Wednesday, May 1, 2024

ትግሬዎች የተጠሉት በትግሬነታቸው ሳይሆን በወያኔነታቸው ነው መልስ ለልደቱ አያሌውና ጋዜጠኛ ያየሰው ሽመልስ ጌጌታቸው ረዳ 5/1/24


ትግሬዎች የተጠሉት በትግሬነታቸው ሳይሆን በወያኔነታቸው ነው

መልስ ለልደቱ አያሌውና ጋዜጠኛ ያየሰው ሽመልስ

ጌታቸው ረዳ 

5/1/24

 

ሰሞኑን ሁለቱ ታዋቂ ሰዎች አንዱ በተጋበዘበት የቃለ መጠይቅ መድረክ ሁሉ ፤ ሌላው ደግሞ በቅርቡ ባሳተመው መጽሐፍ ውስጥና በራሱ ኢትዮፎረም “ዩ-ቲዩብ” ላይ ትግሬዎች እዚህ ችግር ውስጥ ለመውደቃቸው ምክንያት እኔ ትግሬው ኢትዮጵያዊ እና ሌሎች ኢትዮጵዊያን ባካሄድናቸው “ትግሬ ተጠቃሚ ነበር” የሚለውና “ሥርዓቱም የትግሬዎች ነበር” በማለት የተከራከርንበት መስመር ምክንያት ለትግሬዎች መጠቃት ምክንያት ሆኗል። እያሉ ተጠቃሚዎቹ የትግሬ ምሁራን ልሳን በመደገፍ እኛን ተጠያቂ ማድረግ ጀምረዋል (አዲሱ ዘመቻቸው ማለት ነው)።

እነዚህ ሁለቱ ሰዎች እና እራሳቸው ተጠቃሚዎች የነበሩት 99.5 (አሃዙን ቀንሱት የፈለጋችሁ አድርጉት፤ ብቻ አብዛኛው ቁጥር በሉት) የትግራይ ምሁራን እና በርካታ ኢትዮጵያን ለትግሬዎች መከራ እራሳቸው ትግሬዎችን ከመወንጀል ይልቅ እኛኑን ተጠያቂ እያደረጉ ፕሮፓጋንዳ ሲሰሩ እያደመጥን ነው።

 ያ ብለው ሳያንሳቸው “የፍትሕ ሰቆቃ” በሚል ኦሮሙማው አብይ ሥልጣን ላይ ከወጣ ባጭር ወቅት “በትግሬ አፓርታይድ ሥርዓት እየታሰሩ አካላታቸው ሲጎድል እየተቀጠቀጡ፤ግብረሰዶም ሲፈጸምባቸው እንደነበርና ደብዳቢዎቹም “ትግርኛ ተናጋሪ ትግሬዎች” እንደነበሩና ‘ከምላሳቸው የሚወጣው መርዘኛና ዘረኛ ቃላት ታሳሪ አማራዎችን (ሰለባዎቻቸው) ምን ያህል ያሰቃይዋቸው እንደነበር’ ስለገለጹ፡ እነ ልደቱ አያሌዎና ያየሰው የተባለው አምላኪ ወያኔ “ትግሬዎች አሁን ለደረሰባቸው ጥቃትና መከራ ታሳሪዎቹ “ትግርኛ ተናጋሪዎች ናቸው የከፋ ሰቆቃ ያደረሱበን” ብለው  ስማቸው ሳይቀር በመግለጻቸው “በዛው ሰበብ ትግሬዎች ተጠቂ ሆነዋል” እያሉ እነዚህ ሁለት ሰዎች ይከሱናል።

 ‘ትግሬዎች” ላደረሱት መከራ በራሳቸው ያመጡት ሆኑን በመክዳት "ተጠቂዎቹን" መወንጀል የነዚህ ሁለት የወያኔ ወዳጆች "መደበኛ ፕሮፓጋንዳቸው" አድርገውታል። ስለም እነዚህ ሁለት ነጥቦች አንስቼ ባጭሩ እንመለከታለን። (ሰነድ ለምትጠይቁም ካስፈለገም በክፍል ሁለት በማስረጃ አቀርባለሁ። ያንን ከጠየቃችሁ)

ትግሬዎች አብዝሃውን ትግሬ ተጠቃሚና የወያኔ አምላኪ ነው ብየ እኔም የእኔንም ሃሳብ የሚጋሩ ሰዎች ባቀረብነው ሰነድ አንድም የሻረው ፖለቲከኛ አላየሁም። ለኔ ድጋፍ ሲሰጥ የነበረው የፈንቅል መሪ የነበረው “ወያኔ ያስገደለቺው” ሟቹ የማነ ገብረመስቀል ባንዳንድ ሃሳቦቹ ነገሮች ብለይም፤  <<እውነታው ሲገለጥ... ፈንቅል የወ/ሮ ኬሪያን ጉድ አዝረከረከው! || ፈንቅል በቀጥታ ||>> የሚለውን በዩቱብ አድምጡትና እስኪ ያንንም ተምልከቱት። አፍቃሬ ወያኔው ያየሰው ግን የማነን (ፈንቅል የሚባል ቡድን) የአብይ ተቀጣሪ “ጋንጎች” ናቸው ይላቸዋል በምጽሐፉ (ማስረጃው ሳየው ከሳቅ አላለፍኩም)

ያንን የኛን ሃሳብ በመጻረር የሚሰጡት መልስ ግን <<ትግሬ ብቻ አይደለም ተጠቃሚው ፤ ሌሎችም ባለፎቆችም፤ሚሊዮነሮችም እኮ አሉ>> ይላሉ (አዲስ አበባ ውስጥ <<ትግሬ ለማኞችም አሉ ብለው ፕሮፌሰር መስፍን እንደተከራከሩት ባስቂኝ ሙግታቸው (ነብሳቸው በሰላም ይረፍ)። ለዚያ መልስ የትግሬ ማሕበራዊ አገልግሎት ለያንዳንዱ ትግሬ ለማኝ ለጠቆመ ብር እንደሚከፈለውና ለማኞቹ ወደ ትግሬ ሄደው መሬትና ገንዘብ እንደሚሰጣጨው በማስረጃ ያቀረብኩትን ቪዲዮ በወቅቱ ታስታውሳላችሁ። ያ ማስረጃ አሁንም አለ። )። ወያኔ እንደ የዛሬዎቹ ኦሮሞዎች “ሁሉም ኬኛ” ባይሆኑም ወያኔዎች ሥልጣናቸው ብቻ አትቀራመትባቸው እንጂ ከነሱ የተረፈ በሥራቸው ሆነህ የተረፈውን ፍርፋሪ ትግሬ ላልሆነውንም ሲጥሉለት ነበር። ያ ሃቅ ነው። ሌላ ቀርቶ “መለስ ዜናዊ በመሞቱ ኢትዮጵያ ታላቅ ሰው አጣች ያለንን ታጋይ ልደቱ አያሌውም እኮ “ለነብሱ መከላከያ “ሽጉጥ አስታጥቃው” ነበር። ለትግሬዎች ምን ይሳናቸው ነበር።

ያ ብቻ እንዳይመስላችሁ እኛ “በዊል ቸይር” የሚሄዱት 'ቶ አለቃም' እኮ ሚሊየነር ነበሩ። ሰውየው አሁን ትዝ ሲሉኝ

ወዳጄ ይነጋል ስለ ሰውየው ያጫወተንን ላስታውሳችሁ፡

“ እንደው ካልጠፋ ሰው የመቶ ዓመት ዕድሜ የዊልቼይር ተጠቃሚ ጃጃታም ሽማግሌ በፕሬዝደንትነት ያኔ የሾሙልን እኮ ሲያሾፉብን ነው! – ዓለም እንዴት ይስቅብን እንደነበር መቼም አይረሳም – ከ80 ሚሊዮን ሕዝብ አንድ ታማኝ ቤት ጠባቂ ጠፍቶ ያንን ሰው ሲያደርጉ ኢትዮጵያን ለማዋረድ መቋመጣቸውን እናውቅ ነበር፡፡ ወያኔዎች በሰውና በሀገር መቀለድ በጣም ይችላሉ፡፡” ነበር ያለው።

እነሱን እና ይመሳሰሉት አዎ ትግሬዎች እነዚህን ሚሌየነሮች አድርጓቸው ነበር። ግን ከትግሬ ታጁሮች ጋር ማነጻጸር የት የሌለ ነው። አዎ “ሲም ካርዱን ዋና ዋናዎቹ ወያኔዎች ይዘው አገልጋዮቻቸውን በቀፎነት መጠቀም” የትካኑበት የትግሬዎች መንሥት ትዝታ ነው”፡፡ጣዖታዊ ቤተ መቅደሳቸው የሆነው ሕወሓታዊ ሠነድ ከተቀበልክ ፍርፋሪው ሞልቶ ተትረፍርፎ ነበር።

ሁሉም ሲባል “ቃላት እየሰንጠቁ ለመዋሸት እንዲመቻቸው “ሁሉም አልተጠቀመም” ይላሉ። በየትኛው ተፈጥሮ ሁሉም የሰው ልጅ ሊጠቀም፤ ሁሉም  ባንዴ ሊሞት፤ ሊጨፍር፤ ሊያዝን ፤ ሊጠቀም ፤ ሊዋጋ ፍቅር-ሊይዝ፤ ትዳር ልይዝ፤ ሊነግድ ፤ ሊያራስ፤ አይችልም። ሁሉም ሲባል አብዛኛው (ለዓይን የሚታይ ጎላ ያለ ቁጥር) ለማለት እንደሆነ ደጋግመን ብንነግራቸውም አይሰሙም።

 አዎ በወያኔ ጊዜ “ሁሉም” የሚለውን ላስምርና በላይኛው ትርጓሜየ፤ ትግሬዎች ተጠቃሚ ባይሆኑም ወያኔዎች ትግሬዎች ናቸው፤ እነሱን ወደ ሥልጣን ያመጣቸው 99.9 % የትግራይ ሕዝብ ደግፎ፤ተዋግቶላቸው (የኔ ወብድሞችና ዘመዶች ሳይቀሩ ማለት ነው) ወደ ሥልጣን ሲመጡ፤ ሁሉም ተጠቃሚ አልነበሩም በሚሉት “እሺ እንበልና” የመንፈስ ኩራት ግን ከማንኛውም ኢትዮጵያዊ በላይ “ኩራት ፤ትዕቢት፤ጥጋብ” ይሰማቸው ነበር (እኔን እና ጥቂቶችን ሳይጨምር ማለት ነው)። (ድሮም እንደዛው ነበር። ሥልጣን ወደ ሸዋ ተሸጋገረ ሲባል የዮሐንስና የአሉላ አድናቂዎች በዘሙኑ ተጠቃሚዎች ባይሆኑም ድሃው ሳይቀር ትግሬዎች ንጉሳቸው ሲሞቱ ሥልጣን ወደ ሽዋ በመሄዷ፤ ቁዘማ እንደገባ በመጽሐፌ ገልጫለሁ። ) አዎ <<ወያነ ማለት የትግሬ ሕዝብ ማለት ነው ፤የትግራይ ሕዝብ ማለት ደግሞ ወያኔ ነው>> ብየ ለአመታት ተከራክርያለሁ። አዎ እውነታው ያ ነው! ብትፈርጡ ብትደቁ፤ ከዛው እውነት መሸሽ አቻልም።

ሌላኛው ወዳጄ ዳግማዊ ጉዱ ካሳ አዲስ አበባ ውስጥ ያየውን እንመልክትና የጻፈልኝ በየድረግጹም የተለጠፈውን እንዲህ ያለውን አስታውሳለሁ።

“ሌት ከቀን የሚዝናናው፣ በመኪናው ውስጥ በሚከፍተው የሙዚቃ ድለቃ ሕዝብን እንቅልፍ የሚነሳው፣ በየቡና ቤቱ እየዞረ ትግርኛ ካልተከፈተልኝ በማለት ሌላውን ዘፈን በነፍጠኛነት የሚፈርጀውና የሚያስፈራራው ጠግቦ እየዘለለ የሚገኘው ትግሬ ወያኔና አሽከሮቹ ናቸው፡፡ የሚገርመው ጠጪዉና ተዝናኙ ትግሬ ብቻ ነው ተብሎ በአዋጅ የተነገረ ይመስል በየመዝናኛውና በየምሽት ክበቡ የሚከፈተው ዘፈን ከሞላ ጎደል ትግርኛ ብቻ ነው፡፡ ትግርኛ ካልከፈታችሁ ቡና ቤታችሁ ይዘጋል የተባለ ይመስል አዳሜ ከገዢው ወገን ጋር የተዛመደ እየመሰለው የሚከፍተው ሙዚቃ ትግርኛ ብቻ የሚሆንት አጋጣሚ ሞልቷል፤ ሁሉም ነገር የብሔር ተዋፅዖ በሚለው የወያኔ አስመሳይ ፍልስፍና እየተመራ ለምሳሌ የሞቀ ኦሮምኛ ተከፍቶ በምትጨፍርበት ሠርግ ላይ ሳታስበው ድንገት ትግርኛ ወይም ወላይትኛ ሊከፈት ይችላል - ያኔ የውዝዋዜ ሥልትህን በቅጽበት ትቀይርና “በኩኑ ከማሆሙ” ነባር ኢትዮጵያዊ ብሂል አንተም አለውድ በግድህ ትወዛወዛለህ፡፡ አለዚያ “ይህን አይወድም፣ ይህን ይጠላል” በሚል ኢመደበኛ ግምገማ የሰው ዐይን ውስጥ ልትገባ ትችላለህ:: በዚያም ሰበብ የምታጣው ነገር ሊኖር ይችላል፡፡

እስከዚህን የወረድን ሕዝብ ሆነናል:: በዘፈን ምርጫ ሰውን መገምገም የሚዳዳባት ሀገር፡፡ እዚህ ላይ ትግርኛ መከፈቱ አስከፍቶኝ ሳይሆን ራስን ያለመሆን ጠባይ እየጎላ መምጣቱ ግን አስገርሞኝ ነው፡፡ በየትምህርት ቤቱማ ብታዩ ታሪኩ ብዙ ነው፡፡ በየቦታው የምትሰሙት ሙዚቃ አስመሳይነትን እንጂ እውነተኛ ፍላጎትንና ምርጫን አያመለክትም፡፡ ገበያን ለመሳብ ብቻ እንዴት የአንዲት ከተማ ቡና ቤቶች ተመሳሳይና የተሰለቹ ዘፈኖችን አንድን ወቅት እየጠበቀ (የስካርና የመዝናኛ) ይከፍታል? ወረተኝነት ከምን ጊዜውም በላይ እየተስፋፋ ነው፡፡

 ነገ ደግሞ የሽናሻ መንግሥት ቢመጣ ቡና ቤቱ ሁሉ ሽናሽኛ ዘፈን እየለቀቀ ካለተዝናኙ ፍላጎት ሊያደነቁረው ነው ማለት ነው፡፡ ትንግርቱ ብዙ ነው፡፡ ይህን የምለው በጥራዝ ነጠቅ የማውቃት የሥነ ልቦና ትምህርት ግንዛቤየ እየታወሰችኝ ሰዎች የሚያደርጓቸውን ነገሮች ለምን፣ እንዴትና መቼ እንደሚያደርጉ ወይም እንደማያደርጉ የጫረብኝ አስጠሊታ ምስል ነው፡፡ ሰው ግን ምን ያህል አስመሳይ ፍጡር ነው!? አዲስ አበባ ውስጥ ከሚዝመነመኑ ግሩም አውቶሞቢሎች ከአሥሩ በትንሹ ሰባቱ የትግሬዎች ናቸው ቢባል ስህተቱ ለኩነኔ አያደርስም፡የንግድ መኪናውን ብትመለከትም እውነቱ ከዚህ ብዙም አይለይም፡፡

ትግሬ ግን ከኢትዮጵያ ሕዝብ አጠቃላይ ብዛት ግፋ ቢል 8 በመቶ ቢሆን ነው፡፡ የጥንቱን ስድስት በመቶውን አሁን እርሱት - አዲስ አበባ ላይ የሚርመሰመሰው ወያኔ ብቻውን ከአምስት በመቶ የሚያንስ አይመስለኝም - ለቁጥር ያለኝ ቀረቤታ እንደ በእውቀቱ ሥዩም እስከዚህም ቢሆንም፡፡ አማራው ቀንሷል - ትግሬው ጨምሯል፤ በምናውቃቸውም በማናውቃቸውም ምክንያቶች የተነሣ፡፡ ዘር ማብዣ ማዳበሪያ ወደትግራይ - ዘር ማምከኛ በስሪንጋ የሚሰጥ ብልቃጥ መርዝ ወደአማራ፡፡ ታሪክ ይፋዊ የምሥክርነት ቃሉን ሊሰጥ በቋፍ ላይ ነውና በትግስት እንጠብቅ፡፡ አለ ገና - ብዙ ነገር ይታያል፡፡ ዕድሜና ጤና መለመን ነው፡፡ አንድዬ የሚሳነው ነገር የለምና ያቆየን፡፡ የምመክራችሁ እንድትናደዱ ነው፤ ስትናደዱ ወደመፍትሔው ትጠጋላችሁ፡፡” ይላል ወዳጄ።

ሰማዩን ምድሩን የሚያነቃንቅ ጥጋባቸው በግልጽ ይታያል። አንድ አዲስ አበባ ደርሶ ከመጣ ወዳጅ የተላከልኝን ላስነብባችሁ፦

<<…….እግዚአብሔር ይስጥልኝ ወንድሜ። ወደ ኢትዮጵያ ሄጄ ነበር የተወሰነ ወር ቆይቼ ነው የመጣሁት። የሰውን ፊት አይተው ይለያሉ ሊቃወመን ይችላል ብለው የሚያስቡትን ኤርፓርት ኢሚግሬሽን ቡት ውስጥ ከሚቀመጡት ዘረኛ ትግሬዎች ጀምሮ። በተለይ ቦሌ መድሐኒአለም ፊት ለፊት በኤድና ሞል ዝቅ ብሎ ብዙ ዘመናዊ ባለ 5 ኮከብ ሆቴሎች ተከፍተዋል ሁሉም የትግሬ ናቸው። ነጮቹ ‘ሆቴል ዲስትሪክት’ ይሉታል። የኛ ህዝብ መቀሌ እና አፓርታይድ ይለዋል ሰፈሩን። በተለይ “ቬኒሺያን” የሚባለው የትግሬ ሆቴል ገብተን 10 ዲቂቃ እንደተቀመጥን ካውንተሩ ላይ የሚቀመጠው እጅግ በጣም የጠገበ ሲራመድ መሬት የሚነቀንቅ ትግሬ የተቀመጥንበት ድረስ መጥቶ ያፈጣል። አስተያየቱ ሀሉ በጣም ነው የሚከብድው። ህዝቡ ኪሱ ውስጥ ያለውን ብር ቶሎ አራግፎ እንዲወጣ ነው የሚፈልጉት። ጥላቻቸው በግልፅ የሚታይ ነው። በዘረኝነት እና በጥላቻ ከተመረዘ ህዝብ ጋር መኖር በጣም ነው የሚከብደው። ህዝባችን በገዛ አገሩ ላይ እንዲሸማቀቅ እየተደረገ ነው። ባካባቢው ባሉት ሌሎች የትግሬ ሆቴሎች ውስጥም ተመሳሳይ ዘረኝነት ነው ያየሁት። “> ይላል  ለዚህ ደራሲ  የተላከለት ደብዳቤ (176)። ይህንን ወታደሮች ያልሆኑ የወያኔዎቹ  ወጣት ደጋፊ ትግሬዎች ኢትዮጵያ አይታው በማታውቀው ያንድ ነገድ ከፍታ ዘመኑ የትግሬ መሆኑን ምንም መደባበቅ አያስፈልግም።

ትግሬዎች በገበያውና በኢኮኖሚው ረድፍ እንዴት ተጠቃሚ እንደነበሩ ሰፊ የሰነድ የባጀት ኢንዳስተሪ ልማት የሕክምና ፤ የትምሕርትና የማሰልጠ ጣቢያ ወዘተ…በሚመለከት ከሌሎች “አፓርታይድ ክልሎች” እንዴት ተጠቃሚ እንደነበሩ ካሁን በፊት ደጋግ ስላቀረብኩት ዛሬ በዚያው ጥልቅ ሰንድ አልገባም። ብቻ ላይ ላዩን ልሂድበት

ታዋቂው የፍልስፍና እና የፖለቲካ እንዲሁም የሕግ ምሁር የሆነው “ወሎ” ተወልዶ ያደገው የተምቤን ታላላቅ ተወልጄ ሰዎች ተወላጅ የሆነው ፕሮፌሰር ተኮላ ወ/ሓጎስ እንዲህ ይላል።

< On balance, One surmise that ordinary Tigreans have lost most of their human and democratic rights, and will continue to lose more in years to come. However, in one area of government interference, the current TPLF dominated government is pouring hundreds of millions of dollars in development funding neglecting almost all other regions, or some sector of economic development programs. Although such privileged treatment was a source of tremendous resentment of Tigreans by the rest of the Ethiopians population.> Tecola W.Hagos Guest Lecturer Harvard University (Demystified Political Thought, Power and Economic Development- Page 66)

ወደ አማርኛ በግርድፍ ሲተረጎም

< በሚዛናዊነት፣ በሚገርም ሁኔታ ተራ ትግሬዎች አብዛኛውን ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶቻቸውን አጥተዋል፡ በሚቀጥሉት አመታትም የበለጠ ኪሳራ እንደሚደርስባቸው መገመት ይቻላል። ነገር ግን አሁን ያለው  የህወሓት የበላይነት ያለው መንግስት ሁሉንም ክልሎች በሚባል ደረጃ የኢኮኖሚ ልማት ፕሮግራሞችን ችላ በማለት በመቶ ሚሊዮን የሚቆጠር ዶላር  (ትግራይ ውስጥ ማለቱ ነው ተኮላ) ለልማት ፈንድ እያፈሰሰ ነው። ምንም እንኳን እንደዚህ ዓይነት ልዩ ጥቅም ያለው ድጋፍ (ለትግሬዎች/ትግራይ/ ማለቱ ነው ተኮላ) በመደረጉ በወቅቱ በተቀረው የኢትዮጵያ ሕዝብ ዘንድ በትግሬዎች ላይ ከፍተኛ ቅሬታ አስከትሏል።” (Tecola W.Hagos ተጋባዥ ሌክቸረር ሃርቫርድ ዩኒቨርሲቲ (Demystified Political Thought, Power and Economic Development- ገጽ 66)> ይላል ተኮላ ወ/ሐጎስ።

በነገራችን ላይ እንደምታውቁት ፕሮፌሰር ተኮላ ወ/ሓጎስ በወያኔ ዘመን ከፍተኛ ሚኒሰቴር ባለ ሥልጣን የነበረ በላ ትቷቸው ወደ አሜሪካ የተሰደደ ትግራዋይ ምሁር ነው።

በመጨመር በገጽ 62 ላይ ተኮላ ስለ ትግሬዎች ምንነት እንዲህ ይገልጻቸዋል።

<<Tigreans in general have a much more pronounced narrow ethnic chauvinistic attitude than most Ethiopians: as individuals, they are the most materialistic and narcissistic. Such narrow –mindset has negatively affected the leadership of TPLF: and as a consequence the entire political process in Ethiopia has been polarized by narrow nationalism and negative ethnic separation. Most of the atrocities in 1992-1998 in the Harar, Kaffa, Wollega and Arisi region were a direct result of the type of ethnic or sectarian and divisive leadership policy signal broadcasted by the TPLF leaders at the beginning of the establishment of the TGE.> ((Demystified Political Thought, Power and Economic Development-P.62)

አማርኛ ትርጉም፡

<<ትግሬዎች ባጠቃላይ ከብዙዎቹ ኢትዮጵያዊያን በበለጠ ጎልቶ የሚታየው ጠባብ የጎሳ አመለካከት አላቸው፡ እንደ ግለሰብ ቁሳቁሰኞች (አፍቃሬ ገንዘብና አፍቃሬ ቁሳቁስ) ናቸው። እንዲህ ዓይነቱ ጠባብ አስተሳሰብ በህወሓት አመራር ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ አሳድሯል፡ በዚህም ምክንያት የኢትዮጵያ የፖለቲካ ሂደት በጠባብ ብሔርተኝነትና በአሉታዊ ጎሳ መለያየት ፖላራይዝድ (የትካረረ) ሆኗል። ከ1992-1998 በሐረር፣ ከፋ፣ ወለጋ እና አሪሲ ክልል የተፈፀመው አብዛኛው  (በአማራዎች ላይ የደረሰው ማለቱ ነው) ግፍ የህወሓት መሪዎች ህወሓት ሲመሰረት ባስተላለፉት የብሄር ወይም የቡድናዊ እና ከፋፋይ የአመራር ፖሊሲ ምልክት ቀጥተኛ ውጤት ነው።>> ((Demystified Political Thinking, Power and Economic Development-P.62) ይላል።

እንግዲህ ትግሬውና የወያኔ ፡ሹመኛ የነበረው ፕሮፌሰር ተኮላ ሁለት ነጥቦችን አንስቷል (በመጽሐፉ ውስጥ) አንዱ ትግሬዎች በመንግሥታቸው በኩል የምጣኔ ሃብት ልማት ተጠቃሚዎች መሆናቸውና በዚህም በብዙ ኢትዮጵያውያን ቅሬታን እንደፈጠረ፡ ሌላው ደግሞ  ትግሬዎች ቁስ አምላኪ ከመሆናቸው በላይ ስግብግብ ንብረትና ንግድ ባለቤቶች እንደነበሩ ጠቋሚ መሆኑን እንረዳለን። ከዚህ ባሕሪያቸው አክሎ ግልፍተኞች፤ ትዕቢተኞች ራስ ምስል ወዳጆች እና ጠባቦች መሆናቸውን ሲገልጽ በዚህ ምክንያት ሥልጣን ላይ የወጡት ጎሰኛ ወያኔዎችን በመደገፍ ሥልጣን ላይ ስላወጡዋቸው በጠባብ ባሕሪያቸው የተነሳ አገሪቱ ላይ በተለይ ከላይ በተጠቀሱ ቦታዎች አማራዎች እንደተጨፈጨፉና የነገድ መካረር ምክንያት እንደሆኑ ነግሮናል።

ይህ እንግዲህ እነዚህ ጠባብ ፋሺስቶች መላው የትግሬ ሕዝብ የራሱን ባንዴራ እያውለበለበ ከጀርባቸው ቆሞ ደግፎ “ሆ!” እያለ እየመራ እየመገበ፤ እሞተላቸውና እየቆሰለላቸው አዲስ አበባ ድረስ አምጥቶ ስላነገሳቸው፤ የትግሬ ማሕበረሰብ ተጠቃሚ ሆኖ ታንኩም ባንኩም ትግሬዎች ተቆጣጥረውት ነበር የምለው እኔ ትግሬው ጌታቸው ረዳ ብቻየን እንዳልሆንኩኝ ከላይ አንድ ምሳሌ ያቀረብኩት አማላካች ነው።

 ወደ 2ኛው ነጥቤ ልግባ

በህግ ጥላ ሥር የሚገኙ ዜጎችን በዘራቸውና ለመብታቸው በመታገላቸው ምክንያት ሊሰሙት በሚዘገንንና ከባህላዊ ዕሤቶቻችን በእጅጉ ባፈነገጠ ሁኔታ የሚያሰቃዩ ሰይጣናውያን ትግርኛ ተናጋሪ ገራፊዎች በገራፊዎቻቸው አንደበት ለምን “ትግሬዎች ተብለው ተጠቀሱ” በመጠቀሳቸው ምክንያት ትግሬዎች ለጥቃት ተጋልጠዋል እያሉ የሚወነጅሉን ለእነ ልደቱ እና  ጋዜጠኛ ያየሰው ሽመልስ መልሴ የሚከተለው ነው።

ትግሬዎች በብዙ ኢትዮጵያዊያን የመጠላታቸው ምክንያት እራሳቸው ደግፈው ባመጡት መከራ ለጥቃትና ለጥላቻ ተጋለጡ እንጂ “ገራፊዎችና ግርፍያውንም ሆነ ደህንነቱን የሚዘውሩት ዋና ሞተሮቹ ትግሬዎች ነበሩ” ስለተባለ ለምከራ ተጋለጡ ማለት ፡ትግሬዎች የፈጸሙትን ወንጀል እንዲደበቅ መጣር ወይንም አድርባይ መሆን ብቻ ነው።

ትግርኛ ተናጋሪ ገራፊዎችና የደህንነት ሹሞቹ የፈጸሙት የሚከተለው ወንጀል፤ ዛሬም ነገም ለሕዝብና ለታሪክ መገለጥ አለበት፡ እስኪ የሚከተለው ሰቆቃ በጋዜጠኛ ሃብታሙ አያሌው (ኢትዮ 360) እና በትግሬው ዶ/ር ሃይሉ አርአያ የተነገረው ሁለት የተለያዩ ንግግሮች ግን አንድ ዓይነት እሮሮ ፤ አንድ ባንድ እናደምጣቸውና ፍርዱን ስጡና እኔን ከዚያው ወቀሳችሁ አግልሉኝ።

ሓብታሙ አያሌ እንዲህ ሲል ስለ ትግርኛ ተናጋሪ ገራፊዎች ይናገራል፦

<< እስር ቤት ውስጥ ያሉ ገራፊዎች 99% ትግርኛ ተናጋሪዎች ናቸው። ሲገርፉም በተለያየ ጊዜ እንደተናገርኩት ትግሬ ማለት እንደዚህ ነው፤ ግድግዳ ግፋ እያሉ ሲያስገፉን ይቆዩና እየሞከራችሁት ያላችሁት ይሄንን ነው፤እኛ ማለት እንደዚህ ነን (የማንገፋ ግድግዳዎች) እያሉወክለው (እኛ ትግሬዎች እያሉ) ነው የሚነግሩን።  እና በዚህ አጋጣሚ አንድ መልእክት ለማስተላለፍ እፈልጋለሁ። በቅርቡ ህጻናትና አሮጊቶቸን በጥይት አየቦደሱ ሰው እየገደሉ አያሉ ሰዎች ያችን አገር  እየገዙ እንዳይቀጥሉ ከተፈለገ፤ ጎጃም ላይም ጎንደር ላይም ፤ ጅማ ላይም ወልቅጤ ላይም ፤ ጋምቤላም ፤ ቤንሻንጉል ላይም ፤ በየትኛውም ቦታ ደረቱን በጥይት ለተመታ ለሞተው ልጃቸው ለሐዘን አደባባይ ሲወጡ አሮጊቶች መገደላቸው መቀሌ ላይም ከተሰማ እባካችሁ ስለ ኢትዮጵያ አምላክ ዚህን ልጆችየኛ ልጆች አይደላችሁምበቃን!በልዋቸው።ብየ መልእክት ለትግራይ ሕዝብ አስተላልፋለሁ።>> <<፡ማሕሌት ካሳሁን እና ኤዶም ካሳየ ወጥተው ለሚዲያ ተናግረዋል። ሌለት እራቁታችን አስወልቀው ስፖርት ያስሰሩን ነበር፡ አሉ። በእነ ዘመነ ምሕረት ገላ ላይ ሽንታቸውን የሚሸኑ። ወንድ ልጅን እግር እስጃቸውን አስረው ከላቸው ላይ የሚሸኑ ገራፊዎች ! እነዚህ ኢትዮጵያዊያን አይደሉም። ከሰብአዊነት ውጭ የወጣ ነው።>> (ብታሙ አያሌው ለሕዝብ ከተናገረው የተገኘ አውድዮ ቪዲዮ ምንጭ ቱብ)

አሁን ደግሞ ወደ ትግሬው ዶ/ር ሃይሉ አርአያ ምስክርነትና እሮሮ አድምጡና ልሰናበታችሁ፡

እንዲህ ይላሉ፤

“…ከቤቴ እየደበደቡና እየተሳደቡ የወሰዱኝ የትግራይ ልጆች ነበሩ ማዕከላዊ እንደደረስኩ ቀበቶዬን ያስፈታኝ የትግራይ ሰው ነው ከእርሱ ተቀብሎ አንድ የፍሪጅ ያህል የሚቀዘቅዝ ክፍል አስገብቶ የቆለፈብኝ የትግራይ ሰው ነው ሲመሽ ሽንት ቤት ወስዶ ያሸናኝ ሰው የትግራይ ሰው ነው።እየተሳደበ ቃሌን የተቀበለኝ የትግራይ ሰው ነው።በእርግጥ እኔ የትግራይ ሰው ሆኜ ከአንድ አካባቢ በወጡ ሰዎች ጥቃት እየደረሰብኝ እንደሆነ ከተሰማኝ ሌላው ሰው ምን ሊሰማው እንደሚችል አስቤ ለትግራይ ህዝብ ከልቤ አዘንኩለት። ይሄ ሁሉ የሚደረገው ለትግራይ ህዝብ ሲባል ነው መባሉ ደግሞ የበለጠ ሰላሜን ነሳው።

ይህን ምስክርነት የሰጡት የትግራይ ተወላጁ የቅንጅት party አመራር የነበሩት ዶክተር ሃይሉ አርአያ ናቸው

እንግዲህ እንደ እኔና እንደ እነ ዶክተር ሃይሉ አርአያ እንደ እነ ገብረመድህን አርአያ የመሳሰልን ሃቁን የተናገርን ሰዎች “ትልቅ ሰው አይጥፋ!” ብለው ከሚመርቁን ይልቅ “ለትግራይ ሕዝብ መጠቃት ተጠያቂዎች ናችሁ/የትግራይ ሕዝብ ለጥቃት የተጋለጠው ሳይጠቀም ተጠቀመ እያላችሁ፤ እንዲሁም ትግርኛ ተነጋሪዎች ግፍ ሳይፈጽሙ እንዲህ ያለ ግፍ ፈጸሙ እያሉ“ ሳይደበድብ ደበደበ ፤ ይገድል ገደለ” “ሳያስር አሰረና አሳሰረ” እያሉ የትግራይን ተወላጆች ለጥቃት አጋልጠውታል፡ እያሉ የሚወነጅሉንን እነ ልደቱና ጋዜጠኛ ያየሰው ሽመልስ ለምን ሃቁን ሊክዱ ፈለጉ?

“እስር ቤት ውስጥ ያሉ ገራፊዎች 99% ትግርኛ ተናጋሪዎች ናቸው። ሲገርፉም በተለያየ ጊዜ እንደተናገርኩት ትግሬ ማለት እንደዚህ ነው፤ ግድግዳ ግፋ እያሉ ሲያስገፉን ይቆዩና እየሞከራችሁት ያላችሁት ይሄንን ነው፤እኛ ማለት እንደዚህ ነን (የማንገፋ ግድግዳዎች) እያሉወክለው (እኛ ትግሬዎች እያሉ) ነው የሚነግሩን።” ሲል ሃብታሙ ነግሮናል። ታዲያ ገራፊዎች 99% ትግርኛ ተናጋሪዎች ከሆኑ። ሲገርፉም እኛ ትግሬ ማለት እንደዚህ ነው፤’ እያሉ እራሳቸው እያስተዋወቁ  ታሳሪን የሚገርፉና የሚደፍሩ ከሆኑ እነ ልደቱና ያየሰው ለምን ትግርኛ ተናጋሪዎች ተባሉ ብላችሁ ከምታውኩን “ሌላ ስም ስጥዋቸውና በዛው ስም እንድንጠራቸው ይደረግ”

እኛ አይደለንም ለትግሬዎች መጠቃት ምክንያት የሆንነው። እራሳቸው በአኝዋክና በአማራ ማሕበረሰብ የዘር ጭፍጨፋ (ጀንሳይድ) የፈጸመውን ወንጀለኛውን ድርጅታቸው ወያኔ በመደገፋቸው ተጠቂዎችም ተጠሊዎች ሆነዋል።  በአገሪቱ ላይ የደረሱት ግፎች በስማቸውም ይሆን ያለስማቸው ቀጥተኛ “ኢምፓክት” እንደሚኖርና አዲስ የመንግሥት ለውጥ ሲደረግ  ትግሬዎች እንዳይጠቁና ስጋት እንዳላቸው ቢያስጠነቅቁም፤ ትግሬዎች እራሳቸው “ጆሮ ዳባ” ብለው እራሳቸውን ሊያርሙ አልቻሉም። ሃብታሙ አያሌው እንኳ ከላይ የጠቀሰውን ለትግሬዎች ያስተላለፈው መልዕክት <<መቀሌ ላይም ከተሰማ እባካችሁ ስለ ኢትዮጵያ አምላክ እነዚህን ልጆችየኛ ልጆች አይደላችሁምበቃን!በልዋቸው። መልእክት ለትግራይ ሕዝብ አስተላልፋለሁ።>> ሲል ትግሬዎች ሲያሾፉበት ነበር። አቤቱታው አልተሰማም!

ተምራማሪው President of Genocide Watch Dr. Gregory Stanton ኢሳት ላይ ቀርበው የተናገሩትን ማስጠንቀቂያና ምክርና ስጋታቸውና መደረግ ያለበትን ምክር ስለተናገሩ እንደ እነ / ገላውዴዎስ አርአያ የምሳሰሉት የትግሬ ምሁራን በኩል ሲሰደቡ ነበር።

በመጨረሻም በትግሬዎች መንግሥት ግፍ ያንገፈገፈውና የብዙሃኑ ትግሬዎች ተባባሪነትና ዕብሪት “ቋቅ” ብሏቸው፤ ሕዝቡ የትግርኛ ሙዚቃ ሲያደምጠው የነበረውን ሙዚቃውንም እንኳን ሳይቀር ማድመጥ ሁሉ ጠልቶት እንደነበር አንድ ማስረጃ በትግሬው / ገላውዴዎስ አርአያ ምስክርነት “ውራይና” ከተባለ ጽንፈኛ የወያኔ አጨብጫቢ መጽሔት ለውጡ ሊመጣ አመታት ሲቀረው ያደረገውን ቃለ መጠይቅ በትግርኛና አማርኛ ተርጉሜ ላስደምጣችሁና ልሰናበት።

ትግርኛው ላስቀድምና አማርኛው ከታች አለ።

<<ሓደ ሓደ ጊዜ ገለ መዘናግዒ መደባት ንምርኣይ   ናይ ኢትዮጵያ ይኸፍት እየ እሞ  ሓደ እዋን ሰይፉ ሸው ይርኢ ነይረ፤  ኣበኡ ሓንቲ ትግራወይቲ ድምፃዊት ትሕተት ነይራ። ትደርፍ ከመይ ዝበለ ድምፂ ዘለዋ ቆልዓ እያ፤ ከምዚ ዝበለ የለን። እቶም ኣብታ መድረኽ  ዝነበሩ ግን ኣየጣቕዑ፣ ኣይስዕስዑ ኣእዳዎም ኣጣሚሮም "ስቕ!" ኣነ ሽዑ ብጣዕሚ ገሪሙኒ። ብጃንሆይ ጊዜ እኮ ትግርኛ ክድረፍ እንተሎ ጉራጌኡስ ኣምሓራዩስ ምሳና እዩ መፂኡ "ሹሽ" ዝብል ዝነበረ። ክሳብ ክንዲዚ ንትግርኛ ናይ ምፅላእ ኩነታት ተፈጢሩ። ንሕና ጥራይ ተዘይገዛእና ዝብል ኣተሓሳስባ ክጠፍእ ኣለዎ። እዚታት ክተዓረቕ እዩ ዘለዎ።>> (/ ገላውዴዎስ አርአያ። ውራይና ሕታም 31 2010)

አማርኛ ትርጉም

“አንዳንድ ጊዜ በኢትዮጵያ ውስጥ የተዘጋጁ ለሕዝብ ሚቀርቡ መዝናኛዎች አያለሁ። አንድ ቀን “ሰይፉ ሸው” መዝናኛ እመለከት ነበር። የፕሮግራሙ አዘጋጅ ሰይፉ አንዲት የትግራይ ተወላጅ የሆነች ድምጻዊት ቃለ መጠይቅ ያደርግላት ነበር። ሰይፉም ለተመልካቾቹ ከትግርኛዋ ሙዚቃዎችዋ አንዱን እንድትዘፍንላቸው ጠየቃት። እሷም እሺ ብላ በጣም ቢመገርም ድምጽ የትግርኛ ዘፈንዋን አቀረበች። አዳራሹ ውስጥ የነበሩት ተመልካቾች ግን “አያንጨበጭቡ”፤ “እስክስታ አይመቱ”፤ “እጆቻቸውን አጣምረው ዝም ፤ዝም፤ ብቻ ዝም ብለው ይመለከትዋታል”።እኔ ያኔ በጣም ገረመኝ። በጃንሆይ ጊዜ እኮ ትግርኛ ሲዘፈን ጉራጌው፤አማራው፤ኦሮሞው ከኛ ጋር አብሮ ነበር አስከስታውና ደስታው ሲያስኬደው የነበረ። እስከዚህ ድረስ የትግርኛ ሙዚቃ እንኳ እስከመጥላት የሚደርስ ሁኔታ እየተከሰተ ነው እኛ ብቻ ካልገዛን የሚለው አስተሳሰብ መወገድ አለበት።>> ይላል / ገላውዴዎስ አርአያ።

ከላይ እንዳነበባችሁት ሕዝቡ የግፉ ብዛት የትግርኛ ሙዚቃ ሳይቀር ለመጥላቱ “ጠባብ ብሔረተኛው ገላውዴዎስ አርአያ” እንደሚለው “እኛ ብቻ ካልገዛን” ከሚል ስሜት ሳይሆን ግፉ እስከዚያ ድረስ አድርሶታል በነገራችን ላይ ትግሬዎች ሥልጣን ላይ ሆነው ኢትዮጵያን እየገዙ መኖራቸውን እራሱ ገላውዴዎስ <<እኛ ብቻ ካልገዛን የሚለው አስተሳሰብ መወገድ አለበት>> የሚለው ንግግሩ ማስረጃ ነው። ዶ/ር ገላውዴዎስ ዛሬ የዲያስፖራ ምሁራን ትግሬዎች ከፍተኛ መሪ ሆኖ ጦርነቱ ሲደገፍ ከነበሩት ; ዛሬም ግንጠላን ከሰብኩ ቁንጮ አንዱ የትግሬ ምሁር ነው።

ትግሬዎች የተጠሉት በትግሬነታቸው ሳይሆን በወያኔነታቸው ነው።

ስለዚህ ዘመን ወደ ጅብነት ሲቀየር “ሀኝ” ነው የሚያደርግህ። ሕዝብ ግፍ ሲበዛበት ጅብ ይሆናል። ሕዝብና ዝምብ የሚያሸሻቸው አይወዱም፡ ሁለቱም አስተዋዮች ይሁኑ እንጂ “ጫና ሲበዛባቸው ጠንጋራዎች” ናቸው፡ ሲሸሹ አያዩም፡ ሲከንፉ ግድግዳውም ላይ ይጋጫሉ። ሕዝብ ራሱንም የገዛ መሪዎቹን ይበላል፡ የሚባለው አልሰማችሁም? እኛን ለቀቅ!

መልካም ፋሲካ ይሁንላችሁ

ጌታቸው ረዳ