Wednesday, February 1, 2017

በፋሺሰት ስርዓት የሚታበይ የመምህር ገብረኪዳን ደስታ ሞልቶ የፈሰሰው ውሸት ጌታቸው ረዳ (የ Ethiopian Semay አዘጋጅ) 2/2/2017



በፋሺሰት ስርዓት የሚታበይ የመምህር ገብረኪዳን ደስታ ሞልቶ የፈሰሰው ውሸት
ጌታቸው ረዳ (የ Ethiopian Semay አዘጋጅ) 2/2/2017
Gebrekidan Desta
በወያነ ትግራይ የተጠነሰሰው የፋሺዝም መርሆ፤ በአስፈሪ ሁኔታ በተከታይ ወጣቶቻቸው፤በኪነት ባለሞያዎቻቸው(በተለይም ወጣት ሙዚቀኞቻቸው የሚዘፈኑ ግጥሞችን) እና በትግራይ ብሔረተኛ ምሁራኖች ዘንድ ተስፋፍቷል። ፋሺዝም ተወረርን፤ተነጠቅን በሚል ቅስቀሳ ይነሳና፤ እቅዱን ለማስፈጸም የኔ የሚለውን ነገድ ይህ “ተረግጠሃል፤ተንቀሃል” በሚል የማነሳሻ ሰበብ ተንተርሶ ተከታዮቹ እንዲቆጩ በማድረግ ፤የድሮ ትውልድ ታሪክ፤ጀግነት፤የበላይነት፤ተስፋፊነት፤ቀማኛነት እና ቂመኛነትን ባንድ ነገድ ላይ ያነጣጠረ ግድያና ጥቃትን በመፈጸም፤ አስፊሪ ማሕበራዊ ቀውሶችን “መመሪያው በማድረግ”፤ በተለይም “በባሕልና የቆየ ታሪክን በእቀባ አመክንዮ” እንዲቀሰቀስ በማድረግ ‘የሙዚቃና የጽሁፍ ቅስቀሳዊ ስብከት’ ወደ ተከታዮቹ ባማስሰረጽ ተከታዮቹን “የሕሊና እውሮች በማድረግ” በስሜት አስክሮ አስፈሪ ጸረ ሰላም እና የጠብ አጫሪነት፤ ሞገደኛነትን እና የሃብት ክምችት ባንድ ነገድ የበላይንትን የሚያበረታታ አደገኛ መርሆ ነው። ይኼውም ሁላችሁም እያያችሁት ያለው የወያኔ መርሆ እና ድርጊት ‘ፋሺዝም’ ነው።

ትግራይ ኦን ላይን በተባለ የወያኔ ጀሌ ድረገጽ አንድ ምሳሌ ጠቅሼ ልለፍ፡
“Extraordinary historian Memhir Gebrekidan Desta exposes the fake issue of Wolkayit and Tsegede. This valiant Tigrawai historian is doing what he can. What about about the rest of us? We need to speak out before it is too late. Our land, and our history is continuously stolen. "ንሕና ዳግም ድም ክንከፍል ዳግም ክንስዋእ ዳግም ክንጥቃዕ ኣይብልናን" መምህር ገብረኺዳን ደስ” Tigraionline ይላል::

 “Our land, and our history is continuously stolen” ይላል። መሬታችን፤ታሪካችን በተከታታይ ስንወረር ቆይተናል…. ይህ የፋሺዝም እምነት ዓይነተኛ ምሳሌ ነው። በዚህ ሌላ ቀን እንመለስበታለን። አሁን ትግራይ ኦን ላይን የመምህር ገብረኪዳንን የታሪክ ትንታኔ ትግሬዎች አንዲከተሉ አበክሮ ይተውታል። መምህር ገብረኪዳን ሁላችሁም ታውቁታላችሁ ብየ እገምታለሁ። ፎቶግራፉም ከላይ በአፄ ዮሐንስ መኖርያ ግቢ በመቀሌ ከተማ የተነሳው ፎቶግራፍ ከላይ የምታዩት ነው። “ይድረስ ለጎጠኛው መምህር” በሚል ርዕስ መጽሐፍ የጻፍኩበት ሰው ነው። 

ባጭር አገላለጽ ሰውየው፤ ጠባብ የትግራይ ብሔረተኛነትን የሚያቀነቅን፤ የትግራይ የበላይነትን በሌሎች ነገዶች ላይ ገዢነቱን እንዲጠበቅ አጥብቆ የሚወተውት፤በጉልተኛ፤ የትግራይ መሳፍንት፤ በትግራይ ነገሥታት እና ዘመናዊው የወያኔ ፋሺዝም ሥርዐተ መንግሥት አድናቂ እና በተለይም በዘመድ በአዝማድ፤በሥጋ በአጥንት ቁርኝት፤ በወንዝ እና በአበካባቢ ትስስር ሕሊናው የሰከረ፤ እንዲሁም “ወያነ ትግራይ” የተባለው በሻዕቢያ ልሳን እየጠባ ያደገ፤ የባሕር ወደቦቻችንን በስጦታ ለዓረብ አሽከሮችን የለገሰ፤ አገር ድፍን ያወቀው ‘ፋሺስታዊ እና የባዕዳን ተለላኪ ቡድን’፤ ሰብአዊ ወንጀል በመፈጸም የተዋቀረው ቡድናዊ “ትግራዋይነት ፖለቲካን” እንደ ጀግንንት ቆጥሮ የሚፎልል ትግራይ ካበቀለቻቸው ማፈሪያዎች አንዱ የሆነ የታሪክ አጭበርባሪ “falsifier of History” ግለሰብ ነው።

ባለፉት ወራቶች በተከታታይ ከተለያዩ የወያኔ ጋዜጠኞች ጋር ቃለመጠይቅ ሲያደርግ ተከታትለነዋል። በቅርቡ ደግሞ አጭር ቆይታ ያደረገው ስለ ወልቃይት አመጣጥ ወይንም ወልቃይት የማን ነው? የሚል ጥያቄ ቆርቦለት የሰጠው የተለመደው በሰነድ የማይገኝ፤ታሪክ የማይደግፈው ውዥምብራም የትግራይ መሬት ነው የሚል መከራከሪያ በትግርኛ ባደረገው ቃለ መጥይቅ ሲመልስ አድምጠናል። ከዚህ በታች ወደ አማርኛ ትርጉሜ ሳቀርብላችሁ የወልቃይት ታሪክ የምታውቁ ወልቃይቴዎችም ሆናችሁ ሌሎች ኢትዮጵያዊያን መልስ ለመስጠት አንዲያመቻችሁ በሚል ተርጉሜላችኋለሁ። ስትጠቅሱ ግን እባካችሁ እኔ አንደተቀስኩት (ተርጓሚው) ልክ ጥቀሱ (ምንጩንም ትርጉሙም)

ውሸቱን ከእውነታው ለይታችሁ ኣእምሮ ላለው አንባቢ እና ማሕበረሰብ እንድታስተምሩ ይረዳ ዘንድ የተናገረውን ቃል ሳልጨምር፤ሳልቀንስ እነሆ ገብረኪዳን እንዲህ ሲል ለተጠየቀው መልስ ሰጥቷል።

የወያኔ ጋዜጠኛ፤

የወልቃይት ታሪክ አመጣጥ ምንድ ነው?

መልስ፤-

የወልቃይት አመጣጥ እና ምንነት በሁለት ሦስት ቃላቶች የሚገለጽ አይደለም።  ታሪኩ ረዥም ነው።ወዴት ነው የሚወስደን/የሚሄደው/የጣሊያን አመጣጥ እና የአፄ ዮሐንስ እና የዳግማዊ ምኒሊክ ንግሥነት/መንገሥ የተያያዘ ነው። ወልቃይት ጸገዴ እየተባለ ያለው “ፀለምቲ” ነበር ሲባል የነበረው።ከተከዜ ማዶ ያለው በሙሉ ‘ፀለምቲ” ነበር እየተባለ ሲጠራ የነበረው። በ1886 ዓ.ም  ምኒሊክ ከትግራይ ነጥቀው ለእቴጌ ጣይቱ በልዩ መተዳደሪያ ጉልትነት የተሰጠ ነው። ለምሳሌ እንደርታ የራስ አርአያ ጉልት ነበር።በዛው ወቅት ሌሎች ማሳፍነቶች በሙሉ የሚተዳደሩበት የተሰጣቸው ጉልቶች ነበርዋቸው። ስለዚህም (ወልቃይት) እቴጌ ጣይቱ ግብር የሚያስገብሩበት፤የሚያስተዳድሩበት ወዘተ ተብሎ በምኒሊክ ትዕዛዝ የተሰጣቸው ነው። ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ወልቃይት የእቴጌ ጣይቱ ልዩ ጉልት ሆኖ ቆይቶ ነበር።

በ1940/ዎቹ ገደማ ወደ ደጃች አዳነ ወደ ዳበት እንዲጠቃለል/እንዲገዙት ተደረገ።ስለዚህ ወልቃይት ተባለ፤ ጸለምት ደግሞ ለብቻው ተለየ።በዚህ መንገድ ጠለምት በዚህ መንገድ ሲተዳደር ቆይቷል።የወልቃይት ሕዝብ ግን ከጥንት ከአክሱም ዘመነ መንግሥት ጀምሮ የትግራይ ግዛት ነው። ያ ብቻ ሳይሆን፤ሰቆጣ ፤አለውሃ ምላሽ፤ለማልሞ ምላሽ፤ “ማይ ፈሰሶ ይባላል”። እነኚህ ሁሉ የትግራይ ግዛቶች ናቸው። 

አሁን ትግል ተካሄደ። ህወሓት ትግል አካሄደ።ሕዝቦች በቋንቋቸው እንዲከለሉ ተባለ። በአዋጁ መሰረት  ትግራይ በቋንቋ ተከልሏል አልተከለለም አላውቅም።አላወቅኩም ብቻ ሳይሆን “የቀረው ብዙ (ቦታዎች) አለ”። ዓዲ አርቃይ ቀርቷል፤በቅርቡ በ1945 ዓ.ም የተወሰደብን የትናንትናዋ “አለውሃ ምላሽ” በዛው ተወስዳ ቀርታለች፤ የትግራይ ሕዝብ ግን መንግሥት ባሰመረላቸው አክብረው ይኖሩ ነበር። ስለዚህ የወልቃይት ፀገዴ አካሄድ ይህንን ይመስላል። 

ወልቃይት በዘመነ አፄ ዮሐንስ የትግራይ ግዛት ነበር የነበረው፤እነ ራስ ሓጎስ ነበሩ ሲያስተዳድሩት የነበረው። ወልቃይት፤ጸገዴ፤አለውሃ ምላሽ፤’ለማልሞ ምላሽ (ለማልሞ እኮ ነው የሚባለው! እነሱ “ሊማሊሞ” ይሉታል እነሱ፡ ስሙን እንኳ በደምብ አይጠሩትም)፤ወልቃይት ፀገዴ ደግሞ “ወልቃይት ጠገዴ” ይሉታል። ፀለምቲ ደግሞ ‘ጠለምት’ ይሉታል፡ “ጸለምቲ” ነው የሚባለው።ስለዚህ የቦታዎቹ ስም እንኳ በትክክል አይጠሩትም።ስለዚህ “የትግራይ አካል ነው!!”
ምኒሊክ ከመጣ በኋላ፤….ጣይቱ መቸስ ሰሜነዊት ነች። (ገብረኪዳን “ጣ” የሚለው የጣይቱ ስም “ወልቃይቴዎች ለምን ‘ፃይቱ አይሏትም” ብሎ እንዳይሟገት ብቻ ያስፈራል። ጠ/የሚለው የጠገዴ አጠራር ‘ፀ ለምን አይሉትም ብሎ የፀገዴን ቃላት ፀጉር ስንጠቃ እየሰነጠቀ እንደዳከረው፤ አስገራሚ!!) ጎጃም፤ጎንደር ወሎ ነች።ሚስቱ ነች። ጉልት ነው ብሎ ሰጣት።በዚህ መንገድ አካባቢው በእጇ (በይዞታዋ ስር ነበር) ቆይቷል። አፄ ሃይለስላሴ ከነገሱ በኋላ ፤የጣይቱ ልዩ ግዛት የነበረው፤ከዳባት አውራጃ ጋር እንዲደባለቅ አደረገ ፡ በ1940 ዎቹ አካባቢ። ታሪኩ ይኼ ነው።
ጥያቄ፦

ስለዚህ ወልቃይት ከጥንቱ ከመነሻው ከታሪኩ የትግራይ ነበር ማለት ነው።

መልስ፤-

አዎ፤እንዴ ወልቃይት ብቻ ሳይሆን “ለማልሞ ምላሽ በሞላ እኮ ነው የምልህ።ወልቃይት እማ በሙሉ ነው። የቀረብን አረ ስንት ሌላ ቦታ አለ።እነ “ዓዲ ሠላም”፤ ለሁለት የተከፈለው ጠለምት ሁሉ የትግራይ ነው። የትግራይ ሕዝብ ግን ፤እንጃ የመሬት ጉዳይ ብዙም ቀልብ/ደንታ አይሰጠውም መሰለኝ ብዙም አላተኮረበትም።ትግራይ ነው በሙሉ። እሱ ብቻ አይደለም፡ “ፀገዴ” እኮ አሁን በሁለት ነው ተከፍሎ ያለው። አንድ “ፀገዴ” ብቻ ነው በታሪክ የሚታወቅ።ወደ እዛው የቀረው “ፀገዴም” የትግራይ ነው።

ምክንያቱም አለውሃ ምላሽ፤ለማልሞ፤ ራስ ደጀን፤አንገረብ ምላሽ “ሱዳን” ወደብ ነው የሚያዋስነው።ስለዚህ አሁን ቀርቶብን ያለው ቆላ ፀገዴ የትግራይ ነው። ዛፎቹ/ወንዞች፤ መንደሮቹ እኮ ማን መሆኑ እራሱ በመጠሪያው ይጠቁምሃል።ማለት መሬቱ እራሱ አፍ አውጥቶ ማንነቱ ይነግርሃል እኮ!

ጥያቄ፤ 

ታዲያ መምህር፤ ለምድ ነው እንደዚህ ከሆነ ይህ ጥያቄ ዛሬ ለምን ተነሳ?

መልስ፤-

ለኔ እንደገባኝ፤ ለ25 አመት ቅስቀሳ ሲያካሁዱበት የቆየ ጉዳይ ነው፤ “ወልቃይት ጸገዴ” እያሉ “በማይመለከታቸው” እየዘፈኑ ቆይተዋል። ለምሳሌ በአንፃሩ የትግራይ ሕዝብ “አለ ውሃ ምላሽ”፤ ሰቆጣ  ቀረብን” ወዘተ….እያለ ሲዘፍን አልሰማንም፤ አልተሰማም። ካድሬዎቻችንም ሲቀሰቅሱ፤ሲናገሩ አልተሰሙም። ትግራዋይ ግን አለውሃ ምላሽ የማን መሆኗን ያውቃል፤ ግን አይዘፍንም። “እነሱ” ግን 25 አመት ዘፍነዋል። ስለዚህ ቀስቅሰውታል።

ሁለተኛ ምክንያት፤ “ከኤርትራ ወንድሞቻቸው ጋር አጣልተናቸዋል፤ ከኋላ ከጓሮአቸው እሳት ተለኩሷል የሚል አምነት ላቸው።ሦስተኛ ምክንያታቸው ደግሞ፤ “ህወሓት” ከመለስ ዜነዘዊ በኋላ ተዳክሟል፤ እንዲሁም የትግሬ ታጋይ በዕድሜ እያረጀ እንዲሁም በትዳር፤ በልጅ፤ በኑሮ የተጠመደ እና የተዳከመ ነው፡ ስለዚህም (ወቅቱ አሁን ነው) የሚል እምነት አላቸው።

ሌላ ቀርቶ አዲስ አበባ ያሉት ህንፃዎች የትግሬ ነው እያሉ ይቀሰቅሳሉ፤ መቸስ የሌላ “ብሔር” ሰው ፎው ሲቆጥሩ ሰምተን አናወቅም። ትግሬዎች ወርረውሃል እየተባለ ቅስቀሳ እየተደረገ ነው። ይህ ሁሉ ሲቀሰቅሱብን ፤ እኛ “ምን እየተነገረ ነው፤ ምን እየተወራ ነው፤ ብለን ተናገረን ጠይቀን አናወቅም”፡እነዚህ ሰዎች በእውጭ አገር ብዙ ቅስቀሳ ያደርጋሉ፡አገር ውስጥም የነሱ ቴሌቪዥን የሚናገረው ይሄንኑ ነው። ውጭ አገር ያለው ትግሬ ግን ምንም አይናገረም። እዚህ ያለነውም ምንም አልተናገርንም፤ ዝም ነው ያልነው። ምክንያቱም ትግራዋይ ‘ዝም ካልክ” ሰላም ይመጣል ብሎ ስለሚያምን ይመስለኛል!

ግን ትግራዋይ ጉልበት ካገኘ በኋላ ነው ኢትዮጵያ ውስጥ ተከብሮ ያለው እንጂ ፤ትግሬ ለምኖ ተከብሮ አያውቅም በታሪኩ በጭራሽ። ትግሬ ሲዳከም/ሲደክም ነው የሚመታው/የሚጠቃው።በዘመነ ሱሑል ሚካኤል የትግራይ ሕዝብ ሃይለኛ ነበር፤ሱሑል ሲሞት ማን መጣ “ሃይለኛው ራስ ወልደስላሴ”፤ በዛውም ዘመን ትግሬ ተከብሮ ቆይቷል፡ ከዚያ በኋላ ደጀዝማች ስባጋድስ መጡ፤ ስበጋድስ ሲሞቱ ፡ “ትግራይ” ተወረረች። በደጃች ውቤ ተወረረች።ስለዚህ ደጃች ውቤ (ትግራይን) “አፈር ድሜ” አበሏት።ስለዚህ ትግራይ አጼ ዮሓንስ በነበሩበት ጊዜ ትግሬ የተከበረ፤የተፈራ ነበር።፡ትግራዋይ ግን ጉልበት አለኝ ብሎ የሌላውን ቦታ፤መሬት፤ለመያዝ ለመውረር አይፈልግም፤ወርሮ አያውቅም። ስለዚህ ዮሐንስ ሲሞቱ ግን እንደገና ተደፈረ፤ ትግሬ ተገፋ፤ተጨቆነ፤ተረገጠ፤ተገዛ።ስለዚህ “እነሱ” የገመቱት “ትግራዋይ/ትግሬ” ተዳክሟል እና ወቅቱ አሁን ነው በሚል ነው ዛሬ የተነሱበት ምክንያት እና፡ ይህ ሁሉ ሁካታ።

ጥያቄ፤--

መምህር በአፄ ዮሐንስ እና በአፄ ሃይለስለሴ ዘመን የወልቃይት ጥያቄ ተነስቶ ያውቃል?

መልስ

 ማን ያበደ ነው እንዲህ ያለው ጥያቄ የሚጠይቅ?! እምቢ ላለው ሰው ጥይት አጉርሰው እኮ ነበር ዘመኑ።ትግሬ አይናገርም፤፡ እስከ 1940  ዓ.ም ሲወስዱት እኮ ራስ ሥዩም ነበሩ። ራስ ምንም አላሉም። ምንድ ነው ያሉት፡ ልዕልት ወለተ እስራኤል፤የአልጋወራሽ አስፋወስን ባለቤት ነበሩ። ወለተ እስራኤል ደግሞ የራስ ስዩም ልጅ ናቸው።ስለዚህ ካንተ ጋር ቢቆይ የልጅህ ግዛት ነው፤ ወደ ወሎ ቢሄድም የልጅህ ግዛት ነው፡ሲሏቸው፤ እሺ ብለው ተቀበሉት።

ጥያቄ፦ 

እሺ መምህር፤ በመጨረሻ የሚያስተላልፉት መልእክት ካለዎት ዕድሉን ልስጥዎት፤

መልስ

የማስተላለፈው መልእክት ለትግሬ ወጣት እና ለትግራይ ሕዝብ ነው። እኛ ከእንግዲህ ወዲህ “ዳግም ደም ልንከፍል፤ ዳግም መስዋእት መክፍል፤ዳግም መጠቃት የለብንም!” ይህች በተለይ ይህች መልእክት የትግራይ ሕዝብ፤በተለይ የትግራይ ወጣቶች ሊገነዘቡት ይገባል።ስለዚህ ትግራይ የጀግና አገር እንጂ አንክርዳድ አይበቅልባትም ብሎ ደፍሮ መናገር አይቻልም። ምክንያቱም፤ “እንክርዳድ” የጠላት መሳሪያ ነው። ስለሆነም (እንክርዳዶች አሉን)። ስለሆነም የትግራይ ሕዝብ አንድነቱ አጥብቆ በመያዝ፤ ያለፈው ታሪኩ በመንከባከብ፤ ለ17 አመት ታግለን ያገኘናት መብት “ከእጃችን እንዳታመልጥብን” ልክ እንደ አንድ ሰው ሆነን ሁላችን ልንጠብቃት ይገባል። በታሪካችን በባህላችን እና በቋንቋችን የውጣ ውረድ ገበያ ማድረግ የለብንም።ሁላችንም አንድ ሆነን ማንነታችንን እንጠብቃት እላለሁ።

ጥያቄ፤-

እሺ መምህር አጠር ላለው ጥያቄ አጥር ያለ መልስ ስለሰጡኝ አመሰግናለሁ፡

መልስ፤- እኔም አመሰግናለሁ።

ትርጉም ጌታቸው ረዳ (ኢትዮጵያን ሰማይ ድረገጽ አዘጋጅ) Ethiopian Semay – getachre@aol.com