Sunday, May 19, 2013

በፖለቲካና በሃይማኖት የማሻኮር ባሕሪ


My next commentary will deal  on Part 2 of those Ethiopian Muslim leaders  and their false teaching of the Ethiopian history.  I will show in brief their variety of distortion that will  continue next time from Part 1 of this page. My next commentary will be on Ahmedin Jebel on his distortion of Ethiopian history book from 615-1700 that he published and his claim of Ethiopia’s 1oo year independence as a sovereign  country.  This young Ustaz (Islamic preacher)  got his distorted history  from  the deluded and mercenary elements of the TPLF/OLF/EPLF Dedebit and NaKfa university  professors , best known as the  "University of distortion".  For your information, this young man has BA, MAS degree. This guy is also one of the Ethiopian Muslim leaders currently under TPLF prison cell. Those distorters of history are now currently called "our leaders" by deluded elements in the Muslim community and some  Christian elements and many of the opposition media reporters and website operators who accept teachers of distortion as their leaders.

With that segment- I will also question the validity of the so called The Bilal Show radio and TV Islamic teaching broadcast stations in the Diaspora and inside Ethiopia the symbol they install on the top of the TPLF current map.
Here is the sample. if this was a lion holding Ethiopian Christian cross as a symbol of Christianity,  which many Muslims complained about it over and over- they could have cry all over the glob, all over their conference. The naïve Christian opposition leaders such as Tamang Beyene could have cry loud on their behalf as he is accustomed to it. Unfortunately, here is the Islamic moon and star symbol on the top of the current TPLF Ethiopian map where no one, including their Tamang or the Islamic spokes people have  said nothing of such violation, except to accept it as legitimate symbol/emblem  of the Ethiopian people. What could the message of such symbol meant? Sharia/Islamic sate to be born in Ethiopia or what?  Can we get an answer?

በፖለቲካና በሃይማኖት የማሻኮር ባሕሪ


(ጌታቸው ረዳ)

 


Top photo UstaZ Abubeker Ahmed and the lower part photo is Mr.Tamang Beyene
 

Young Muslims in Ethiopia listening Abubeker's lie between Christian and Islam faith and Grang Ahamed as Saint who sent by Allah to bring justice and peace to the Ethiopian people by declaring Islamic government and Islamic faith to rule the desperate Christian Ethiopians who were suffering by the Kufar/ Infidel Christian rulers.
 
ጽሑፉ ኡስጣዝ አቡበከርና ታማኝ በየነን የሚመለከት በሰፊ ትንተና የተዘጋጀ ስለሆነ፤ ሬስቶራንትና የአሜሪካን ሶፍትቦል፤ የእንግሊዝ እግር ኳስ  ጨዋታ ማየት፤ ወይንም  ስታር ባክ ቡና ቁጭ ብሎ ለወሬ ለቀማ የምትጣደፉ ዘመነኞች ካላችሁ አንገታችሁ ተጎንብሶ የማንበብ አቅምና ልምድ ከሌለው፤ ንባቡን ከመጀመር አቁማችሁ፤ የተጣደፋችሁበት ጨዋታ እንዳያመልጣችሁ ጊዜ የሌላችሁ ሰዎች፤ጽሐፉንጸለማንበብ፤ከመጀመር፤ተቆጠቡ።


The Lady with Microphone on her hand with Yellow cover on here head is urging Amharic language to be replaced by Arabic and English. This lady if true is the one who said "Sharia and Islam not only in Ethiopia, but also will rule the whole world. If this is the lady who said such ridiculous Jihadist speech- it is concerning issue in such gatherings For for more information about the source please listen to the following You Tube information posted by some body.
Ethiopian Women Jihadist In washington DC Preaching about Islamic State 
 
 
ታሪካችን አንደ ፋሲካ በግ ለእርድ የሚያቀርቡ ግልብ ግለሰቦች ብዙ ናቸው። ‘ግልብ’ ሰው በጦቢያው ደራሲ በአቶ አፈወርቅ ገብረ ኢየሱስ ትርጉም “ቢከፍቱት ተልባ” ማለት ነው፡ ይላሉ። ደራሲው ሰፋ አድርገው በሰጡት የተልባ ትርጉም፤ “ምስጢር የማይቋጥር” የሚለው ትርጉማቸው ዛሬ በዚህ ትችት እኔ ለምሰነዝርበት የመድረክ ሰው የሚስማማ ትርጉም አንኳ ባይሆንም፤ በትግርኛችን ትርጉም  ግን ተልባ በጋለ ምጣድ እየተቆላ ቢከፍቱት በዙርያው ያሉትን ሰዎች እየነጠረ ቆዳቸውን ያቃጥላል፡ የሚለው ትርጉም ብወስድ፤ “ግልብ” የመድረክ ሰዎች በስሜት እና በአድርባይነት የሚሰነዝሯቸው አንዳንድ የታሪክ ንግግሮቻው ከሃቅ የራቁ ላንዳንዶቻችንም የሚያስቀይሙ/የሚያቃጥሉ ሆነው እናገኛቸዋለን።

 

መቸም መተቸት አንድነትን የሚያፈርስ ነው እያሉ እራሳቸውን “በመረጃ አስደግፈው” ከሚተችዋቸው ተቺዎችን ለመገላገል ሲሉ ትችት የሚጠሉ፤የመድረክ ሰዎች አሉ። ትችቱ አንዲቆም ከተፈለገ፤ እራሳቸው ከተምታታ ንግግር እና ማሻኮር (ማሳበቅ) መጠንቀቅ አለባቸው።

 

በዚህ ትችቴ ታማኝ በየነ እና እስልምናን የሚመለከት ነው። ሰውየው ብዙ ተከታይ እንዳለው ባውቅም፤ በየቦታው የተተከሉት ቱኪዎቹ (ጭቃ ሹሞቹ) በአሽኮኮ አስቀምጠው አትንኩብን ቢሉም፤ ሰውየው የሚያሻኩረው አንደበት ማቧደኑን ካላቆመ ትችታችን ይቀጥላል።



Yellow- the flag symbol the lord of terror Grang Ahamed who devastated Ethiopian Christianity in the 15th Century

 
ታማኝ በየነ፤አሁን ካለበት የማሻኰሩ ባህሪ ከመከተሉ በፊት፤ተፈጥሮአዊ ሁለገብ ችሎታው የለገሰቺውን ስጦታ ተጥቀሞ ያሳየው ሕብረተሰባዊ ሱታፌ በጣም አከብረው ነበር። እያደረ፤እየዋለ ስታዘበው፤በአንዳንድ ንግግሮቹ ‘ውሸታሞቹን’ እያጐረመሰ ሲመጣ የነበረኝ አስተያት ለሁለት ተገመሰ። ሰውየው በተሰጠው የተፈጠሮ ጸጋ በየቦታው እየተዘዋወረ የሚሰልበው የአድማጮቹ ልቦና ተደናቂነቱ እንዳለ ሆኖ፤ አብሮ ከሚሰብካቸው ስብከቶቹ ውስጥ  የሚሰነዘሩ አስቀያሚ ወይንም የተምታቱ የታሪክ ንግገሮቹ ተከታዮቹ እንዳይነጫነጩ ተብሎ በቸልተኝነት የሚተው አይደሉም።

 

በቅርቡ አሜሪካ ቨርጂኒያ ውስጥ እስላሞቹ በጠሩት ጉባኤያቸው ተገኝቶ፤ “አሰላም አሊኩም ወበረካቶ! አላሁ አክበር! ተክቢር! ተክቢር! ተክቢር!” ከሚለው እስላማዊ ሃይማኖታዊ መፈክራዊ ንግግሩ ብነንሳ፤ ለእኛ ለአንዳንዶቻችን ለክርስትያን አድማጮች ከሃይመኖታችን ሕግጋት ውጭ አንድ የኦክርስትያን ሃይማኖት እከተላለሁ ከሚል የፖለቲካ ሰው እና የክርስትያን ማሕበረሰብ አባል የናንተ ‘አላህ የኛም ‘አላህ ‘ ነው ከሚል ፖለቲካዊ ምዝመዛው (ኤክሰፕሎይተሽን) ብንነሳ፤ እከተለዋለሁ ከሚለው ኦርቶዶክሳዊ ሃይማኖት ሕግጋታዊ ሙግት የሚያምታታ እና የሚደባልቅ አዲስ ክስተት ነው። ምክንያቱም አስላሞቹ “የኦርቶዶክሳዊት ክርስትያን ምዕመናን አምላክ ‘እየሱስ ክርስቶስ’ የመሐመድን ያህል ቦታና ክብር እንጂ እንደ አምላክ አያዩትም። ስለሆነም ‘እየሱስ ከርስቶስ/ Eesa ታላቁ አምላክ ነው’ ብለህ በጉባኤያቸው ተገኝተህ መፈክሩን አንዲደግሙት ብታስፈክራቸው “እስላሞቹ” እንኳን ሊያስተጋቡት ቀርቶ ‘ሃይማኖታቸውን ለመዝረግ/ለማበላሸት’ የተላክህ “እስልምናን የምትንቅ /ኢንፊደል/ኩፋር” ተብለህ ‘ጸረ እስላም’ እንደሆንክ ታይተህ “ትደበደባለህ ወይንም ትባረራለህ። ሃቁ ይኼ ነው።

 

ለዚህም ምክንያቶች  አላሁ አክበር!  ማለት ይላሉ አንዳንዶቹ "Allah hu Akbar" which means 'God is great". It is not true that the 3 main Abrahamic religions all worship the same god. If you go by the book of Islam- you will go to hell if you worship the Christian god, and the same is true for Christians, who, by the bible will go to hell if they worship the Muslim 'Allah'. Same with the Jews. because we don't worship the same God as the Muslims. Allah doesn't claim Jesus as his son. "Allah" the word was there before Mohhamed/Isalm was born. itself the original Arabic language is originally the Arabian pagan Moon god.  The theology of the Arab Christian who uses the word Allah is completely different from the theology of the Muslim who also uses the word Allah.

ለምሳሌ የግብፅ ኦርቶዶክስ አረቦች እና የግብፅ እስላሞች አላህ በሚለው ቃል ሁለቱም ላይ በቃላቱ አጠቃቀም ላይ ልዩነት አለ ይላሉ። አንድ ጻሐፊ እንዲህ ይላሉ፦ ለምሳሌ 95% ግብጻዊያንወላሂ” "Walahy" ሲሉ ኮፕቲክ ክርስትያኖቹ ግን "Tesdane"تصدقني  በማለት በአላህ ላለመማል ይምላሉ። (as replacement, just to avoid using the name Allah.)  

 

ባጭሩ እስላሞቹ እኛ የምናመልከውን ፈጣሪ እንደ አምላካቸው/ ፈጣሪያቸው አይቀበሉትም፡ እኛም የምናመልከው ፈጣሪ፤ እስላሞቹ ከሚያመልኩት ፈጣሪም ሆነ መልእክቶች፤ትርጉሞች፤ሕግጋቶች፤አምነቶችና ሰበካዎች፤ ስለማይገናኙ አይቀበሉትም። ለዚህም ነው በእስልምና እና በክረስትያን መካካል ከተፈጠረ ጀምሮ እስካሁን ድረስ ጦርነቱ እየጦፈ ያለው።ስለዚህም ነው የታማኝ “አሰላም አሊኩም ወበረካቶ! (ለምን  እንደሚጠቀሙበት ባይገባኝም ፤ ይህኛው ለዓረቦች እንጂ የራሳቸው ቋንቋ ላላቸው ለአበሾች የሚሰነዘር የሰላምታ ልውውጥ አይደለም። ምክንያቱም እያንዳንዱ እስላም በየቤቱ ሲገባ  ከሚስቶቻቸውና ከወላጆች ጋር የሚነጋገሩባቸው ቋንቋዎች “ዓረብኛ” እንዳለሆነ ስለምናውቅ። እስላሞቹ ባላጡ ቋንቋ ለምን አዘውትረው እንደሚጠቀሙበት ባይገባኝም) እና “አላሁ አክበር! ተክቢር! ተክቢር! ተክቢር!” የሚለው የታማኝ አሻኳሪ ሃይመኖታዊ አዘል ፖለቲካዊ ‘ምዝመዛ’፤ ካንድ “ኢትዮጵያዊ  ኦርቶዶክስ ክርስትያን አማኝ” ሃይማኖቱ ሳይለውጥ በአደባባይ “አላሁ አክበር/ተክቢር፤ተክቢር! ተክቢር!” የሚለው እስላማዊ የሃይማኖት መፈክር ሊደመጥ ከክርስትያናዊ ደምብ የጣሰ ስነ ምግባር ነው።

 

ለማጠቃለል ያህል፤ ከክርስትያን እምነት ውጭ የቁርዓንን ሕግጋት የሚከተሉ እስላሞች ‘የመጽሐፍ ቅዱስ’ ሕግጋት ከሚከተሉ ከክርስትና የተከታዮች እምነት አንድ ስላላሆነ ነው በሃይሞበት የምንለያየው። ለምሳሌ ቁርዓን/እስላሞች እኛን “ኩፋር” ከሚሉን እስላሞች ያልሆነን ሕብረተሰብ ወደ እስልምና ለማጥመቅ ቢያንስ እስልምናን ለማስፋፋት 109 አንቀጸች “ሃይልን” የመጠቀም ትምህርት እንደሚያስተምር የሃይማኖት ተከራካሪዎች ይጠቁማሉ።

 

ለምሳሌ Quran (8:12) - "I will cast terror into the hearts of those who disbelieve. Therefore strike off their heads and strike off every fingertip of them" የሚል ብምወስድ እና Quran (8:39) - "And fight with them until there is no more persecution and religion should be only for Allah"   ይህ ባጭሩ ምን ማለት ነው?  From the historical context we know that the "persecution" spoken of here
was simply the refusal by the Meccans to allow Muhammad to enter their city and perform the Haj.  Other Muslims were able to travel there, just
not as an armed group, since Muhammad declared war on Mecca prior to his eviction.  The Meccans were also acting in defense of their religion, since it was Muhammad's intention to destroy their idols and
establish Islam by force (which he later did).  Hence the critical part of this verse is to fight until "religion is only for Allah."

 

Quran (9:123) - "O you who believe! fight those of the unbelievers who are near to you and let them find in you hardness."

 

በዚህ ሕግጋት እና በመሳሰሉት በረካታ ሕግጋቶች የሚለያዩን መሆናቸውን እየታወቀ፤ እነዚህ የቁርዓን እምነቶች የመይቀበል የክርስትያን አማኝ፤ እንኚህን ስብከቶች/ሕግጋቶችን ከሚተገብሩ እና ከሚያከብሩ የእስላም ወንድሞቻችን/እህቶቻቸን ጉባኤ ላይ ተገኝቶ የናንተ አላህ የኔ አላህ ነው፤ ማለት ከሕጋችንና ከእምነታችን ውጭ ነው፤ በማለት ቅር የተሰኙ የክረስትና አማኞች አጋጥመውኛል። ጉባውን ላመስተላለፍ የሚችልበት በርካታ ሰብአዊ ነክ ንግግሮች ሳያጣ ለምን ጫፍ እንደረገጠ ግራ የጋባ ሃይማኖትን ተጠቅሞ የፖለቲካ ምዝምዛዊ ምስጢር ከመሆን አልፎ ‘አሻኳሪነት” ነው።

 

ባለፈው ወር ‘ታማኝ በየነ’ እኔ ከምኖርበት ከተማ መጥቶ እንደነበር ሰምቻለሁ። ታዲያ ታማኝን ከሚያደንቁ አድናቂዎቹ ከአንድ ቦታ ላይ ተገናኝተን እንደዋዛ ‘ለምን ታማኝን እንደምቃወመው’ ጠየቀኝ። በትዕግሰት በጎ ጐኑ ጠቅሼ፤ ጥንቃቄ ማድረግ ሲገባው፤ በማን አለኝነት ስሜት የሚዘነቋቁላቸው ፖለቲካዊ ንገግሮቹ ደግሞ ቅር እንዳሰኙኝ እና እኔም የሚዘላብዳቸውን ፖለቲካዊ እና ሃይማኖታዊ ሰበካዎቹ ሕዝቡ የማወቅ መብት ስላለው እኔም ካነጋገሩ የሚሰነዘሩትን መተቸት መብቴ ተጠቅሜ የማስረዳት መብት አንዳለኝ ተጠቅሜ እንደሆነ ለማስረዳት ሞከርኩ። ሰውየው እንደሺዎቹ በተማኝ የጦዘ አምልኮ ስላደረበት መጥፎ ጎኑን ያስረዳሁትን ተቃውሞ በማሰማት “ ስራችሁ መተቸት ብቻ ስለሆነ አንጂ፤ታማኝ አንተ አንደምትለው ንግግር አልወጣውም።” ሲል ተከራከረኝ። በረዢም የፖለቲካ ትግል ዘመኔ የታዘብኩት ዋና ትዝብት ካለ፤ የተሰለቡ ሰዎችን ለማሳመን (በተለይ በኢትዮጵያ ማሕበረሰብ ውስጥ ተያይዞ የመጣ ፤ሰውን የማምለክ ባሕሪ በጣም አስቸጋሪ ያደረግዋልና ሰውየው ዘመና ቀለም የቀመሰ መሆኑንም ስለማውቅ ማዕረጉን አክብሬ ብይዘውም ፤ “አብዛኛዎቹ ባለ ዲግሪዎቹ ምን ያህል ድንቁርና አንደከበባቸው ስለማውቅ፤ በተለይም ከተለያዩ ፖለቲከኞች የሚሰነዘሩ እና የሚጻፉ ፖለቲካዊ  ጽሑፎች ስራየ ብለው ስለማይከታተሏቸው፤ ‘እገሌ አንዲህ አለ’ ሲባሉ “የናንተ ፈጠራ ነው” የሚል ድምዳሜ ይደርሳሉ። ይህ ደግሞ ሥር የሰደደ መጥፎ ባህሪ ነው።  

 

ብዙዎቹ የኢትዮጵያ ምሁራን ከመጣው ነፋስ አብሮ የመንጐድ ባህሪ ይታይባቸዋል። ያዕቆብ ሃይለማርያም ፤መረራ ጉዲና፤…ወዘተ ..ወዘተ ወያኔ ሲገባ እንዲህ የሚል አቋም ነበረው፤ ወያኔን ደግፎ ሲከራከር ነበር…. ተገለባባጭ አንደበት አለው …..ስንላቸው፤ በጣም የሚቆጡ ሰዎች አጋጥመውኛል። ሰዎች በሗላ አቋማቸው ሊለውጡ ይችላሉ፡ መጥፎ ነገር አይደለም፡ ነገር ግን አነኚህ ሰዎች ፖለቲከኞቹን አፍ ስለማይከታተሉ፤ያልተናገሩት እኛ የፈጠርነው ናዳ አድርገው ይመለከቱታል። ገብሩ አስራት “የወልቃይት ሕዝብ/አማራውን) “ባርኖስ” ብለህ አስነዋሪ ስድብ ተሳድበህ ነበር፤ ለዚህ ይቅርታ መጠየቅ አለብህ ብለው ሕዝብ በተሰበሰበበት አዳራሽ  ለጠየቁ ሰዎች ውጭ ከወጡ በሗላ “የአንድነት ጠንቅ፤ትግልን የሚያሰናክሉ” እያሉ የስድብ ናዳ ያወርዱባቸዋል። ፖለቲከኞችን ቀርቶ የመንግሥቱ ሃይለማርያምን የንግግር/የመጻፍ በሰብአዊ መብት አኳያ መከበር አለበት እያለ የሚሟገተው ፕሮፌሰር አለማዮህ ገ/ማርያም እንኳ፤ ስየ አብርሃ ከእስር ቤት ወጥቶ ለመጀመሪያ ጊዜ በስያትልና በዋሽንግተን ከተማ ተገኝቶ ኡደት (ቶር) ሲያደርግ ‘ስየን’ የተቹትን ግለሰቦች፤ ዘ ‘ሲኒክ’ ግሩፕ፤-በ cynicism የተጠመዱ ‘ጫኺዎች’ እያለ ሲያብለጠልጠን እንደነበር የሚታወስ ነው።  በመረጃ የተደገፈ ትችት አትተቹ የሚሉን ሰዎች በስሜት የተጠመዱ “ለመጣው ሁሉ’ አርጋጆች (‘ሳብሚሲቭ’) ናቸውና ተከራካሪዬ ይህንን ጽሑፍ አንደሚያነበው ተስፋ አደርጋለሁ። ለዚህም ነው ሳላስበው ይህንን ትችት አንድጽፍ ድንገት ያዘጋጀሁት።

 

የታማኝ በየነን ሌሎች አነጋጋሪ የሆኑት (ሰንሲቲቭ)በርካታ ነገሮቹን ከማስቀመጥ ተቆጥቤ ለምሳሌ አንዳንድ ነገሮችን ለማስረጃ ልጥቀስ። በአንድ የሕዝባዊ መድረክ ንግግሩ አንዲህ ይላል።

(1)“ኦነግ ኢትዮጵያዊ አልነበረም” ብለው የሚያምኑ አክራሪዎች አሉ።” 

(2)  ኢትዮጵያ የክርስትያኖችን በዓል ስታከብር የእስላሞችን አታከብርላቸውም ነበር።

(3) እኔ አቡበከር ነኝ /ሁላችንም ኡበበከሮች ነን፤

(4) በሌላ በኩል ደግሞ እዚህ አልነበርንም (ኢትዮጵያዊያን አይደለንም የሚሉ ሌሎች አክራሪዎች ድገሞ አሉ)፤

(5) የኢትዮጵያ ሙስሊም ‘አክርሮ’ ጐራዴ ይዞ ቢመጣ ከወያኔ ጥይት

ይልቅ የሙሲሉን ጐራዴ እመርጣለሁ እኔ።” ተክቢር! ተክቢር! ተክቢር! በማለት እስላማዊ መፈክር አስተጋበቷል።ይህ የተናገረው “እስላሞች አትተኙ!” ቢ- ፕሪፔር! (ተዘጋጁ) ጠመንጃሁን በጂሃዳዊ መልክ አንሱት! ተኽቢር! ተክቢር!’ በማለት ውጭ አገር/አሜሪካ ውስጥ የሚኖር ግበብጻዊ ‘ሼኽ’ ለአንዳንድ የኢትዮጵያ እስላም ሕብረተሰብ በአማካሪነት “የሚያምኑት” የትግል ስትራተጂ አማካሪያቸው በተገኘበትና ንግግር ባደረገበት አብሮ ባንድ አዳራሽ ከታማኝ ጋር ተገኝተው ሁለቱ የተናገሩትን ንግግር ለማድመጥ ይህንን ሰነድ ለማስረጃ ያድመጡ ፤Tamagn Beyene and radical Islam   http://youtu.be/nXeE3Wq_fWM 

 

እኚህ እና የመሳሰሉት በጣም አስገራሚና አሻኳሪ ንግግሮች በቸልተኝነት ከመታለፋቸው አልፎ በአድናቂዎቹ ተቀባይነት አላቸው። እነኚህ የፖለቲካ ንግግሮች የተፈተሉት ሆን ተብሎ ነው ወይስ አለማወቅ? የሚለው የያንዳንዱ አንባቢ ወይንም አድማጭ ፍርድ ሊለያይ ይችላል።

 

እኔ እንደ ተቺ ግን የተሰማኝን ላንባቢዎች እገልጻለሁ። መብቴን እንደማትጋፉትም ተስፋ አደርጋለሁ። የግብጻዊው ኢትዮጵያዊያን እስላሞች ‘የሃይል እንቅስቃሴ አንዲያደርጉ ጂሃዳዊ’ ስሜት በኢትዮጵያ

ምድር አንዲነሳሳ የሰበከው ንግግሩን ለመተቸት “ጊዜ’ አልፈጅም። እሱን ትቼ በመጀመሪው በታማኝ የስድብ ንግግር አንጀምር።ከዚያ ‘በሽብርተኝነት’ ወያኔዎች ከስሰውት እስር ቤት ውስጥ የሚገኘው የእስልምና እንቅስቃሴ መብት አስከባሪ መሪ አንዱ ከሆነው ወደ ኡስጣዝ አቡበከር አህመድ ንግግር እገባለሁ።

 

ወደ ሗላ ተመልሼ በታማኝ አንዳንድ ንገግሮቹ ላይ ትችቴን ልጀምር።

(1)(“ኦነግ ኢትዮጵያዊ አልነበረም” ብለው የሚያምኑ አክራሪዎች አሉ።”) የሚለው ስድብ ማንን ነው እየሰደበ ያለው? እኛን አንጂ ኦነግን አይደለም። ይህ ገለባነት/ባዶነት አጉል ማሻኮር ከመሆን አልፎ “ኦነግ” የተባለው በዘር ማጥፋት ወንጀል የሚጠየቅ ጸረ አማራ እና ጸረ ኢትዮጵያ ቡድን፤ የተከተለው የፖለቲካ ንድፍ ትክክለኛ ባህሪውና ምንነት የኦነግን ፖለቲካ ላልተከታተሉ የአዲስ ትውልዶችን የመመራመር ብቃቱ አንዲሸመረር ማደናገር ነው።

 

ኦነግን በሚመለከት የታማኝ በየነ የማሻኮር ፖለቲካ ስራ በእሱ ብቻ አልተጀመረም። ከእርሱ በፊት የዶክተር ማዕረግ ያላቸው ብዙ ሞኞች እና አሳባቂዎች የጀመሩት የፖሊቲካ ሴራ ነው። ለምሳሌ ዶ/ር ዜሮ የሚል የተጸውኦ/የቅጥያ ስም የተሰጣቸው ዶ/ር ጌታቸው በጋሻው አንዲህ ይላሉ።

(1)     “it is almost impossible to find an Oromo who does not support the OLF.”  

(2)    ኦነግ “ኢትዮጵያዊ አይደለሁም” ብሎ አያውቅም

(3)   ኦነግ “የመገንጠል ጥያቄ” አቅርቦ አያውቅም

ሲሉ ባደባባይ ተናግረዋል።በዚህ የውሸት እና የደላላነት ፖለቲካ ንግግራቸው ምክንያት ዶክተር ጌታቸው በጋሻው “ዶ/ር ዜሮ” የሚል መጠሪያ ተሰጥቷቸዋል።ሲያትል ከተማ ባደረጉት ይህ አሳፋሪ የውሸትና የክህደት ንግግራቸውም በስሜት ከከነፈው ከአዳራሹ ሕዝብ “የጋለ ጭብጨባ” ተችሮላቸው ነበር። ከዚህ ግምገማ በመነሳት ማሕበረሰቡ ምን ያህል በስሜት የሚጋልብ ሕሊና እንዳለው ጥልቅ ምርመራ አያስፈልግም።

 

እንግዲህ ይህ የአሳባቂነት ባህሪ የኪነት ባለሞያው ታማኝ በየነንም የለበደ (የጨመረ) ትግሬዎች “ሕማም ተላበድ” (ወረርሺኝ በሽታ) የምንለው የአሻኳሪነት ለበዳ/ ኤፒደሚክ/ወረርሺኝ ሲያጠቃው ታዝበናል።

 

ታማኝ (1)(“ኦነግ ኢትዮጵያዊ አልነበረም” ብለው የሚያምኑ አክራሪዎች

አሉ።”) በማለት እኛ ዜጐች ባልዋልንብት “በአክራሪነት” መክሰስ ለምን አስፈለገው? አንዴትስ  ወደ እንደዚህ ዓይነት ድምዳሜ ሊደርሰ ቻለ? ኦነግ በታሪኩ ከተመሰረተበት አንስቶ የጻፋቸውና በመመሪያው ያሰፈራቸው ጽሑፎቹ እና ዓላማዎቹ የነገርን ነገር፡ ”እኔ ኦሮሞ የተባልኩ ከኦሮሞ ሪፓብሊክ የተፈጠርኩ ዜጋ አንጂ ኢትዮጵያዊ አይደለሁም። ኢትዮጵያ የምትባል የመቶ አመት ታሪክ ያላት ኮሎኒያሊስት አገር ናት። አበሾች ያልሆንን እኛ የኦሮሞ ሕዝቦች አፍሪካዊ “ኩሽ” ነን። አበሾቹ አፍሪካዊ ያልሆኑ ከዓረብ አገር የመጡ “ጠያይሞች” ሴማዊያን ናቸው።  በኢምፔሪያል ነፍጠኛዋ አቢሲኒያ የተያዝን  የኦሮሚያ አገር ዜጋ ሕዝብ ነን” …. ወዘተ… በማለት ለ40 ዓመት ደጋግሞ ነፍጥ ይዞ የታዋጋን “አክራሪውን” ኦነግ ሆኖ እያለ፤ ኦነግን ነፃ ለማድረግ አብሮአቸው አዳራሽ ውስጥ ተቀምጦ እያለ እኛንን “ኦነግ ኢትዮጵያዊ አይደለም የሚሉት ናቸው አክራሪዎች እንጂ ኦነግ አክራሪ አይደለም ” በማለት የተገላቢጦሽ ሲሰድበንና አሸባሪዎች/አክራሪዎች የሚል ቅጥአ ስም ሰጥቶናል። ለምን? ይባስ ደግሞ፤ ከተቻችሁ አንድነታችን ይላላልና ከመተቸት አፋችሁን ክደኑ ለምን እንባላለን?  መቸም ኦነግ ኢትዮጵያዊ አይደለሁም ያለበትን መረጃ የላችሁም ብሎ ታማኝ በየነ አንደማይከራከረን አምናለሁ። እሱን ትተን በተራ ቁጥር 2፣ 3፣ 4 እና 5 የተመለከቱትን አንመልከት።

 

(2) ኢትዮጵያ የክርስትያኖችን በዓል ስታከብር የእስላሞችን አታከብርም ነበር። የሚለው ንገግሩን ደግሞ እንመልከት።

አንዲህ ይላል።  “እኔም በግሌ እንዳጠናሁት፤ኢትዮጵያ ለሙሰሊሙ ምን አገር አንደሆነች፤በሙሰሊሙ ልቦና ውስጥ ምን አይነት ቦታ አንዳላት ሳውቅ የሚሰማኝን ስሜት መግለጽ ያቅተኛል።አውነቴን ነው የምላችሁ! ደጋግሜ አንደገለጽኩት ሁላችንም ተበድለናል።እኔ ነብስ አውቄ ወደ ሗላ ታሪክ ስመረምረው፤ትምህርት ቤት ልጅ ሆኜ፤ የኛ በዓል ሲከበር የናንተ አይከበርም ነበር።ይህን ዓይነት በደል ነበር።ሙሰሊሙ ይህንን በደል ዓይቶ ኢትዮጵያን እናጥፋ አላላም።” ታማኝ በየነ በእስላሞቹ ስብሰባ ዋሺንገተን ዲሲ(?)”

 

ታማኝ በየነ ፤ኢትዮጵያ ለናንተ ለሙሰሊሙ ምን አገር አንደሆነች፤ሳውቅ የሚሰማኝን ስሜት መግለጽ ያቅተኛል። ሲላቸው ፊት ለፊት አዳራሹ ውስጥ ተቀምጠው  የሚያንጨበጭቡለት ቀና ልቦና ያላቸው እስላሞች እንኳ ቢኖሩም ከታች የሚደመጠው/ ዩቱብ ላይ የተለጠፈው የዚህች ሴትዮ ጂሃዳዊ ንገግር ነው ተብሎ የተለጠፈው ድምፅ የሷ ከሆነ፤  አብረው ከድምጻችን ይሰማ ቡድን ጋር ሲደበላለቁ ያሳስበናል። እውነት ከዚህ በታች ያለው ምንጭ ይህች ሴትዮ የተናገረቺው “ከሆነ” እስላሞቹ ለምን አብረዋት እንደሚቀመጡ ለኔ ግራ የገባኝ ነው።እኔ አይደለሁም የምትል ከሆነ፤ ሴትዮዋ በሚዲያ ማስተባበያ ማቅርብ አለባት። ካልሆነ የተናገረቺው ንግግር በጣም አስፈሪ ከመሆኑ አልፎ፤የድምጻችን ይሰማ ቡድንም ሆነ ጉባኤ አስተናጋጆች ለምን እንደዚህ አይነት ሰዎች አንደሚያስተናግዱ ግራ የሚያጋባ ነው።እውነት ይህች ሴትዮ የተናገረቺው ድምጽ የሷ ነው?

Ethiopian Woman Jihadist In washington DC Preaching about Islamic State http://youtu.be/lemvyk5KCp8

 

በነገራችን ላይ የህች ሴትዮ ጃዋር መሐመድ በተገኘበት ስብሰባ ለይ “አማርኛ” በእንግሊዝኛ እና በዓረብኛ አንዲተካ ስትማጸን ነው የሚያሳየው ፎቶግራፍ። ዩቱብ ላይ ግን ጂሃዲሰቱ ‘ከቢን ላዲን’ ምስል ጋር ለጥፈዋት “ስለ ጂሀድ እና ዓለም በሙሉ በሸሪዓ እስላማዊ ህግ መገዛት አንዳለበት ስትሰብክ ነው የሚደመጠው። እውነት እሷ ነች?

 

የኛው ታማኝ በየነ ደግሞ ኢትዮጵያ የክርስትያኖችን በዓል ስታከብር የእስላሞችን አታከብርም ነበር። የሚለው የታመኝ ንገግሩን ደግሞ እንመልከት።

ልክ ነው። ቢሆንም፤ ክርስትያኖች ኢትዮጵያን ሲያስተዳድሩ ብቻ ሳይሆን አድልዎ የተደረገው፡ ኢትዮጵያ በእስላሞች ለብዙ ዓመት በ21 ዓመቱ ወጣት በግራኝ አህመድ ስትተዳደር እንኳን የክርስትያን በዓል ሊከበር ይቅር እና ክርሰቲያን ማሕበረሰቡ እና ቤተጸሎታቸው እንዲሁም ቅርሶች እና የታሪክ ቦታዎች “እንዲወድሙ፤ እንዲቃጠሉ፤ እንዲደፈርሱ እና አማኞችም እየታደኑ አንዲገደሉ የተቀሩ ካሉም እንዲሰልሙ ተደርጎ አንደነበርስ ታሪክ ተንታኙ እና የሰው ልጆች መብት ጠበቃው ታማኝ በየነ ይህ የኢትዮጵያ ክርስትያኖችን አሰቃቂ ግፍ የደረሰው አሁን ባለችበት (ኤርትራን ጭምር ) መለክአ ምድር ያካተተ መላዋ ኢትዮጵያን ከጫፍ እስከ ጫፍ የእስላም መንግስት ባስተዳዳረበት ወቅት የደረሰው አሰቃቂ በደል ለም ሊጠቅሰው አልፈለገም? አሳባቂነት ወይስ አለማወቅ?

 

የታማኝ በዓል አልተከበረላችሁም ተብሎ የሚሰበከው ይቅርታ ‘ወያነ ትግራይ ሥልጣን አንደተቆጣጠረ  ሳይውል ሳያድር ፓርላማው ውስጥ ለእስላሞቹ የሰበከው ሰበካ እና አስመራ ድረስ ተጉዞ ሄዶ አንድ አማራ የወያኔ ጀሌ ተልኮ “እኛ አማራዎች ጨፍጭፈናችሗልና ለኤርትራ ሕዝብ ይቅርታ አንጠይቃለን” ብሎ አንዳለው አሰባቂነት ፖለቲካ  የሚያስታውሰን የየቅርታ አሳባቂ ንግግር ይመስላል።  እስላሞች ኢትዮጵያን ሲያስተዳድሩ የደረሰው በደል ይበልጣል ወይስ ክርስትያኖች ሲያስተዳድሩ በነበረበት የደረሰ የሃይሞንት ግፍ ያመዝናል? ማን ማንን ነው የሚያመኘው? ሁላችንም የዛች አገር ዜጎች እኮ ነን።ምን እንደተፈጸመ እናወቃለን እኰ። ታሪክ ለሁላችንም እኩል እንድንመለከተው ፈቅዶልናል።  ማስረጃዎቹን ለማመዛዘን የፈለገ አንባቢ እጅግ ሩቅ ዘመን፤ በዛው ወቅት የነበሩ ጸሐፍት የተውት ዘገባ ፤ በግዕዝ ቋንቋችን የተጻፈው በየገዳማቱ ከተለቀሙ ተጽፈው የተገኙ የታሪክ መረጃዎች/ዘገባዎች “ ጥንታዊ የኢትዮጵያ የሰላም ጥበቃ ታሪክ (ከቅራት -ዘመናዊ ፖሊስ) ከታወቁት ሊቅ ጸሐፊ ‘አእምሮ ንጉሴ’ በየገዳማቱ ሄደው በመሰብሰብ ያገኗቸው ከግዕዝ ወደ አማርኛ የመስዋቸው እስላማዊ መንግስት ኢትዮጵያን ሲያስተዳድር በክርስትያኑ ሕይወት ላይ የደረሰው አሰቃቂ ግፍ ማንበብ አለባችሁ።

 

እስላም ወንድሞቻችን የግዕዙን መረጃ ሰነድ ከጠሉት ደግሞ፦ እስላሞች በክረስትያኖች ያደረሱት አሰቃቂ ሽብር በክርስተያን ጸሃፊዎች ሳይሆን ከግራኝ ጋር አብሮ በጦርነቱ የዘመተውና ከግራኝ አህመድ ጋር ያልተለየው Sihab ad Din Ahmadin Abd al-Qader bin Salem bin Utman ወይንም በሌላ የተጸውኦ ስሙ “ዓረብ ፋቒሕ” ( Arab Faqih) የተባለው የመናዊው ዓረብ ጋዜጠኛ  “ፉቱሕ አል ሐበሻ” ( Futuh Al- Habasa – the  Conquest of Abyssinia {16th Century} በተባለው በዓረብኛ ቋንቋ በጻፈው መጽሐፉ ላይ እስላመዊው መንግሥት በኢትዮጵያ ክርስትያናዊ ሕብረተሰብ የተደረጉት ጸረ ክርስትያን ግፎች በ1535 ዓ.ም ገደማ (በፈረንጆች አቆጣጠር)  ከጫፍ እስከ ጫፍ ከሐረር ጀምሮ እስከ ሰራዬ (ኤርትራ-) ጐጃምና ጎንደር ድረስ የዘለቀ በክርስትያኑ ሕብረተሰብ ላይ የደረሰው ግፍ በግልጽ ለታሪክ አስፍሮ ትቶልናል።ለምንድነው ክረስትያኑ መንግሥት ብቻ ግፈኛ፤ጨቋኝ፤ገዳይ እና አድላዊ እየተደረገ የሚዘመትበት? ይህ በክርስትያን መንግሥት እና በክርስትያኑ ሕብረተሰብ ላይ ሚዛኑን ያልጠበቀ የተቀነባበረ የክስ ዘመቻ ስንት ጊዜ በቸልተኝነት ልናልፈው ትፈልጉናላችሁ? አንዲህ ያለ ክስ አላስፈላጊ ክርክር ውስጥ የሚያስገባ ብቻ ሳይሆን በክረስትያኑ ብቻ ያነጠጣረ ክስ በመሆኑ፤ ጊዚያዊ ፖለቲካን ለመጠቀሚያ እንዲያመች የሚደረግ ምዝመዛ አደገኛ ነው፤ አንቃወመዋለን። በክርስትያኑ መንግስት ላይ ወቀሳ እና ተጠያቂነትን መደርደርና የመረባረቡ ፖቲካ ልጓም ይበጀለት! ለዚህ ለዚህ ወያኔ ይበቃናል፤  ወያኔ ያለ ምንም ደገብ ያርከፈከፈብን አሳባቂ ነዳጅ አንዳይበቃ ሌላ ተጨማሪ አሳባቂ ነዳጅ ከመረብረብ የተቃዋሚ መሪዎችና የሰብአዊ መብት ጠበቃዎች መቆጠብ ይኖርባቸዋል።

 

የታማኝ በየነ “ሁላችንም አቡበከሮች ነን” መፈክር እና አሁን በፋሺስቱ ወያኔ እሰር ቤት ውስጥ ታስረው ከሚገኙት የእስላሞች አንቅስቃሴ መሪው ወጣት ‘አቡበከር” የተባለው ግራኝ አህመድን እያሞካሸ፤ ኦሪት ዘፍጥረት መጽሐፍት የተጻፉ የክርስትያን አምላክ ሰው ገዳይነትና ጨፍጫፊነት ፤ደም አፍሳሽ መሆኑን ሲሰብክ፤ አፄ ዮሐንስንና አፄ ምኒሊክን በጨካኝነት እና በቆራጭ  ገዳይነት እየከሰሰ “ምንም ታሪክ ያላነበበ የዋህ አዲስ የእሳልም ተከታይ ወጣት ትውልድ” እየዋሸ ሲሰብክ የነበረውን የተምታታ አድላዊ እና የተቀነባበረ የውሸት የተሪክ ትምህርትም ሆነ እስላሙ ሥልጣን አልነበረውም፤ ወይንም እስላሙ ሥልጣን ሲይዝ የክርስትያን ወዳጅ እና ፍትህ አስፋኝ ነበር የሚለው የአቡበከርም ሆነ የተከታዮቹ ውሸት እውነቱን አንድትመለከቱት በተጠቀሰው መጽሐፍ ለማስረጃ አንዳንዱን አቀርብላችሁአለሁ።

 

ይህ መጽሐፍ ክርስትያኖች አልጻፉትም፤ እስላሞች/ዐረቦች ፤በቦታው የነበሩ የጻፉት ነው። አንዳንድ እስላም ወንድሞቻችን “ክርስትያን ነገሥታት” ሲያስተዳድሩን የእስላሞችን ታሪክ እንዳይጻፍ አድርገዋል ይላሉ። ይኸው እኮ በቦታው የነበሩ ጋዜጠኞች ጽፈውታል። ይህ የተተወልን ታሪክ መረጃ ስናቀርብ የሚገርመው ነገር፤  ይመለከተናል የሚሉት የሃይማኖቱ ባለቤቶቹን ሳይሆን “አሻኳሪዎቹ/አሳባቂዎቹን” ነው ይበልጥኑ እያሳከካቸው ያለው። ስለሆነም ነው “እስላሞች በክርስትያን አስተዳደር ተበድለው ነበር” እያሉ ሚዛኑን ያልጠበቀ  ትችና ይቅርታ ለመጠየቅ ሲወሻክቱና ሲዳዳቸው ዝም በሉ አትበሉን ብየ የምከራከረው።

 

ይህ መረን የለቀቀ ተደጋጋሚ ክስ አልበዘም ወይ? ለመሆኑ እስላሞቹ እንደሚከሱት በሁለተኛ ዜጋ ታይተው ያውቃሉ? አስሬ ሳያፍሩ የሚከስሱት ክስ ይኼው ነው “ሁተኛ ዜጋ ነበርን ነው”። ለዚህ የልብ ልብ የሰጣቸው ደግሞ ምክንያት አለው። ምክንያቱም ጋዜጠኞች እና አሳባቂዎች የሚዋሽላቸው ውሸት እያደመቁ ሲያስተጋቡላቸው እነሱ ምን ያድርጉ? (የአገራችን ሚዲያዎችም ነገሩ በውል ሳያጤኑና በበቂ ሳይረዱ በአክራሪ እስልምናው ወጥመድ ውስጥ ተዘፈቁ።በዚህም ለእነርሱ መብት የሚታገሉ ወይም ክብር የሚሰጡ መሆናቸውን ለመግለጽ ሲጣደፉበሌሎቹ ፕሮፓጋንዳ’ ውስጥ ወድቀው የግፍ ተባባሪዎች ሆኑ።አክራሪ እስልምና እና የሚዲያዎች ባሕሪ አዘጋገብ በኢትዮጵያ፡ በሚል  ካንድ ዓመት በፊት የተጻፈውን ኢትዮጵያን ሰማይ ድረገጽ ይመልከቱ)

 

እስለሞች በሁለተኛ ዜጋ ታዩ ሲባል ‘እስላም ስለሆንሽ በሆስፒታል ወሊድ ማካሄድ ላንቺ አይፈቀድም፤ አንቺም ልጅሺም ክትባት አትሰጡም፤ ትምህርት ቤት/በየደረጃው እስከ ዩኒቨርሲቲ ድረስ ልጅሺን አስመዝግበሽ ማስተማር አትችይም/አትችልም….እስላም ስለሆንከ/ሽ ንግድ መነገድ አትችልም/ይም ፤በት መስራት አትችልም፤ማከራየት አትችልም፤ ሳውዲ ሜካ ድረስ ሄደህ ጸሎት ለማድረስ ወይንም ‘ሃጅ’ ለማካሄድ አይፈቀድልህም…” የተባለበት ጊዜ አለ? ተብሎ ከሆነስ እስላሞች ሲያስተዳድሩ የደረሰው በደል ጋር ለምንድ ነው አነጻጽረው አቻችለው ታሪኩን የማይዘግቡትና የማይሰብኩት? (ከ15 ዓመት በፊት በጋዜጣ ላይ የእስለሞችን መብት መከበር አለባቸው በሚባሉባቸው ሁኔታዎች በመደገፍ በጋዜጣ ላይ ሰፊ ትንተና እና ክርክር አድርጌአለሁ)። ወንድሞቻችን ግን ተገቢ መብቶችን ከመጠየቅ ይልቅ ጭራሽኑ “ክርስትያን ኢትዮጵያ ሲያስተዳድሩ እኛን በሁለተኛ ዜጋ አይተውናል” “የአፄ ዮሐንስ ሀውልት ይፍረስ” እያሉ መፈክር ያስተጋባሉ/ይከሳሉ። ይህ ምን ማለት ነው? ምንጩ ማን ነው? አሳባቂዎቻችውም ይህንኑ ያስተጋቡላቸዋል። ለምን?

 

በነገራችን ላይ  ንጉሥ ዮሐንስ እስላሙን ብቻ አይደለም መብት የተጋፉት ፤የክርስትያኑም ጭምር ነው። ተኽለ አልፋ የተባሉ ‘ደብረ በርበሬ’ ተብሎ በወቅቱ ሲጠራ የነበረ አካባቢ የሚኖሩ የታወቁ የቅባት እምነት ተከታይ የነበሩት አባ ተኽለ አልፋን አጼ ዮሐንስ (በወቅቱ ደጃዝማች ካሳ አባ በዝብዝ) በአባት ነብሳቸው በኩል አስጠርተው ወደ ተዋህዶ ሃይማኖት እንዲገቡ ካስጠሯቸው በሗላ፤ አባ ተኽለ አልፋ የደጀዝማች በዝብዝ አባነበስ “በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱሰ’ ትርጓሜው ምንድ ነው? ብለው ቢጠይቋቸው “የደጀዛምች በዝብዝ አበነብስ “አላውቅም” ስላልዋቸው፤ ደጃዝማች ካሳም “ደንቆሮ ነህ?” ብለው አበነብሳቸውን ገረፉት’ “ትግራይ ውስጥ ያለ ቅባት ሁሉ ወደ ሃይማኖቴ ይግባ፤ እምቢ የሚል ሁሉ በምገዛው አገር አይኑር አሉ፡ በትግሬ ያሉ ቅባቶች ሁሉ ወደ አባ በዝብዝ ሃይማኖት ገቡ። አባ ተኽለ አልፋ ግን አምቢ ስላሉ ከትውልድ ቦታቸው ከትግራይ ለቅቀው አንዲሰደዱ ሆነ።” በማለት  ደብተራ አሰጋኸኝ የተባሉ ለአንቶኒ ዲ አባዲ (Antonie d’ Abadie) በየካቲት 6/ 1861 ዓ.ም (1869 በፈረንጆች ዘመን አቆጣጠር) ከትግራይ በጻፉለት የግል ደብዳቤ ይገልጻል። ለዝርዝር መረጃ  Internal Rivalries and foreign threats 1869-1879 Edited by Sven Rubesnson (Document 4 p/6 Assegeheng to Antonie d’ Abadie, 12 Feb, 1869 ዋና የግዕዙና የአማርኛ ደብዳቤ ጽሑፍ እና የእንግሊዚኛውን ትርጉም አብሮ ተያይዞ ስላለ ያንን ይመልከቱ።

 

 የህ ብቻ ሳይሆን ንጉሠ ነገሥት ከተባሉ በሗላም ክርስትያን ቀሳውስትም በሃይማኖት ክርክር “ቦሩ ሜዳ” ላይ እጃቸው አንዲቆረጡ አድርገዋል። እነኚህ ሁሉ በክርሰትያኑ ላይ የደረሰ ግፍ ነው። ታዲያ ለምንድነው እስላሞቹ ወንድሞቻችን እና አሳባቂዎቻቸው “ግፉ የተፈጸመው በእስላሞቹ ላይ “ብቻ ነበር” እያሉ ክርስትያኑ የሃይማኖት ነፃነት አንደነበረው አስመስለው በክርስትያን ነገሥታት እና በእናት ኢትዮጵያ ላይ ሚዛኑን ያልጠበቀ የክስ ዘመቻ የሚያስተጋቡት?

 

ለምሳሌ እስላሞቹ አክሱም ውስጥ እንደ የጭቆና ማስረጃ አድርገው የሚከራከሩበት (እኔም  ደግፌው የነበረው የእስላሞች መስጊድ አክሱም ውስጥ የመስራት መብት) የመስጊድ መስራት ጉዳይ ነው። ይህ ደግሞ ሕዝቡ አንጂ መንግሥት ውሳኔ ማሳለፍ መብት የለውም (ይህንን ሳናውቀው ስንከራከር ነበር)። ይህ ከሆነ መንግሥት በሃይማኖት ጣልቃ መግባት ይሆናል። ስለዚህም ነው በዛሬው ዘመን እስላሞቹ በሃይመኖታችን ጣልቃ አትግቡ እያሉ ወያኔዎችን የሚቃወሙት። ስለዚህ አክሱም ውስጥ በባህል የቆየ አንጂ በመንግሥት ወይንም በመጽሐፍ ቅዱስ በሕግ ተበይኖ የተደነገገ ሕግ የለም።  ለእውነት አንነጋገር ከተባለ አክሱም ውስጥ እስላሙ ሕብረተሰብ ብቻ አይደለም የሚጸልይበት ህንጻ ሰርቶ መጸለይ መብት የተነፈገው። የአክሱም ክርስትያን እናቶቻችንም እኩል እንደ እስላሞቹ መብታቸው ተነፍጓል። እኔ ከእናቴ ጋር ጥዋት ወደ እንዳ ጽላት /ቤተክርስትያን ስሄድ ‘እሷ’ በተንጣለለው ግቢ ውስጥ ከደጅ እካቡ ላይ ባለው ሜዳ በበቀሉት ዛፎችና ከመቃብር ድንጋዮቹ መካከል ጥላ ስር ሆና ለመጸለይ ወደ ላ ስትቀር ከማህጸንዋ የተገኘሁ እኔ ‘ወንድ’ ነኝ እና ወደ ቤተመቅደሱ ውስጥ ገብቼ የቅዳሴው ስርዓት ተከታትየ፤አስቀድሼ፤ ቅብአ ሜሮኑን ተቀብቼ ስርዓቱ ተከናውኖ ሲያበቃ ወደ ደጅ ወጥቼ ፤ በግማበሬ የተቀባውን ቅብ ሜሮንኑን በእጄ ወደ ግምባሯ ቀብቼ ፤እሷን አጅቤ ወደ ቤታችን አንሄዳለን። አንግዲህ የወለደቺኝ እናቴ “የቤተከርስትያኑን ውስጣዊ ሰርዓት” ለማየት መብት ሳይኖራት እኔ በወንድነቴ ከማህጸኗ የወጣሁ ጮርቃ ህጻን ልጇ ግን ገብቼ ለማየት እና ለማስቀደስ መብት አለኝ። ይህ የቆየ ‘ሰንሲቲቭ’/ወጣሪ ባህላዊ የመብት ሁኔታ ወንድሞቻችን እሳለሞች እና አሳባቂዎቻቸው ይህንን እያወቁ “በእስላሙ” ብቻ የተደረገው የመብት ጥሰት እየመዘዙ ክርስትያኑ እና ስርዓቱ የእስላሙ መብት ተጋፊ እያደረጉ ዘመቻ ማካሄድ በሰማይም በምደርም ቅንንት የተከተለ ክስ አይደለም። ነገሮችን ፤ታሪኮችና የቆዩ ባህሎች “በእርጋታና በጥንቃቄ”  መመርመር ለአብሮነት አስፈላጊ ነው። እውነቱን እና ውሸቱን በመረጃ መደገፍ አለብን።

 

እስላሙ መሬት አልነበረውም፤ መብቱ ተገፏል እያልን ተከራክረናል። ነገር ግን በእስላሞቹ መንደርም ክርስትያኑ መሬት አንዲይዝ ቤተክርስትያን አንዲገነባ የማይፈቀድባቸው ቦታዎች አሉ። እኔ የነበርኩባቸው እሳላመዊ መንደሮች ይኼንን ነው የሚያስረዱ። አክሱም ውስጥ ዘመናዊ ቤተክርስትያን ሲታነጽ ንጉሱ ዋናው ከተማዋ አዲስ አበባ ውስጥ አንዋር መስጊድ አንዳሰሩት ይነገርላቸዋል (ሌላም ሌላም በጐ ነገር አድርገዋል።የሶማሌ እስላሞች በወያኔ ፓርላማ ያሰሙት የትምህርት ዕድል ክስ “ አርበኛው ሟቹ ሻለቃ አድማሴ ያደረጉት በመረጃ የደገፉት በወያኔ ፓርላማ ክርክር ታስታውሳለችሁ)። ይህ ሁሉ ሆኖም፤ አሳባቂው ስለበዛ፤ ታሪክ ለመገለበጥ ብዙ ምቹ ጊዜ ተፈጥሯል። ክርስትያን ሃይሞአነት ጨቋኝ ነው፤ የአማራ ስም ያላቸው ዜጎች እስላሙን ስለተጋፉ ወይንም ኦሮሞውን እና ሌላውን ስለተጋፉ ወደ ስልጣን እንዳይመጡ ፤ በምትካቸው መረራ፤ሐጎስ፤ ፈሪሳ፤ አህመድ….የሚሉ ስሞች ያላቸው ወደ ስልጣን ይምጡ እያሉ የሚያሳብቁ ክፉ ዘረኞች አሁንም በተቃዋሚው ውስጥ አሉ። (ይህ የሚደመጠው ከወያኔው ብቻ ሳይሆን ከተቃዋሚው ቡድንም ጭምር ነው።) ዮሐንስ አንጂ ምኒሊክም ሆኑ ሃይለስላሴም አማራዎች አንጂ አክሱማዊነት/ትግሬነት ወይንም የሳባ/የነገሥታት ዘር የላቸውም የሚሉ አሳባቂዎችም ብቅ ብለዋል። ንጉሡ (ሃይለስላሴ) የነበረው ስርወ መንግሥት ዘር ነበሩ። (በአፄ ልብነድንግል 11ኛ ለንጉሡ ሳሕለ ስላሴ 3ኛ ናቸው የሚሉ የታሪክ ዘጋቢዎች አሉ)።ሌላ ቀርቶ አጼ ሃይለስላሴ ትግራይ ውስጥ የተምቤን ተወላጅ መሆናቸው በመጽሐፈት ከነትውልድ ሐረጋቸው እና እራሳቸው የተናገሩት ርስት ጉልት ቦታ አንዳለ የተጻፈ መረጃ በእጄ አለኝ።ነገሥታቶቹ የዘር ቆጣራ ይግቡ አይግቡ አበሻነታቸውና ኢትዮጵያዊ ዜግነታቸው ወሳኙ ምዐራፍ መሆኑ ተዘነግቶ፤ንጉሾቹ በፈጠሩት  በነበረ አፈታሪክ የሚጐትቱን ግብዞች በወያኔ ዘመን መበራከታቸው ሕሊናችን ወደፊት አንዳይራመድ በመንገዳችን ላይ በረካታ ደናቁርት ክምሮች ክምችት ተቆልሎ መግፋት አቅቶናል።

 

ትግራይ ሃበታም ነበረች፤ ረሃብ የተከሰተው ለመጀመሪያ ጊዜ ምኒሊክ እና ሃይለስላሴ ከገዙን በሗላ ነው የሚሉ የወያኔ  ዋሾችም አሉ። ትግራይ በግራኝ ዘመን በ15ኛው ክኢፈለ ዘመን አንኳ የሚላስ የሚቀመስ እንዳልነበረ በረሃብ ምክንያት ግራኝ አካባቢው ተሎ አንደለቀቀ ጽፎታል። በአጼ ዮሐንስ ዘመንም ትግራይ ውስጥ  ረሃብ ስለገባ ፤ አንድ ሰው ዓድዋ ውስጥ የሰው ሥጋ ስለበላ፤ አጼ ዮሐንስ ሰውየውን ይዘው ረሽነውታል።Internal Rivalries Foreign threats 1869-1879) የሚለው በግዕዝና አማርኛ የተጻፈ ሰነድ ይመልከቱ። ወያኔዎችም ሆኑ በተቃዋሚው በኩል ይህ ሁሉ የተለያየ ውሸት እየተበራከተበት የመጣው ምክንያት ውሸት እየተደጋገመ ሲሰራጭ “ተው” የሚል ጸሐፊ እና ተከራካሪ በጣም ውስን እየሆነ በመምጣቱ እየተጋገረ ተራራ ያህል የፖለቲካ ወዥምብር ተቆልሎ ከፊታችን ቆሞ ይታያል።

 

ለሃያ አንድ ዓመት ሲነዛ የነበረ ውሸት አቁሙ የሚል ሰው በብዛት ስላልተገኘ ውሸት እውነት ሆኗል፤፡ በእየ አዳራሹ እነ ታማኝ በየነ “ምኒሊክ ግፍ እየፈጸሙ ” ወደ ደቡብ ሲስፋፉ” ከዛ በፊት የኢትዮጵያ ነገሥታት ዛሬ ኦሮሞዎች እየኖሩበት ያሉ  ቦታዎች አላስተዳደሩትም፤ የሚለንን  ውሸት ሲደመጥ ተጨብጭቦለታል። ታማኝ የጠቀሳቸው ቦታዎች የኦነጉ የታሪክ ምሁር ወጣቱ ‘መሀመድ ሐሰን’ በመጽሐፉ ተመርኩዘው የወሻከተው ውሸት የሚነዙ በርካታ ናቸው። ታማኝ በየነ ‘መረራ ጉዲና” በጦቢያ መጽሄት  አሁን ያለው መንግሥታዊ ግዛት ሆኖ የወጣው ሰፊ ግዛት አብዛኛው የኦሮሞ ሕዝብ የተጠቃለለው በምኒሊክ ዘመን ሲሆን ግፍ ተፈጽሟል፤ መካድ የለብንም” በማለት አንደ መረጃ መረራ ጉዲናናን ስለ ድምበራችን ስፋትነት እና አዲስነት ሲጠቅስ አስገራሚ ነው። ከንጉሥ ወናግ ሰገድ ጋር የጀመረው የግራኝ አህመድ ሃይማኖታዊ ጦርነት ሌላ ቀርቶ አህመድ “ግራኝ አንኳ” ከዓረብ አገር የመጡ “አሳሪስ” የሚባሉ በደዊን ዓረቦች እና ከመግረብ (ሞሮኮ?ሳሐራ) እና ማሕራ የተባሉ ዓረቦች አንዲሁም ከሱዳን “ኑባ” የተባሉ 15,000 ሱዳናዊያን ተዋጊ እግረኛ ወታደሮችን ይዞ በ15ኛው ክፍለ ዘመን እስልምናን በኢትዮጵያ ሲያስፋፋ አንደ ንጉሥ ሆኖ የገዛው ንጉሥ ምኒሊክ ያስፋፉት  ሳይሆን አሁን ያለው ካርታ አህመድ ግራኝም ያስተዳድረው የነበረም ነው። (ኤርትራን ጨምሮ እስከ ምፅዋ ድረስ።) ለምሳሌ የሰራየ አውራጃ አስተዳዳሪ ተስፋዊ የተባለው ለግራኝ አህመድ ያደረ ሲሾመው ፤ አፍራ የተባለ ሰው ደግሞ የባህር ነጋሽ (ምጽዋዕ/ምፅዋ:: ሁለቱ ስሞች የተለያዩ ትርጓሚዎች ያዘሉ ይሁኑ አንጂ ቃላቶቹ ትግርኛ  ናቸው።) ሲሾመው፤ ዘርአ ሰናይ ደግሞ የሃማሴን ገዢ  አድርጐት ትግራይን ለቅቆ ወደ ወልቃይት እና ጐንደር አቀና። ትግራይ ክ/ሀገር ሲለቅ ሕዝቡ በረሃብ/ድርቅ ተምትቶ ስለነበር የግራኝ ተዋጊ ሃይል ፈረሶች እና በቅሎዎች  የሚበሉት ሳር አጥተው  በመሞታቸው፤ ግራኝ እና ወታደሮቹ ትግራይ ውስጥ 1 ዓመት (አንዳንዱ 6 ዐመት ነበር የኖረው ይላሉ) ሲኖሩ ትግራይን ለቀው ወደ ጐንደር ሲሄዱ ለመጓጓዣ ሲጠቀምባቸው የነበሩት የሰራዊቶቹ አጋስሶች በሙሉ ስላለቁ  ‘እቃቸው/ጛዛቸው” “በጭንቅላታቸው ተሸክመው” ነበር ትግራይን ባስቸኳ ለቀው ወደ ጐንደር እንዲለቁ የተገደዱት)። Ahmad elects to leave Tegre for Bagemder በሚለው ንኡስ ርዕስ በገጽ 374  “ዓረብ ፋቒሕ” ( Arab Faqih) መጽሐፍ ይመልከቱ።

 

እነ ታማኝ ግን ምኒሊክ ነው በኦሮሞው ላይ “ግፍ’ እየፈጸመ አሁን ያለው ግዛት ያስፈፋውና የገዛው እያሉ ሕዝብን ይሰብካሉ። የኢትዮጵያ ግዛት ደቡብም ቢሆን ምኒሊክ የተጀመረ ሳይሆን በነ አብርሃ አጽብሃ ዘመን/አክሱም ዘመን የተተታደረውን ትተን በይኩኖ አምላክ 12ኛው ክፍለ ዘመን እና በዛጉዌ  ንጉሥ (ጋምቤላዎቹ/ከፋዎቹ/አናሪያዎቹ “ሓሳሴ ፍትሕ”/የፍትሕ ሚኒስቴር አድርጎ ሲሾም የነበረውን)  ወደ 8 ያክል ነገሥታት ደቡብን ክፍል አስተዳድረውታል። በዓይናቸው ያዩ  ሊቃውንት የሚነግሩን፤ ነቀምት ከተማ የምትገኘው የመቤታችን ቤተ ከርስትያን፤ጅማ ከተማ የሚገኘውን ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስትያን አፄ ሰርፀ ድንግል እንዳሰሩት በጥንታዊ ሰነዶች ተጽፎ ይገኛል። ስለዚህ እነ ታማኝ “የሚኒሊክ ወረራ/መስፈፋት” እያሉ የሚጠቀሙባቸው ቃላቶች ከታሪክ ጋር የሚጋጩ ናቸው። ንጉሱ የሚሉት ግን “ከጥንት ሲወርድ ሲዋረድ የነበረ የወላጆቼ ቦታ ለማቅናት ነው” ነው የሚሉት። ማቅናት ማለት ‘ወድሞ ጠምሞ አጐንብሶ፤ጠውለጐ የነበረን ነገር ህይት መዝራት፤እንደ ገና ማስተካካል ማለት ነው። ማስፈፋት እንሱ (ነገሥታቱ) ቢጠቀሙበትም አሁን ካሉት የቃላቱ ተጠቃሚዎች ትርጉማቸው የተለየ ነው።    

 

ሶማሌዎች ከግራኝ ጋር ሆነው የግራኝን የሽብር ባንዴራ እያውለበለቡ ከጫፍ ጫፍ ሕዝበ ክርስትያኑን ሲፈጁት የነበረውን ረስተው፤ ወያኔዎች በ1991 ዓ.ም ከትግራይ ጫካ ገስግሰው ኢትዮጵያን ሲቆጣጠሩ የሶማሌ ተወካዮችና (ኦሮሞዎች እና ሶማሌዎች ተናጋሪዎቹ በሙሉ እስላሞች ናቸው) በወያኔ ፓርላማ ተገኝተው “ይህች ሰንደቃላማ የአባቴ እና የእናቴ ገዳይ ናት” ቀለሟ በጥቁር ቀለም መሰረዝ አለበት፤ እያሉ ባልተገረዘ ምላሳቸው በመላ በኢትዮጵያ ሕዝብ ፊት ሲከስሱና ሲዘልፏት፤ “አዎ አውነታቸውን ነው” “እስላሞች፤ኦሮሞዎች፤ሶማሌዎች…” በአማራው፤በነፍጠኛው፤በክረስትያኑ ተጨቁነው ነበር፤ ኢትዮጵያ የነሱ አገር አልነበረቺም፤ ያለፉት ኑሮ “መቻል አንጂ መቻቻል አልነበረም”፤ እያሉ ስድቦቻቸውና ዘለፋዎቻቸው ሚዛን ባልጠበቀ ክስ ያስተጋቡላቸው በርካታ “ማሞ ቂሎቻቸውን” አድምጠናል፤ ተከራክረናል።  

 

ይህ ሁሉ ውሸት ለምን በብዛት ተሰራጨ? ምክንያቱም የፖለቲካ እና የግል ዝና እና ጥቅም ለማስከበር በአድርባይነት በተሳለ ምላሳቸው የሚሯሯጡ የልተጣሩ “ድፍድፎች” ስለተበረካቱ ውሸቱን ለማቆም ብዙ ደፋሮች በመታጣቸው ነው። ለዚህም ነው እኔ በድፍረት እነዚህን አሳባቂዎች እና ውሸት የሚያሰራጩ ታከታዮቻቸውንን በሁለት ዓይናችን እንድናይ የምጠይቀው። ዛሬ እየታየ ያለው አዲስ የፖለቲካ ጉዞ ደግሞ፤ ተቃዋሚው ፈሪ እና በራሱ አንጀትና ሐሞት ስለማይንቅሳቀስ (ነብስ ስለሌለው)’ ጨክኖ በተነሳው የእስላማዊው ሰልፈኛ ተቃዋሚ አንጀትና ሐሞት ተወሽቆ ፖለቲካውን ላማፋጠን  እየሞከረ ነው። ሃይሞነተኞቹ ፖለቲከኞችን እየመሩ ማየት በጣም አስገራሚ ዘመን ነው።

 

አሁንም በታማኝ በየነ በተራ ቁጥር 3ኛ እና 5ኛ የተጠቀሱ ንግግሮቹ ማለትም(3) እኔ አቡበከር ነኝ /ሁላችንም ኡበበከሮች ነን፤

(5) የኢትዮጵያ ሙስሊም ‘አክርሮ’ ጐራዴ ይዞ ቢመጣ ከወያኔ ጥይት ይልቅ የሙሲሉን ጐራዴ እመርጣለሁ እኔ!”  የሚላቸው  ቢጫ ቀለም ከናቲራ ለብሶ የተናገረው ሌላው አስገራሚና አስፈሪ  ንግግሩን ደግሞ አንመልከት።

 

 የኢትዮጵያ ሙስሊም ‘አክርሮ’ ጐራዴ ይዞ ቢመጣ……” የሚለው አሸባሪነትን አንደ አማራጭ መውሰድና “ግብዝ ስብከት” የሚያስከትለው መዘዝ ወደ መጨረሻ  ስለምመለስበት ለጊዜው  እኔ አቡበከር ነኝ! ሁላችንም አቡበከሮች ነን!” የሚሉ የታማኝም ሆኑ የተከታዮቹ መፈክሮች ምን ማለት ናቸው? የሚለው እንመልከት። አቡበከር ማለት አሁን በወያኔ እስር ቤት ውስጥ በሽብርተኛ ነት ተከስሶ የሚገኝ የእሳለሞች እንቅስቃሴ ወጣት መሪ ነው። አቡበከር የእስላሞች መንግሥት ለማቋቋም የተነሳ ነው ወይስ  አይደለም የሚለው ለመከራከር አይደለም። ክርክሬ መፈክሮችን ስናስተጋባ ፤አንድ መሪ ሲያስተምራቸው የነበሩት የታሪክ/ የፖለቲካ/ የማሕበራዊ/የፍትሕ ትምህርቶች ለሕብረተሰቡ እና ለተከታዮቹ ምን ይመስላሉ? ከሚሉ መመዘኛዎች ነው ተነስተን “ይህ መሪ አኔን የመጥነኛል፤ይመራኛል፤ ለሕብረተሰቡ እውነት ይሰብካል፤ ጥሩ ምሳሌ  ነው” “እሱ ማለት እኔ ነኝ” ብለን  አርአያነቱን የምንከተለው። ሆኖም ኡስጣዝ አቡበከር አህመድም ሆኑ ሌሎቹ እንደ እነ Ustaz Abdul Menan (ABUYASIRE በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉት እነሱን የሚቃወሙ ወያኔ ስር ያሉ እስላማዊ መሪዎች የሚሏቸው በአይሁዶች የሚመሩ፤ አሁዶች እጅ ያለበት ነው፤ ትግላችን ከአይሁድ ጋር ነው፤ ብሎ የሚከስ ነው።)…. የመሳሰሉ ወጣት የእስልምና መብት አስከባሪ መሪዎች ለመሪነት የማይመጥኑ በውሸት የወጣቱን ሕሊና የሚሰልቡ፤ የኢትዮጵያን ታሪክ አጣምመው የሃይማኖታቸው ተከታዮች የነበሩ ሼኮች እና ነገሥታቶች ለማዳላት ሲሉ የክርስትና ሃይማኖት ተከታይ ነገሥታትን ሚዛን ባልጠበቀ አተቻቸት የሚወነጅሉ ወጣቶች ናቸው።

 

የክርስትያኑ ሰርዓት በአሸባሪነትና ሲከስሱ እና በሸሪዓ ስርዓት ኢትዮጵያን ሲያስተዳድር የነበረው እስላማዊ የግራኝ መንግሥት በቅዱስና ፍትሐዊነት እያመገሱና እያወዳደሩ የሚሰብኩ፤ ለሃይማኖት አስተማሪነት ቀርቶ ውሸት ለሚበረክትብት የፖለቲካ መሪነትና አንኳ  የማይመጥኑ የዓረቦቹ ውሸት የሚያስተጋቡ ራሳቸው ያልቻሉ ልዩ ሴራ ያዘሉ ወጣቶችች ናቸው። ስለሆነም ታማኝም ሆነ ተከታዮቹ “እኔ አቡበከር ነኝ! እኛ አቡበከሮች ነን” በሉ የሚለንን የስብከት መፈክሩ ተቀባይነት የለውም። አቡከር የሚሰብካቸው የውሸት ስብከቶች እስካላረማቸው ድረስ በአኛነታችን አንጂ በእሱነት” አርአያ አንጠራም!

 

ታማኝ በየነ እና የተቀሩት ተከታዮቹ “እኛ አቡበከሮች ነን” እያሉ በሕዝብ ፊት መፈክር ሲያስደምጡን፤ “አቡበከር” ከመታሰሩ በፊት እስላም ወጣቶችንና (በጣም ታዳጊ ህጻናት ወጣቶች ሳይቀሩ)  ሰብስቦ ምን አይነት ትምህርቶችን ሲያስተምር ነበር? የሚለውን እንመልከት። “ከወያኔ ጥይት ይልቅ የእስላሞችን ሰይፍ እምርጣለሁ” የሚለን ታማኝም ሆነ አቡበከር “የእስላሞችን ሰይፍ” የመዘዘው ግራኝ አህመድ አድናቂነት ወይስ ምን ለማለት ነው?። የኼ ደግሞ አቡበከርም ሆነ በየፓልተኩ ውስጥ የምናዳምጣቸው የእስላሞች ፓልቶኮች ክፍል ውስጥ “አህመድ ግራኝን” የእስላሞች መብት አስከባሪ አንደሆነ ቅዱስ ሰው አድርገው ነው የሚሰብኩት። ሆኖም ኢማም አህመድ እንደ ሰብሩ ተክሌ የመሳሰሉት በጣም በርከት ያሉ ክርስትያኞች ለዓረቦች በገጸ በረከት በባርነት ያበረከተ ሰው ነው።

 

ታማኝም ሆነ አቡበከር የእስላሞችን ሰይፍ አንመርጣለን የሚሉን ሰዎች፤ የእስላሞች ሰይፍ በኢትዮጵያ ምድር በክርስትያኑ ሕብረተሰብ ምንን አስከትሎ ነበር ብለን ታሪክን አንጠይቅ። የራሳቸው ጸሐፊዎች እንዲህ ይላሉ።

 

In the land of infidels, nothing was to be seen but cut-off heads, spirits in the throats of death, and palms of hands flying in the air. The Muslims cried out with a mighty cry: ‘there is no God but Allah,’ and ‘God is the Greatest’  (98)

 Literally with the Tahlil and the Takbir’ (the Takbir is the cry Allahu Akbar”.   (ምነጭ በ15ኛው ክፍለዘመን ከግራኝ አህመድ ጋር የነበረ “Sihab ad Din Ahmadin Abd al-Qader bin Salem bin Utman ወይንም በሌላ የተጸውኦ ስሙ “ዓረብ ፋቒሕ” ( Arab Faqih) የተባለው የመናዊው ዓረብ ጋዜጠኛ  “ፉቱሕ አል ሐበሻ” ( Futuh Al- Habasa – the  Conquest of Abyssinia {16th Century} በተባለው በዓረብኛ ቋንቋ ተጽፎ ወደ አንግሊዝኛ ቋንቋ የተተረጐመ)

 

እንግዲህ ታማኝ በየነም ሆነ አቡበከር ‘የአክራሪ እስላሞች ሰይፍ በኢትዮጵያ ምድር ዳግም መከሰት ከወያኔ ይልቅ የኢማም አህመድ (ግራኝ አህመድ) አክራሪ ሰይፍ ቢመጣልን እንመርጣለን የሚሉን አባባላቸው፤ከምን የመነጨ ነው?  ‘ታክቢር! ታክቢር! ታክቢር!” “አላሁ አክበር!” ብሎ ኢማም አህመድ ሲነሳ አክርሮ በመምጣት ሰይፉን ያውለበለበው በማን ላይ ነበር?

በእስላሙ ወይስ በክርስትያኑ ሕብረተሰብ ላይ? በክርስትያኑ ሕብረተሰብ ላይ ነው። በ15ኘው ክፍለዘመን አክርሮ የመጣው የእስላሙ ሰይፍ ዛሬም ኢትዮጵያ ምድር በወያኔ ዘመን በተለያዩ (ለምሳሌ በጂማ…) እስላማዊ መንደሮች ክርስትያኖች ላይ የተሰነዘረው “አክርሮ የመጣ” የእስላሞቹ ሰይፍ” የቅርብ ትዝታ እና በዩ- ትዩብ የተለጠፈ ስለሆነ ይህንኑ ለማስረዳት ጊዜ አልፈጅም። ቪዲየው (ኢትዮጵያን ሰማይ ድረገጽ ላይ ወደ ቀኝ በኩል ተለጥፎ ስለሚገኝ ያንን ይመልከቱ)። ይህ አንደሆነ እያወቀ ታማኝ በየነ ‘አክርሮ የሚመጣ የእስልምናን ሰይፍ” ምረጡ እያለ ሲደልል ማድመጥ በጣም ‘አስፈሪ፤አስገራሚና አስደንጋጭ ንግግር ነው”።

 

ወጣቱ ኡስጣዝ አቡበከር በአክራሪው/ሽብርተኛው ንጉሥ ኢማም ላይ የነበረው በጐ ዓይን አንመልከት።በጐ ዓይኑ ኢማማም አሕመድ የክርስትያኖችን የፀሎት ስፍራ ገዳማት አላፈረሰም። ጸረ ክርስትያን ቢሆን ኖሮ፤ ላሊበላ እና  የአክሱም ቤተክረስትያናት ማውደም ነበረበት። ነገር ግን ኢማም ፍትሓዊ ንጉሥ ስለነበረ ይህነንኑ አላደረገም። ኢትዮጵያን አንድ አድርጓል፤ በማለት አቡበከር አክራሪውን ኢማም ያልነበረው ፤ያልተቸረው የዋህንት በዛው ጨካኝ እና አሸባሪ ግለሰብ ያልነበረው ስብዕና ሊያለብሰው መመኮር አውነትን መጋፋት ነው። ሙሉውን ንግገሩን በሗላ አስነብባችሗለሁ።

 

እውነት ኢማም አህመድ እንዲህ ያለ የዋህ፤ገራገር፤ሃይማኖተኛ  ክርስትናን እና የክርስትናን ማሕበረሰብ፤መነኰሳት፤መሪዎችና ተቋሞቻቸው መብት የሚያስከብር፤ክረስትያኖችን የሚወድ/የሚያከብር የማይገድልና ግድያን የላዘዘ፤ ባርነትን ያላካሄደ፤ የሰው ልጅ ምንንት የማይጋፋ የፍትሕ ንጕሥ ነበር?  (Arab Faqih) የተባለው የመናዊው ዓረብ ጋዜጠኛ “ፉቱሕ አል ሐበሻ” (Futuh Al- Habasa – the Conquest of Abyssinia {16th Century} በዓይኑ የተመለከተው እማኝ የታሪክ ዘጋቢ የነገር ደግሞ ከነ አቡበከር እና ከነታማኝ በየነ የሚያስፈራ እና እነሱ ከሚመርጡልን የዋህ ምርጫ የተለየ ነው።

 

አህመድ ግራኝ በቱርኮችና ዓረብ እና በኑባ እግረኛ ተዋጊ ወታደሮች እየታገዘ ሥልጣንን በሰይፍ እንደተቆጣጠረ የሰራቸው ግፎች ባጭሩ ላሳያችሁ፡-

 

ፉቱሕ አልሐበሻ በተባለው መጽሐፍ ውስጥ  ከኢማም አሕመድህ ጋር አብሮ በጦርነቱ ወቅት ያልተለየው “ዓረብ ፋቂሕ” (ሳሒብ አድ አዲን) የተባለው ጸሐፊው ያየውን ምስክርነት ከመጻፌ በፊት “ሐሰን አህመድ” የተባሉት አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ እስልምና በኢትዮጵያ ውስጥ በሚመለከት የታወቁ  መምህር  ስለ “ ፉቱሑ አልሓበሻ” ታሪክ ማለትም አቡበከር የሃይማኖት አልነበረም የሚለውን ውሸቱን በተጻራሪ አንዲህ ይላሉ።  In the history of conflict in Africa and beyond, “few stories of drama and human tragedy equals” Imam Ahmd’s conquest of the Christian kingdom of Ethiopia (1529-1543).  His short lived spectacular victories and determination to replace Christianity by Islam and the remarkable survival of Christianity in Ethiopia” is a story of epic proportions” which still generates strong emotion among both the christian and Muslim population of Ethiopia. In other words, Imam Ahmad’s Jihadic war besides being legendary was a major turning point…” በማለት የአሕመድ ጂሓዳዊ ጦርነት በክርስትያኑ እና እስላሙ ኢትዮጵያዊ ሕብረተሰብ ልብ ተቃራኒ የስነ ልቦና ስሜት ቀርፆ

ትቶ አንዳለፈ እና አሁንም ያ ስሜት እንዳለ የሚጠቁም አስተያየት ነው ከላይ ያነበብነው።ሙሁሩ የሚሉት፤ ባጭሩ እስልምናን ተክቶ ክርስትና ሃይማኖትን ለማጥፋት ነበር የጦርነቱ መነሻ ነው የሚሉት።

 

በተጠቀሰው መጽሐፍ የተቹት ሌላው ተቺ ደግሞ  (የኦነግ አባል) እና የታሪክ ምሁር ዶ/ር መሓመድ ሐሰን (ፕሮፌሰር ኦፍ አፍሪካን ስታዲ አት ጆርጂያ ስቴት ዩኒቨርሲቲ/አትላንታ) አንዲህ ይላል።

 “… anyone interested in understanding the intensity and brutality of religious war will be rewarded by reading this class” Mohammed Hassan).

 

የነ ታማኝ በየነ የአክራሪ እስላሞችን ሰይፍ መምረጥ እና እኛ አቡከሮች ነን! የሚሉን ሰዎች አቡከር ለወጣት እስላሞችና ህፃናት ሰብስቦ (የህጻናቶችን ፎቶ ግራፉ በቪድዮው ላይ ተመልከቱት) የዋሸው ግን አህመድ ግራኝ ያካሄደው ጦርነት ሃይማኖታዊ አልነበረም፤ ለፍትህ የተካሄደ ጦርነት ነበር ይለናል። ጦርነቱ ሃይማኖታዊ አንደ ነበረ ከላይ የመሰከሩት ምሁራን ብቻ ሳይሆኑ በጦርነቱ ወቅት ከኢማሙ ጋር የነበረው ጻሐፉ የተመለከተው ምስክርንት እነሆ አንዳንዱን ላቅርብ።

 

በ1525 ገደማ ከምስራቁ ኢትዮጵያ አካባቢ ሲነሳ ወጣቱ ኢማም አህመድ ቢን ኢብራሂም አል ጋዚ “ጋራድ አቡን” ከተባለው (መጠጥ እንዳይጠጣ እና እንዳይሸጥ ያወጀ በከበሮ የሚታጀብ ዘፈን እና እስክስታ በሕግ ያጸደቀ) አሚር/ልዑል/ገዢ ስር ወጣት ተዋጊ ወታደር ሆኖ የነበረ ነው።  ጂሐድ ሲያውጅ የ21 ዓመት ወጣት ነበር። ይላል የዓይን ምስክሩ ጸሐፊው “ዓረብ አለፋቂሕ” አንዲህ ይላል። አህመድ ኢብራሂም አል ጋዚ (ግራኝ) በኩፋሮቹ/ ክርስትያኖቹ ላይ ጦርነት በመራበት ወቅት መሬቷ ምን ትመስል አንደነበር “አልፋቂሕ” እንዲህ ይላል።

 

“…In the land of infidels, nothing was to be seen but cut-off heads, spirits in the throats of death, and palms of hands flying in the air. The Muslims cried out with a mighty cry: ‘there is no God but Allah,’ and ‘God is the Greatest’  (98)

 Literally with the Tahlil and the Takbir’ (the Takbir is the cry Allahu Akbar”.  

 

“Islam was raised up, and manifested  and faithlessness was humiliated and forced to take flight…. They made  the sacrifice of their Jihad in order to please Alah”

 

በጦረነት የተማረኩ ክርሰትያኖች እጣ ፈንታ ምን ይገጥማቸው አንደነበር ደግሞ  እንዲህ ይላል

“The Imam thereupon summoned the prisinors , who were brought into his presence. Some of them he sent to Zabid, to the emir Suleiman  the governor there. They were enslaved to the amir of Zabid Someothers of them he had killed. Others of them simply died.” P26

 

ከራጅ karaj/ቀረጥ በሚመለከት  karaj/tax upon land or revenue from land. This was  a tax from which Muslim were exempt and its imposition on Christian and other none-Muslims was one of the principal  incentive toward conversion to Islam”. በክርስትያኑ ላይ እስላም ንጉሥ ሲነግሥ ንጉሱ እና አሚሮቹ በክርስትያን ሕብረተሰብ ሲያደርጉት የነበረው የቀረጥ አቀራረጥ ፖሊሲ እነ አቡበከር እና እነ ታማኝ ሊናገሩት ቀርቶ ክረስትያኑ ግፈኛ አድረገው ብቸኛ ተከሳሽ አድርገውታል። አቡበከር እማ በክርስትያኑ ላይ የተደረገው አድላዊ ቀረጥ ሕጋዊ ነው ብሎ ነው ወጣቶችን ሲሰብክ የተደመጠው( ቪዲዮወን አድምጡ!~) ይህ ሰባኪ ነው እነ ታማኝ “አኛ አቡበከሮች ነን!” እያሉ በአርአያነት የሚያስተዋውቁን።

 

የግራኝ አህመድ ጂሃዳዊ የጦርነት ባንዴራ ቀለሞች ምን ነበሩ? አለፋቂሕ አንዲህ ይላል፡

“He (the Imam) tied red banner to a spear and entrusted it to the emir Husain al- Gatura to whom he detached one-hundred knights from among his warririors and fighters.

Then tried a white banner to another spear to entrusted it to Wazir Nur to whom he also gave more than a hundred knights. 

In those days the banner of the imam was yellow, and under it were two-hundred knights chosen from among the courageous and heroic fighters, skilled in the cut and thurst of war; they were fighters par excellence” (page31)

 

እንግዲህ ዛሬ እኛ አቡበከሮች ነን የሚሉን የአቡበከር ትምህርት የሚሰብኩ እስላም ወንድሞቻችንና እህቶቻችን በትግላቸው እና በየስበሰባቸው አንዲሁም በሰለማዊ ሰልፍ ትዕይንታቸው አየሚያውለበልቡት እና ደምቀውበት የሚታዩት የአገራቸው ሰንደቃላማ የኢትዮጵያ ሳይሆን አህመድ ግራኝ በክርስትያኖች ላይ ጂሃዳዊ ጦርነት ሲያካሂድ  ሲያውለብልባቸውና ሲደምቅበት የነበረው እሱ ሲያብለወልበው የነበረውና ባረፈበት መንደር (ቴንዳ እና ቤት) ሲተከል  ባንዴራው “ቢጫ” ቀለም ነበር። ዛሬ እስላም ወንድሞቻችን ያገራቸውን ሰንደቃላማ ማውለብለቡን ትተው “ቢጫውን ቀለም” የሚያነቡት ወረቀት ሳይቀር፤ ሴቶች እስላሞች የተከናነቡት የራስ መሸፈኛቸው ሳይቀር “ቢጫ ቀለም” ሲሆን እጅግ ጥልቀት ያለው የተቀነባበረ ምስጢራዊ ከመሆኑ አልፎ የግራኝን ሰንደቃላማ በሕሊናችን እንድናስታውስ አድርጎናል።



 በአንድ የታሪክ ጽሑፍ ሳነብብ ግራኝ የተከተሉት ወታደሮች ደክመው ፈዝዘው ኩርምት ብለው ሲታዩ የጦር መሪዎቻቸው የግራኝ አህመድ “ቢጫው” ቀለም የያዘ ሰንደቃላማ ‘ከፊታቸው እንዲውለበለብ ያደርጉ እና አንደ ማነቃቂያ ያደርጉት አንደነበረ አንብቤአለሁ።  አሜሪካ ውስጥ እስላሞቹ በጠሩት ታማኝ በተገኘበት ጉባኤ ውስጥ ተሰብሳቢው የመድከም /የመደበር ምልክት በማሳየቱ ይመስለኛል አንዱ የጉባው አስተባባሪ  አዳራሹን “ምነው ደክምክም አላችሁ ድብርብር አላችሁብኝ እሳ?! ‘በዛው በቢጫው ቀለሙን አድምቁት እስቲ! ሲላቸው በሙሉ ከመቀመጫቸው ተነስተው ቢጫውን ቀለም የያዘ ወረቀት/ጨርቅ… ማውለብለብ ጀመሩ። ይህ እጅግ አስገራሚ ኮ-እንሲደንስ/የታሪክ ግጥምጥም ወይስ ምን ይሆን? ሰንደቃላማችን ለመብት አስከባሪነት በቂ ምልክት ሊሆን የማይችልበት ምን ምክንያት ተገኝቶ ይሆን?

Kahal Bari in the vicinity of Dawaro where they battled with some infidel infantrymen who had assembled in a narrow defile hemming in the Muslims who were fighting there. The Muslims were eventually were victorious with the help of the most High God. The infidels fled, after a group of them was killed. There was a church there called ‘zahraq’, belong to the ancient kings. The muslims set fire to it, and then turned back, seeking returning to their own country…… in Antokya there was a chritian church, when they could not find any treasures in it, they also set fire to it, and destroy it.”

 

በጂሃዳዊው ጦርነት ክረስትያኑ ማሕበረሰብ በእስላም ተዋጊ ሃይሎች መርፌ እና ክር ሳይቀር ሲዘረፍ አንደነበረ አንዲህ ይላል።

After this Muslims went on until they came to Dir, on on the border of the Muslim territory. There the imama pitched the White Tent, and brought out the fifth part of the booty even to the very thread and needle. ”

 
ትግራይ ውስጥ 10 5,550 ሰዎች ተሰይፈዋል። Arab AlfaQih አንዲህ ይላል።


[The people of Tigre are betrayed: 10, 550 are slaughtered.]

 
በሚል ርዕስ በለው የተባሉ ትግሬ እስላም ማሕበረሰቦች (ኤርትራ ውስጥ ይሁኑ ትግራይ ውስጥ አልታወቀም) ትግሬዎችን ከድተው አህመድ ግራኝን በመጠቆም “ትግሬ ክርስትያኖች ከነ ቤተሰቦቻቸውና ሃብታቸው፤ከብቶቻቸው ይዘው በትልቁ ተራራ ላይ ተሸሽገው ይገኛሉ ብለው ስለጠቆሙት አህመድ ግራኝ ጦሬን በሁለት አቅጣጫ አዝምቶ አንዱ እሱ የሚመራው ሌላው ‘አብደ አን ናስር’ የተባለው አዝማች በሌላ አቅጣጫ ተራራውን አንዲወጡ በማድረግ 10550 ቤተሰቦችን አንዴት አንዳረዳቸው በእንዲህ ይተርካል። “… so, the imam spent Ara’da  the night in the encampment; until sunrise. Then he divided his forces two divisons….The imam himself` then set off with his army wich was the second division, taking the left –hand side of the mountain.   On the summit, the idol –worshippers had fortified  themselves in their citadels. The Muslims penetrated their fortification and the Christians were put to flight, and captured. Then imam commanded that they be beheaded. There was no way of their escaping from there. Not a single one manged to slip away. They killed them in the forts, in the valleys and in the gorges. The ground was so thickly covered with their corpses, that is was impossible to walk in that place because of the dead bodies.

 

It is said that some people who were with them on the top counted the number of idol- worshippers.  It trasnspires that their numbers, including their patrician, came to ten-thousand five-hundred-and fifty. Not one of them survived. The Mulsim plunderd their cattle and livestock in quantities that could not be captured or calculated. (P. 352-353) ካለ በሗላ፤ ወደ አምባሰነይቲ ፊቱን አዞረ ይለዋ። ከዛ አንደገና አዝማች ፋኑኤል እና አምሃ የተባለ ክርስትያን አለቆች ተምቤን ውስጥ መመሸጋቸው መረጃ ካገኘ በሗላ ፈረሱን በመጫን ሌት ተቀን ተጉዞ

 ትግራይ ተምቤን አውራጃ ገባ፤፡ በዛው አዳሩ ካደረገ በሗላ ማንም ተዋጊ እፊቱ ዘንድ የተጛጠመው ሰው ስላልነበረ በየቦታው ከቆየ በሗላ ወደ ወግዳን (ዋግዳ ሰገድ/ልብነ ድንግል) ለማደን ወደ ጐንደር አቀና ይላል “ዓራብ አልፋቒህ’ በፉቱሕ አልሓበሻ የጦርነቱ ውሎ ዘገባው ላይ። አቡበከር ግራኝ አህመድ ወይንም የእስላሞች መንግሥት ሰው/ሕዝብ አይገድሉም፤ኢማሙ የፍትሕ ሰው ነው፤እያለ የተናገረውን እጅ አግር አይቆርጡም ያለንን ውሸቱን ንግግሩን ቆይቼ እጠቅሳለሁ። ምንጩ ግን እነሆ 

Abu Abubekere and Abdul Menan

andenet2

http://youtu.be/4hNYcg0GrdI- Ustaz Abdul Menan (ABUYASIRE)

ድምፃችን ይሰማ! Part 2: Clip 3 of 9


ከላይ የጠቀስኩት ከፉቱሀ አል ሐበሻ ታሪክ የተገኘው ዘግናኝ የጂሃዲስቶቹ ሥራ ስታነብቡ፤ አቡበከር የጂሃዲሰቱ የግራኝን ሽብርተኛ ሥርዓት፤ ‘ፍትሓዊ እና የሰላም አስተዳደር አስፋኝ” ነበር ብሎ ለወጣት እስላም ተከታዮቹ እያምታታ ለምን ሊሰብክ ፈለገ? ዮሐንስና ምኒሊክስ ለምን ከግራኝ አህመድ ጋር አወዳድሮ ዮሀንስ አና ምኒሊክን ‘ጂሃዲሰቶች’ ናቸው በማለት እየወነጀለ ለምን በሃይማኖታዊ-ፖለቲካ የፕሮፓጋንዳ ስብከት ተጠመደ? እኛ አቡከሮች ነን የሚለን ታማኝና ተከታዮቹ ሊነግሩን ይችላሉ? ኩፋር ዕምነት የሌለው፤ፍትሕ የማያውቅ ሽብርተኛ ስለነበረ፤ “ቅዱስ ኢማም አህመድ” ግን አውነት፤ ፍትሕና ሰላም ለማስፈን ነው ጦርነቱ የተካሄደው ብሎ ማለት “እስምና ሰላማዊና ፍትሓዊ” ክርስትና (በአቡበከር አጠራራር ኩፋሮች) ግን “ሽብር አስፋፊዎች፤ፍትሕ አልባ ሃይ፣ማኖት ነው” ለማት የበቃው እውነትን እሰብካለሁከሚል የሃይማኖት ሰባኪ የሚጠበቅ ነው?

 አክሱም እና ላሊበላ ግራኝ አህመድ ምንም የነካው ጂሃዳዊ ስራ የለም ሲል ዓረብ አገር በተማረው ዓረብኛ አቀላጥፎ በሚናገረው ፈጣን ምላሱ ወጣቱን ሰብኳል።  ዓረብ አለፋቂሕ የሚነገረን ደግሞ ትናንት ወደ እዚህ ምድር ከመጣው ወጣት ኡስጣዝ አቡበከር አህመድ  የተቃራኒው ነው። ስለ አክሱም አብያተ ክርስትያናትን ውድመት በሚመለከት መደመደሚያ ላይ አቅርቤዋለሁ ይመልከቱ።

ከዚያ በፊት ግን  ኡስጣዝ አቡበከር አህመድ ስለ የእስላሞቹ ‘ነቢይ መሃሐመድና ስለ ኢማም አህመድ/ግራኝ መሃመድ’ እንዲህ ይላል “ሰውን አስገድደው አላሳመኑም፤ ካፊሩን እስላም ሁን ብለው አላስገደዱም። የተደረገ ታሪክ የለም!  ብሎ የሰበከውን ከላይ አስቀድሜ አድምጡት ብየ  የሰጠሗችሁን የስዕለ ድምፅ ምንጭ ቃል በቃል እነሆ።

“የአገራችን ታሪክ አንኳ የተደረገ ታሪክ ምስክር ነው። የነ አፄ ዮሀንስ እና ምኒሊክ ታሪክ! ‘የቦሩ ጉባኤ’ ግልፅ ታሪክ ነው።የክፈር ዘመቻ ታውጆ፤ ሙሰሊሙ ካልከፈረ ተብሎ፤ ‘ሲገደል፤ እጁ ሲቆረጥ’ የነበረ መሸይኰች እናውቃለን አይደለም እንዴ? ቁርአን ሲቃጠል፤ መሸይኮች ሲገደሉ የነበረው ‘በነሱ’ (በሃይማኖተ ቢሶቹ፤ኩፋሮቹ) ታሪክ ላይ ነው። ቤየትኛው ታሪክ?! ኢማሙ አህመድ ወይንም ደግሞ “ግራይ አሕመድ” ያሉት ‘ግራይ’ ያሉት ‘ግራ የሆነባቸው ሰዎች ናቸው።’ ኢማሙ ታሪክ ላይ ‘ትልቅ ነገር’ ሰርተዋል፤ኢትዮጵያ ታሪክ ላይ። ኢትዮጵያን አንድ አደርገው ለመግዛት ተንቀሳቅሰዋል።ያን ተግባር ሲፈጽም “ኢማም አሕመድ” ቤተክርስትያን አጥፍቷል፤አገር አጥፍቷል ይላሉ፤ እውነት  ቢሆን ኖሮ፡ ኢማም አሕመድ የሚያጠፋው ላሊበላን ነበር፡ አማም አሕመድ፤ የሚያጠፋው አክሱምን ነበር፡ የክርስትያን እምብርት፤ማዕከሎች የሞባሉት። ነገር ግን፤ኢማም አሕመድ አላጠፋም፡ (ጉዳት አላደረሰም) ክርስትአናና ለማጥፋት የመጣ ጂን/(ዲን) አይደለም። ‘አላህን ፍሩ’ እያለ ነበር ጦሩን ያንቀሳቀሰው፤የሰው ልጅ ፍትሕን ለማስፈን፤” በባጢል የተዘለበውን ማሕበረስብ በፍትሕ ላማሳደር ……በየትኛውም ዘመን ላይ ከእስልምና ዕምነት ውጭ ያደሩትና በፈትሕ የኖሩት በሰላም ያደሩት “ወላሂ!!” እስልምና ዓለምን በመራበት ጊዜ ብቻ እና ብቻ ጊዜ ነው። ፍትሕ ተከብሮላቸው፤ደሕንነታቸው ተረጋግጦላቸው የኖሩት፤ከጭንቀት የወጡት። እስልምና ‘አኽላቅ  አልሐርቢ’ የጦርነት ስነ ምግባር’ ያለው ብቸኛ ጦርነት የተስተናገደው ብቸኛው ጦርነት ነው። የተደረገው ታሪክ የሃቅ  እና የባጥል ሥራ ፍጥ ጫ እውነታ ታሪካችን ይኼ ነው፤ ለማለት አንጂ፤ ደም የተሰተናገደበት በደም የተሞላበት  ጦርነት አይደለም እስልምና።”  

በማለት ኢትዮጵያዊውን ወጣት በፈጣን ዓረብኛ ቋንቋ ጣልቃ እያስገባ ውሸት ሲመግብ ታሪክ ሲያጣምም፤ የፈጠራ ሰበካ ሲሰብክ ሃይማኖት “ውሸት” አታስተምር የሚለውን ትምህርት እየጣሰ ‘ውሸት” ሲሰብክ ቃል በቃል ያነበባችሁት የኡስጣስ አቡበከር የሰበካ ትምህርት ነው። 

እንደዚህ ያሉትን ሃይማኖታዊ እና ፖለቲካዊ የውሸት መሪዎችን ነው ታማኝ በየነ “እኛ አቡከሮች ነን! እኔ አቡበከር ነኝ!’ በሉ እያለ በያዳራሹ መፈክር የሚያስተጋባው።

 ኡስጣዝ አቡበከር ስለ ነብዩ መሐመድ የሃይማኖት ጦርነት እና አስገዳጅነት (ጂሃድ) ኡስጣዝ አቡበከር እንኳን ነቢዩ መሐመድን እስልምናን በጦርነት ሳይቀር አስገብሮ አስፋፍቷል ብሎ ሊያስተምር ይቅር፤ የቅርብ ታሪካችን ስለ ግራኝ አህመድ የተናገረውን አንኳ ከላይ በቀላሉ የሰውየው ዋሾ ምላስ በቀላሉ ምን ያህል ታማኝነት የጐደለው ምላስ መሆኑን መረዳት አያዳግትም። ሌላ ቀርቶ “በወቅቱ በወረራው የተጠቁ ሰዎች “ግራኝ” ብለው ስላወጡለት ሰለባዎችም ጭምር “”ግራ የገባቸው” በማለት ይዘልፋቸዋል። አንግዲህ አሕመድ ግራኝ በአክሱም ቤተክርስትያን በላሊበላ እና በጠቅላላ ባገሪቱ ገዳማትና መነኰሳት ያደረገው ጥፋት ለመረዳት የጠቀስኩት የዓረብ አልፋቂሕን መጽሐፍ አፈላልጎ ማንበብ ነው።

አቡበከር ከተናገረው የጠቀስኩት ከዚያ አነጋጋሩ “ጂሃዲስት ህሊና” ያለው ይመስላል ብል አልሳሳትም። ዓለም በእስልምና ስትደዳር ዓይተን ሰምተን አናወቅም። የዓለም ሕዝብ በእስልምና/ሸሪዓ መንግሥት/ስርዓት ተዳድሮ ነበር፤በወቅቱ ሰላምና ፍትሕ ሰፍኖ ነበር፤ የሚለን ዓለም የትኛዋ መሆኑን አናውቅም። የጠፋ ዓለም ካለ የዛች ዓለም ዘመን መቸ እንደሆነ ከነመሪዎቹ ጭምር ስማቸውን አንዲነገረን ተከታዮቹ የሚያውቁ ከሆነ አንጠብቃለን። ዓለም በእስልምና/በሸሪዓ እስላማዊ ሕግ/መንግሥት አንድትዳደር የሚፈልገው ኡስጣዝ አቡበከር፤ እንደ ምኞቱ እና አነጋጋሩ ቢሆንለት ኖሮ ‘ዓለም በእስልምና በሸሪዓ ሕገ መንግሥት” እንድትዳደር ፍላጐቱ የበረታ መሆኑን ከዚህ ንግግሩ ለመረዳት ዳገት ቁልቁለት ጭሮ መልዕክቱን ለማግኘት የሚያደክም አይሆንም።

ለመሆኑ ግራኝ ቤተክርስትያን ገዳማት አላቃጠለም?፤ ፍትሕ ሰፍኖ ነበር ወይንም ፈትህ ለማስፈን ነበር ጦርነቱ የተካሄደው የሚለን “ምን የሚሉት ፍትህ ነበር’? ሸሪዓ በኢትዮጵያ ምድር ለማስፈን ግራኝ ያደረገው የሽብር ጦርነት “ፍትሓዊ ነው”? አንዴት ስለ አውነት እሰብካለሁ የሚል አቡበከር የመነኮሳትን ደም ፤የገዳማትን ቃጠሎ ፍትሓዊ ነው ይላል? የክፋሮች ታሪክ  እያለ የሚጠራውስ “የኢትዮጵያ ታሪክ” አንዴት ነው  በሸሪዓ ለመለወጥ የተደረገ ጦርነት ፍትሓዊ ነው ማለት የሚቻል?  ሕብረተሰብን ማሸበር አንዴት ፍትሕ ሊሆን ይችላል? እስልምና ማለት ያ ከሆነ እስልምና ሞገደኛ ሃይማኖት ነው። ከአቡበከር ሰበካ ተነስተን አስልምና “መጐደኛ” ነው ብንል ልንሳሳት አንዴት እንችላለን?   

በ1521 ግራኝ አህመድ ለረጂም ዘመን ፀንቶ የኖረውን የክርስትያኑን መንግሥት ገልብጦ  በግልጽ የእስልምና ሃይማኖት ካልተቀበላችሁ እያለ ክርስቲያኑን ሕዝብ ጨፍጭፎ የክርሲያኑን ሀብትና ንብረት፤ ጥንታዊ የገዳማት እና የማይገኙ በጣም ጥንታዊ መጻሕፍት አቃጥሎ ገንዘብ፤ወርቅ ብር፤ ውድ ጥንታዊ መስቀሎች ንብረት ሙልጭ አድርጐ ዘርፎ ለቱርኮች ከቀበላቸው በሗላ፤ ያንን አልበቃ ብሎት፤ ከሞት የተረፈውን ወጣት ሴት ወንድ በሺዎቹ ሰብስቦ በባርነት እንደ ገበያ በግ እየተነዳ ወደ ዓረቦች እና እንዲሁም የመን  ላይ ለነበረው የቱርክ እንደራሴ ለ “ዘቢድ ፓሻ” በገፀ በረከት እንደተላለፉ “ዓረብ አልፋቂሕ” ሃቁን አስፍሮታል።

ዓረብ ፋቒሕ “ኢማም” እያለ በአክብሮት እና በቅዱስነት የእስልምና ሃይማኖት በሰይፍ አስፋፍቶ የጠበቀ የሚለውን ስለ “ግራኝ አሕመድ” የጻፈው መረጃ አንመልከት እና አንደምድም።

ከሰው ተለይተው ሕገ እግዚአብሔር ጠብቀው ከማናቸውም ከዓለም ነገር አርቀው በፆም ተጠምደው በየገዳማቱ የሚኖሩ መነኰሳት እንዴት አንደተገደሉና ቤተክርስትያናት እንዴት አንደተቃሉ እነሆ። “ግራ የገባቸው” ብሎ አቡበከር መነኰሳቱን የሚዘልፋቸው የደረሰባቸው ግፍ ባጭሩ አንድ ምሳሌ ‘የደብረሊባኖስ’ ገዳምና መነኰሳትን አሟሟት እንመልከት።

[The imam defends the burning of the church] በሚል ንዑስ አንዲህ ይላል። ቤተክርስትያኑን አታቃጥሉብን የገዳሙ ወርቅና ብር እንሰጣችሗላን  ብለው ለኢማሙ ጦር ተወካይ ፤ለአሚር ‘አቡበከር ቃቲን’ (Abu bakr Qatin) በልምና እያነጋገሩት እያሉ፤ ኡራይ አቡበከር (Ura’I Abu Bakr) የተባለው ከተቀመጠበት ተነስቶ እየተንደረደረ በቁጣ ሄዶ የእሳት ከሰል ይዞ በመሄድ ቤተክርስትያኑን በመለኰስ በእሳት አጋየው። ወዲያውኑ መነኰሳቱና አሚሩ የወረቅና የብሩ ድርድር መነጋገራቸውን አቁመው እየተቃጠለ ወዳለው ቤተክርስትያን ቀልባቸው ዞር ብለው ሲመለከቱ ጭሱ ሰማዩን ባንዴ ጋረደው። መነኰሳቱ ይህንን ሲመለከቱ ድርድሩን አቁመው እየሮጡ በመሄድ ፌንጣ/የሳት እራት ወደ እሳት አንደምትገባ ሁሉ መነኰሳቱ እየዘለሉ ወደ ነበልባሉ እሳት ዘልለው በመግባት የሳት እራት ሆኑ። “…When the monks and the emir saw the fire, their peace was sundered, and the monks plunged into the fire, as moths dive into the wicks of a lamp; all but a few of them.  … ይላል። …Then emir Abu Bakar Qatin questioned Ura’I Abu Bakr who had set the church. He asked him ‘why did you burn down the church when we were negotiating a peace?’ ‘I set fire to it! Do what you like with me. I set fire to it. The imama did not command us to do anything but burn it down.  He did not commission us to make peace for the sake of treasure.’ So he released him, and they took what booty they could find and returned to the imam. It took them a twelve days a march to go back, and they reached the imam in the country of Berarah on the day of ‘Arafat’. 

The emir Abu Bakar notified the imam Ahmad, may Almighty God have mercy upon him, who it was that had burnt the church. The imam said “there was nothing wrong in burning it down. After all, wasn’t burning it down what I ordered you to do, from the very outset- since it meant much more to them than anything else?. Then the imam said, ‘return to your camp. Then come back to me in the morning, for I have a certain matter that I want to discuss with you.’ So they return to their camp.”

የተቃጠሉት ገዳማት እና መነኮሳት፤ ተገድደው ወደ እስልምና እንዲገቡ የተደረጉ ክርስትያን ማሕበረስብ፤ፍጅቱና እልቂቱ ለማየት  የጠቀሰኩት የ Futuh Al- Habasa  እና ከግዕዝ የተተረጐመው  “ትንታዊ የኢትዮጵያ የሰላም ጥበቃ ታሪክ (ከቅራት- ዘመናዊ ፖሊስ)” የተባለው አስገራሚ ጥንታዊ ሰነድ የያዘ መጽሐፍ በደራሲው በሊቁ ‘እምሮ ንጉሤ’ ይመለከቱ። በዘመኑ የነበሩ ሰዎች ለምን ግራኝ እንዳሉት ያገኙታል። ኡስጣዝ አቡበከር አህመድ ግን “ኢማሙን” ግራይ ይሉታል “ግራ የገባቸው” በማለት ሰላባዎቹን “ግራ የገባቸው” ይላቸዋል። በቱርክ እየታገዙ በወቅቱ  በኢትዮጵያ ያልነበረ፤ ዘመናዊ ነፍጥ ታጥቀው የኢትዮጵያ ምድር ዓረቦች፤ ኑባዎች፤ሶማሌዎች… ተባበርው ወደ ምድሪቱ በመግባት የግራኝን ‘ቢጫ’ ባንዴራ እያውለበለቡ፤ የሁከት፤የጩኸት፡የደም እና የሽብር መሬት በሆነቺበት በዛው አሰቃቂ ዘመን የተፈጸመውን ሃይማኖታዊ የሽብር ጦርነት፤ ነው፤ የፍትሕ ዘመን ‘ግራይ’ ያሉት ‘ግራ የሆነባቸው ሰዎች ናቸው።’ ብሎ ያስተማረው። እነ ታማኝ ይህንን ሰው አርአያቻው እንደሆነ ሳያፍሩ ይነግሩናል።

ኡስጣዝ አቡበከር አህመድ  “ ኢማም አሕመድ አላጠፋም፡ ክርስትናን ለማጥፋት የመጣ ዲን አይደለም።አላህን ፍሩ እያለ ነበር ጦሩን ያንቀሳቀሰው፤የሰው ልጅ ፍትሕን ለማስፈን ነው።” በማለት የግራኝ የሽብርና የጂሃድ/ሃይማኖት ጦርነት  “በባጢል የተዘለበውን (ባጢል የተዘለበው የሚለው ዓረብኛ ቋንቛ ነው)  ማሕበረስብ በፍትሕ ላማሳደር ነው” በማለት ሽብርን ፍትሕ ነው ያለውን እስልምና ‘አኽላቅ  አልሐርቢ’ የጦርነት ስነ ምግባር’ ያለው ብቸኛ ጦርነት የተስተናገደው ብቸኛው ጦርነት ነው። የተደረገው ታሪክ የሃቅ  እና የባጥል ሥራ ፍጥጫ እውነታ ታሪካችን ነው የሚለው አቡበከር አክሱም ቤተክርሰትያን ግራኝ አህመድ ያደረገው ቃጠሎና ውድመት እስኪ አንመለክትለና ጽሑፌን ልደምድም።

ይኸየው፡

“The king removes the great white statue from Aksum” ኪንግ/ንጉሥ የሚለው ‘አህመድ ግራኝ” ን ነው። [“The king removes the great white statue from Aksum” በሚል ንኡስ ርዕስ ገጽ 354፤] ፋሲል ያሰሩት የ17ኛው ክፍለዘመን አሁን ያለው ቤተክርስትያን አይደለም እየተናገረ ያለው። አልቫሬዝ የተባለው ጎብኚ ጐብኝቶት የነበረ ብቸኛ ሰው ያየው እሱ ብቻ ነበር። ከአልባሬዝ ጉብኝት በሗላ ያየው የውጭ ጐብኚ አልነበረም። ምክንያቱም ግራኝ አሕመድ ያ እጅግ ጥንታዊ የነበረው ቤተክርስትያን ስላቃጠለው። ውድመቱ አንጂ ቁመናው አልታየም። ነጭ ድንጋይ የሚለው/ሁዋይት ሰቶን የሚለው ከዚህ በታች የምታነብቡት የጥንት ቅዱሳን ‘ከእየሩሳሌም’ ይዘውት የመጡ የታቦቱ ማሳረፊያ ቅዱስ ድንጋይ አንደሆነ ይነገራል (ስለ ሁኔታው ሌላ ቀን እመለስበታለሁ)። ታሪኩ እነሆ፦

[They removed the great statue from the church of Aksum.] በሚል ንኡስ ርዕስ አልፋቂሕ በዓይኑ ያውን አንዲህ ሲል ዘግቦታል።

They removed the great statue from the church of Aksum.It was of white stone, studded with gold. So large was it that the statue could not be taken from the church through its principal gate. Because of its size they were obliged to make a hole in the church’s wall through which they took it out. It took four- hundred men to carry it. They took it to the citadel known as Tabir. They took it to the citadel known as Tabir in the land of Sire, where they left it.

(ታብር የሚለው መደባይ ታብር ማለቱ ነው።ሲሬ የሚለው ሽሬ አውራጃ ማለቱ ነው።) ትልቅ አምባ የሚገኝብት ገጠራማ አካባቢ ነው።)

The imam was in his camp in the land of Tamben when a man from the tribe of the Balew from the city of Aksum, came to him. His name was ‘Abd al- Wahib. He said ‘Are you aware that the king of Abyssinia has arrived at Aksum?’ Then the Imam immediately ordered them to strike camp, and they did so.

By the next day they had reached the district of Aba Garima, two parasangs from Aksum. Where they made camp. Some of the local people said to the imam., ‘The idol worshippers here art Abba Garima have barricaded themselves up in three forts, because, they have no means of fighting you’. When  imam heard this news, he pitrched his camp there, and then set out against them.

The inhabitants of two forts yielded to him, and he imposed the poll-tax upon them. The defended of the third forts refused, so he fought them and God put them to flight and he Alah put them to fight and he killed them to the last one of them.

On full battle alert the Muslims set off for Aksum. They arrived there without encountering any hostility……Some monks in the city of Aksum said to him, ‘Spend today with us so that we can pay you the poll-tax in gold’.The imam refused and set out on a strenuous journey to Mazagar to assist the muslim (went to look for the king a head of him). So they set out, but the Muslims had no chance to provide themselves with supplies.

At dusk, he pitched camp in the church of Abba Samu’el in the land of Sire. This church was glorious building, embellished with very colour. Its monks assembeled together and they killed them all inside the church, so that the blood flowed through the doors. There were five-hundred of them. (Futuh al Habesha. p354-355)

አንግዲህ ኡስጣዝ አቡበከር ግራኝን ግራኝ የገባቸው ሰዎች ግራይ ይሉታል፤ ፍትህ ያነገሰ፤ ሰው ያልገደለ፤ የኩፋሮችን ቤተከርስትያን ያላቃጠለ፤ ከፋሮችን/ሃይማኖተቢስ፤ ጣኦት አምላኪ ክርስትያኖችን “አላህን ፍሩ” እያለ ጦሩን ያንቃሰቀሰ ‘ቅዱስ ንጉሥ ” እያለ ያሞኳሸው ሽብርተኛው ግራኝ አህመድ ማለት ይኼ ነው።

እስላሞች በዓላቸው አልተከበረላቸውም፤ ሁለተኛ ዜጋ ነበሩ..ወዘተ ወዘተ ክርስትያኑ ተንደላቅቆ ኖሯል፤ ክርስትያኑ ደልቶታል፤ እነሱ ግን አንዲህ ሆነዋል፤ አነዚያ ሁለተኛ ዜጋ ነበሩ…..ወዘተ. ወዘተ …. ይህች የኢትኦጵያ ባንዲራ የክርስትያኞች፤ያማራዎች፤የትግሬዎች…..ነበረች;…..ወላጆቻችንን በድላለች፤ገድላለች፤ጩቁናናለች ወዘተ …….ወዘተ..ወዘተ…የሚለው ደላላነት እና ሚዛኑ ያልጠበቀ ክስ መጋፈጥ የሚያስፈራቸው ኢትዮጵያዊያን እኔ ተጋፍጨዋለሁ። አንዲህ ዓይነት የጂሃዲስቶች እና ታሪክ የሚያጣምሙ ውሸታሞችና ሴራው ተቀባይነት አንዲኖረው የሚረዱ ነዳጅ አቀባዮችና በማሻኮር ፖለቲካ የተሰለፉ ሰዎችንና አማርኛ ቋንቋን በእንግሊዝና በዓረብኛ ቋንቋ ይተካ የሚሉ ‘ደናቁርት’ ፊት ለፊት ካልተጋፈጥናቸው፤ አገሪቱ አሁን ካለችበት ወድቀትና ቅጥፈት እጅግ የከፋ ይሆንባታል።የነሱም የኛም የልጅ ልጆች መካራ ባሕር ውስጥ እንዲዋኙ መተባበር ይሆናል። ውሸታሞች የዲሞክራሲ እና የመብት አስከባሪ መሪዎች እየተባሉ በአርአያነት የሚጠሯቸው አሻኳሪ ግለሰቦች በየድረገጹ የሚለቀልቁ የውሸታሞችን ብርሌ አጣቢ ጸሐፊዎች ማለቅለቅ ያቁሙ። በቃ! ማለት በቃ! ነው።አመሰግናለሁ። ኢትዮጵያ አገሬ ለዘላላም ከነሰንደቃላማሽ ለዘላለም ኮርተሽ እያውለበለብሽ ኑሪ! እውነት ትመነምን አንደሆን እንጂ አትሰበርም። በመጨረሻ እውነት አሸናፊ ናት። ጌታቸው ረዳ (የኢትዮጵያ ሰማይ ድረገጽ አዘጋጅ 2005 ዓ.ም/2013 በፈንጂኛ አቆጣጠር)  getachre@aol.com