አፋቸው እንደ ባሕር ኦይሰተር የሚከፍቱ በጨረቃ ላይ የሚጮሁ ተኩላዎች
ጌታቸው ረዳ
(Ethiopian Semay) 12/25/24
““Oysters የተባለ እንሰሳት በጠፌ ጨረቃ ጊዜ ሙሉ በሙሉ ይከፈታል ይባላል።Crab የተባለው እንሰሳ (አብዛኛው ዓለም ይበላዋል) ኦይስተሩን ሲያይ ትንሽ ድንጋይ ወይም የባሕር አረም (አራሙቻ) ይወረውርበታል። ኦይሰተሩ እንደገና ራሱን መዝጋት ያቅተዋል። የክራቡ ምግብም ይሆናል። አፉን በጣም በመክፈት ራሱ ላይ ከፍተኛ ችግር ሚያደርስ ሰውም ዕጣ ይኸው ነው።>> {ጸጋዬ ገብረመድህን አርአያ- ጦቢያ መጽሄት-ቅጽ8-ቁጥ-12/1993 -ከኢትዮጵያና ከኢትዮጵያውያን ጋር የተፈራረሙት ውል (ኮንትራት) የላቸውም”}
የባሕር ዓሳዎች ብቻ ሳይሆኑ አፋቸው
ከመጠን በላይ የሚከፍቱ የሰው ኦይሰተሮችም አሉ። አንዱ ዘመድኩን በቀለ የተባለ ሲፍረዘኒክ ነው። ሲፍረዘኒኮች ለነሱ በማይታወቃቸው ክስተት ከውስጣቸው ይደናገጣሉ፤
የሚረብሻቸውን ውስጣዊ ፍርሃት ለማስታገስ “ይጮሃሉ፤ ይወራጫሉ”
በተከታታይ ሰው ይዘልፋሉ ወይንም ጭራሽኑ ራሳቸውን አጥረው
ጥሞና ውስጥ ይገባሉ። ባሕሪው ብዙ ነው።
መጥፎ ደረጃ ሲደርሱም “ያለ ምክንያት ያለቅሳሉ”፤ ሲያለቅሱም በላይቭ ቪደዮ ራሳቸውን እየቀዱ በሕዝብ ፊት ሲያለቅሱ ይታያሉ።ሁለት ሰዎች በላይቭ ቪዲዮ እራሳቸው ቀድተው እዬዬ ሲያለቅሱ ያያናቸው አሉ። አንዱ ዮኒ ማኛ የተባለው እና ዘመድኩን በቀለ ናቸው። ለልቅሶአቸውም ምክንያት ፍለጋ ራሳቸው ይጠይቁና “ምን እንደነካኝ አለውቅም” ሲሉ ለልቅሶአቸው ምክንያት ሳይውቁት ከሕሊናቸው ጋር በልቅሶ ሲታገሉት አይተናቸዋል።
እንዲህ ዓይነት ስሜት እንዲገቡ ገፊው (ካልፕሪት) የሆነው ሃይል ከነሱ ውጭ ቁጥጥር የሆነ “የመረበሽ” (ዲስተርብድ) ስሜት ሲከማች በሁለተኛ ዕርከን የሚከሰት “ጭንቀት” ውስጥ ይገባሉ። ሁለቱም መረበሽ እና ጭንቀት ተደምረው “ያለ ምክንያት ከማልቀስ” አልፈው ከዚያ አጥር ለመውጣት የአደባባይ ውግያ (ኮምባታንት- ሆነው ይታያሉ) ለከት የለሽ ንትርክ በመክፈት “ከሚቃረኑት ሰው ብቻ ሳይሆን የሚቃረኑዋቸው ቤተሰቦቻቸውንም ጭምር በመጥቀስ ስድብና ተከታታይ ስም የማጠልሸት ዘመቻ” የመሳሰሉት ባሕሪዎች በመግባት ከግለሰብም ከቡድንም ጋር ዕብደት የሚመስል የባሕሪይ ቋንቋ ሊቃውንት “Loquacious” የሚሉት አይነት ንትርክ ውስጥ በመዘፈቅ የጭንቀትና የመረበሽ ግፊታቸውን ለማስታገሻ ይጠቀሙበታል።
ሁለቱ ሰዎች ሲያለቅሱ የዘረጉት ፤ “ላይቭ ቪዲዮ” የሚያሳየንም ይህ እውነታ ነው። አሳዛኙ ደግሞ በነዚህ ሰዎች ጭቅጭቅና መሰዳደብ የሚረኩ በርካታ ተከታዮች አፍርተዋል። የተከታዩ ብዛት ክስተት የሚያመላክተን “የባሮ-ሜተር መለኪያው” ውጤት ተከታዮቹ በተመሳሳይ “ታነል - Tunnel” የሚሰቃዩ የነሱ ቅጂ (copy) ወይንም የዘመኑ የአዲስ አበባ ወጣቶች እንደሚሉት “የነሱ ጀለሶች” ናቸው።
ለምሳሌ በዚህ “የሲፍረዘኒክ ባሕሪ“ የሚጓዙ ሰዎች ጭንቀታቸው እና የውስጥ ርበሻ (ዲስተርባንስ) ወስደው የሚደፉበት ጫንቃ የግድ በየሚዲያው እየገቡ እንደ ውሻ እያፈናፈኑ መጮህያ ክፍል ይፈልጋሉ። ለምሳሌ ዘመድኩን በቀለ እንደምሳሌ ብንመለከተው- ሰውየው ወዳጅና ጠላት የሚባል መስመር የለውም። ጭንቀቱና ረብሻው የሚደፋበት ቦታ ምርጫ የለውም። አምና ዘመነ ከሴን ሲዘልፍ እስክንድርን ሲያወድስ ፤ ዛሬ ደግሞ እስክንድርን ሲዘልፍ ዘመነ ካሴን ሶያሞካሽ የምናየው ባሕሪ cumulative emotions የሚባሉ የተጠራቀሙ የውስጥ ጭንቀቶችና ርበሻዎች መጠናቸው አልፈው ሲገነፍሉ “መንገድ” ላይ “ባደንቋሪ ጩኸት እየጮኸ” ባገኘው ሰው ላይ ድንጋይ እንደሚወረውር ዕብድ ሁሉ ጤነኞች የሚመስሉ ግን አስፋልት ላይ ያልወጡ እንደ ዘመድኩን ያሉ ማንም ከማንም ሳይመርጡ ሁሉንም በየተራ ይጨረግፋሉ። ሲጨረግፉ ደግሞ>> እኔ ማንንም አልፈራም>> የሚል እኩያዎቻቸውም ጭምር ሳይቀር በንግግራቸው ጣልቃ እያስገቡ የሚጠቀሙበት “ኮመን” ሐረግ ይጠቀማሉ።
ሲጨረግፉ ደግሞ ለነገ አይሉም። ለነገ ብቻ ሳይሆን “ይሉኝታ” የላቸውም። ለምሳሌ ዘመድኩን በቀለ እስክንድርን ሲዘለፍ፤ ከነ ባለቤቱና ልጁም ጭምር አብሮ ቀላልቅሎ ይጨረግፋቸዋል።ሚሰቱን “ትግሬ” በማለት ትግሬ መሆን ነውር እንደሆነ ለማስመሰል በሚመስል መልኩ ነገድዋን ለማስተዋወቅ “ትግሬ” ሚሰቱ ይላታል፡ ሚሰቱና ልጁም በሕዝብ ገንዘብ እያኖራቸው ነው ሲል እስክንድርን ይወነጅላል።
እንዲህ ሲል፡
<<ሚሊዮን ዶላር ከአማራና ለአማራ ትግል የሰበሰበ ነው።በሰበሰበው ገንዘብ ልጆቹን ዘጭ አድርጎ እያኖረ ነው፤ ሚሰቱን ዘጭ አድርጎ እያኖራት ነው>> ይላል።
እንደምናውቀው እስክንድር ያለው አንድ ልጅ እንጂ ብዙ ልጆች እንደሌሉት ነው በበኩሌ የማውቀው። ዘመድኩን ግን እስክንድር ካንድ ልጅ አልፎ ልጆች እንዳሉትና እስክንድር በሕዝብ ገንዘብ በምቾት እያኖራቸው እንደሆነ ይናገራል።
እስክንድር ሚሊዮን ዶላር ከሕዝብ ሰብስቦ ለባለቤቱና “ለልጆቹ” (?) አንደላቅቆ እያኖራቸው እንደሆነ አንዲትም የሰነድ ማስረጃ የሰው ምስክርነት ፤ የፍርድቤት ማስረጃ ሳያሳይ እስክንድርና ባለቤቱ እንዲሁም ልጁ (ልጆቹ ?) በተዘረፈ የሕዝብ ገንዘብ አሜሪካ ውስጥ እየኖሩ እንደሆነ የእስክንድርን ስምና የልጁን፤ የባለቤቱንም ስም በውሸት ሲያጠፋ ትንሽ አይሰቀጥጠውም። ይህ ደግሞ ከላይ ካየነው ባሕሪ የመነጨ ነው። ሰዎች <<በፕሪሚቲቭ/ኢንስቲንክት ኮንዳክት>> ሲመሩ ርሕራሄና ይሉኝታ የማይሰማቸው እጅግ አረሜኔ ጨካኞች ይሆናሉ። በዘመድኩን ያያነው ይህ “ፓተርን/ትሬንድ” ነው።
በዚህ አላበቃም፤ ዘመድኩን እንዲህ ይላል።
<<እስክንድር ማለት ለኔ አዲስ አበባን የሸጠ ፤ ያዲስ አበባን ወኔውን የሰረቀ፤ የአዲስ አበባን ሕዝብ ልምሻ ያደረገ ፤ሰንታየሁን ይዞ በየታክሲው በየ ምናምኑ እየሄደ ቪዲዮ እየቀረጸ “ዋይ!ዋይ! ሲል የነበረ’ እስክንድር ለኢትዮጵያዊያን የጠቀመ እንጀራቸው የነበረ አማራን ግን ቅርቃር የቀበረ ፤ጉድጓድ ውስጥ የከተተ ፤ ጠንቋይ ቀላቢ ነው…>> ይላል።
እንግዲህ ይህ በሬ ወለደ የስም ማጠልሸት ባሕሪ እውነትነት እንደሌለው አንድ ባንድ እንሂድበት፡
“ያዲስ አበባን ወኔው የሰረቀ” የሚለው በሚከተሉት የቪዲዮ ማስረጃዎች ያዲስ አባባን ወኔ ያነቃቃ እጅግ አስገራሚ ኢትዮጵያ እንደሆነ ከታች በምሰጣችሁ ቪዲዮ እንመለከታለን።
፤ሰንታየሁን ይዞ በየታክሲው በየ ምናምኑ እየሄደ ቪዲዮ እየቀረጸ “ዋይ!ዋይ! ሲል የነበረ>> የሚለውም ከታች የማቀርባቸው የቪዲዮ ሊንኮች የሚያሳየው “እስክንድርና ስንታየሁ” የሰሩት ታምራዊ ጀግንነት በግፍ ከየመኖርያ ቤቶቻቸው እየተገፈተሩ ከረምት በዝናብ ውስጥ የበሰበሱትን አዛውንቶችና የህጻናት እናቶች ዕምባ ሄዶ አነጋግሮ ያጽናናቸው ፤ ምግብ የሰጣቸው፤ ዕምባቸው ያበሰላቸው፤ ስቃያቸው በሚዲያ በቪዲዮ ቀርጾ እንዲሰማ ያደረገ (ሁለቱም ጀግኖች) ኢትዮጵያዊያን በደልና ጩኸት ድምጽና ዋይ ዋይታን ነው ሲያስተጋባና ለሕዝብና ለዘጋቢዎች ሲያስተላልፍ የነበረ እንጂ “”በየምናምኑ በየታክሱ እየሄደ ለታይታ “ዋይ ዋይ” የሚል ሰው አልነበረም”። ዘመድኩን <<የናቶችና የህፃናት እምባ ይውጋህ>> እንዳልልህ ልጆችና ውድ በለቤትህ ስላሉህ ላንተ ይህንን አልመኝም>>። ግን ንግግርህ በጤንነትህ ከሆንክ ነውር ነው። የሕዝብን ድምጽ የሆነን ሰው ማቃለል፤ በሰማይም በምድርም ያስኮንናል።
በመቀጠል፡
<<እስክንድር ለኢትዮጵያዊያን የጠቀመ እንጀራቸው የነበረ አመራን
ግን ቅርቃር የቀበረ ፤ጉድጓድ ውስጥ የከተተ፤>> ስለሚለው ውንጀላው ደግሞ
ዘመድኩን በቀለ ኢትዮጵያና አምሐራ ሕዝብ ለየብቻ አድርጎ በመመለክት ልክ እንደ ወያኔዎች “ኢትዮጵያ” ለትግሬው ምኑ ናት እንደሚሉት ሁሉ ዘመድኩንም ኢትዮጵያ ለአምሐራው ምኑ ናት ሲል በግልጽ ኢትዮጵያ አገሩ አንዳልሆነች ይዘባርቃል። ኢትዮጵያ አምሐራ ሲጠቃ አልጮኸም ሲል በደንቆሮ ክርክሩና ውግዘት ኢትዮጵያዊያንን (ኢትዮፒያኒስቶች) ሲያወግዝ እሰማዋለሁ። ለመሆኑ አምሐራውን የበደለው ኢትዮጵያዊያን ናቸው ወይስ አምሐራው ራሱ ካብራኩ የወጡ ልጆቹ?
አምሐራ ተበድሏ/ተበድላለች እና ጩሁላቸው ሰንላቸው እነኚህ ዛሬ “አምሐራ ነን” የሚሉ ተመጻዳቂ አምሐራዎቹ ምን ነበር ሲሉ የነበረው? ከማንስ ጋር ነበር በማበር አፍንጫቸውና ኣፋቸው ከድነው ቆመው የነበሩት? ጎጃም፤ ጎንደር፤ ወሎ ማን ጋር ነበር ቆመው እስክስታ ሲመቱ የባዕዴን ባንዴራ እያውለበለቡ፤ የባዕዴን መታወቂያ አንግታቸው ላይ እያንጠለጠሉ ከማን ጋር ነበር የወገኑት? ከወያኔና ከኦሮሙማው አብይ አልነበሩም (እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ? የአምሐራ ወጣት የት አባቱ ነበር ተሸሽጎ ወይንም ወግኖ ሲታገል የነበረው ? ወጣቱና ምሁሩ “የማን አባቱ ጎፈሬ ሲያበጥር” ነበር ሌላው (ኢትዮጵያዊው) አምሓራ ሲገደል ቆሞ ያይ ነበር የምትለው?
እስክንድር ለኢትዮጵያ የጠቀመ ለአምሐራ ጉድጓድ የከተተ የሚል አንዲህ ያለ በጣም የጨመለቀ ስድብና ውንጀላ ዕብድ ሰው የሚለው ካልሆነ ምን ሊባል ይችላል? ለኢትዮጵያዊያንም ለአምሐራውም እንዴት እንደታገለላቸው ከታች በሊንኩ የቀረቡት ቪዲዮዎች ማስረጃውን ተመልከት!!!
በዚህ በረዢም የትግል ዘመኔ አፋቸው እንደ ኦይሰተር ሲቀዱና ሲዘጉ አይቻለሁ። አፋቸው የሚቀዱ ኦይሰተሮች ብዙ ያየሁ ብሆንም እንደ ዘመድኩን አይነት በጣም የሚከፈት ግን አላየሁም። ደግሞ ወደ ውጭ አገር የመጣው ባጭር ጊዜ ሆኖ መአት ኦይሰተሮች ነው ያፈራው።
እንዲህም ይላል፡
<<እስክንድር ጠንቋይ ቀላቢ ነው፤ ማሰረጃ ቪዲዮም አለኝ>> ሲል ይናገራል። እንዲህ ያለ ቀዳዳ ስም የማጠልሸት ባሕሪ አይቼም ሰምቼም አላውቅም። ይህ ስም ማጠልሸት ሃሜት ያገኘው ሌላ ጊዜ ማንነቱን ለማሳየት ከምመለስበት የሻዕቢያ ባንዴራ እየሳመ በሚለፈልፍበት አዳራሽ ውስጥ እያውለበለበ ታዳጊ ህጻን የሚመስል በጣም የደነቆረ "Strange" የሚሉት ዓይነት “በላይ መንገሻ” የተባለ አዲስ አበባ ውስጥ የሚኖር በአፓርታይድ ግርድናነቱ የሚዋብ የአብይ አሕመድና <<የሻዕቢያ የፖለቲካ ማዓረስነት>> /Stooge/Puppet/” ግርማ የሚመስለው ምናልባትም ዘመድኩን የስም ማጠልሸት መረጃው ያገኘው ከዚህ ወፍ ዘራሽ ኦይሰተር ሳይሆን አይቀርም።
ይህ ሲነሳ አንድ ነገር ትዝ አለኝ።
የትግሬ ምሁራን ልክ እንደ እነዚህ ያሉ
ስም አጥፊዎች የሸዋ ሕዝብ ከቤተክርስትያን መልስ ወደ ጠንቋይ የሚሄድ ሕዝብ ነው እያሉ በሸዋ ሰዎች ስም ሲያጠፉ ብዙ ጊዜ
ሰምቻለሁ (መምህር ገብረኪዳን ደስታ እና ዶ/ር ገላውዴዎስ አርአያ ለምሳሌ…) አሁን እየሰማነው ያለው ደግሞ ተመሳሳይ ዘመቻ
ነው።
በመጨረሻም “ኢትዮጵያውያን ሆይ” የዚህ ሰው “ክፋትና መርዛማ ሰም ማጠልሸት” ምን ያህል “ፕሪሚቲቭ” ሰው እንደሆነ ወደ እዚህ “ውጭ አገር” በቅርቡ የተቀላቀለን አደገኛ ስም አጥፊ መሆኑን እና “ኢትዮጵያኒስት” የሚል ቃል ለዘመድኩን በቀለ፤ ምን ያህል ጥላቻ እንዳለው ለማየትና እስክንድር ማን መሆኑን እንድታዩት “ዘመድኩን ከዋሻቸው ውሸቶች እውነቱን ለማበጠር እንዲያስችላችሁ” ይህንን ከታች የማቀርባቸው ለማስረጃ ከማሳያችሁ ከመቶዎቹ የቪዲዮ ሊንክ ማስረጃዎች ጥቂቶቹን ሊንኮች ላሳያችሁ። ቪዲዮዎቹ የሚያሳዩት ዘመድኩን እንደሚለው “ወደ አሜሪካ የመጣው ባለቤቱና ልጁን ለመቀለብ ከሕዘብ ገንዘብ ለመዝረፍ ሳይሆን የእስክንድር ቃል ልዋስና <<ከቀበሮ ጉድጓድ>> ወጥቶ << አምሐራ ከፍተኛ ጀነሳይድ እየተፈጸመበት እንደሆነ ለማስቆም እነ ፕሮፌሰር ጌታቸው ሃይሌን እና የመሳሰሉ አገር ወዳድ ምሁራን ይዞ ወደ ተባበሩት መንግሥታት ስሞታ ለማስሰማት እንጂ ገንዘብ ለመስረቅ እንዳልሆነ ብዙ የሰነድ ማስረጃዎች አሉ።
ዘመድኩን እንደሚለው አዲስ አበባን የሸጠ ፤ ያዲስ አባባን ሕዝብ ያላሸቀ ሳይሆን፤ የሕዝብ ልቅሶ፤ የቤቶች መፍረስ፤ የአምሐራ መፈናቀል፤ አርበኞች እና አርበኝነት ምን እንደሆነ ጧፍ አብርቶ ወጣቱን ሃውልት ፊት ለፊት ቆሞ ያስተማረ፤ ስለ ዲሞክራሲ (ሕዝባዊ ደምጽ)፤ ስለ ጥቃትና መብት “ምሁራን ጋብዞ” በራሱ ሚዲያ ሕዝብን እንዲነቃ ያደረገ ፤ ኢትዮጵያዊ አርበኛ እስክንድር ለታሪክ የተቀረጹ ቪዲዮዎቹ ለዘላለም የሚኖሩ ምሰክሮቹ ናቸው። ቪዲዮው እስክንድር በዋና ኢዲተርነት ሲያካሂደው ከነበረው “ኢትዮጲስ” የካሜራ ቀረጻ እና ከመሳሰሉ ሚዲያዎችና ጋዜጠኞች ጋር በመተባባር የተካሄደ የሚዲያ ማስረጃ እነሆ፤ <<ፍርዱ ለናነተው ልተው!!>>
የ80 ዓመቷ አዛውንት ከሚኖሩበት ቤት ከነእቃቸው በአንሶላ ተጠቅልለው ውጭ ተጣሉ!!
| ተሻገር ጣሰው!
https://youtu.be/DxckMgCkThY?si=-106ekJjXEueZzT2
#Ethiopis #Home less People #Home deconstruction
#Citizens forceful displacement #Addis Ababa
https://youtu.be/MPSIs8PGFeI?si=cidBePqDHKZ4o2q8
#ከባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ እርዳታ እንዳይቀበሉ የተከለከሉ የአዲስ አበባ ተፈናቃዮች #ኢትዮጲስ
https://youtu.be/hKwQKR_-PQU?si=NJ_v41SqULY37SW_
#ኢትዮጲስ #ቆሻሻ መጣያ የሆነው የለገሀሩ አንበሳ #የባልደራስ ከፍተኛ አመራሮች በለገሀር #እስክንድር ነጋ #ገለታው ዘለቀ #ስንታየሁ ቸኮል #Ethiopis
https://youtu.be/380N498wq0w?si=Ge9taPA7HTJZesSF
#Ethiopis #በአዲስ አበባ፤ ኮልፌ ቀራኒዮ፤ ካባ መኖሪያ ቤት የፈረሰባቸው ዜጎች #Force full
displacement in Addis
https://youtu.be/NLkDHcowdLY?si=3tW3VELTU7gF729Q
#ኢትዮጲስ #ቆሻሻ መጣያ የሆነው የለገሀሩ አንበሳ #የባልደራስ ከፍተኛ አመራሮች በለገሀር #እስክንድር ነጋ #ገለታው ዘለቀ #ስንታየሁ ቸኮል #Ethiopis
https://youtu.be/380N498wq0w?si=bVYlarwjehPRWt3O
የካቲት 12 የሰማዕታት መታሰቢያ ቀን
https://youtu.be/dQvn3jh5ksg?si=urzp5G8TdSszcwIl
#ኢትዮጲስ #በአዲስ አበባ፤ አውቶብስ ተራ መንግሥት ያፈናቀላቸው
https://youtu.be/-tWhsuIohy4?si=jm9Xj3x1ikblL7Go
#የአማራን ሕዝብ ለማፈን እየተደረገ ያለ መንግሥታዊ የትጥቅ ዘመቻ #ፋኖ #Ethiopis #Bahire Hasab
https://youtu.be/g7tlCL10Ki8?si=lOgBDvmeW-kpQox4
Ethiopian journalist Eskinder Nega on
World Press Freedom
https://youtu.be/7EUDiLYLpz8?si=QF0FPf4ARdGvOWrT
አፋቸው እንደ ባሕር ኦይሰተር የሚከፍቱ በጨረቃ ላይ የሚጮሁ የሰው ተኩላዎች የአፋቸው “ክፋት” እና “ክፍተት” አሳሳቢ ደረጃ መድረሱ ለነሱ ጤና ጎጂ የማሕበረሰባችንም “ቀውስ” ምን
ያህል ጥልቀት ውስጥ እንዳለ
አመላካች ቀስት ነው። ለማንኛውም በተጠና መንገድ ማይሙም ፊደል የቆጠረውም፤ ምሁሩም እንደ ከብት መንጋ የተነገረውን ሳያላምጥ
እየዋጠ እስክንድርን መዝለፍ እጅግ ነውረኛነትና የተጠበቀው የብርሃን ተስፋም ጭምር እንዲደበዝዝ አስተዋጽኦ ማድረግ ነው።
ሰላሙን ለናንተ ይሁን!
ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay