሰለት ስሞታቸው ማቅረብ ነበረባቸው እያላችሁ እንዲሰቀሉ የምትፈርዱባቸው?
እኔ እማ የምለው “ቁርጠኛ እና አገር ወዳድ ወታደር ከመሃላቸው ቢፈጠር ኖሮ
ወያኔያዊው መሪያችሁ ባስወገዱልኝ እና የኢትዮጵያን ሰነደቅ ተክሎ “ኦኖጎችን” አባርሮ የአፓርታይዶችን የክልል ባንዴራ “ሁሉንም”
ባንዴራ አቃጥሎ ወታደራዊ አዋጅ የሚያውጅ ቢሆን ኖሮ ደስታውን ባልቻልኩት! ያኔ ምድረ ተደማሪ ካልሲሽን ከተኛሽበትን ሆቴል
ጥለሽ እግሬ አውጪኝ ብለሽ ወደ አሜሪካሽ እና ወደ ለንደንሽ በፈረጠጥሽ እና በሳቅኩኝ ኖሮ። አሁንም የጊዜ ጉዳይ እንጂ እንዲህ
እንደማይቀጥል እመኑኝ።
ተደማሪ ሁላ በወታደሩ ሳይሆን በተደማሪው ላይ ነው መስጋት ያለብሽ። ለመሆኑ ምን አዚም ነው የጣለባችሁ? “ትጥቅ ይዞ አልፈታም” ያለውን ታጣቂ “አልፈታም አይልም ‘የአፍ ወለምታ
ነው”፡እያለ ኦኖሌ ሃውልት እንዲያቆም ፋሽታዊ ትምህርት እያስተማረ ባሳደገው ድርጀት “ኦነግ” ላይ አንጀቱ አላስችል ብሎት መጨከን
ባቃተው መሪያችሁ ላይ ‘አፍሽን ሳትከፍቺ ሰንብተሽ’ ዛሬ ምደረ ነፈዝ እንደ ማታ ጅብ በወታደሩ ላይ የሞት አዋጅ ስታስተጋባ
መስማት የሚገርም ብቻ ሳይሆን የሚገርም ‘መርመም’ ነው። የሚገርመውም
ደግሞ ‘በመፈንቅለ መንግሥት የመጣውን ወታደራዊ ሥርዓት ከመንግሥቱ ሃይለማርም ወንበር ጎን ቁጭ ብሎ ሲያገለግል የነበረ ከጦር ሜዳ ትግል የፈረጠጠ ሻለቃ ሁላ ፤ዛሬ ደርሶ ሕግ አስከባሪ ሆኖ “በወታደሮቹ’ ላይ ተቺ እና
ፈራጅ ሆኖ ስለ የወታደራዊ እዝ ሰንሰለት ደምብ እና ስነስርዓት ለእኛኑን አድማጭ ለማስተማር” ተጋብዞ ለጋዜጠኛው አድማቂ ሆኖ ሲመጻደቅ
ሰምቼው “ወይ ለታይ! ንስኺ’ውን በኔ ላይ?” (ወይ
ለታይ አንቺም በኔ ላይ?) እንዳለው ፍርድ ቤት ተከስሶ ቀርቦ “ለታይ” በምትባል ትግሬ ሴት ምስክርነት የተገረመ ‘አማርኛ እና
ትግርኛ’ የተደበላልቆበት እንደተገረመው አንድ የትግሬ ሰው እኛም “መርመም”
ሆኖብን በጋዜጠኞች “የስቀሉት ስቀሉት” የመረባረብ
ትችታቸው ተገርመናል።
ሰላም እንሰንብት!
ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay) getachre@aol.com